ለነጋሪ ሳይተርፉ የረገፉት የማይካድራ ቅጠሎች! "አራት የወለደችለትን ሚስት አርዶ የጠፋ አለ።"

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ለነጋሪ ሳይተርፉ የረገፉት የማይካድራ ቅጠሎች! "አራት የወለደችለትን ሚስት አርዶ የጠፋ አለ።"

Postby ኳስሜዳ » Fri Dec 04, 2020 10:39 pm

በ 30/02/2013 ትሕነግ የዘር ማጽዳት ጭፍጨፋ ማድረጉ ይታወቃል። በጥቅምት መጨረሻ በሕዳር መባቻ ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ ሳምሪ የተደራጁ ወጣቶች ቡድን የፍየል ግንባር በምታክለው ከተማ ሃምሳ ሃምሳ ሆነው በአራት ቡድን በመከፈል 49ኙ ካራ ገጀራ ፈራድ(ፋስ) መጥረቢያ ማጭድ የያዙ ሲሆን የቡድኑ መሪ ደግሞ ክላሽ ከእነ ትጥቁ የያዘ ነው። ከጭፍጨፋው መጀመር በፊት የአካባቢው ሚሊሻወችን በማገት እንዲሁም በመግደል አጥርተዋል በትግራይ ልዩ ኃይል። ዘጠኝ ሰዓት ጭፍጨፋው ሲጀመር መጀመሪያ ሑመራ ላይ እንዳደረጉት አውራ ባለሀብቶችንና ተሰሚነት ያላቸውን ሰዎች ቅድሚያ የሚገድል ስኳድ ግዳጁን ከዘጠኝ ሰዓት በፊት ፈጽሟል።

ሲጀምሩ ወራሪ መጥቷል ጦርነቱ ማይካድራ ደርሷል በማለት ኑ እናሽሻችሁ በማለት ሁለት ትራክተር ሕዝብ ከከተማው ራቅ ወደ አለ ስፍራ በመውሰድ ቶሎ ለመጨረስ በትግራይ ሚሊሻና ተኩስ በሚችሉ የሳምሪ አባላት ገድለው ባዘጋጁት ኤክስካቫተር (በባለሀብቶች የተሰጠ) በስሱ በመቆፈር ከቀበሩ በኋላ በድጋሜ በዚህ መንገድ ለመቀጠል ቢፈልጉም ሕዝቡ ቤቱን ዘግቶ በመቀመጡ ከተማው ጭር በማለቱ ወደ ቤት ለቤት ጭፍጨፋ ገብተዋል። ሲያጓጉዙበት የነበረው የአንዱ ትራክተር ሹፌር መምህር ሲሆን አንደኛው ደግሞ ተኬ ባህታ ለተባለው ባለሀብት በሰራተኝነት የተቀጠረ ነው። ይህ መምህር በያዘው ሽጉጥ በአንድ የአማራ ቤት ሳምሪዎች በሩን ከሰበሩለት በኋላ ባል ሚስትና ልጅን በመግደል ጭፍጨፋ ሲጀምር ለማምለጥ ሲሯሯጡ የነበሩ ሶስት ወጣቶችን በመግደል ሽንት በአፋቸው ከሸና በኋላ ሳምሪዎች በድንጋይ ጭንቅላታቸውን እንዲያፈርሱ አድርጓል። (በሕግ ጥላ ስር ሰውየው ያለ በመሆኑ ስሙን ይፋ ከማድረግ ተቆጥቢያለሁ) ተኬ ባህታ የተባለው ባለሀብት 10 ትራክተር ስለታማ መሳሪያዎችን ከመጋዝኑ እንዲጓጓዝ አድርጎ ሳምሪዎቹ ይዘዋል ተጠምቀ የተባለው ባለሀብት ደግሞ ሦስት ቢያጆ ተቀጣጣይ ፈንጅና መሳሪያ በሳጥን የታሸገ ተተኳሽ ጥይቶችን እንዲሁ አቅርቧል። በሁሉም የወልቃይት ከተሞች ትሕነግ ያቀደው 160 አውራ ተሰሚ ሰዎችንና ባለሀብቶችን ከእነ ልጆቻቸው መግደል ከዚህ በኋላ በየዙሩ 400 //400 ሰዎችን በመጨፍጨፍ መቅበር እንደ ነበር ከቦታው አረጋግጫለሁ። መጀመሪያ የከሸፈባቸው በአዲረመጥ/ወፍ አርግፍ ከተማ ነው ለዚህም ኑዋሪዎቹ አስተዳዳሪው ዋጋ ከፍሎ እቅዱን እንዳከሸፈው ነግረውኛል።

በማይካድራ ከዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ ከተማዋ ላይ ዘር ማጥፋት ጭፈጨፋ እስከ ሌሊቱ 10 ሰዓት ድረስ የቀጠለ እንደነበር ተራፊዎቹ ገልጸውልኛል። የተጎጂ ቤተሰብ እንኳ ሳያስተርፍ ሳምሪ የተባለው ቡድን ጭፍጨፋ አድርጓል። በአባዎራ ቤቶችና መጠጥ ቤት ባለቤቶች ከገደሉ በኋላ በስለት ሆዳቸውን እየቀደዱ ይሄ ጉበት ነው ይሄ አንጀት ነው ይሄ ልብ ነው ወዘተ እየተባባሉ ሲጨፍሩና ሲጠጡ እንደ ነበር ነው ኑዋሪዎቹ የሚያወሱት። "አሕያ አማራ" "ሀድጊ አምሐራይ" እያሉ ሆ እያሉ በመጨፈር ጭፍጨፋውን አሳልጠዋል። በትራክተር ከተወሰዱት 100 ሰዎች መካከል ለነጋሪ የተረፉት ሶስት ቢሆንም እኔ ማግኘት የቻልኩት አንዱን ብቻ ነው ስለ አገዳደሉ ሲገልጽልኝ "ውረዱ ልናስታጥቃችሁ ነው ስማችሁን ተመዝገቡ እያሉ በየተራ ወረድን የሚቀበለን ግን ጥይት ነበር። ትንሽ ከመቱ በኋላ ተጠቃቅሰን እየዘለልን ወደ ሸመጥ (ሳርና ትናንሽ እንጨት ያሉበት ጫካ መሳይ) እየገባን ሮጥን የተረፈ ግን የለም ሶስት ነነ ያመለጥነው"። ሲል አጋጣሚውን አሳታውሶ ገልጾልኛል።

የትግራይ ተወላጅ ሴቶችም ሳምሪዎችን ይደግፉ እንደነበር ኑዋሪዎቹ ነገረውኛል። "ሳምሪዎች ስር ለስር ገጀራቸውን ወደ ላይ አድርገው እየጨፈሩ ወደ ሰማይ አይመለከቱም ያንጊዜ የወሰዱት አደንዛዥ ነገር ይኖራል እንጂ ሰው እንዲህ አይሆንም ያመለጥቁት ዛፍ ላይ ወጥቼ ነው። ሁሉንም ተመልክቻለሁ ውሃ ሲሰጡ የነበሩ ሲሮጡ ሱሪያቸው ዝቅ ሲል ከፍ የሚያደርጉ ነበሩ።" ብለውኛል። በየቤቱ እየገቡ ሕጻን ሽማግሌ ሴት ሁሉንም ጨፍጭፈዋል። ባል ሚስትን ሚስት ባልን አርደው በደም ዘፍቀዋል "ማሽላ ውስጥ ሶስት ወልዳለት አረተኛ የወለደችለትን ሚስት አርዶ የጠፋ አለ" ብለውኛል ልጆቹ ትልቁ እስካሁን አፉ አይናገርም። አስከሬኑ ሽታው እኔ እከገባሁበት ጊዜ ድረስ ሽታው አልጠፋም መቼም የሚጠፋም አይመስለኝም። እስከ 5 ሜትር ድረስ የጉርጓዱን ጥልቀት በማርዘም የፈረሱ አስከሬኖችን በአንድ ላይ ቀብረዋል። ቁጥር አልባ መሆኑኑም ነግረውኛል። ለመቁጠር የተሞከረው ያልፈረሱ አስከሬኖችን ቶሎ የተገኙትን ነው ቢሆንም ግን አልተቻለንም ብለውኛል የሀገር ሽማግሌዎች። ቁጥሩ ከ2500 እንደሚልቅ ገልጸውልኛል ለዚህም" ከ6 በላይ ጅምላ መቃብሮችን ማን ቆጥሯቸው? እ ቶሎ አፈር እናልብስ ተከፋፍለን ወይስ እግር አንገት እንቁጠር አልተከፈኑም እኮ!" በለው በስስ ቁጣ አስረድተውኛል። ወጣት አለበል ደግሞ "ቁጥሩ ከተባለው ያልፋል ይህን የአስከሬኑ ሽታ ከ6ወር በኋላ ስለሚጠፋ አውጥቶ መቁጠር ይቻላል።" ሲል ነግሮኛል አክሎም ከከተማዋ ወጣ ባለ ስፍራ አዲስ ጅምላ መቃብር መገኘቱን ነግሮኝ ተመልክቻለው አቆፋፍሩ ሩቅ አይደለም ግን ሰፊና አደላደሉ የይድረስ ይድረስ መሆኑን አይቻለው ሽታ የለውም። ይህንንም ለጊዚያዊ አስተዳደር ለጸጥታ ኃይሉ እንዳመለከተ ነግሮኛል። በከተማዋ ኑዋሪዎቹ እህል ለሽማግሌና ለሕጻናት ካልሆነ ደፈር ብሎ በአፉ የሚያዙር በይፋ የተሟሟቀ ነገር የሚያደርግ የለም ጉልት ገበያዎች ፍዝ ሱቆችም ድንዝዝ ብለዋል ማይካድራ በደም ጎርፍ ታጥባለች ይህም መካነ መቃብሩ በመቀነቷ ካድራ ወንዝ ድረስ እንዲደርስ ሁኗል።
ኳስሜዳ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2894
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests