ወትሮም ቢሆን ቡድኑ ብዙም የአቆአም መዋጀቅ አይታይበትም:: በአገር ውስጥ ውድድር ድልን ባያገኝ እንክዋን ምንጊዘም ተፎካካሪ ሲሆን ይታያል:: ለዚህም ይመስላል ስታስቲክሱ እንደሚያመላክተውከ1898 አንስቶ ከማናቸውም ቡድኖች በላቀ 28 ግዘ ስኩደቶ አቸናፊዎች ሲህኑ የቅርብ ተከታይ የሚባለው ሚላን 16 ግዘ ብቻ ነው ባለድል የሆነው::
እንደሚታወቀው የጥአልያን ኩራት የሆነው ፊያት መኪና ማምረቻ እናት ከተማ ቱሪን ነች:: የቱሪን ከተማ መኩሪያ ደግሞ ታላቁ ጁቨንቱስ!!!! እናም የፊያት ኩባኒያ ባለበቶች ማለትም የአኝሊ ፋሚሊዎች ይህን ግሩም ቡድን ድሮ ገና በባለበትነት ቢይዙት ብዙም አስገራሚ አይሆንም:: የአኝሊ በተሰቦች በጥንካሪያቸው እና ታታሪ ሰራተኝነታቸው ፊያት ካምፓኒን በመላው አለም ያሳወቁ ለመሆናቸው ሁሉም ያወራላቸዋል:: ደከመን ሰለቸን ሳይሉ ስከትን ለዘመናት ሲያባርሩ የኖሩ እንደመሆናቸው ሁሉ ለስማቸው የሚመጥንና promot የሚያደርጋቸው ጥንካራ ቡድንን ጁቨንቱስን በስራቸው ሲያስገቡ እንደተራ ባለበትነት ሳይሆን እንደልጃቸው አድርገው ነበር:: ከአሰልጥአኝ ቅጥር አንስቶ እያንዳንዱ ውሳነ በነሱ ስር የሚያልፍ ቢሆንም ከተቀናቃኝ ቡድኖች ለየት ባለ መልኩ በቡድን ስራ ውስጥ እጃቸውን አያስገቡም:; መች የነሱ ጥአልቃ መግባት እንዳለባቸው በደንብ የተረዱ ብልህ ሰዎች ናቸው:: ለምሳለ ሚላን ቡድን ጥሩ የማይጫወት ከሆነ ባለበቱ በርልስኮኒ ከክቡር መቀመጫ ሳጥናቸው ሆነው "እገለን አስወጥተህ እገለን አስገባ" እንዲሁም ደግሞ ቸቭቸንኮ ምንም ይሁን ምን መስለፍ አለብት የሚል አስተያየት መሰል ቀጭን ትዛዞችን ሲያስተላልፉ ይስተዋላል:: ይህ ነገር በጁቨ በት ውስጥ ግን ከቶም አይደረግም:: ይልቅ የጁቨ ሰዎች ግሩም የአስተዳደር ሰዎችን በጀነራል ማናጀርነት በመሽኦም በነሱ አማካይነት ቡድኑን ያስተዳድራሉ::እዚ ጋር ነው እንግዲህ የጁቨንቱስ ቡድን ቁልፍ ሰው የሆነውን ሉቺያኖ ሞጂን የምናገኝው::
>>>>>>ሉቺያኖ ሞጂ=የጁቨንቱስ ልብ!!
አሮጊቷ (የጁቨ ቅጽል ስም) ንቁ እና healthy ልብ ባይኖራት ኖሮ እንደአንጋፋነቷ እዚም እዛም በተወለካከፈች ነበር:: ይህ ልቧ ደግሞ ጀነራል ማናጀሩ ሉቺያኖ ሞጂ ነው:: ይህ ሰውየ የቡድን አመራሩ አጀብ የሚባልለት በተለይ ተጫውቾች ግዥ ላይ ብልጥነቱን ደጋግሞ ያሳየ ሰው ነው:: በሱ የቅርብ ውሳነና ክትትል ካስፈረማቸው ውስጥ ዚዳን, ትረዚገ, ነድቨድ, ቡፎን ዛምብሮታ, በቅርቡ ደግሞ ቪየራ የሚጥቀሱ ሲሆን ከኪፐሩ ቡፎን በስተቀር ሁሉም በመጥነኝአ ዋጋ መተው ቡድኑን ያገለገሉና የሚያገለግሉ ናቸው:: ዚዳንን የወሰድን እንደሆን እስካሁን ባልተሰበረ የአለም ሪኮርድ $65 ሚሊየን ዶላር ለሪያል ማድሪድ ሽጥው ከዛ ላይ ትንሽ በመቆንጥር ፓቨል ነድቨድን ከላዚዮ ገዙ:: ፓቪየልም ማንንነቱን በጁቨ ማሊያ አስመስክሮ የ2004 የአውሮፓ ኮከብ ተጭዋች ለመባል በቅቷል:: እንዲሁ በአኝሊ ፋሚሊ ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የሆነው ሮቢባጂዮን ወደ ሚላን በድፍረት ሲሽኝበ1993 ከቨሮና የተገዛውደልፒየሮ በብቃት እንደሚተካው አውቆና አስቦበት ነበር:: እዚህ ላይ የምንውስደው ነገር ቢኖር ጁቨ ውስጥ አንድን ተጨዋች ሲለቁ ለዛ ተጭዋች ተተኪ አዘጋጅተው ነው:: አልፎ አልፎ ወሳኝ ካልሆነ በተቀርገንዘብን ደግሞ ዝም ብለው ብቅ ባለ ተቻዋች ላይሲረጩ አይስተዋልም::
>>>>የዘንድሮ ጁቨንቱስ ያስፈራል::
ከጥቂት ወራት በፊት ስለቪየራ አርሰናልን ለቆ ጁቨንቱስ መግባት ስጽፍ አያይዥ ጁቨ ከማናቸው ቡድኖች በላይ ተሟልቶ ይቀርባል ብየ መጻፈን አስታውሳለሁ:: ግን ከግምተ በላይ በሆነ የተሟላ ብቃት ይህእውና የዘንድሮ ያውሮፓ ንጉስ ጁቨንቱስ ሊሆን በቅቷል:: በተለይ በዋናነት emerson, viera, nedved የተዋቀረው አማካይ ክፍሉ ለቡድኑ ባላንስን የሰጥእው ሲሆን ተቃራኒ ቡድን ይህን አማካይ ዐጨዋወት ሰብሮ ጨዋታን በቁጥጥር ስር ሲያደርግ አልታየም:: ቪየራም ካለምንም ችግር ከዚህ ቡድን አጨዋወት ጋራ ተዋህዶ እንዲያውም የቀድሞ ብቃቱን እየመለሰ ይገኝአል::አጥቂው መስመር በዋናነት የሚመራውግብ አዳኝ የሆነው ዳቪድ ትረዘገ ሲሆን ከሱ ጋር ደግሞ አምና የሊጉ ኮከብ ተጫዋች ተብሎ የተመረጥው ዝላታን ኢብራሂሞቪች ነው:: ዝላታን ምንም እንክዋን ዘንድሮ የግብ ድርቅ ቢመታውም የአካል ጥንካረውና የተክኒክ ብቃቱ ለተከላካዮች ቆምስቅል ከመሆን አልተረፈም:: ደልፒየሮም ከሰሞኑ የድሮ ብቃቱን የሚያስታውስ እንቅስቃሰ እያደረገ ይገኝአል::በቱራም እና ካናቫሮ የሚመራውስለተከላካይ ክፍሉ ብዙም ማለት አያስፈልግም:: ዘንድሮም እንዳምናው ሁሉ የሊጊ ምርጥ ተከላካይነቱን እያስመሰከረ መሆኑን መጥቀስ በቂ ይሆናል:::: አዎን ብናምንም ባናምንም ቢያንኮነሪዎች(ነጭ እና ጥቁሮቹ) ካደረጉት 8 ጨዋታ ስምንቱንም በመርታት 24 ነጥብ ይዘው ሰሪአውን እየመሩ ይገኝአል::በተከታታይ የማሽእነፍን ሪከርድንም ይሰብራሉ ተብሎ ይታመናል::ይህ ጥንካሪያቸው በአውሮፓም መድረክ በቻምፒየንስ ሊጉ ላይ እየተንጸባረቀ ሲሆን ባለፈው በባየርሙኒክ ሙኒክ ላይ 2-1 በሆነ ጥባብ ውጥየት ቢሽነፉም የባየርን home ሪኮርድ ለተመለከተና ለሚያውቅ ኮአስ አፍቃሪ የጁቨን የሙኒክ ላይ ሽንፈት ብዙም አያስደንቀውም::እናም ዘንድሮ በሚገርም ሁነታ 2 ጊዘ ብቻ የአቸነፉትን የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ለማግኝን ቆርጥው ተነስተዋል:: የመሀል መዳው ጀነራል ነድቨድም ለአመታት ሲመኝ የነበረውን ይህን ድል ዘንድሮ ሳይቃመስ አይቀርም::