ራውል..ነድቨድ... ከአለምዋንጫ ላለመቅረት የሞትሽረት ትግል::

ስፖርት - Sport related topics

ራውል..ነድቨድ... ከአለምዋንጫ ላለመቅረት የሞትሽረት ትግል::

Postby አፍሪክ » Wed Nov 09, 2005 9:03 pm

በአለፈው ሳምንት ወይም ሳምንቶች መለስ ብለን ብናይ.... በእንግሊዝ የአርሰንወንገር እና ሞሪንሆ እሰጥ አገባ, የሮይ ኪን አወዛጋቢ መግለጫን እና ከምንም በላይ ደግሞ የቸልሲ በማንችስተር መሽነፍ ዋናዎቹ ወረዎች የነበሩ ሲሆን, ወደስፓኝ ስንወርድ የባርሰሎና ማንሰራራት, የሪያል ማድሪድ አጥጋቢ ያልሆነ ጉዞ እናም ኦሳሱና ባልተለመደ ሁነታ እየመራ መሆኑ አይተናል:: ሊጋ ካልቺዮ(ኢታሊ) ጎራ ስንል እነን ጨምሮ ብዙ ያወራንለት ጁቨንቱስ በ ሚላን 3-1 መዶቀስ, የአድሪያኖ ኢንተርሚላን ማፈግፈግ እና የደሊፒየሮ ብቃት ከጨዋታ ወደጨዋታ መስተካከልን ዋና ዋና ወረወች ሆነው አልፈዋል::
ያለፈውን ወደህዋላ ትተን ወደፊታችን መልከት ስንል እጅግ አግዋጊ ጨዋታዎችን እናገኝለን:: ቅዳመ አርጀንቲና ከእንግሊዝ የሚያረጉት ወዳጅነት ጨዋታ (የፎክላንድ ጥኦርነት) እንዲሁም በመጪው መጪው እሁድ ባርሰሎና ከማድሪድ የሚያረጉት ደርቢ "ሱፐርክላሲኮ" ሚድያ ከቨረጅ ቢኖራቸውም ወቅታዊ ሆኖ ከሁሉም ቅድሚያየሚይዘው ግን የመጨረሽዎቹ የአለም ዋንጫ አላፊዎች የሚለዩበት ደርሶመልስ ጨዋታዎች ይሆናሉ:;

**ቸክ ሪፐብሊክ ከ ኖርወይ ላለባት ትግል ለአስራስምንት ወራት ራሱን አግለሎ የነበረው ወሳኝ ተጫዋች ፓቭየል ነድቨድ ተመልሶላታል:: ያን ኮለር እና አምበሉ ጋላሰክ በጉዳት እንደማይሰለፉ ቢወራም የነድቨድ መመለስ ግን ያን ችግር ኢምንት አስመስሎታል:: ኦስሎ ላይ ቅዳምኤ ለታ የመጀመሪያውን ይጫወታሉ::
** ስዊትዘርላንድ ከተርኪ የምታደርገው ደርሶመልስ ጨዋታ ከሁሉም ከባዱ የተባለለት ሲሆን ማን ማንን ጥሎ እንደሚያልፍ ለመተንበይ አዳጋች ነው::
** ስፓኝ ከስሎቫኪያ ላለባት ፍልሚያ ክተተ ሰራዊት ብላ አሉኝ የምትላቸውን ተጭዋቾች አካታ በ "ቪሰንተ ካልደሮን" ስታዲየም (አትለቲኮ ማድሪድ መዳ) ስሎቫኪያን ታስተአግዳለች:: ስሎቫኪያ በጉዳት ሰበብ የአርሰናሉ አለክሳንደር ህእልብ አይሰለፍላትም:: ተአምር ካልተፈጥረ በተቀር ስፓኝ ታልፋለች የሚለው የብዙዎች ግምት ነው::
** ባህረይን ከትሪኒዳድና ቶበጎ ደርሶመልሷን አከናውና እድሏን ታያለች::
** ዩራግዋይ አውስትራሊያን በመጀመሪያው ጨዋታ በሞንትቪደዮ "ሰንቲናሪዮ" ስታዲየም ታስተናግዳለች:; ለጃፓን/ኮሪያ አለምዋንጫ እንዲሁ በተመሳሳይ ተገናኝተው ዩርግዋይ አላፊ ለመሆን በቅታለች:; ያ ታሪክ ነው ዛረም ለላ ቀን ነው::


መልካም እድል ለሁሉም::
አፍሪክ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 505
Joined: Fri Feb 18, 2005 9:05 pm
Location: united states

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest