አወዛጋቢው ምርጫ 2012

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

Re: አወዛጋቢው ምርጫ 2012

Postby ምክክር » Thu Feb 06, 2020 10:59 pm

ለውጡ ያስገኘዉን ሁሉ ችላ ብለሃዋል፡፡ ይሁን፡፡
ለውጡን ተከትሎ የሚመጣ ችግር እንዳለ አይካድም፡፡ ወያኔ ጥሎት የሄደው የብሄረሰቦች አወቃቀር አንድ ሌላ ነቀርሳ ነው፡፡ እስኪ የመፍትሄ ሃሳቦችን አቅርብ፡፡
Be nice to yourself
ምክክር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 440
Joined: Thu Jun 26, 2008 10:10 am
Location: Super Earth

Re: አወዛጋቢው ምርጫ 2012

Postby ዘርዐይ ደረስ » Fri Feb 07, 2020 8:07 am

አቶ ምክክር፡-በየትኛውም አገር ሆነ ማህበረሰብ ውስጥ ለውጥ ሲካሄድ ተጠቃሚም ተጎጂም መኖሩን የምንተማመን ይመስለኛል፡፡ባለፉት 22 ወራት የታየው ለውጥ አልታየህም ስትለኝ የህዝቡ ኑሮ ተሻሽሏል ማለትህ ይመስለኛል፡፡በየዕለቱ የምንሰማቸው ነገሮች ግን የሚያሳዩን ለአንድ ህዝብ ህልውና እስፈላጊ የሆኑ ነገሮች በተጨባጭ እየታዩ እንዳልሆነ ነው፡፡እነዚህም ሠላም፤ኢኮኖሚ፤ፍትሕ፤አስተዳደራዊ ሥነ ምግባር፤የውጭ ፖሊሲ፤የሰብዓዊ መብቶች መከበር፤አድሎ የሌለበት ሥርዓት ወዘተ ናቸው፡፡ታዲያ በነዚህና በሌሎችም መመዘኛዎች ሁለት ዓመት ሊሞላው ጥቂት የቀረው ሥርዐት መሻሻል ያሳየው የት አካባቢ ነው?ወይስ ሌላ አማራጭ ስለሌለ አርፋችሁ ተገዙ እንደሚሉን እንደ ኢዜማና ኢሳት ያሉ ተቃዋሚ ተብዬዎች ተሸማቀን ዝም እንበል?ያለፈውን ሥርዓት በማውገዝ ብቻ ፖለቲካ ማራመድ አይቻልም፡፡እንደዚህ ዓይነቱ አካሄድ ደርግም ህወሓትም አላዋጣቸውም፡፡
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1337
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: አወዛጋቢው ምርጫ 2012

Postby ምክክር » Sun Feb 09, 2020 5:42 am

መፍትሄ ይሆናል ብለህ የምታስበው ምንም የለህም ማለት ነው፡፡ ስራየ ብለህ የያዝከው አቃቂር መፍጠርና መአት ከዚህም ከዚያም ቀራርሞ ማውረድ ነው፡፡ የወያኔን 25 ዓመታት ሰቆቃ በዓመት ከምናምን እያጣጣሃው ትታያለህ፡፡ አሁን ጨዋታው ግልፅ ነው፡፡ ግን ‘ኮ ወያኔ የነፈገንን አሁን አግኝተናል፡፡ ተገፍትረህ ሳይሆን ባገርህ መፍትሄ እያቀረብክ ተሳተፍ በሚናህ፡፡ ችግሮች እንዳሉ አይካድም፡፡ ይህ ማለት ግን ከችግር ፈጣሪ ጎን ተሰልፎ መንግስትን ሃላፊነት በማሸከም ብቻ ፖለቲካ ነግዱ ማለት አይደለም፡፡ በነገርህ ላይ ወቅቱን ተንተርሰህ እንኳ ስለ እብሪተኛው ጀዋር ምንም አላልክም! ሥለ ህውሓትም መሠሪ ምግባር እንዲሁ ትንፍሽ አላልክም! ዞረህ ዞረህ እዚያው፡፡ ክብ ሆንክብኝ እንደ ክበበው፡፡ ብዙ ሥለ ችግር ስታወራ ብዙ ችግር ፈጣሪዎችን አለፈሃል፡፡እለፈን ያሉህ ይመስል!! ምን ዓይነት መነፅር እንዳለህ ገርሞኛል፡፡ እውነትን የምታይበት አንግል ከወያኔ ውሃ ልክ ጋር ይቀራረባል፡፡

ወያኔ ያፈራው ትውልድ የክልሉን እንጂ የኢትዮጵያን ባንዲራ እንዳያውቃት አርጎ ነው ጭራሹኑ ሊያጠፋት ትንቅንቅ ላይ ነው፡፡ እኛ ደግሞ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ ፍንክች አንልም፡፡ ፍልሚያው በዚህና በዚያ ትውልድ መሃከል ነው፡፡ ከዚህ ፍጥጫ ነጥሮ የሚፈጠር አንድ ሃይል ሊመጣም ይችላል፡፡ አሁን ግን ያለው ሁነታ በአሉ ግርማ እንዳለው ”የአንድ እናት ልጆች ተጣልተው፡ በአስተሳሰብ ተለያይተው፡ በአመለካከት ተነጣጥለው፡ አስታራቂ ጠፍቶ፡ የእብድ ገላጋይ በዝቶ” የሆነ ያህል ነው፡፡
Be nice to yourself
ምክክር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 440
Joined: Thu Jun 26, 2008 10:10 am
Location: Super Earth

Re: አወዛጋቢው ምርጫ 2012

Postby ዘርዐይ ደረስ » Tue Sep 22, 2020 7:50 am

እንግዲህ የጤና ሚንስትሯም ኮረና ምርጫውን ለማካሄድ ስጋት አይሆንም ብለዋል፡፡ሌላ ምክንያት ካልተፈጠረ በቀር ምርጫ ቦርድ ዝግጅቱን መጀመር አለበት፡፡
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1337
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: አወዛጋቢው ምርጫ 2012

Postby ክቡራን » Tue Sep 22, 2020 11:15 am

እኔን የሚገርመኝ የትግራይ ህዝብ መሪዎቼን መምረጥ እፈልጋለሁ ብሎ ሲነሳ በሱም ሆነ በድርጅቱ ላይ ህግ እየተጠቀሰ እንደ ወንጀለኛ ይዘመትበታል፡፡ ይፎከርበታል፡፡ የፌዴራል መንግስቱ ምርጫ መደረግ አለበት ሲል ትክክል ብሏል፣ እውነት ነው እያሉ ለማጭበረበሪያ ያላህን ስም የሚጠቀሙት እነ ማሰሮ ( በነገራችን ላይ አላህ ለጀነትም ለገሃነምም ገና ሲፈጠሩ የመረጣቸው አሉ ) የኋላ እሸታቸውን ያስመርቃሉ.. ቂቂቂቂ... እቺ አለም ስንት የምድር ጉድ ይዛለች? ስትል ትጠይቃለች የኔዋ ጃለታ ጃፈሮ ካካካካ...በነገራችን ላይ መእምናን የምድር ጉድ ሲል የእውቀት እጥረትን ብቻ ሳይሆን የቁመት እጥረትንም እንደሚያካትት ልብ ይሏል ፡፡ ህጋዊነት ሲጠፋ ( ኢንስቱትይሻናላይዝድ ) መሆን ስናቆም ነው ሃገር መፈራረስ የምትጀምረው፡፡ መንፈስ ለዋርካውያን የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ!!
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9198
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: አወዛጋቢው ምርጫ 2012

Postby ዘርዐይ ደረስ » Fri Nov 20, 2020 7:48 am

አሁን ምርጫ የሚጠይቅ የአእምሮ ጤንነቱ ያጠራጥረኛል!አገር እስኪረጋጋ ቢያንስ 2 ዓመት ማንኛውም ምርጫ ባይኖር መልካም ነው
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1337
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: አወዛጋቢው ምርጫ 2012

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sat Dec 26, 2020 8:57 am

ምርጫ ቦርድ ትላንት እንዳሳወቀው ግንቦት 28ቀን2013 በጊዜያዊነት ተከታዩ ምርጫ የሚደረግበት ቀን አድርጎ ወስኗል፡፡
https://www.reuters.com/article/us-ethi ... SKBN28Z0JN
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1337
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: አወዛጋቢው ምርጫ 2012

Postby ዘርዐይ ደረስ » Fri May 21, 2021 4:48 am

''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1337
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: አወዛጋቢው ምርጫ 2012

Postby ዘርዐይ ደረስ » Fri Jun 11, 2021 6:04 am

ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ የሶማሌ ክልልን ጨምሮ በ54 የምርጫ ክልሎች ሰኔ 14/2013 ዓ.ም ምርጫ እንደማይካሄድ አስታወቀ።

ቦርዱ ከዚህ በተጨማሪም ከ6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ ጋር በተመሳሳይ ዕለት እንዲካሄድ ቀን ተቆርጦለት የነበረው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ለመመሠረት ይደረግ የነበረው ሕዝበ ውሳኔም ወደ ሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ መደረጉ ተገልጿል።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሶማሌ ክልል ሊደረግ የነበረው ምርጫ እና የደቡብ ምዕራብ ሕዝበ ውሳኔ እንዲተላለፍ የተደረገው በተለያዩ የምርጫ ክልሎች የድምጽ መስጫ ወረቀቶች ላይ ጉድለቶች መገኘታቸውን ተከትሎ ነው ብሏል።

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ የሶማሌ ክልል እንዲሁም የምዕራብ ኢትዮጵያ ክልልነት ሕዝበ ውሳኔ ጳጉሜ 1/2013 ዓ.ም. ይካሄዳል ስለማለታቸው የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ምርጫ ቦርድ ትናንት በሰጠው መግለጫ የድምጽ መስጫ ወረቀቶች ላይ የተለያዩ ጉድለቶች መገኘታቸውን አስታውቆ ነበር። ቦርዱ 54 የምርጫ ክልሎች ድምጽ መስጫ ወረቀቶች ድጋሚ ህትመት የሚያስፈልጋቸው ሆነው ተገኝተዋል ብሏል።

ትግራይን በተመለከተው ውይይት የአሜሪካ እና የአውሮፓ ሕብረት ባለስልጣናት ምን አሉ?
መንግሥት በትግራይ ክልል ረሃብ አለ መባሉን አጣጣለ
በወጣቱ ግድያ ጥፋተኞች እንዲጠየቁ ሂዩማን ራይትስ ዋች ጠየቀ
ቦርዱ ይህን ችግር ለመቅረፍ ሁለት አማራጮች አሉ ብሎ ነበር ትናንት ከፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር በነበረው ወይይት። የመጀመሪው አማራጭ የድምፅ መስጫ ወረቀቱ ህትመት አገር ውስጥ ማከናወን ሲሆን ሁለተኛው አማራጭ ብሎ ያቀረበው ሃሳብ ደግሞ በ54 የምርጫ ክልሎች በጸጥታ ችግር የተነሳ ሰኔ 14 ቀን ድምጽ ከማይሰጥባቸው የምርጫ ክልሎች ጋር በጋራ ማከናውን ይሆናል ብሎ ነበር።

በዛሬው መግለጫ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚዴቅሳ ክፍተት የተገኘባቸው የምርጫ ክልሎች የጸጥታ ችግር አለባቸው ተብለው ሰኔ 14 ድምጽ ከማይሰጥባቸው የምርጫ ክልሎች ጋር ድምጽ ይሰጥባቸዋል ብለዋል።

በዚህም መሠረት ምርጫው በሁለት ዙር እንደሚካሄድ የተወሰነ ሲሆን የመጀመሪያ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ሰኔ 14 የሚካሄድ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በዓመቱ መጠናቀቂያ ላይ ጳጉሜ 01 ይካሄዳል።

በትናንቱ የምርጫ ቦርድ መግለጫ ላይ የድምጽ መስጫ ወረቀቶች ድጋሚ ህትመት ያስፈልጋቸዋል ተብለው የተለዩት 54ቱ የምርጫ ክልሎች በሚከተሉት ክልሎች የሚገኙ ናቸው።

ሶማሌ- 14 (የክልል ምክር ቤት)
አፋር - 6 ምርጫ ክልል (1ዱ የተወካዮች ምክር ቤት)
አማራ- 11 ምርጫ ክልል (3ቱ የተወካዮች ምክር ቤት)
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ - 2 ምርጫ ክልሎች ( የክልል ምክር ቤት)
ጋምቤላ - 3 ምርጫ ክልሎች (የክልል ምክር ቤት)
ኦሮሚያ - 2 ምርጫ ክልል (የክልል ምክር ቤት)
ደ/ብ/ብ/ህ- 15 ምርጫ ክልሎች (1 ለተወካዮች ምክር ቤት)
ድሬዳዋ - 1 (የከተማ ምክር ቤት) ድጋሚ ህትመት የሚያስፈልጋቸው ምርጫ ክልሎች ያሏቸው ናቸው።
በዚህ ዓመት የሚካሄደው ምርጫ በመደበኛ የጊዜ ሰሌዳው መካሄድ የነበረበት ባለፈው ዓመት የነበረ ቢሆንም በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት ወደ ሌላ ጊዜ መተላለፉ ይታወቃል።

ምርጫው በዚህ ዓመት በግንቦት ወር ሊካሄድ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም አስፈላጊ የምርጫ ቁሳቁሶች በተያዘላቸው ጊዜ ተዘጋጅተው ባለመጠናቀቃቸው በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍሎች ውስጥ ሰኔ 14/2013 ዓ.ም እንዲካሄድ ተወስኖ እንደነበር ይታወሳል።
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1337
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: አወዛጋቢው ምርጫ 2012

Postby ዘርዐይ ደረስ » Tue Oct 05, 2021 7:18 am

አወዛጋቢው ምርጫ በትላንትናው ዕለት ተቋጭቷል ማለት ይቻላል፡፡ይህ ማለት ግን የምርጫውን ውጤት ሁሉም ተሳታፊዎች ተቀብለውታል ማለት አይደለም፡፡ያም ሆነ ይህ በመሐሉ ያልተጠበቀ ክስተት ካልተፈጠረ ለሚቀጥሉት አምስት አመታት ብልፅግና ፓርቲ ከተለጣፊዎቹ ጋር ሆኖ ስልጣን ላይ ይቆያል፡፡በትላንትናው የተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ስብሰባ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩና የአፈ ጉባኤዎች ምርጫና ቃለ መሐላ ተካሂዷል፡፡ በዚህም መሠረት አቶ ታገሰ ጫፎ በድጋሚ የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ሲመረጡ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ደግሞ የቀድሞው የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አገኘሁ ተሻገር በአፈ ጉባኤነት ወይዘሮ ዛሕራ ኡመድ ዓሊ ደግሞ በምክትል አፈ ጉባኤነት ተመርጠው ቃለ መሐላ ፈፅመዋል፡፡ከሰዓት በኋላም በመስቀል አደባባይ የበዓለ ሲመት ሥነሥርዓት ተካሂዷል፡፡በዚህም ዝግጅት ላይ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ሣሕለወርቅ ዘውዴ፣የክብር እንግዶቹ የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ሙሐመድ ቡሐሪ፣የኬኒያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ፤የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሙሐመድ ፎርማጆ፤የጂቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ዑመር ገሌ፤የኡጋንዳው ፕሬዝደንት ዩሄሪ ሙሴቬኒ፤የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ማያድሪት፤የሴኔጋሉ ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል ፣የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳማ ሉኮንዴ ንግግር አድርገዋል፡፡የአብይ የቅርብ ወዳጅ እንደሆኑ የሚነገርላቸው የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ግን ራሳቸው ካለመገኘታቸው በተጨማሪ ተወካይም አለመላካቸው አስገርሞኛል፡፡ በዛሬው ዕለት ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የካቢኔ አባሎቻቸውን ይፋ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1337
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: አወዛጋቢው ምርጫ 2012

Postby ዘርዐይ ደረስ » Thu Oct 07, 2021 4:04 am

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ኦክቶበር 06 ያቀረቡት የካቢኔ አባላት ሹመቶች በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሁንታን አግኝቷል።

በአብላጫ ድምፅ ይሁንታ የተቸራቸው ሹመቶች በድምፅ አሰጣጥ ወቅት 2 ተቃውሞና 12 ድምፀ ተአቅቦ አግኝቷቸዋል።

በዚህም መሠረት፦


ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር - ደመቀ መኮንን
መከላከያ ሚኒስትር - ዶ/ር አብረሃም በላይ
የገንዘብ ሚኒስትር - አህመድ ሽዴ
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር - ሙፈሪሃት ካሚል
ግብርና ሚኒስትር - ኡመር ሁሴን
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር - ኢ/ር አይሻ መሃመድ
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር - ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ
የትምህርት ሚኒስትር - ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ
የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስትር - ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር- አቶ ገብረመስቀል ጫላ
የኢንዱስትሪ ሚኒስትር- አቶ መላኩ አለበል
የሰላም ሚኒስትር- አቶ ብናልፍ አንዷለም
የፍትህ ሚኒስትር- ዶ/ር ጌዴዎን ጤሞጢዎስ
የጤና ሚኒስትር- ዶ/ር ሊያ ታደሰ
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር- አቶ በለጠ ሞላ
የቱሪዝም ሚኒስትር- አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ
የገቢዎች ሚኒስትር- አቶ ላቀ አያሌው
የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር - ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ
የማዕድን ሚኒስትር- ኢ/ር ታከለ ኡማ
የፕላንና ልማት ሚኒስትር - ዶ/ር ፍጹም አሰፋ
የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር- ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር - አቶ ቀጄላ መርዳሳ ሆነዋል።
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1337
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Previous

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Bing [Bot], Google [Bot], ምክክር and 2 guests

cron