


ሰላም የስፖርት አፍቃሪዎች!
መቼስ Yankee, Red sox, White Sox, Padres, Blue jay, Rockies., Dodgers, Giants, Twins , Cubs ....... ሲባል ሰምታችኋል:: ካልሰማችሁም ምንም አይደል ! እነሱ የአሜሪካን ቤዝቦል ቡድኖች ናቸው:: ጨዋታውን ካላወቃችሁ አገር ቤት በተለይ ገጠር ያደጋችሁ <<ኪሎ>> ወም << ቦንብ ቦንብ>> ዐይነት ነው:: ሜዳው 3 ኮርነርና ዳይመንድ ቅርጽ ያለው ነው:: ተጫዋቾቹ ወርዋሪ/ Peacher: 1st Baseman/1ኛ መደብ ተከላካይ 2nd Baseman 3rd Baseman Ceneter fielder catcer & Out fielder በሚል ይታወቃሉ:: መቺው ኳሷን ለመምታት 3 ዕድል ሲሰጠው ወርዋሪው 4 ዕድል ይሰጠዋል:: ከመቺው ጀርባ መከላከያ ያጠለቀ አንድ ዳኛ Home plate ampire ወርዋሪው በትክክል ለመወርወሩ ይቆጥራል:: ከግራና ከቀኝ 1st and 2nd base ampires ደግሞ የግራና የቀኝ ክንፍ የመስመር ዳኞች ናቸው:: ባጠገቡ ቁጭ ብሎ ኳሷን የሚቀበል/Catcer የወርዋሪው ቡድን አባል ነው:: መቺው ሳይስት መትቶ ሳያዝበት ወደአንደኛው ቤዝ ከደረሰ Base - hit Single ይባላል:: መቺው በአየር ላይ ከተቀለበበት ግን ዙሩ ያልፈዋል ወይም ተቃጥሎ 3 ሰው እስኪወጣ ድረስ ሌላ ተረኛ እየመታ ይቀጥላል:: መቺው ፋውል ወደኋላ ሳያወጣት ፊት ለፊት ወደ ተመልካች ከሰደዳት Solo Homerun ይባላል:: በዚህ ጊዜ መቺው እየዘነጠ ሮጦ 3ቱንም ቤዝ በእግሩ እየነካ ዞሮ ወደመታበት Homeplate ሲመለስ Score ያስቆጥራል:: መቺው ግን ሌላ ተጨማሪ ሰው ይዞ ከገባ 2 run Homerun ይባልና 2 ያስቆጥራል:: እንግዲህ ጨዋታው ካላዩት ቶሎ ስለማይገባ በዚህ የአዕምሮ እርካታ በሚሰጥ የአሜሪካኖችና የላቲኖች ባህል ጨዋታ የማታውቁ ካላችሁ በይበልጥ ብትጠይቁኝና ሌሎቻችሁም ስለ ቤዝቦል የምታውቁ ብታግዙኝ እንዲሁም ይህ ጨዋታ ወደ አገራችን ቢገባስ በሚል ዙሪያ ብንወያይበትሳ?