ኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ ገባ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ ገባ

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sat Mar 14, 2020 12:00 am

COVID-19 በመባል የሚታወቀውና ከ 100 አገሮች በላይ እንደተሰራጨ የሚነገርለት የቫይረስ ዓይነት ኢትዮጵያ ውስጥ በአንድ ጃፓናዊ ላይ እንደተገኘ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር አስታወቀ።በዚህም ምክንያት ከግለሰቡ ጋር ግንኙነት የነበራቸው 25 ሰዎች ለምርመራ ከህዝቡ ተለይተዋል።
https://www.aa.com.tr/en/africa/ethiopi ... se/1765130
https://www.bbc.com/news/topics/cwlw3xz047jt/ethiopia
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1372
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ ገባ

Postby ዘርዐይ ደረስ » Wed Mar 18, 2020 9:51 pm

ከጃፓኑ ጋር ግንኙነት የነበራቸው ግለሰቦች ለምርመራ ተለይተው ሶስት ተጨማሪ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡የኦሮምያ ትምህርት ቢሮ ኃላፊም ከጃፓኑ ጋር ግንኙነት ስለነበረው ራሱን አግሏል ተብሏል።ከዓረብ አገር ሲገባ በጥርጣሬ ለምርመራ ሲወሰድ ያመለጠው ግለሰብና ወደ አገሩ በአውቶብስ ሲሄድ አብረውት የተሣፈሩት የምርመራ ውጤት ገና ይፋ አልሆነም፡፡በትላንትናው ዕለት ደግሞ አንዲት ከዱባይ ወደ ኢትዮጵያ የገቡ የ59 ዓመት ብሪታኒያዊ ሴት በተደረገላቸው ምርመራ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ተዘግቧል፡፡
ሰሞኑን በአገሪቱ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እየተካሄደ ነው፡-
-በጎ ፈቃደኞች አውቶብስና ቀላል ባቡር ውስጥ የሚገቡ ተሣፋሪዎችን እጅ በማስታጠብ እያገለገሉ ነው
-በአዲስ አበባ አንድ ሆስፒታልና ሁለት የጤና ጣቢያዎች ለኮሮና ህመምተኞች ማቆያ እንዲሆኑ ተመድበዋል
-መገናኛ ብዙኃን በስፋት ስለ ቫይረሱ ለኅብረተሰቡ ግንዛቤ እየሰጡ ነው
-ከውጪ በሚገቡ ግለሰቦች ላይ ጠበቅ ያለ ቁጥጥር እየተካሄደ ነው
-ለአስራ አምስት ቀን ያህል ትምህርት ቤቶች ፣የስፖርት ውድድሮችና ተመሳሳይ በርካታ ህዝብ የሚገኝባቸው ዝግጅቶች ተከልክለዋል።
-የየሃይማኖቶቹ ተወካዮች ምዕመኖቻቸው በሽታውን ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው እንዲከላከሉ ማሳሰቢያ እየሰጡ ነው።
-ግርግር ለሌባ ይመቻል እንደሚባለው ወቅቱን በመጠቀም በህክምና በንጽህናና ምግብ ነክ ነገሮች ላይ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው።
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1372
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ ገባ

Postby ዘርዐይ ደረስ » Wed Apr 08, 2020 8:34 pm

ይህንን ርዕስ ከከፈትኩት ሶስት ሳምንታት አለፉ፡፡በዚህ ጊዜ ውስጥ ይህ ቫይረስ በጣት የሚቆጠሩ አገሮች ሲቀሩ ሁሉንም አዳርሷል፡፡ወደ ኢትዮጵያ ስንመጣ በዛሬው ዕለት በኮቪድ 19 የተያዙት ቁጥር 55 ደርሷል፡፡እነዚህም ዕድሜያቸው ከዘጠኝ ወር እስከ 85 የሚደርስ ነው፡፡እስካሁን በተሰጠን መረጃ ከ55 ውስጥ ሁለት ሲሞቱ 4 ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል፡፡አንደኛው ደግሞ ጽኑ ታማሚዎች ከሚባሉት የሚመደብ ነው።ሁለቱ ጃፓናውያን ወደ አገራቸው መመለሳቸው የተነገረ ስለሆነ በአሑኑ ወቅት በመታከም ላይ የሚገኙት 47 ናቸው ማለት ነው።ከነዚህ ውስጥ 1 ሞሪሸሲያዊ 2 ኤርትራውያን ሲሆኑ የተቀሩት ኢትዮጵያውያን ይመስሉኛል።በተጨማሪም በሺህ የሚቆጠሩ "ተጠርጣሪዎች" በለይቶ ማቆያ ውስጥ ይገኛሉ።እነዚህም ቫይረሱ እንዳለባቸው በላብራቶሪ ምርመራ ከተረጋገጠባቸው ሰዎች ጋር ግንኙነት የነበራቸው፣ከውጭ አገር ወደ አገር ውስጥ በመግባት ላይ ያሉ፣የበሽታው ምልክቶች የታየባቸው ናቸው።ከውጭ የሚገቡት አቅም ያላቸው መንግሥት ባዘጋጃቸው ሁለት ሆቴሎች ብቻ (ግዮንና ስካይ ላይት) በራሳቸው ወጪ 15ቱን ቀናት እንዲያሳልፉ ሲደረግ አቅም የሌላቸው ግን በመንግሥት ወጪና በግል ባለ ሃብቶች ዕርዳታ በተገኙ ማቆያዎች እንዲቆዩ ይደረጋል።በአሁኑ ወቅት ከፍተኛውን ቁጥር የያዙት ከዓረብ አገራት የሚገቡት መሆናቸው ታውቋል።ከሳዑዲ ዓረቢያ ብቻ በሳምንት 1500 የሚሆኑ ዜጎች እንደሚገቡ ታውቋል።
ሊመጣ ያለውን ችግር ለመቋቋም ርብርብ እየተደረገ መሆኑ ይነገራል።ባንኮች፣ባለ ሃብቶች፣ያደጉ አገሮች መንግሥታት፣እንዲሁም ብዙሃኑ ህዝብ ባለው አቅም እየተረባረበ መሆኑ መረዳት ይቻላል።በሕክምናው በኩል ግን በቂ ዝግጅት የተደረገ አይመስልም።ያለፉትም ሆነ የአሁኑ መንግሥታት ለሌሎች ጉዳዮች ቅድሚያ ይሰጡ ስለነበር ይህ ክስተት መፈጠሩ አይገርምም።
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1372
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ ገባ

Postby ዘርዐይ ደረስ » Mon May 25, 2020 9:38 pm

የመጀመርያው የኮሮና ታማሚ ከተገኘ ሁለት ወር ከሁለት ሳምንት ሆኗል፡፡ለረጅም ጊዜ ቁጥሩ አዝጋሚ ነበር፡፡ሰሞኑን ግን በየዕለቱ የሚመዘገበው ቁጥር አሳሳቢ ሆኗል፡፡ያለፉትን ሶስት ቀናትን እንኳን ብንመለከት፡-73+88+61=222 ከቁጥሩ በተጨማሪ እያሰጋ ያለው የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸው ወይም በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ሳይኖራቸው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በፍጥነት እያሻቀበ መምጣቱ ነው፡፡መጪው ክረምት ከመሆኑ አንፃር ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል፡፡
https://www.covid19.et/covid-19/
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1372
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ ገባ

Postby ዘርዐይ ደረስ » Fri Mar 12, 2021 7:18 am

ኢትዮጵያ ውስጥ ኮሮና መግባቱ በይፋ ከተነገረ ድፍን አንድ ዓመት ሆነው።መጀመርያ ውቅታዊው አስታቲስቲክስ ምን ይመስላል የሚለውን እንመልከት።
መጋቢት 2 ቀን 2013
ባጠቃላይ የተያዙ፡-171ሺህ210 .....በዛሬው ዕለት የተያዙ፡-1332......ባጠቃላይ የሞቱ፡-2483...በዛሬው ዕለት የሞቱ፡-17....ባጠቃላይ ያገገሙ፡-140ሺህ840......አሁንም በሕመም ላይ ያሉ፡-27887.......ፅኑ ታማሚዎች፡-428.......ባጠቃላይ የተመረመሩ፡-2ሚሊዮን 207ሺህ195

በዚህም መሠረት በበሽታው በተያዙ ሰዎች ብዛት ከእፍሪካ በ5ኛ ከዓለም ደግሞ በ71ኛ ደረጃ ላይ ስትገኝ ባጠቃላይ ሟቾች ብዛት ደግሞ ከአፍሪካ6ኛ ከዓለም ደግሞ በ70ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1372
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ ገባ

Postby ዘርዐይ ደረስ » Thu Oct 14, 2021 6:22 am

የአገራችን ችግር ከመብዛቱ የተነሳ ኮሮና ችላ እየተባለ የመጣ ይመስላል፡፡ከሰዉ ግንዛቤ ቢርቅም መስፋፋቱ ግን እልቀረም፡፡ለተወሰነ ጊዜ ጋብ ያለ ቢመስልም ባለፉት ሁለት ሳምንታት ግን ከመቸውም ጊዜ በበለጠ አሻቅቧል፡፡ብዙዎች የሚያውቁት ሰው መያዙን ይናገራሉ፡፡በበሽታው የሞተ የሚያውቁም ጥቂት እይደሉም፡፡ጥንቃቄ ግን በጣም ቀንሷል፡፡ባለፉት ሁለት ሳምንታት ዕለታዊ ሟቾች ቁጥር ከ30 በታች ወርዶ አያውቅም፡፡የትላንቱን ብንመለከት


ባጠቃላይ የተያዙ፡-356,772
በዛሬው ዕለት የተያዙ፡-929 ባጠቃላይ የሞቱ፡-6103 በዛሬው ዕለት የሞቱ፡-37.ባጠቃላይ ያገገሙ፡-325,865 አሁንም በሕመም ላይ ያሉ፡-24804 ፅኑ ታማሚዎች፡-708 ባጠቃላይ የተመረመሩ፡-3,574,218

በዚህም መሠረት በበሽታው በተያዙ ሰዎች ብዛት ከእፍሪካ በ4ኛ ከዓለም ደግሞ በ74ኛ ደረጃ ላይ ስትገኝ በሟቾች ቁጥር ደግሞ ከእፍሪካ 5ኛ ከዓለም ደግሞ 69ኛ ላይ ትገኛለች፡፡በፅኑ ታማሚዎች ከእፍሪካ 1ኛ ከዓለም 21ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1372
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest

cron