እስቲ ስለ BASE BALL ቦል እንነጋገር!

ስፖርት - Sport related topics

እስቲ ስለ BASE BALL ቦል እንነጋገር!

Postby ጩጉዳ » Tue Nov 15, 2005 7:57 pm

Image

Image

Image

ሰላም የስፖርት አፍቃሪዎች!
መቼስ Yankee, Red sox, White Sox, Padres, Blue jay, Rockies., Dodgers, Giants, Twins , Cubs ....... ሲባል ሰምታችኋል:: ካልሰማችሁም ምንም አይደል ! እነሱ የአሜሪካን ቤዝቦል ቡድኖች ናቸው:: ጨዋታውን ካላወቃችሁ አገር ቤት በተለይ ገጠር ያደጋችሁ <<ኪሎ>> ወም << ቦንብ ቦንብ>> ዐይነት ነው:: ሜዳው 3 ኮርነርና ዳይመንድ ቅርጽ ያለው ነው:: ተጫዋቾቹ ወርዋሪ/ Peacher: 1st Baseman/1ኛ መደብ ተከላካይ 2nd Baseman 3rd Baseman Ceneter fielder catcer & Out fielder በሚል ይታወቃሉ:: መቺው ኳሷን ለመምታት 3 ዕድል ሲሰጠው ወርዋሪው 4 ዕድል ይሰጠዋል:: ከመቺው ጀርባ መከላከያ ያጠለቀ አንድ ዳኛ Home plate ampire ወርዋሪው በትክክል ለመወርወሩ ይቆጥራል:: ከግራና ከቀኝ 1st and 2nd base ampires ደግሞ የግራና የቀኝ ክንፍ የመስመር ዳኞች ናቸው:: ባጠገቡ ቁጭ ብሎ ኳሷን የሚቀበል/Catcer የወርዋሪው ቡድን አባል ነው:: መቺው ሳይስት መትቶ ሳያዝበት ወደአንደኛው ቤዝ ከደረሰ Base - hit Single ይባላል:: መቺው በአየር ላይ ከተቀለበበት ግን ዙሩ ያልፈዋል ወይም ተቃጥሎ 3 ሰው እስኪወጣ ድረስ ሌላ ተረኛ እየመታ ይቀጥላል:: መቺው ፋውል ወደኋላ ሳያወጣት ፊት ለፊት ወደ ተመልካች ከሰደዳት Solo Homerun ይባላል:: በዚህ ጊዜ መቺው እየዘነጠ ሮጦ 3ቱንም ቤዝ በእግሩ እየነካ ዞሮ ወደመታበት Homeplate ሲመለስ Score ያስቆጥራል:: መቺው ግን ሌላ ተጨማሪ ሰው ይዞ ከገባ 2 run Homerun ይባልና 2 ያስቆጥራል:: እንግዲህ ጨዋታው ካላዩት ቶሎ ስለማይገባ በዚህ የአዕምሮ እርካታ በሚሰጥ የአሜሪካኖችና የላቲኖች ባህል ጨዋታ የማታውቁ ካላችሁ በይበልጥ ብትጠይቁኝና ሌሎቻችሁም ስለ ቤዝቦል የምታውቁ ብታግዙኝ እንዲሁም ይህ ጨዋታ ወደ አገራችን ቢገባስ በሚል ዙሪያ ብንወያይበትሳ?
ጩጉዳ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1267
Joined: Mon Jan 31, 2005 6:40 am
Location: Studio City, Wilson Republic

Postby ሰበቡ » Wed Nov 16, 2005 12:34 pm

ቤዝ ቦል በጣም በጣም ያስጠላኛል ልነግርህ አልፈልግብ እንዴት እንደምጠላው
ሰበቡ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 127
Joined: Thu Oct 13, 2005 5:01 pm
Location: UK

Postby አሹ78 » Wed Nov 16, 2005 10:43 pm

ቤዝቦል አዎን በጣም ጥሩ ስፖርት ነው:: በዚህ ጨዋታ ኩባዊያንና ቤኑዝዌላዎች በጣም የታወቁ ናቸው:: ጨዋታው ወደ አገራችን ቢገባ እንኳን ቶሎ ከሕዝቡ ጋር ለማዋሀድ እንኳን አስቸጋሪና ብዙ ጊዜ የሚወስድ ስለሆነ የማይታሰብ ነው:: በአፍሪካ በዝንባብዌና ደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ የተወሰኑ ነጮች ከመጫወታቸው በቀር ሌላ ተፎካካሪና የሚያዘወትሩ አገሮች ስለሉና ብዙ የተደራጁ ኮሌጆች ስለለሉን ለኛ አገር ትርጉም አይኖረውም::

ጩጉዳ እኔም በዚህ ጨዋታ የዳጀርስና የፓድሬስ ደጋፊ ስለሆንኩም አርዕስቱን አስበህ እዚህ በማምጣትህ ግን ሳላደንቅህና ስላመሰግንህ አላልፍም::

በዚህ ጨዋታ በበኩሌ የማደንቀው ከመቺዎች ተጫዋች: የቺካጎ ካብ የነበረውና ባሁኑ ጊዜ የባልትሞር Oriols ሳሚ ሶሳን ሲሆን ከፒቸሮች የያንኪውን ራንዲ ጃንሰንን ነው:: ካሰልጣኞች ዘንድሮ የዐለም ሻምፒዮን የቺካጎ ወጣቱን የዋይት ሳክስ አሰልጣኝ ቤኑዙዌላዊውን አዚ ጉሊያንን ነው::
Never trade what you want at the moment for what you want the most
አሹ78
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 75
Joined: Tue Feb 01, 2005 5:22 am
Location: united states

Postby ማካሮቭ » Sat Nov 26, 2005 7:42 pm

እኔም የቤዝቦል አፍቃሪ ስለሆንኩ ይህን አርእስት ሳይ በጣም ደስ ብሎኛል:: የምወደው ቡድን የቀድሞ አናሄም ያሁኑን ሎሳንጀለስ ኤንጀልስን ነው:: የማደንቀው ተጫዋች የሳን ፍራንሲስኮን ቤሪ ቦንድን ነው::
Wisdom is better than weapons of war: but one sinner destroyeth much good.
ማካሮቭ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 337
Joined: Tue Dec 07, 2004 7:20 am
Location: united states

ቤዝ ቦል

Postby ጌታ » Sun Nov 27, 2005 12:18 am

ውድ ጨጉዳ:

እንኳን ቤዝ ቦል ሊገባኝ ይቅርና ከፉትቦል ጋር ያለውን ልዩነትም በቅርቡ ነው ያስተዋልኩት:: አሁን አሁን ፉትቦሉ ሕጉን አብጠርጥሬ ባላውቀውም በደመነብስ ይገባኝ ጀምሯል:: ቤዝ ቦሉ ግን ሕጉን ብጠይቅም በደንብ የነገረኝ ሰው አላገኘሁም::

ይህንን ርዕስ በመክፈትህ በጣም ተደስቻለሁ:: አሁንም እስኪገባኝ በደንብ አነበውና ጨዋታውን ለመመልከት እሞክራለሁ:: ከቻልክ ግን የበለጠ ብታብራራው ደስ ይለኛል::

አሹ78 እና ማካሮቭም ብታግዙት መልካም ነው::

ከታላቅ ምስጋና ጋር
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3083
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Re: ቤዝ ቦል

Postby ማካሮቭ » Tue Nov 29, 2005 6:45 pm

ጌታ wrote: እስኪገባኝ በደንብ አነበውና ጨዋታውን ለመመልከት እሞክራለሁ:: ከቻልክ ግን የበለጠ ብታብራራው ደስ ይለኛል::

አሹ78 እና ማካሮቭም ብታግዙት መልካም ነው::

ከታላቅ ምስጋና ጋር


ሰላም ያገር ልጅ ጌታ :
በስፖርት ዐለም ብዙ ጊዜ ስለማይገባ ጨዋታ አበሻ ስለማይጨነቅበት እንዲያውም ስለሚያስጠላው አንተ የዚህ ተቃራኒ ሆነህ ለመማር ስለተዘጋጀህ አደንቅሀለሁ::
በቤዝቦል ወርዋሪው ማለትም አልሞ ለመቺው የሚልክ ለቡድኑ ድልም ሆነ መሸነፍ ወሳኝ ተጫዋች ስለሆነ ብዙ ጊዜ ያንድን ቡድን ስም ከመጥራት ይልቅ የወርዋሪውን ስም ጠርተው እገሌ ከእገሌ ጋር ይገጥማሉ ይባላል:: ምክንያቱም ወርዋሪው ቀሺም ሆኖ ዝምብሎ የሚመታ ኳስ እየሰጠ የሚያስመታ ከሆነ ነጥብ ስለሚቆጠር ነው:: ሌላው ጩጉዳ እንዳለው ከኋላ የቆመው ዳኛ በተጠንቀቅ ቆሞ እጁን እያነሳ ድምጹን ከፍ አርጎ <ስትራይክ!> ካለ መቺው ላይ ተቆጠረ ማለት ነው በዚህ ዐይነት 2 ተቆጥሮ በ3ኛው ግን ከሳታት <<ስትራይክ አውት!!>> ይባልና መቺው ዙሩ ይቃጠልበታል::

ኳሷን ግን ከጨረፋትና ወደኋላ ከሰደዳት ግን <ፋውል> ስለሆነ ሳይቆጠር መቺው ሌላ ዕድል ይሰጠዋል:: እንደሱ እየመታ ግን እስኪስተካከልለት ዝምብሎ ሙከራውን መቀጠል ይችላል:: በዚህ ጊዜ ወርዋሪው ጎበዝ ከሆነ በሰውነቱ እንቅስቃሴ ይሸውደውና በሀይል የወረወረ አስመስሎ አየር ያሳፍሰውና ኳሷን ሳያስነካት <ስታራይክ አውት!> ያወጣዋል:: አሊያም መቺው ተሳክቶለት ኢላማውን አስተካክሎ ፊት ለፊት አጡዟት ከተመልካች ውስጥ ከከተታት <ሆምራን!> ነጥብ አስቆጠረ ማለት ነው::

በዚህ ጨዋታ ኳሷ ተመታ በአየር ላይ ከተቀለበች መቺው ወዲያው የሚወጣ ሲሆን ሌላ ወገኑ ሜዳ ውስጥ ኖሮ ከሆነ ግን ኳስዋ ከተያዘችበት ሰኮንድ ጀምሮ ሮጦ ወደሚቀጥለው ቤዝ መድረስ ስለሚችል እንዲህ ዐይነት አመታት <Suicide> ይባላል:: ምክንያቱም ራሱን ገሎ ሌላውን አድቫንስ ስላረገ ነው:: በቤዝቦል ጨዋታ ዳኛው ከፍተኛ ስልጣን አለው:: ዳኞው ማንኛውንም ተጫዋች አሰልጣኝ ሆነ የቡድን መሪ ብቻ እንደፈለገ ማባረር ይችላል:: ይህ ብቻም ሳይሆን ከተመልካቹም መሀል የሚረብሽ ካለ ጨዋታውን አስቁሞ ከስታዲየሙ ማስወጣት ይችላል::

ወንድሜ ጌታ እንግዲህ ሌላ የማይገባህ ነገር ካለ ብትጠይቅ ደግሞ በይበልጥ እንወያይበታለን::
Wisdom is better than weapons of war: but one sinner destroyeth much good.
ማካሮቭ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 337
Joined: Tue Dec 07, 2004 7:20 am
Location: united states

ምስጋና ለማካሮቭ

Postby ጌታ » Tue Nov 29, 2005 7:21 pm

ማካሮቭ wrote: ወንድሜ ጌታ እንግዲህ ሌላ የማይገባህ ነገር ካለ ብትጠይቅ ደግሞ በይበልጥ እንወያይበታለን::


ጥሩ አብራርተኸዋል:: ካሁን በኋላ በደንብ እየተከታተልኩኝ ሕጉን ለማብላላት እሞክራለሁ:: ጥያቄም ሲኖረኝ ለመጠየቅ አላመነታም::

ሚሊዮን ምስጋና..........እሺ ሁለት ሚሊዮን አድርጌልሃለ :lol: :lol:
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3083
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ዞብል2 » Tue Nov 29, 2005 8:23 pm

ሰላም......ወዲ_ማካሮቭ ጥያቄ? ለመጀመሪያ ጊዜ የቤዝቦልን ኳስ በቴስታ የመታ ማነው?
መልስ: አርከበ እቁባይ :P :lol: :lol:

ዞብል ከፒያሳ
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2381
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Postby ማካሮቭ » Tue Nov 29, 2005 9:49 pm

ዞብል2 wrote:ሰላም......ወዲ_ማካሮቭ ጥያቄ? ለመጀመሪያ ጊዜ የቤዝቦልን ኳስ በቴስታ የመታ ማነው?
መልስ: አርከበ እቁባይ :P :lol: :lol:

ዞብል ከፒያሳ:lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:

ሰላም ያገር ልጅ የፒያሳው ዞብል እንደምን ሰነበትክ? ለመሆኑ በግል የላኩልህን ደብዳቤ አይተሄዋል?? እስቲ በጥሞና አንብበውና ተመለስ:

ሰላሙን ሁሉ የምመኝልህ
ወንድምህ ማካሮቭ
Wisdom is better than weapons of war: but one sinner destroyeth much good.
ማካሮቭ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 337
Joined: Tue Dec 07, 2004 7:20 am
Location: united states


Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests