ያለም ዋንጫ ላይ አፍሪካን የሚወክሉ

ስፖርት - Sport related topics

ያለም ዋንጫ ላይ አፍሪካን የሚወክሉ

Postby ትህትና2 » Mon Oct 10, 2005 10:52 am

ሰላም ኳስ ወዳጆች ,

እደሰማችሁት ቶጎ ,አይቬሪኮስት, ጋና እና አንጎላ አፍሪካን ወክለው ጀርመን አለም ዋንጫ ላይ ሊስሳተፉ ነው. ቶጎ ሀገር ዛሬ ሰራ የለም አሉ. በደስታ ብዛት ፕሬዝዳንቱ ነው ያወጀው.

እኔ በካሜሮን እና ናይጄሪያ አዝኛለሁ. በነ ሮጀር ሚላ ግዜ የተገኘሁን ደስታ...ሳስብ...ያኔ ያለም ዋንጫ ግዜ....ሮጀር ሚላ እንዴት እንደደነስ ትዝ ይለኛል. አሁንም በጨዋታ የጠነከር ቡድን ወደ ጀርመን ቢሄድ 8 ሀገሮች ዉስጥ የመገባት እድል ነበርን. ኢቭን 4 ዉስጥም. ሴኔጋል እንኩዋ የለም. What a disappointment. ግን ደሞ እንዳየነው ያለፈውን ያውሮፓ ዋንጫ "ግሪክ " ነች የወሰደችው. You never know.

ነገሩ ኳስ እድልም..........ያስፈልገዋል. እንግሊዝም ያው በሆላንድ እርዳታ ለአልም ዋንጫ ኳዋሊፍይ እንዳረገች ነው ትላንት እንደተዘገበው.
ትህትና2
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1362
Joined: Sun Jan 09, 2005 1:47 am
Location: ethiopia

ትህትና ሮጄር ሚላን አልሽ እስኪ

Postby ONLINE ጠንቆይ » Mon Oct 10, 2005 8:06 pm

ትህትና ሮጀር ሜላን በነበረበት ግዜ የነበርሽ ሰው ከሆንሽ አሁን እድሜሽን ስኮለኩለው 1990-2005
ከአስራ አምስት አመት በፊት ማለትም ምናልባት የ20 አመት ሰው ትሆኝ ነበር ምክንያቱም ብዙ ትዝታ አለሽ ስለዚህ አሁን የ35 አመት እመቤት ነሽ እድሜ ጸጋ ነው ወይ መታደል እስኪ ለሁሉም ትንሽ ልጠንቁል በአሁኑ ሰአት አፍሪካን ወክለው የሚሄዱት ሀገሮች ከቱኒስ በስተቀር ሁሉም በጣም በአውሮፓ ውስጥ ስታር ባይባሉም ነገር ግን እንደእነ ጉራምባው አይነት የቼሊስ ስታር በአሁኑ ሰአት ለመጀመሪያ ግዜ በአፍሪካ ታሪክ ውስጥ በትልቅ እንግሊዝ ፓውንድ የተዛቀው ውድ እና በአለማችን ብቸኛ የመሀል ተጫዋች ተብለው ከሚመደቡት መካከል ማይክል እሴይን እንዲሁም የጣሊያኑ ኡዴነዚ የዴቹም እያልኩ የጀርመኑም እያልኩ ብቀጥል ግዜ ያንስብኛል እኔ ትንሽ የሚያሳስበኝ ነገር በተጫዋቾቻችን ላይ አድልዎ ከተደረገ እና እንዲህም ከዴዝ ጉሩፕ አውቀው በተንኮል ካስገቦቸው እንጂ አይቬሪኮስት እና ጋና ፍጻሜ ላይ ይደርሳሉ ብል 99% ሀሰተኛ አይደለሁም
ከቱኒስ ይልቅ ሞሮኮ አለመምጣቱ በጣም ነው ያዘንኩት ምክንያቱም ቱሲት ብዙ ኢንተርናሽናል እድል አግኝተው ተልፈስፍሰው ነው የቀሩት አዲስ እስታር የምናይበት ግዜ እንደሚሆን ከዚሁ ጠንቁያለሁ ጥንቆላዬ ይህ ነው
አይቬሪኮስት ብራዚንል 3-0
ጋና እንግሊዝን 5-0
ቶጎ አሜሪካንን 20-0
ቱኒስ ጃፓንን 2-2
አንጎላ ኢራንን 12-6
በሁለተኛው ዙር ደግሞ
አይቬሪኮስት ስፔንን 2-0
ቶጎ ጀርመንን 3-0
የአፍሪካው ብራዚል ብራዚልን 6-0 ያዋርዳል
ቱኒስት በመጀመሪያ ጨዋታ ዙር ወደቤቱ ይሄዳል
ወደፍጻሜ የሚደርሱት ጋና እና አይቬሪኮስት ብቻ ናቸው ይህንን ደግሞ በአይናችን እናያለን ኖ ሞር አውሮፓ ቪቫ ጋና አይቬሪኮስት
ለዋንጫ ፍጻሜ ለመድርሰ ከጋና እና ከአይቬሪኮስት ጋር የሚጫወቱት ቡድን ቶጎ እና አንጎላ ብቻ ናቸው
ኖ ሞር ብራዚል , ኖ ሞር ጀርመን ኖ ሞር ስፔን የፈለጋቹኅትን ጥሩ አፍሪካ ለመጀመሪያ ግዜ የአለምን ዋንጫ ይወስዳል በሁለት ታላላቅ አፍሪካ ቡድኖች በጋና እና በአይቬሪኮስት ከዚያም ዋንጫውን ይካፈላሉ
ለሁሉም እስኪ ይህንን ተመልከቺ
http://fifaworldcup.yahoo.com/06/en/p/cp/cmr/milla.html
አልደረስኩም
ኦንላይን ጠንቆይ
ከነማመዬ ሰፈር
ONLINE ጠንቆይ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 9
Joined: Mon Oct 10, 2005 7:25 pm
Location: gibraltar

Re: ትህትና ሮጄር ሚላን አልሽ እስኪ

Postby ትህትና2 » Mon Oct 10, 2005 9:35 pm

ONLINE ጠንቆይ wrote:ትህትና ሮጀር ሜላን በነበረበት ግዜ የነበርሽ ሰው ከሆንሽ አሁን እድሜሽን ስኮለኩለው 1990-2005
ከአስራ አምስት አመት በፊት ማለትም ምናልባት የ20 አመት ሰው ትሆኝ ነበር ምክንያቱም ብዙ ትዝታ አለሽ ስለዚህ አሁን የ35 አመት እመቤት ነሽ እድሜ ጸጋ ነው ወይ መታደል


:lol: ታዲያ የዛሬ ልጆች እኮ በእድሜዬ መከበር ሲኖርብኝ አላከበሩኝ. ተባረክ አንተ ብቻ ነህ ያከበርከኝ. በእርግጥ በሀያ አመታቸው እግር ኳስ ማየት የጀመሩ ስዎች ብዙ ትዝታ መናገር ቢችሉም , እውቀቱ አብሩዋቸው ስላላደገ እንደኔ እውቀተኛ የሚሆኑ አይመስለኝም. :lol: :lol: .ኳስ እኮ ከልጅነት ጀመሮ መወደስ ያለበት ነገር ነው. (አርፍዳቸሁ ለጀመራችሁ ከይቅርታ ጋር :lol: ) ሮጀር ሚላን በደምብ አስታወስዋለሁ. ግብ አግብቶ እንዴት ሮጦ ኮርነር የሚመታበት ጋር ቆሞ እንዴት እንደደነስ እስካሁን አይኔ ላይ አለ ከዚህ ሁሉ አመታት ቦሀላ. ጎበዝ አይደለሁ ? :lol: :lol:. እነ ማካናኪን ,እነ ላርሰን (ስዊድን ) ,እነ ቆንጆ ካኒጃን :lol: ,እነ ቶማስ ሀስለርን , በነሩዲ እና ክሊንስማን ,እነ ማልዲኒ ኪውቲ :lol: ዘመን የነበሩትን ሁሉ አስታወሳለሁ.ወይ ሞት ይርሳኝ....ባጂዮን ረሳሁት ! አሁንስ እውነትም አረጀሁ ! የነፕላቲኒ እና የነፔሌ ዘመን ብቻ ነው ትንሽ ያመለጠኝ. :lol: ግን እነሱንም ቢሆን በማወቂያ አቃለሁ እንዳቅሚቲ. :lol:

በእርግጥ 4 ዉስጥ ብንገባ ደስ ይለኝ ነበር. በጋና ኮንፊደንስ አለኝ.እድሜ ይስጠን እስቲ.አንጎላዎች ዘነጡ ነው የሚባለው. አለም ሊያያቸው ነው. :lol: .በዚህ አይነት ኢትዮጵያም ተስፋ አላት...የዛሬ 8-12 አመት.እኔ ሳልሞት ባይ... ምኞት አይከለከል. አቶ ይድነቃቸው ተሰማ እንኩዋ አላዩም. አቶ ይደነቃቸውን ታቃቸዋለህ በስም ?

ቤት ዉስጥ ላላችሁ ወጣቶች በተለይ የስፖርት ፍቅር ያላችሁ አቶ ይደነቃቸው ተስማን በስም መለየት አለባችሁ. ለኢትዮጵያ ስፖርት በጣም ትልቅ አስተዋጾ ያደርጉ በጣም ትልቅ ሰው ናቸው. ፊፋ ዉስጥ ሳይቀር አባል ሆነው የስሩ ብዙ ቋንቋ የሚናገሩ ,ትልቅ መጽሀፍ አንባቢ ,የስፖርት ሚንስተር ሆነው ያገለገሉ ከዚህ ምድር በ 63 አመታቸው ከ 20+ አመት ምናምን በፊት (ይመስለኛል ) በህመም ያለፉ ሰው ናቸው. ያፍሪካ የስፖርት ፌዴሬሽን "አለት" ብሎ የጠራቸው ጠንካራ የነበሩ ሰው ናቸው. ከስራቸው ሁለት ብጠቅስ...

1) ደቡብ አፍሪካ አፍሪካ ሆነ የምን ዋንጫ ላይ እንዳትሳተፍ አድርገዋል አፓርታይድ ሰለነበረ( አፓርታይድ አስካልተወገደ ድረስ )

2) ስታዲዮም ዉስጥ የሲጋራ ማስታወቂያ እንዳይታይ ወይም ሲጋራን ፕሮሞት ለማድረግ ስፖርት ሜዳ ውስጥ ምንም ነገር እንዳይፈቀድ ያደረጉ ሰው ናቸው

ብሉ ይህን በቃላችሁ እንደታጠኑ! :lol:
ትህትና2
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1362
Joined: Sun Jan 09, 2005 1:47 am
Location: ethiopia

ትህትና እኔ እኮ 1000 አመት አለፈኝ

Postby ONLINE ጠንቆይ » Mon Oct 10, 2005 10:00 pm

እድሜዬ እኮ 999 አልፎ 2006 ሲመጣ 1000 አመቴን አከብራለሁ እኔ እኮ 10 ዙር እየኖሩኩ ነው ያለሁት አንቺማ ገና ጩጬ ነሽ እደጊ ተመንደጊ
የእግር ኮስ ጠንቆይ
ከጀርመን ራዲዬ
ONLINE ጠንቆይ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 9
Joined: Mon Oct 10, 2005 7:25 pm
Location: gibraltar

Re: ትህትና እኔ እኮ 1000 አመት አለፈኝ

Postby ትህትና2 » Mon Oct 10, 2005 10:03 pm

ONLINE ጠንቆይ wrote:እድሜዬ እኮ 999 አልፎ 2006 ሲመጣ 1000 አመቴን አከብራለሁ እኔ እኮ 10 ዙር እየኖሩኩ ነው ያለሁት አንቺማ ገና ጩጬ ነሽ እደጊ ተመንደጊ
የእግር ኮስ ጠንቆይ
ከጀርመን ራዲዬ


የአቶ ይድነቃቸው ተሰማን የጻፍኩትን አንብበህ ለሌላም እንድታስተምር :lol: .ግን የጻፍኩት ከስራቸው 2% ብቻ ነው.
ትህትና2
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1362
Joined: Sun Jan 09, 2005 1:47 am
Location: ethiopia

Postby ጊዮርጊስ » Fri Dec 02, 2005 11:49 pm

ውድ ትህትና ቅ. 2

ይህ ርእስ በጣም ጥሩ ነው:: እንደውም ኢትዮጵያስ መቼ ነው ተራ የሚደርሳት ቢጨመር ደስ ይላል:: በዘንድሮው የአለም ዋንጫ ከአፍሪካ ያልፉት ቡድኖች ጥሩ ናቸው:: አንቺ/አንተ /ለጊዜው. አንቺ ላበል/ ያዘንሽላቸው ቡድኖች ባያልፉ እመርጣለሁ:: ውድድሩን ርስት አርገው ይዘውት ነበር:: በርግጥ የድሮው ካሜሮንም ሆነ ናይጄሪይ አሁን አይገኙም:: በሮጀር ሚላ ጊዜ ብዙ ውበት ያለው ጨዋታ የሚጫውቱ ልጆች ነበሩ:: ለምሳሌ አቤጋ (ካሜሩን), አሞካቺ, ያኬኒ, (ናጄሪያ), አ. ፔሌ (ጋና) እና የመሳሰሉት.....ለነገሩ በዛ ወቅት አልጄሪያ (እን ቤሎሚ) ና ግብጽም የዋዝ አልነበሩም..አሁን ግን ተረት አደረጉት...
ከቅርብ ጊዜ ወዲህማ የአፍሪካ እግር ኳስ በጣም የሚያስጠላ ሆኗል:: እኔማ ባያልፉ ሁሉ ደስ ይልኛል:: ትንሽ ሳሙኤል ኤቶ ቢታይ ደስ ይልኛል::

ስለ ይድነቃቸው ተሰማ የተጻፈው ከልብ የሚያርካ ነው ግን ያንሳል:: የሚጨመር ካል ብትጨምሪበት ደስ ይላል ያልዛ በስፊው እጨርሰዋልሁ::
ጊዮርጊስ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 45
Joined: Sun Oct 16, 2005 2:36 pm
Location: ethiopia

Postby ሳምሶን13 » Sat Dec 03, 2005 2:57 pm

:lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:
ሳምሶን13
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 207
Joined: Wed Sep 15, 2004 3:48 pm
Location: sudan

Postby ትህትና2 » Sun Dec 04, 2005 6:29 pm

ጊዮርጊስ wrote: አንቺ/አንተ /ለጊዜው. አንቺ ላበል/ ያዘንሽላቸው ቡድኖች ባያልፉ እመርጣለሁ:: ውድድሩን ርስት አርገው ይዘውት ነበር:: በርግጥ የድሮው ካሜሮንም ሆነ ናይጄሪይ አሁን አይገኙም::
ስለ ይድነቃቸው ተሰማ የተጻፈው ከልብ የሚያርካ ነው ግን ያንሳል:: የሚጨመር ካል ብትጨምሪበት ደስ ይላል ያልዛ በስፊው እጨርሰዋልሁ::


አንዱ አበሻ ስለናይጄሪያዎች ሳወራ ሰምቶ "አንቺ ለነዚህ ኢዲየቶች ታዝኛለሽ ? ያኔ እኮ "ዳቦ" ስቴዲየም ወርውረውብናል " ብሎ በሳቅ ሲገለኝ ነበር. የምስራቅ አፍሪካውን ዋንጫ ያሸንፈን ግዜ ነው መሰል ያረጉት እንደዛ. ለማንኛውም አለምኖራቸው ይጎናል ባይ ነኝ.
የአቶ ይድነቃቸው ተሰማን ታሪክ ፕሊስ በደምብ አርገህ ጨርሰው. አባቴ ሊያመልካቸው ምን ቀረው. ስራቸውን በደምብ ያቃል.
ትህትና2
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1362
Joined: Sun Jan 09, 2005 1:47 am
Location: ethiopia

Postby ትህትና2 » Sun Dec 04, 2005 6:35 pm

ሳምሶን13 wrote::lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:


አንዴ አንዱ "ናይጄሪያዊ" ስለሀገሩ ጥሩነት ሲያወራ እኔ በኳስ ጥሩ እንደሆኑ ስናገር ሆዱን ይዞ እስኪያመው ደርስ የእውነት ተጎንብሶ ሳቀ . የሳቀበትን ምክንያት ,ነገሩን በጥሞና ብመረምረው ,ባለኝ ጥበብ ባወጣ ባወርደው,መልሱን አልደረስኩበትም. ሳምሶን አሁንም ያንተን 'ፈግታዎቹን" አይቼ ,በጥበቤ ልረዳው እንዳልቻልኩት.

ኦ ማይ ጋድ......ለምን እንደተሳለቀብኝ አሁን ገባኝ ! ያኔ ዳቦ እንደወረወሩብን "ትዝ" ብሎት ነዋ ? እኔኮ ከኔ አፍ የኳስ ወሬ ስለመጣ የሳቀብኝ መስሎኝ ነበር. ወይ ነዶ ቢግ ታይም !
Last edited by ትህትና2 on Sun Dec 04, 2005 9:55 pm, edited 1 time in total.
ትህትና2
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1362
Joined: Sun Jan 09, 2005 1:47 am
Location: ethiopia

Postby ጊዮርጊስ » Sun Dec 04, 2005 9:29 pm

ውድ ትህትና

ናይጄሪያ ዳቦ የወረወሩት በ 1977 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ላይ ነው:: በዛ ጨዋታ 3 - 0 አሸንፈውን ሄደዋል::

ስል ይድነቃቸው ተሰማ ይህን አንብበው/አንብቢው

http://ethiosports.com/Ydnekachew.html

አመሰግናለሁ
ጊዮርጊስ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 45
Joined: Sun Oct 16, 2005 2:36 pm
Location: ethiopia

Postby ትህትና2 » Sun Dec 04, 2005 9:37 pm

ጊዮርጊስ wrote:ውድ ትህትና
ናይጄሪያ ዳቦ የወረወሩት በ 1977 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ላይ ነው:: በዛ ጨዋታ 3 - 0 አሸንፈውን ሄደዋል::


ጊዮርጊስ,
ያሸነፉበት ጨዋታ ላይ ነው እንዴ ዳቦውን የወረወሩት ? ማለቴ ምክንያቱ "ንዴት" አይደለማ ! ዳቦውንስ አስበው ለመወረወር ነው ይዘው የነበረው ወይስ ገዝተው ነው ? አንዳንዱ ነገር እኮ እንዴት ያስቃል. ቅቅ. በል ካሁን ወዲያ ናይጄሪያ ነኝ ያለኝን ግልምጥምጡን አውጥቼለት ነው የምሄደው :lol: :lol: ከጨዋታ ቦሀላ ማልያ ልውውጥ ላይ የኛ ልጆች ይሽሹ ነበር አሉ ምክንያቱም ማልያውን የሚያወጡት እቃ አሲዘው ነው እና ማልያውን የሰጠ ይከፈል ነበር እያሉ ሲያስቁኝ ነበር.
ትህትና2
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1362
Joined: Sun Jan 09, 2005 1:47 am
Location: ethiopia

Postby ጊዮርጊስ » Mon Dec 05, 2005 6:53 pm

አንቺን ያሳቀሽ ነገር በርግጥ የሚያጋጥም ነው:: እንደምታቂው ብሄራዊ ቡድኑም ሆነ ክለቦች ያላቸው የፋይናንስ አቅም ውስን ነው:: በአመት ላንድ ተጫዋች ከሶስትና ከአራት ማልያ በላይ አይሰጠውም ስለዚህ ከጨዋታ በኌላ ማልያ ለክለቡ ይመልሳሉ:: በርግጥ Intenational ጨዋት ከሆነ እንዲለዋውጡ ይፈቅድላቸዋል:: /ግን አሁን ከኛ ተጫዋች ጋር ማን ይለዋወጣል?/:: እንደዛም ከሆን እንኳን ከአንድ አያልፍም:: በርግጥ ሀብታም የሚባሉት ክለቦች ይህ ይፈቀድላቸው ይሆናል:: ለምሳሌ ባንኮች; ቡና ገበያ; ቅ. ጊዮርጊስ የመሳሰሉት...ሌሎቹ ግን እንኳን ለመቀያየር ለራሳቸው ቅያሪ የላቸውም:: አንድ አጋጣም ላንሳልሽ....ከአንድ ወይም ከሁለት አመት በፊት ኢትዮጵያ ላፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመጨረሻ ጨዋታ ጊኒ ላይ ስታኪያሂድ ማልያቸው ከጊኒ ጋር ተመሳስሎ ስለነበር እንዲቀሩ ሲነገራቸው ሌላ አይነት ባለመያዛቸው ከጊኒ ገበያ ገዝተው ተጫውተዋል:: በጣም የሚገርመው..... ነገር ግን ብዙ ሰው ልብ ያላለው ነገር የተገዛው ቁምጣ የአርሰናል አርማ ያለበት ነበር:: ስለዚህ የክለብ አርማ ለጥፎ የተጫወተ የመጀመሪያው ብሄራዊ ቡድን የኛ ብቻ ይመስልኛል:: ባለ ሪከርድ ደሀ መሆናችን አይደል::

ለዛሬ እዚህ ላይ ላብቃ

ሰላም
ጊዮርጊስ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 45
Joined: Sun Oct 16, 2005 2:36 pm
Location: ethiopia

Re: ትህትና ሮጄር ሚላን አልሽ እስኪ

Postby ጎራዴው » Tue Dec 06, 2005 11:04 pm

ONLINE ጠንቆይ wrote:ጋና እንግሊዝን 5-0
ቶጎ አሜሪካንን 20-0
አንጎላ ኢራንን 12-6
በሁለተኛው ዙር ደግሞ
የአፍሪካው ብራዚል ብራዚልን 6-0 ያዋርዳል
ኦንላይን ጠንቆይ
ከነማመዬ ሰፈር


ቅቅቅቅቅ
አይ ጠንቋይ የአሜሪካንን ፉትቦል የምትዘግብ ያስመስልሀል:: ለመሆኑ 12 ያገባው 6 የሚገባበት ምን ሆኖ ነው? 12 አግቢዎች ከእንግዲህ በረኛ አያስፈልጋችሁም ተብለው ከተጠየቁ ምናልባት ያስኬዳል:: :lol: :lol: :lol:
Wounds from the knife are healed, but not those from the tongue.

በብረት ስለት የቆሰል ወዲያው ይድናል :: በምላስ ለቆሰለ ግን መዳኛ የለውም
ጎራዴው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 227
Joined: Fri Dec 31, 2004 4:51 am
Location: united states

ምድብ ታውቋል

Postby ትህትና2 » Fri Dec 09, 2005 10:34 pm

የጀርመኑ አለም ዋንጫ ምድብ አሁን ወጥቷል

ቡድን A
ጀርመን, ኮስታሪካ ,ፖላንድ , ኤኳዶር
-ወይ ነዶ! ጀርመን አለፈች የመጀመሪያውን ዙር. 150% እርግጠኛ. ለዛው እኮ ተጫዋች የላቸውም !!!

ቡድን ቢ
እንግሊዝ , ፓራጓይ , ትሪኒዳድ ቶባጎ , ስዊድን
-እንግሊዝ ባትዝናና ይሻላታል. :lol:

ቡድን ሲ
አርጀንቲና ,ኮትዲቧር , ሰርቢያ ሞንትኔግሮ , ሆላንድ
-ይህ በእውነቱ ከባድ ነው ለኮትዲቧር. ያ ድሮግባ ኮከብነቱን ያሳይ እስቲ.

ቡድን ዲ
ሜክሲኮ , አንጎላ , ኢራን ,ፖርቹጋል
-እዚህ አንጎላ ተስፋ አላት. ሜክሲኮ ፈጣን ቡድን ነው. ሰውረነ !

ቡድን ኢ
ጣሊያን, ጋና , አሜሪካ :lol: , ቼክ
-የቼክን ኳስ ለማየት እናፍቃለሁ.ኦፍኮስ የመጀመሪያውን ዙር ያልፋሉ. ጋና አሜሪካን መቅጣት አለባት.

ቡድን ኤፍ ,
ብራዚል ,አወስትራሊያ, ጃፓን, ክሯሲያ
-ብራዚል በክሯሽያ ጉዷ ይፈላል. አወስትራሊያ እና ጃፓን ከወዲሁ ቻው.

ቡድን ጂ
ፈረንሳይ ,ቶጎ ,ስዊዘርላንድ ,ኮሪያ
-ቶጎ በጣም ትልቅ ተስፋ አላት. ፈረንሳይ በመጀመሪያ ዙር የወጣችበት ያለም ዋንጫ የቅርብ ትዝታ ነው.

ቡድን ኤች ,
ስፔን ,ዩክሬን , ቱኒዚያ , ሳውዳረቢያ
-ጠንካራ ዩክሬን ያለምንም ጥርጥር የመጀመሪያውን ዙር አለፈች. ቱኒዚያ እና ስፔን እኩል እድል አላቸው.

ምን ተስፋ አለ ላፍሪካ ?

ላላያችሁ ሮጀር ሚላ እና ፔሌ መጥተው ነበር. ውይ ሚላዬ ትልቅ ሰው ሆኗል. ፔሌ መቼም የማያረጅ ሰው.
ትህትና2
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1362
Joined: Sun Jan 09, 2005 1:47 am
Location: ethiopia

Re: ምድብ ታውቋል

Postby ጊዮርጊስ » Sat Dec 10, 2005 5:42 pm

-ብራዚል በክሯሽያ ጉዷ ይፈላል.አትፍሪ......4 - 0 ብራዚል ያሸንፋል::
ጊዮርጊስ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 45
Joined: Sun Oct 16, 2005 2:36 pm
Location: ethiopia

Next

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests