13 ከኒያዊያን Vs አንድ ኢትዮጵያዊ አሸናፊ ኢትዮ. !

ስፖርት - Sport related topics

13 ከኒያዊያን Vs አንድ ኢትዮጵያዊ አሸናፊ ኢትዮ. !

Postby ጎራዴው » Fri Oct 07, 2005 9:10 pm

ባለፈው ሳምንት በ ESPN ቲቪ ቻናል በቀጥታ በተላለፈው የፍላደልፊያ ግማሽ ማራቶን ሩጫ አንድ በጣም አኩሪ ፉክክር ታይቶበታል:: ጋዲሳ ሻንተማ የተባለ አዲስ ኢትዮ/ዊ ወጣት ሯጭ ከ13 ከኒያዊያን ጋር እስከ መጨረሻ የሞት የሽረት ተፎካክሮ 300 ሜትር ያህል ሲቀር በጣም በአስደሳች ሁኔታ ተስፈንጥሮ ከኒያዊያኖችን አስከትሎ በመግባት አሸንፏል:: በሰዐቱ ውድድሩን ያስተላልፉ የነበሩ ኮመንታትሮች ያበሾችን ጥንካሬና የከኒያዊያንን ከኛ ጋር ያላቸውን እልህ ሲተነትኑ መስማት በጣም ያስደስት ነበር::
Wounds from the knife are healed, but not those from the tongue.

በብረት ስለት የቆሰል ወዲያው ይድናል :: በምላስ ለቆሰለ ግን መዳኛ የለውም
ጎራዴው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 227
Joined: Fri Dec 31, 2004 4:51 am
Location: united states

Postby Geni_LA » Sat Oct 08, 2005 6:48 pm

ጎራድው ሩጫውን አይቸዋለሁ:: ኮሜንታተሮች ሲናገሩ እንደሰማሁት ልጁ አዲስ አይደለም:: በሀዋይ ማራቶን 3ነት ዲሲ ላይ ደግሞ 1ኛ ወጥቶ እንደነበረ ነው:: ሻንተማ ጋዲሣ መልኩም ቁመናውም ራሱ መእራብ አፍሪካዊ ይመስላል:: :lol: :lol: በተለይ መጨረሻ ላይ ሲያሸንፍ ምንም አለመድከሙና ጉልበቱን አለመቸረሱ ይታወቅበት ነበር:: እኔም ደስ ብሎኛል:: 8)
Geni_LA
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 35
Joined: Sun Dec 19, 2004 1:17 am
Location: united states

እኔን ያልተረዳኝ ነገር ቢኖር?

Postby ላሊበላ4 » Sun Oct 09, 2005 2:14 pm

ኬኒያዊያን ለምንድነው ኢትዮጵያ ላይ ብቻ ጥላቻና የጥላቻም ውድድር የሚያደርጉት::

1አንድ ለ13ሶስት ይዘው እንደዚያ መድከማቸው በጀግናው ኢትዮጵያዊ ወገናቺን ተረተዋል::

ያሳዝናሉ:: ከሃይሌ ገ/ሥላሴ ጋር ያደርጉ የነበሩት ውድድር:: እሱን ቀድሞ የሱን ክብረወሰን ለመንሣት ያደረጉት ግፊያና ጉንተላዎች::

ቀነኒሳንም ለመወዳደር የሚያደርጉት:: ሲሂንን ለመወዳደር ያደረጉና በሄሌሲንኪ/ፊላንድ ላይ/ ከድሉ በኌላ የሰጠው ኢንተርቪው ስለሺን ብቻ ለማሸነፍ ነበር የሮጥኩት ማለቱ ደስተኛ ነኝ ሲል የነዚህ ሰዎች ጠላቶች አይመስሏቺሁም በስፖርት ዓላም መሸነፍና ማሸነፍ ባህል ነው:: ቅርም አያሰኝም:: ግን እነሱ በኢትዮጵያ ማሸንፍ ዘለዓለማቸውን ይቀናሉ?

ከምስጋና ጋር

ላሊበላ4
ላሊበላ4
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 201
Joined: Fri Dec 24, 2004 8:47 pm
Location: united states

ቪቫ ደራርቱ! እንደጠበቅንሽ!!

Postby ትምህርት » Sun Oct 09, 2005 6:12 pm

Image
WOMEN

Derartu Tulu produced a brilliant performance to shatter the Ethiopian 10 Mile record with a winning time of 51:27 in the women's race.

Tulu, who previously won the race in 1996, was well inside the former national record of 52:55 set three years ago in Washington DC by Teyiba Erkiso

Four people died while taking part in the race, which had some 47,000 participants. Northumbria Police said the four were male competitors but gave no further details.http://slam.canoe.ca/Slam/Track/2005/09/18/1222585-ap.html
ትምህርት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1056
Joined: Sun Mar 21, 2004 7:31 pm
Location: somalia

Re: እኔን ያልተረዳኝ ነገር ቢኖር?

Postby ጎራዴው » Tue Oct 11, 2005 6:45 pm

ላሊበላ4 wrote:ኬኒያዊያን ለምንድነው ኢትዮጵያ ላይ ብቻ ጥላቻና የጥላቻም ውድድር የሚያደርጉት::

1አንድ ለ13ሶስት ይዘው እንደዚያ መድከማቸው በጀግናው ኢትዮጵያዊ ወገናቺን ተረተዋል::

ያሳዝናሉ:: ከሃይሌ ገ/ሥላሴ ጋር ያደርጉ የነበሩት ውድድር:: እሱን ቀድሞ የሱን ክብረወሰን ለመንሣት ያደረጉት ግፊያና ጉንተላዎች::

ቀነኒሳንም ለመወዳደር የሚያደርጉት:: ሲሂንን ለመወዳደር ያደረጉና በሄሌሲንኪ/ፊላንድ ላይ/ ከድሉ በኌላ የሰጠው ኢንተርቪው ስለሺን ብቻ ለማሸነፍ ነበር የሮጥኩት ማለቱ ደስተኛ ነኝ ሲል የነዚህ ሰዎች ጠላቶች አይመስሏቺሁም በስፖርት ዓላም መሸነፍና ማሸነፍ ባህል ነው:: ቅርም አያሰኝም:: ግን እነሱ በኢትዮጵያ ማሸንፍ ዘለዓለማቸውን ይቀናሉ?

ከምስጋና ጋር
ላሊበላ4


ወንድሜ ጥሩ ብለሀል::
በልጦ ወይም ተሽሎ ለመገኘት መንፈሳዊ ቅናት አስፈላጊ ቢሆንም:- የነሱ በዛዛ! ባለፈው ከዐለም ሻምፒዮና ጥቂት ቀናት በፊት ቀነኒሳ በ10K ሪከርድ ሲሰብር የነሱ ኔሺን ጋዜጣ
<ሪኮርድ በአንድ ሰው ስለተሰበረ ማለት ኬኒያዊያን ይሸነፋሉ ማለት አይደለም:: ኢትዮጵያዊያን ይህን ማስፈራሪያ አርገው ሲሸልሉ ያላቸውን አንዱን ቀነኒሳ ወጥረን ካደከምነው ሌሎቹ ቀላል ናቸው::> በማለት በዘገበ ማግሥት ልጆቻችን ተከታትለው ገብተው አሸነፉ:: በማግሥቱ የዛ ጋዜጣ አዘጋጅ አፍሮ ነው መሰለኝ ውጤቱን ብቻ ዘግቦ ሪፖርቱን ባጭሩ ዘጋ::

የኬኒያ ሚዲያዎች ብዙ ጊዜ ተቀናቃኞቻቸው አይለው ሲገኙ ምክንያት የሚያደርጉት የልጆቻቸውን ወይም የአሰልጣኛቸውን ድክመት እንጂ የለላውን ወገን ጉብዝና ማንሳት አይወዱም:: ቢጨንቃቸው ሀይሌንና ቀነኒሳን ግን ሞኒስተርና ሥጋ ለባሽ ሮቦት እያሉ ይጠራሉ:: :wink: ግን አንድ ነገር ደስ የሚለኝ ነገር ቢኖር አገራቸውን ከኛ ያደገና የተሻለ ሀብታም አርገው እያንቋሸሹ ሲቦስቱ በገንዘብ እየታለሉ የሚኮበልሉ ከኢትዮጵያዊያን ይልቅ አብዛኛዎቹ ኬኒያዊያን ሆነው መገኘታቸው ነው::
Wounds from the knife are healed, but not those from the tongue.

በብረት ስለት የቆሰል ወዲያው ይድናል :: በምላስ ለቆሰለ ግን መዳኛ የለውም
ጎራዴው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 227
Joined: Fri Dec 31, 2004 4:51 am
Location: united states

Postby ናኦድ » Tue Oct 11, 2005 7:14 pm

ይህ አዲስ አይደለም
የሚገርመው ደግሞ 20 ኬኒያዊያን በሚሮጡበት አንዱ ሀበሻ ካለ አንዱ አበሻ ሲያስጨንቃቸው ይታያል:: በረጂም ርቀት ሩጫ በድምሩ ኬኒያዊያን ብዙ ጊዜ የሚያሸንፉት ሁሌም እነሱ በገፍ ሯጭ ስለሚያሳትፉ እንጂ ከኛ በልጠው አይደለም::
ናኦድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 156
Joined: Fri Dec 10, 2004 5:03 am
Location: የተባበሩት የአሜሪካ ግዛት :

Postby አደቆርሳ » Tue Oct 11, 2005 7:38 pm

ጎራዴው አመሰግንሀለሁ !
የኬንያውያን በውድድር መኖር ለኢትዮጵያውያን ድል
ሲሆን የኢትዮጵያውያን በውድድር መኖር ግን ለኬንያውያን ሽንፈት(ምጥ)ነው::
በኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳልያው ባለቤት ሶስት ሺህ ዶላር ብቻ በሚከፈልበት አንድ ትንሽ ዝግጅት ላይ ለመካፈል:ጨርቁን ጥሎ ይሄዳል.ለዚያውም ይሸነፋል.
በአጠቃላይ በዓለም ስፖርት አፍቃሪው ዘንድ ተወዳጅነታቸው እጅግም ነው::
Image
kibremengist
አደቆርሳ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 977
Joined: Wed Aug 03, 2005 5:50 pm
Location: ethiopia


Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests