ጌታቸው አሰፋ ትሬዲንግ፡ ከደህንነት ቢሮ እስከ አየርመንገድ የተዘረጋው የኮንትሮባንድ ንግድ!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ጌታቸው አሰፋ ትሬዲንግ፡ ከደህንነት ቢሮ እስከ አየርመንገድ የተዘረጋው የኮንትሮባንድ ንግድ!

Postby ኳስሜዳ » Sat Sep 26, 2020 4:50 pm

አቶ ፍፁም አባዲ በኢትዮጵያ አየርመንገድ የካርጎ ክፍል ሃላፊ፣ ምክትሉ አቶ ናትናኤል ጎበና እና የጌታቸው አሰፋ የቅርብ ዘመድ የሆነው አቶ ዮሃንስ አረጋይ በአየርመንገዱ የካርጎ ክፍል የሚሰሩ የጌታቸው አሰፋ ትሬዲግ ሰራተኞች ናቸው። በዱባይና ቻይና የሚገኙ የኢትዮጵያ አየርመንገድ የጭነት ወኪሎች፣ የቦሌ ጉሙሩክ ሃላፊ ከነበረው ከአቶ ገብረማርያም እስከ ጥበቃ ክፍል ሰራተኞች የሚደርሰው ሰንሰለት የጌታቸው አሰፋ የኮንትሮባንድ ንግድ ሰንሰለት ነው።

ህዝቤ ሆይ... ከዚህ ቀደም ጥብቅ የሆኑ ሚስጥራዊ መረጃዎችን የሰማህ ከመሰለህ ተሳስተሃል። እነ ጌታቸው አሰፋ ከስልጣን የተወገዱበትን ሚስጥር የምታውቅ ከመሰለህ ብዙ ነገር ይቀርሃል። ከሁሉም በላይ ደግሞ በህወሓቶች ስለሚፈፀመው ዘረፋና የኮንትሮባንድ ንግድ በተጨባጭ ማስረጃ የተደገፈ ግንዛቤ ያለህ ከመሰለህ ፍፁም ተሳስተሃል። ምክንያቱም በዚህ ፕሮግራም ላይ የሚቀርቡት ማስረጃዎችን ከዚህ ቀደም ማንም አያውቃቸውም። የጌታቸው አሰፋ ትሬዲንግ ከሶስት ወር ባልበለጠ ግዜ ውስጥ የ800 ሚሊዮን ብር ኮንትሮባንድ ዕቃዎችን በአየርመንገድ በኩል ግብር ሆነ ታሪፍ ሳይከፍል ያስገባ መሆኑን፣ ከቦሌ እስከ መርካቶ ላሉት የኤሌክትሮኒክስ ቤቶች፣ ካዛንቺስ ለሚገኙት ስተሺነሪዎች፣ ለፒያሳ ወርቅ ቤቶች የሚሸጡትን ዕቃ የሚያቀርበው በጌታቸው አሰፋ አስመጪና አከፋፋይ ነው።

አዲስ አበባ ውስጥ የሚሸጡት የወንድ ሱፍ ልብሶች፣ ሴቶች የሚያኝኩት #ትሪደንት ማስቲካ፣ 22 አከባቢ የሚጨሰው #ኮኬይን፣ ከቦሌ እስከ አራት ኪሎ የሚገኙት የኮምፒውተር፣ ሞባይልና ሌሎች ኤሌክትሮኒክስ መለዋወጫዎች አቅራቢ ይሄው ድርጅት ነው። ሌላው ቀርቶ ተክለሃይማኖት የሚገኙት የመኪና መለዋወጫ እና የመኪና ጎማ መሸጪያ ቤቶች ዋና አስመጪና አከፋፋይ በጌታቸው አሰፋ የሚመራው የኮንትሮባንድ ድርጅት ነው። ወዳጄ... "ጌታቸው አሰፋ መቀሌ ተደብቋል፣ የተባለውም የኮንትሮባንድ ንግድ ተቋርጧል" የሚል ሃሳብ ውል ካለህ ተሳስተሃል። ምክንያቱም በመግቢያው ላይ የጠቀስኳቸው ሶስት የአየርመንገድ ሃላፊዎች አሁንም ስራቸውን በመስራት ላይ ይገኛሉ።

በእርግጥ ቀድሞ የኮንትሮባንድ እቃ ወደ ሀገር ቤት ያስገቡ ነበር። አሁን ደግሞ የጌታቸው አሰፋን ዶላር በውድ ማዕድናት በመቀየር ወደ ውጪ በማሸሽ ላይ ይገኛሉ። ይሄ መረጃ ተራ አሉባልታ አይደለም። በራሱ በጌታቸው አሰፋ በሚመራው የብሔራዊ መረጃና ደህንነት መስሪያ ቤት ስር የነበሩ ጥቂት ሀገር ወዳዶች በህይወታቸው ከሞት እስከ እስራት የሚደርስ ውድ ዋጋ የከፈሉበት ነው። በዚህ ልክ በሙሉ ልብ የምናገረው በአንድ ምክንያት ነው። የዛሬው ትንታኔ በተጨባጭ የሰነድ ማስረጃ ላይ የተመሠረተ፣ ማንም እንዴትም ብሎ ሊያስተባብለው የማይችል ሃቅ እንደሆነ ስለማውቅ ነው። ከዚህ በላይ መቆየት አልፈልግም። የራሴን ትንታኔ ለማየት በዚህ ልክ ጓጉቼ አላውቅም‼️
ስዩም ተሾመ
https://www.youtube.com/watch?v=ni96IRj ... Ntbbi3ynys
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2454
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Re: ጌታቸው አሰፋ ትሬዲንግ፡ ከደህንነት ቢሮ እስከ አየርመንገድ የተዘረጋው የኮንትሮባንድ ንግ

Postby ቢተወደድ1 » Mon Sep 28, 2020 9:44 am

አማራን አባይን ተሻግረው ምን ያህል እንዳሞኙዋቸው በአደባባይ ከተነገረን በኋላ፤ ባሕር ዳር ጠርተው ያሞኛቸውን ግለሰብ ካባ አልብሰው ሸለሙት፡፡ ቂቂቂቂ
ይሄን የመሰል ስብእና በአደባባይ ሲሸጥና ሲዋረድ ማየት በ21ኛው ክ/ዘመን የፊልም ክንውን እንጂ እውነት አይመስልም ነበር፡፡
አይ አማራ (ብአዴን) ይሄን ያህል ነው ዜሮ ያገባችሁት፡፡ ያ ግራ የገባውስ አብን የምትሉት፤ ለዚህ ምላሽ አይኖረውም?? እንደዚህም ዘቅጣቹህ አልታያችሁም፡፡ አቤት በላይ ዘለቀ ይሄን ቢሰማ ምን ያረጋችሁ እንደነበር መተንበይ አይከብድም፡፡ ግን ያምርባቹሃል ቀጥሉበት፤ በርቱ፡፡
በአደባባይ ወጥቶ መሳደብ፤ ሰውን ማንቋሸሽ፤ ጥላሸት መቀባት ለሽልማት የሚያበቃ ቢሆን ኖሮ ሕወሃት እነ ታማኝ፤ አበበ ገላውና ኢሳትን ከነግብር አበሮቹ ስንት በሸለመ ነበር፡፡ ለነገሩ ግን የአማራ ክልል ገዢዎች እውነታው ስላስደሰታቸው ባሕር ዳር ድረስ ጠርተው ሸለሙት፡፡ ጉድ በል አማራ ዳስህን ጥለህ ሃዘን ተቀመጥ፡፡ እንደዚህም ተዋርዳቹህ አታቁም፡ መዋረዱንም የታለመዳችሁን ነው የምትመስሉት፡፡ ማን ነበር እስኪ አስታውሱን፤ የህወሃት ተላላኪ ነበርን ያለው? አገር የተበጠበጠችውም ተላላኪ ለሃላፊነት እንደማይበቃ ብቃታቹህ የታየበት የስራው ውጤት በመሆኑ ነው፡፡ ተላላኪነቱን ግን እንደቀጠላችሁበት ነው፤ ለግብጽና ኤርትራ፡፡ ማለቅለቁንም ተክናችሁታል፡፡ ታሪክ ሳይሆን እኛው እንፋረዳቹሃልን፡፡
ታማኝና ቴድሮስ ካሳሁን እናንተንም ክስተቱን አይታቹህ ምንም እንዳልተፈጠር አንደበታቹህ ሲዘጋ ስናይ፤ አፋቹህ ለሰብአዊነትና ለዲሞክራሲ ሳይሆን የዘር ጥላቻን ሲያርከፈክፍ እንደነበረ ካዋቅን ውለን ስላደርን አልገረመንም፡፡ ይሄን አይታቹህ ግን ዝም ትላላቹህ ብሎ ያሰበ አልነበረም፡፡ እናንተም አብራቹህ ደነዘዛቹህ?
የሚቀጥለውን ድራማ ለማየት ያብቃን፤
ሁለተኛውን ሽልማት ጎንደር ከተማ ታስተናግዳለች፡፡
ቢተወደድ1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 383
Joined: Thu Sep 01, 2016 8:48 am
Location: Bisheftu


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests