ቼዝም ስፖርት ነው!

ስፖርት - Sport related topics

ቼዝም ስፖርት ነው!

Postby ዘርዐይ ደረስ » Fri Oct 14, 2005 8:07 pm

ቼዝም እኮ ስፖርት ነው!የጭንቅላት ስፖርት!እስቲ ፍላጎቱ ያላችሁ ስለቼዝ እንወያይ!!
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1053
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Postby 4get.this » Fri Oct 14, 2005 10:54 pm

ብዙ ባልችልም: ፍላጎቱ ግን አለኝ:: እስቲ የምታውቀውን አካፍለን:: እኔ: እንደዳማ 8x8 በሆነ ሜዳ ላይ እንደሚጫወቱት ብቻ ነው የማውቀው::

ምናልባት የምታቃቸው "online games" ይኖሩ ይሆን?
ተመለስኩ ማለት ነው? :-?
4get.this
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 505
Joined: Wed Feb 16, 2005 7:37 pm
Location: escaped from nursing home

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sat Oct 15, 2005 9:18 pm

4get.this wrote:ብዙ ባልችልም: ፍላጎቱ ግን አለኝ:: እስቲ የምታውቀውን አካፍለን:: እኔ: እንደዳማ 8x8 በሆነ ሜዳ ላይ እንደሚጫወቱት ብቻ ነው የማውቀው::

ምናልባት የምታቃቸው "online games" ይኖሩ ይሆን?


4get.this,ቢያንስ ፍላጎቱ እንዳለህ ገልጸሃልና ተሳትፎህ በዚሁ የሚያበቃ እንደማይሆን ተስፋ አደርጋለሁ::እኔ ለበርካታ ዓመታት ተጫውቻለሁ:: ኢትዮጵያ በነበርኩበት ወቅት ይህ ጨዋታ ቢያንስ እኔ በነበርኩበት አካባቢ በብዛት አልተስፋፋም ነበር::ውጭም ከወጣሁ በኋላ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ዳማ እንጂ ስለ ቼዝ እንደማያውቅ ነው የተረዳሁት::በአማርኛ የሠንጠረዥ ጨዋታ እነደሚባልና ቢያንስ በዳግማዊ ምኒሊክ ዘመነ መንግስት በመኳንንት አካባቢ ይዘወተር እንደነበር አንብቤአለሁ::እንደ ገበጣ ወደ 'ተራው' ህዝብ ጠልቆ ለመግባት ግን እንዳልቻለ ነው::

በዓለማችን ቼዝን ለመጀመርያ ጊዜ የተጫወቱት እነማን እንደሆኑ በትክክል እንደማይታወቅ ነው ያነበብኩት::ብዙዎቹ ተመራማሪዎች እንደሚስማሙበት ከሆነ ግን ህንዶች ወይም ፋርሶች(የአሁኗ ኢራን) ሳይሆኑ እንደማይቀሩ ይገመታል::ይህ ጨዋታ የአሁኑን መልክ መያዝ ከመጀመሩ በፊት በየዘመናቱ ብዙ ለውጦች ተደርገውበታል::

ይቀጥላል
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1053
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

ቀጥል

Postby 4get.this » Mon Oct 17, 2005 11:30 pm

እያነበብኩ ነው ...
4get.this
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 505
Joined: Wed Feb 16, 2005 7:37 pm
Location: escaped from nursing home

Re: ቀጥል

Postby ዘርዐይ ደረስ » Tue Oct 18, 2005 10:53 pm

4get.this wrote:እያነበብኩ ነው ...


ይህ ርዕስ Dialog እንዳይሆን ያሰጋል 4get.this.ለማንኛውም በገባሁት ቃል መሠረት ለመቀጠል እሞክራለሁ::

ቼዝ አንተም እንዳልከው እንደ ዳማ 8x8 በሆነ 'ሜዳ'(እኔ እንኳ በአማርኛ ሥም ያለው አይመስለኝም ነበር) ላይ የሚጫወቱት ጨዋታ ነው::ከዳማ በተለየ መልኩ ግን
እያንዳንዱ ተጫዋች ጨዋታው ሲጀመር
1)ሁለት ግንቦች(Castles) በነጭ የሚጫወተው ተጫዋች A1 እና H1ላይ በጥቁር የሚጫወተው ደግሞ A8 እና H8 ላይ የሚያስቀምጣቸው

2) ሁለት ፈረሶች(horses or knights) B1 እና G1 ላይ(ነጩ) እንዲሁም B8 እና G8 ላይ(ጥቁሩ)

3)ሁለት ጳጳሶች(popes) C1 እና F1 ላይ(የነጩ) እንዲሁም C8 እና F8 ላይ(የጥቁሩ)

4)1 ንግስት(queen)D1 ላይ (የነጩ) D8 ላይ(የጥቁሩ)

5)1 ንጉስ(king) E1ላይ(የነጩ) E8 ላይ( የጥቁሩ)
(የንግስቶቹና የንጉሶቹ ቦታ በስህተት ተቀያይሯል ይቅርታ)

6)8 ወታደሮች(pawns) ከA2 እስከ H2(የነጩ) ከA7 እስከ H7(የጥቁሩ)

ይኖረዋል::ፊደሎቹና ቁጥሮቹ የሚያመለክቱት ሜዳውን(board) ነው::

ይቀጥላል
Last edited by ዘርዐይ ደረስ on Wed Oct 19, 2005 9:50 pm, edited 1 time in total.
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1053
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Postby ዘርዐይ ደረስ » Tue Oct 18, 2005 11:33 pm

4get.this ለምሳሌ yahoo ላይ online ቼዝ መጫወት ይቻላል::ለመልሱ ስለዘገየሁ ይቅርታ!
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1053
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

አቀማመጡ

Postby 4get.this » Wed Oct 19, 2005 1:51 pm

ሰላም!
ሌሎችም እንድሚጨመሩ ተስፋዬ ነው:: ለዛሬ: ስለአቀማመጡ ልጠይቅህ::
1-ነጭ እና ጥቁሩ ሁሌ የሚቀመጡበት ቦታ ውስን ነው አይደል? 1እና2ን የሚይዘው የትኛው ነው?
2- ነጭ ንጉስ ጥቁር ላይ ነው የሚያርፈው በሚለው እንጂ በሌላ አላቀውም:: D ነው አይደል እንዴ የንጉሶቹ?

የ"ያሁ"ን አውቀዋለሁ:: በርሱም ሆነ በሌላ: አመቺ ሰአት ካገኘን የዋርካ አባላት አብረን ልንጫወት የምንችልበት .... :?:
Chess is infinite: There are 400 different positions after each player makes one move apiece. There are 72,084 positions after two moves apiece. There are 9+ million positions after three moves apiece. There are 288+ billion different possible positions after four moves apiece. There are more 40-move games on Level-1 than the number of electrons in our universe. There are more game-trees of Chess than the number of galaxies (100+ billion), and more openings, defences, gambits, etc. than the number of quarks in our universe! --Chesmayne
ተመለስኩ ማለት ነው? :-?
4get.this
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 505
Joined: Wed Feb 16, 2005 7:37 pm
Location: escaped from nursing home

Re: አቀማመጡ

Postby ዘርዐይ ደረስ » Wed Oct 19, 2005 9:44 pm

4get.this wrote:ሰላም!
ሌሎችም እንድሚጨመሩ ተስፋዬ ነው:: ለዛሬ: ስለአቀማመጡ ልጠይቅህ::
1-ነጭ እና ጥቁሩ ሁሌ የሚቀመጡበት ቦታ ውስን ነው አይደል? 1እና2ን የሚይዘው የትኛው ነው?
2- ነጭ ንጉስ ጥቁር ላይ ነው የሚያርፈው በሚለው እንጂ በሌላ አላቀውም:: D ነው አይደል እንዴ የንጉሶቹ?

የ"ያሁ"ን አውቀዋለሁ:: በርሱም ሆነ በሌላ: አመቺ ሰአት ካገኘን የዋርካ አባላት አብረን ልንጫወት የምንችልበት .... :?:
Chess is infinite: There are 400 different positions after each player makes one move apiece. There are 72,084 positions after two moves apiece. There are 9+ million positions after three moves apiece. There are 288+ billion different possible positions after four moves apiece. There are more 40-move games on Level-1 than the number of electrons in our universe. There are more game-trees of Chess than the number of galaxies (100+ billion), and more openings, defences, gambits, etc. than the number of quarks in our universe! --Chesmayne


1)4get.this የቼዙ መጫወቻ 'ሜዳ' የሚቀመጠው ከሁለቱም ተጫዋቾች በስተቀኝ በኩል ነጭ field እንዲሆን ተደርጎ ነው:: 1 እና 2 በነጩ ሲያዙ 7 እና 8 ደግሞ በጥቁር ነው የሚያዙት::

2)የንጉሶቹ አቀማመጥ እንዳልከው ነው::ነጩ ንጉስ ጥቁር ላይ ጥቁሩ ንጉስ ደግሞ ነጩ ላይ ነው የሚቀመጡት::ስለሆነም D1 እና D8 ላይ ነው የሚቀመጡት::ስለ እርማትህ እያመሰገንኩ ለሰራሁት ስህተት ይቅርታ እጠይቃለሁ::እዚያው ላይ edit ላደርገው አስቤ ያንተን እርማት የሚያነብ ሰው ግራ እንዳይጋባ ትቼዋለሁ::

በተረፈ ኮት ያደረግከው ፅሑፍ የመቼ ነው?ምናልባት ማወቅ የምትችል ከሆነ::
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1053
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Postby 4get.this » Thu Oct 20, 2005 2:16 pm

The first Chess game between space and earth was played on June 9, 1970 by the Soyez-9 crew. The game ended in a draw.
አሁን ግልጽ ሆነልኝ:: ስለዚህ ሁሌም ለመደርደር ያለው አማራጭ አንድ ብቻ ነው ማለት ነው::ያሁ ላይ ሳየው: A በግራ በኩል ነው የሚሆነው (ነጩን ለያዘ):: እንደዛ ከሆነ ደግሞ የንጉሶቹ ቦታ አንተ እንዳልከው E ነው የሚሆነው ማለት ነው:: እስከዛሬ ግን በተቃራኒው ነበር የማደርገው! :oops:
በነገራችን ላይ: መጠየቄ እንጂ ማረሜ አልነበረም:: :)
ጽሑፉን በተመለከተ ... :arrow: እዚህ ተጫን
ተመለስኩ ማለት ነው? :-?
4get.this
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 505
Joined: Wed Feb 16, 2005 7:37 pm
Location: escaped from nursing home

Postby 4get.this » Thu Oct 20, 2005 2:32 pm

The word "Checkmate" in Chess comes from the Persian phrase "Shah Mat," which means "the King is dead."
በሌሎች ቋንቋዎችስ እንዴት ነው?
ተመለስኩ ማለት ነው? :-?
4get.this
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 505
Joined: Wed Feb 16, 2005 7:37 pm
Location: escaped from nursing home

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sun Oct 23, 2005 10:39 pm

4get.this wrote:
The word "Checkmate" in Chess comes from the Persian phrase "Shah Mat," which means "the King is dead."
በሌሎች ቋንቋዎችስ እንዴት ነው?


ሰላም 4get.this:-

ሰሞኑን ዋርካ ጎራ ስላላልኩ ነው እንጂ ይህን ርዕስ አልረሳሁትም::ባለፈው ትንሽ አምታታሁት አይደል!አንተ ንጉሱ D ላይ አይደለም ወይ የሚሆነው ብለህ የጻፍከውን ሳይ የተሳሳትኩ መስሎኝ(ከዚያ በፊት ብዙ ነገር አንብቤ ነበርና ደክሞኝ ነበር መሰል!) ነበር::

በጀርመንኛ:-Schach(ሻሕ).......chess,check

Schachmatt(ሻሕማት)....check mate.
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1053
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

እስኪ ቼዝ እንጫወት አንዳንዴ እየተቀጣጠርን!

Postby ያማን » Thu Oct 27, 2005 12:00 am

ሰላም ሰላም ሰላም
ቼዝ በጣም እወዳለሁ ለዛ ነው ብዙ ትርፍ ጊዜ ሲኖረኝ ወደ ያሁ ጌም ጎራ እልና ዋጋዬን አግኝቼ.....ከእለታት አንዳንዴ ደግሞ ይቀናኝና አሸንፌ...እወጣለሁ::
እስኪ አንዳንዴ እየተቀጣጠርን እንጫወት...ምነው በዛውም እኮ ያገር ቤት ወሬ ምናምን መጫወት ደስ ይላል::
መልካም ቀን!
ያማን ከ ዌስት ኮስት
ያማን
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 1
Joined: Tue Oct 14, 2003 12:29 am
Location: united states

Postby ዘርዐይ ደረስ » Thu Oct 27, 2005 12:10 am

ሰላም ያማን:-

በል እግዲህ እንዴት እንደምንገናኝ ተነጋገረን መጫወት ነዋ ታዲያ!
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1053
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Postby 4get.this » Thu Oct 27, 2005 8:40 pm

ዘርዐይ
አመሰግናለሁ:: የሚገርም መመሳሰል ነው:: በጀርመንኛም "ሻህ" ንጉስ ከሆነ በተለይ ... :o

ልትሄድበት ያሰብከው ቅደም ተከተል ነገር ከሌለህ ስለ ማቀያየር "ካስሊንግ" ማረጋገጫ ልጠይቅ:: ከተለያዩ ሰዎች የተለያዩ ሕጎች ሰምቻለሁ::
1. ንጉሱ ከተንቀሳቀሰ አይቻልም:: ተሳስቻለሁ?
2. ቼክሜት ላይም ከሆነ አይቻልም::
3. ቼክሜት ላይ ባይሆን ... ግን ከዚህ በፊት ተብሎ ቢሆንስ? እና ያልተንቀሳቀሰ ቢሆን?
4. በንግስቷ በኩል ይቻላል?

ለጫወታው ሰአታችን ከገጠመ እኔም ፈቃደኛ ነኝ:: እስቲ ለማንኛውም: ሁላችንም እንድንግባባ በ ጂ እም ቲ አስቀምጡት:: GMT/UTC
ተመለስኩ ማለት ነው? :-?
4get.this
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 505
Joined: Wed Feb 16, 2005 7:37 pm
Location: escaped from nursing home

Postby ዘርዐይ ደረስ » Fri Oct 28, 2005 5:13 am

ሰላም 4get.this:-

'ክበባችን' በአንድ አባል ያደገ መሰለኝ::አንተው ስም ቀይረህ ካልሆነ በቀር :D :D !ይህን ርዕስ ስጀምረው ስለ ብዙ ነገሮች የመጻፍ ኃሳብ ነበረኝ::ስለ ቼዝ ለመጻፍ ግን በሥዕል እያስደገፍክ ካልሆነ በጣም አስቸጋሪ እንደሆነ ነው የተረዳሁት::

ካስሊንግን በተመለከተ:-
1)ንጉሡ ቼክ ላይ መሆን የለበትም::

2)ንጉሡም ሆነ ካስሎቹ ከመነሻ ቦታቸው ያልተንቀሳቀሱ መሆን አለባቸው::

3)ካስል በሚደረግበት ወቅት ንጉሡ ቼክ ሊባልበት ወደሚችልበት አቅጣጫ መሆን የለበትም::

4)እያንዳንዱ ተጫዋች አንድ ጊዜ ብቻ ነው ካስል ማድረግ የሚችለው::

5)ረጅምና አጭር ካስሊንግ የሚባልም አለ::( Short castling and long castling)

ሀ) አጭሩ ካስሊንግ በንጉሡ በኩል ካለው ካስል ጋር የሚደረገው ሲሆን ረጅሙ ደግሞ በንግሥቷ በኩል ካለው ካስል ጋር የሚደረገው ነው::

በጀርመንኛ Schach ንጉሥ ማለት አይደለም::ከፋርስ ቋንቋ እንዳለ ወስደውት ነው ለቼዝ የተጠቀሙበት::

እንዴት ተገናኝተን እንደምንጫወት ግራ ገብቶኛል::ምናልባት መጀመርያ ቻት ሩም ውስጥ መገናኘት ያለብን ይመስለኛል::ምክንያቱም yahoo ላይ ለመጫወት ሥም ማውጣት ስለሚያስፈልግ ሥማቸንን መተዋወቅ አለብን::በተጨማሪም የትኛው ሩም ውስጥ እንደምንጫወትም መነጋገር አለብን:.እናም ዋርካ ቻት ሩም ውስጥ መቼ እንገናኝ ነው የመጀመርያው ጥያቄ መሆን ያለበት የሚመስለኝ:.እኔ አሁን የሆነ ሠዐት ብነግራችሁ በዚያ ሠዐት እናንተ ላይመቻችሁ ይችላል::እስቲ የናንተን ደግሞ ልስማ:.እስከዚያው.....
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1053
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Next

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest