አወዛጋቢው ምርጫ 2012

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

አወዛጋቢው ምርጫ 2012

Postby ዘርዐይ ደረስ » Wed Jan 22, 2020 7:03 pm

ይህን ርእስ ያየ ኢትዮጵያ ውስጥ ያላወዛገበ ምርጫ ተካሂዶ ያውቃል ወይ ብሎ ቢጠይቅ አልተሳሳተም፡፡ለማንኛውም መጪውን ምርጫ በተመለከተ መንግሥት፡'ተፎካካሪ' የፖለቲካ ፓርቲዎችና ህዝቡ ግራ የተጋቡ ይመስላል፡፡አወዛጋቢ ከሚባሉት ነገሮች መካከል ፡-
1)ምርጫ ቦርድና ፓርቲዎቹ በተሻሻለው ህግ ዙርያ አለመስማማታቸው
2)ሃገርቱ ላይ ተደጋግሞ እንደታየው ከፍተኛ የፀጥታ ችግር በመኖሩ ተጨባጩ ሁኔታ ምርጫ ለማካሄድ አመቺ እንዳልሆነ ብዙዎች ይናገራሉ፡፡ህዝብ መቁጠር ያልቻለ መንግሥት እንዴት ሃገራዊ ምርጫ ለማካሄድ ይደፍራል የሚሉ ድምፆች ጥቂት አይደሉም፡፡የሲዳማ ህዝብ የክልልነት ውሳኔ ህዝብ በሠላም መጠናቀቁን እየጠቀሱ ለሃገራዊው ምርጫ ጥብቅና የሚቆሙ ቢኖሩም ሁለቱን ማወዳደር እንደማይቻል የሚሞግቱም አሉ፡፡
3)የምርጫውን መካሄድ ከሚደግፉት መካከልም ቢሆን በቅርቡ ምርጫ ቦርድ ያሳወቀውን ቀነ ቀጠሮ ያልተቀበሉም ቅሬታቸውን እያሰሙ ነው፡፡ለዚህም የሚሰጡት ዋና ምክንያት ጊዜው ክረምት በመሆኑ በተለይ የገጠሩን ህዝብ ታሳቢ ያደረገ አይደለም በማለት ነው፡፡
4)'ተፎካካሪ ድርጅቶች' ባለፉት 2ዓመታት ሲፈርሱ ሲጣመሩና ሲዋሃዱ ስለቆዩ እንኳን ተራውን መራጭ የፖለቲካ ተንታኞችንም ግራ ያጋባ ክስተት በመፈጠሩ
5)የፖለቲካ ሥነ ምሕዳሩ ሁሉንም ወገን እያስተናገደ አለመሆኑ
6)ላለፉት 25 ዓመታት ሲለፈፍ የቆየውና አሁንም በአዲስ መልክ የቀጠለው ነፃና ፍትሐዊ ምርጫ እናካሂዳለን የሚለው ፕሮፖጋንዳ በብዙዎች ዘንድ አጠራጣሪ መሆኑ
7)የበርካታ 'ተፎካካሪ ድርጅቶች' አቋም ያለው ሥርዓት እንዲቀጥል እንጂ በእሁኑ ወቅት ለውጥ እንዲመጣ እለመፈለጋቸው፡፡ለዚህም የሚሰጡት መልስ የመንግሥት ለውጥ ከመጣ ረብሻ ይነሳል የሚል ነው፡፡በዚህም ምክንያት ራሳቸውን በመናጆነት ለማቅረብ በመዘጋጀታቸው ህዝቡ እንደ ክህደት እየቆጠረው መሆኑ
8)ምርጫ ቦርድ አሁንም እንደ ቀድሞው ገለልተኛ መሆኑ ብዙዎችን ያላሳመነ በመሆኑ
9)ያለው ሥርዓት በዚህ ዓመት ምርጫውን ማካሄድ ካልቻልኩ ህገ መንግሥቱን መጣስ ይሆንብኛል ሲል እራሳችሁ ያወጣችሁትን ህገ መንግሥት ተብዬ መቼ አክብራችሁ ታውቃላችህና ነው አሁን እንደ ምክንያት የምታቀርቡት የሚሉ አሽሟጣጮችም አልጠፉም
10)ምርጫው ካልተካሄደ የአገሪቱ ሠላም እንዳይባባስ ብቸኛው መፍትሄ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት የተውጣጣ የሽግግር መንግሥት መቋቋም አለበት የሚሉ ሃይሎች መነሳታቸው
እነዚህና ሌሎችም ጉዳዮች የ2012ቱን ምርጫ ከመቼውም ጊዜ ባላነሰ አወዛጋቢ አድርገውታል
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1337
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: አወዛጋቢው ምርጫ 2012

Postby ዞብል2 » Thu Jan 23, 2020 1:15 am

ጋሽ ዘርዓይ ደረስ፤ አወዛጋቢው ምርጫው ሳይሆን፤ስለ ምርጫው መደረግ የሚደነግገው ህገ መንግስት ነው፡፡ኢትዮጵያ የምትከተለው ፓርላሜንታዊ ስርዓት ነው፤በፓርላሜንታዊ ስርዓት ደግሞ፤ምርጫ መካሄድ ያለበት ፓርላማው ተበትኖ ወይም ተዘግቶ ነው፡፡በኢትዮጵያ ግን ፓርላማው ሳይዘጋ ወይም ሳይበተን ነው፡፡የህዝብ ተወካዮችን የስራ ዘመን በሚደነግገው አነቀፅ 58/3/ መሰረት የምክር ቤቱ ዓባላት፤የሚመረጡት ለ5ዓመታት መሆኑን አስቀምጦ"የሥራ ዘመኑ ከማብቃቱ፤ከአንድ ወር በፊት አዲስ ምርጫ ተካሂዶ የሥራ ዘመኑ ይጠናቀቃል" በማለት ምርጫ መቼ መካሄድ እንዳለበት በግልፅ ያስቀምጣል፡፡"የምክር ቤቱን የሥራ ግዜ ከመስከረም ወር መጨረሻ ሳምንት ሰኞ እስከ ሰኔ30 ነው"በማለት አስቀምጦታል፡፡

ለማጠቃለል እራሱ ህገ መንግስቱም ሆነ የምርጫ ህጉ አንድን ወገን ለመጥቀም ወይም እንደ ፈለገው እንዲተረጉመው ተደረጎ የተፃፈ ነው፡፡ለዚህም ዋንኛ ምሳሌ ሊሆን የሚችለው ምርጫ 1997ዓ.ም ነው፡፡በ97 ምርጫ ገዢው ፓርቲ ሲሸነፍ፤ፓርላማው ስላልተበተነ፤ መለሰ ዜናዊ በማግስቱ ፓርላማውን ስብስቦ፤አዲስ አበባን የኦሮሚያ ዋና ከተማና፤ማንኛውም የሚሰበሰበውን ቀረጥ ወደ ፌደራል አዙሮ አዲስ አበባን እርቃን አስቀራት፡፡ መለሰ ዜናዊ ይህን ያደረገው አብዛኛዎቹ(በሙሉ ማለት ይቻላል)በምርጫ ከተሸነፉ የፓርላማ ዓባላት ጋር ነበር፡፡

ስለሆነም አወዛጋቢው ምርጫው ሳይሆን፤የምርጫው ህግ ነው፡፡የአሁኑን ምርጫ ከውዝግብ ነፃ ለማድረግ፤ጠቅላዩ የሕገ መንግስቱን አንቀፅ 60/1/ በመጠቀም ፓርላማው የሥራ ዘመኑን ከማጠናቀቁ በፊት"አዲስ ምርጫ ለማካሄድ በሚል" በፓርላማው ምክርና ፈቃድ፤ፓርላማውን በመበተን፤በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ምርጫ ማካሄድ ይቻላል፡፡
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2427
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: አወዛጋቢው ምርጫ 2012

Postby ዘርዐይ ደረስ » Thu Jan 23, 2020 10:17 am

ሠላም ዞብል፡-
9ኛው ተራ ቁጥር ላይ ስለ ህገ መንግሥቱ ጠቀስ አድርጌ አልፌአለሁ፡፡አንተ እንዳልከው ብቸኛ ችግር አድርጌ አላየውም፡፡እስካሁን እንደተከታተልኩት ህገ መንግሥቱ ካልተቀየረ ምርጫው ላይ አልሳተፍም ያለ ድርጅት አላጋጠመኝም፡፡
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1337
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: አወዛጋቢው ምርጫ 2012

Postby ዞብል2 » Thu Jan 23, 2020 10:49 pm

ሰላም ዘርዓይ ደረስ፤ በ9ኛው ላይ ያስቀመጥከውን ምክንያት በማሰብ ነው፤ ጠቅላዩ አንቀፅ 60/1 ተጠቅመው ፓርላማውን አማክረው"አዲስ ምርጫ ለማካሄድ" በሚል ፓርላማውን በትነው በ6ወር ጊዜ ውስጥ አዲስ ምርጫ ማካሄድ እንደሚቻል፤ህገ መንግስቱ ይፈቅዳል፡፡ነገር ግን ይህን ለማድረግ ማንም አልፈቀደም ወይም መኖሩንም ያስተዋለው ያለ አልመሰለኝም፡፡

ህገ መንግስቱ ካልተቀየረ ምርጫው ላይ አልሳተፍም ያለ ድርጅት አላጋጠመኝም ላልከው፤አብዛኛዎቹ ፓርቲዎች አይደለም ህገ መንግስቱን የራሳቸውን የመተዳደሪ ደንብ በቅጡ አያውቁትም፡፡ህገ መንግስቱን በቅጡ ቢያውቁት፤ፓርላማው ሳይፈርስ ምርጫ ይካሄዳል በሚለው አንቀፅ ብቻ ምርጫ አንካፈልም ማለት ይችሉ ነበር፡፡ምክንያቱም ኢትዮጵያ የምትከተለው ፓርላሜንታዊ ስርዓት እስከ ሆነ ድረስ ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ፕሬዘደንቷ ዘንድ ቀርቦ ፓርላማው እንዲበተንና አዲስ ምርጫ እንዲካሄድ ይጠይቃል፡፡በኢትዮጵያ ግን ይህ ሁሉ ፕሮሲጀር አይካሄድም፤ምክንያቱ ሁሉም ያሻውንና የመጣለትን ስለሚናገር ደንብና ስርዓቱን ይረሳዋል፡፡
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2427
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: አወዛጋቢው ምርጫ 2012

Postby ዘርዐይ ደረስ » Fri Jan 24, 2020 4:52 am

ፓርላማውን መበተን ለምን አስፈለገ?ቅድመ ዝግጅት ቢደረግ እኮ ምርጫውን በወቅቱ ማካሄድ ይቻል ነበር፡፡የእገሪቱ የፀጥታ ሁኔታ ደግሞ እንኳን ፓርላማ በትነህ እንዲሁም አደጋ ላይ ወድቋል፡፡ምክር ቤቱ በሌለበት ሁኔታ ማነውስ ምርጫውን የሚያስፈፅመው፡፡በሌሎች አገሮች እንደሚቻል አውቃለሁ ምክንያቱም ገለልተኛ ተቋማት ስላሉ ነው፡፡
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1337
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: አወዛጋቢው ምርጫ 2012

Postby ምክክር » Fri Jan 24, 2020 9:47 am

የፓርላማው መበተን አለመረጋጋትን ያመጣል ብለን እንዴት እንዳሰብን አልገባኝ ብሏል፡፡
ያውም የኛ ፓርላማ! ወንበር ላይ ሖኖ መች የህግ የበላይነትን ተጠቆጣጠረ? ሥራቸው መንግስትን ቼክ ኤንደ ባላንስ ማድረግ አልነበረምን? በምርጫ ወቅት የግል ጥቅሙን እንጂ ሰለመረጋጋት ወርዶ ምን ሊያደርግ ይችላል? መበተኑ ሕጋዊ ነው ወይ ይሁን ጥያቄው? ምርጫው ቢራዘምም ትችትና መዘዝ አለው፡፡ በቀነ ቀጠሮው ቢቆረጥም ለምዶብን ሁለቱንም ወይም ሁሉንም እንቃወማለን፡፡ በቃ እንዲህ ነን ጫኔዎች! ባለመስማማት ጫና የምንፈጥር የሚመስለን ኔጋቲቭ አስተሳሰብ የተጠናወተን፡፤ ወደ ምርጫ ጣብያ ሄደን እንምረጥ፡፤ ወያኔም እኮ ምርጫ አካሂዷል፡፡
ባሁኑ እምነት ይኑረን፡ ከተጭበረበረ ደግሞ መታገል ነው፡፡ እንዲህ እያልን ነው ወደ ትክክለኛው መስመር የምንጠጋው፡፤ወያኔም ተጠልዟል ፡፡ ህዝብ የማይቀበለው ሁሉ ይጠለዛል፡፡ ባሁኑ ግን ችግሩ ባብላጭ ህዝቡ ጋ ነው፡፡
Be nice to yourself
ምክክር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 440
Joined: Thu Jun 26, 2008 10:10 am
Location: Super Earth

Re: አወዛጋቢው ምርጫ 2012

Postby ዘርዐይ ደረስ » Fri Jan 24, 2020 2:59 pm

ሠላም ምክክር፡-
ከተደማሪዎቹ መካከል መሆንህን መገመት ይቻላል፡፡አሁን በኢትዮጵያ ላለው ዘርፈ ብዙ ችግር ዋናው ተጠያቂ ሥርዐቱ ሳይሆን ህዝቡ ነው ማለትህ ግን ወይ የህዝቡን ተጨባጭ እኗኗር አታውቅም አሊያም ከሥርዐቱ ጋር በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ተቆራኝተሃል፡፡ህዝቡማ የዕለት ኑሮውን ማሸነፍ አቅቶት እየተሰቃየ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡በተረፈ ምክር ቤቱ ተበተነ ማለት እንደ ኢትዮጵያ ላሉ አገሮች ምን ማለት እንደሆነ ክርክር ውስጥ መግባት አልፈግም፡፡
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1337
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: አወዛጋቢው ምርጫ 2012

Postby ዞብል2 » Fri Jan 24, 2020 10:04 pm

ሰላም ዘርዓይ ደረስ፤የምንከተለው ፓርላሜንታዊ ስርዓት እስከ ሆነ ድረስ ፓርላማው የግድ መዘጋት አለበት፡፡ይሄን ሲባል መንግስት ይፈርሳል ማለት አይደለም፤ በጊዜው መንግስትን የመሰረተው የፖለቲካ ፓርቲ፤አዲሱ ምርጫ ተደርጎ እስኪጠናቀቅ ድረስ ጊዜያዊ አስተዳደር ሆኖ ህግ የማውጣትና የመሻር ስልጣኑ ተገድቦ፤የዕለት ተዕለት የመንግስትን የሥራ ሃላፊነት ማስፈፀምና፤ምርጫውን የማከናወን ሐላፊነት እንዳለበት በህግ ተደንግጎ ተቀምጧል፡፡
ተቋም ስላልከው ፤ምርጫ ቦርድ አለ፤የተለያዩ ማህበረ ሰብዓዊ ድርጅቶች አሉ፤መንግስት ግን በቅድሚያ እንደ አሸን የፈሉትን በህዝብ ስቃይና ሰቆቃ የሚነግዱትን፤ወፈ ሰማይ አክትቪስትና ፖለቲከኞችን አደብ ማስገዛት አለበት፡፡
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2427
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: አወዛጋቢው ምርጫ 2012

Postby ምክክር » Sat Jan 25, 2020 9:33 am

ሠላም ዘርዓይ በንጉሡ ሠ
እኔን ከተደማሪዎች ስትፈርጅ አንተንም እንዲሁ ከዘኛው ጎራ ነህ ብሎ ታፔላ መለጠፍ ቀላል ነው ግን ይህ አጀማመር የጤናማ ውይይትን መንፈስ ይበርዛል፡፡ አንዱ ችግራችን ይህ ነው፡፡ የማን ደጋፊ የማን ተቃዋሚ እንደሆን አያሳስብም ዛት ኢዝ ኖት ዘፖይንት፡፡ ጥግ ይዞ ማልቀስ እና ማላቃስ መፍትሄ አይሆንም፡ ፡ አገር የምታድገው ሰላም የሚሰፍነው ችግራችንን አጋነን በማላዘን አይደለም፡፡ የመፍትሄው አካል መሆን ያሻል፡፡ ለዛ ደሞ መደመር ክፉ አይደለም፡፡ መደመር ሶሻሊዝም ወይም ኢምፔሪያሊዝም አይደለም፡፡ የአንድነት መንፈስ ነው፡፡ ከዚያ በአመለካከት ልዩነት በሰከነ መንፈስ መፋጨት ነው፡፡ የጠ/ር ዓብይ መንግስት የህግን የበላይነት ማስከበሩ ላይ መስራት እንዳለበት አምናለሁ፡፤ በአንፃራዊ ግን ከወያኔ እጅግ በጣም ይሻላል፡፡
ሠላሙን ላንተ! አሁንም በንጉሡ፡፡
Be nice to yourself
ምክክር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 440
Joined: Thu Jun 26, 2008 10:10 am
Location: Super Earth

Re: አወዛጋቢው ምርጫ 2012

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sat Jan 25, 2020 12:18 pm

በድጋሚ ሠላም እያልኩ፡-
እንዴ!ያልተደመረውን ሁሉ በዘረኝነት መፈረጅ ተጀመረ ማለት ነው?በነገራችን ላይ ህዝቡን ጥፋተኛ ማድረግህ ነው እንጂ ችግሩ ለሥርዓቱ ያለህ ቀና አመለካከት የግል መብትህ ነው፡፡
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1337
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: አወዛጋቢው ምርጫ 2012

Postby ዘርዐይ ደረስ » Thu Jan 30, 2020 7:53 am

ትክክለኛው እኮ ሠላም ነው፡፡
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1337
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: አወዛጋቢው ምርጫ 2012

Postby ምክክር » Fri Jan 31, 2020 8:59 am

ትክክል፡፡
ዓብይ እና ዘርዐይም እንዲሁ፡፡
Be nice to yourself
ምክክር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 440
Joined: Thu Jun 26, 2008 10:10 am
Location: Super Earth

Re: አወዛጋቢው ምርጫ 2012

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sat Feb 01, 2020 1:59 pm

አቶ ምክክር፡-
ዋርካ ከተመለሰች በኋላ ካላየናቸው ታዳሚዎች መካከል አንዱ የሆነው ተድላ ሀይሉ ነበር የፊደላት አመራረጥ ላይ በዋነኝነት የሚጠቀሰው (ምንም እንኳ የራሱ ኒክ ትክክል ባይሆንም)፡፡ለጊዜው የቋንቋውን ነገር ወደ ጎን ትተን እስቲ ስለ ምርጫው እናውራ!የጠቀስኳቸው ነጥቦች ለውይይት በቂ አይደሉም ብላችሁ ነው ችላ ያላችኋቸው?
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1337
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: አወዛጋቢው ምርጫ 2012

Postby ምክክር » Sun Feb 02, 2020 2:50 am

ሥለ ምርጫው መወያየት አይከፋም-ጊዜ ካለ፡፡ ችግሩ በመካሄድ ላይ ያለውን ለውጥ ስታብጠለጥለው ጥቅም የቀረበት ሁዋላ ቀር ወያኔ ያስመስለሃል-ለአንባቢህ፡፡
ይህን መንግስት ማነፃፀር የምትችለው ከወያኔ ጋር ነው ወይስ ከስካንዲኒቭያ መንግስት ጋር ነው? ከግፈኛው እና ዘረኛ አገዛዝ ጋር አይደለምን? ስንት ምሁራን ከስራቸው ተባረዋል (አሁን መመለሳቸዋን ሰምተህ ይሆን?) ስንቱ ታስሮ ተሰቃይቷል ስንቱስ ከሃገሩ ተገፍትሮ ተሰዷል? አገሪቷን ሙጥጥ ጥርግ አርገው ግጠዋታል፡፡ በዜጎች መካከል የማይጠፋ ጠባሳ ጥለዋል፡፡ ይህ በትንሹ ነው፡፡ ከዓብይ የአንድ ዓመት መንግስት ጋር ስታወዳድረው በቅን ሚዛናዊነት መሆን አለበት፡፡ በግልፅ የሚታይ አስደናቂ ለውጥ አለ፡፡ ህዝቡም ይደግፈዋል፡፡ እንደ ወያኔ የዘር ሐረግ ችግሩን ብቻ በመምዘዝ የምትጨምረው የለም፡፡ ምርጫው ላይ ያለህን ቅዋሜ ከሌላ ፖለቲካ አጀንዳ ጋር አዳቀልከው ያው ጆሮ ለመግዛት ብቻ ነው፡፡ አዲስ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ የሚከተለው ዘዴ ነው፡፡ አዲስ እረኛ በጎቹን አያስተኛ ሆነ፡፡
Be nice to yourself
ምክክር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 440
Joined: Thu Jun 26, 2008 10:10 am
Location: Super Earth

Re: አወዛጋቢው ምርጫ 2012

Postby ዘርዐይ ደረስ » Wed Feb 05, 2020 10:02 am

አቶ ምክክር
በእርግጥ ከ22 ወራት በፊት ሥርዓቱ በርካታ ደጋፊዎች ነበሩት፡፡እንዲያውም የተቃዋሚው ቁጥር እንደሌለ ያህል ነበር ማለት ይቻላል፡፡ህወሓቶችም ቢሆኑ ጥቂት ቆየት ብለው ነው ተቃውሞዋቸውን የጀመሩት፡፡አሁን ግን በህዝቡ በኩል ያለው ድጋፍ በጣም እየቀነሰ መጥቷል፡፡በእርግጥ አንዳንድ ተቃዋሚ ድርጅቶች ከሥርዓቱ ደጋፊዎች ባልተናነሰ ሁኔታ አሁን ብልፅግና የሚባለው ፓርቲ ካልተመረጠ የእገሪቱ ህልውና አደጋ ላይ ሊወድቅ ስለሚችል ቢያንስ ይህንን ምርጫ ማሸነፍ አለበት እያሉን ነው፡፡ህዝቡ ግን በሚወራው ወሬ እና በሚካሄደው ድርጊት ግራ ተጋብቷል፡፡በተለይም አማራ ክልልና እዲስአበባ የነበረው ድጋፍ አሁን እየታየ አይደለም፡፡
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1337
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Next

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 8 guests