ይምስራቅ አፍሪካ ዋንጫ

ስፖርት - Sport related topics

ይምስራቅ አፍሪካ ዋንጫ

Postby ደባደቦ » Wed Dec 07, 2005 2:25 pm

ሰላም ወገኖቼ መቼም ቀን አይደርስ የለ ደረስ :: አሁን ሰሞኑን የሀገራችን ቡድን ከሱማሌው አቻው ጋር ግጥሚያ ያደርጋል :: አይ ውርደት አይ ውርደት እኔ ብቻ ሀገራችን ተሸነፈ ቢባል ......... (የምለው የለም ): እነ ኬንያ አሁን አድገው ለአፍሪካ ዋንጫ እንኳን ትፋለች የኛዋ ግን በጣም ጎበዝ ከሆኑ ጊዜ የምስራቅ አፍሪካን ማጣሪያ ያልፋሉ ደሞ ይችም ውጤት ሆኖ ይጎርራሉ :: አይ መጥኔ የፋራ ነገር :: እዚህ አምድ ላይ ባለፈው ጊዜ አንድ ነገር ፅፌ ነበር :: ታዳሚው ሁሉ ተናዶቢኝ ነበር :: ግን ይህ ሀቅ ነው :: እኛ የአለም ዋንጫ ይምንበላው ሳይሆን የምንሳተፈው ይህ እኛ ያለንበት ጀኔሬሽን ሲያልቅ ነው እሱም ድንገት ከተቀየረ ለመብላት ሳይሆን ለመሳተፍና ለመመለስ :: ይህ ማለት ደሞ ምናልባት 2099 አመትምህረት ለመብላት ግን 5000 አመተምህረትም እንጃ ያደሞ
_________________
HTML
ደባደቦ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 467
Joined: Mon Feb 28, 2005 11:27 am
Location: ETHIOPIA

Postby ጊዮርጊስ » Wed Dec 07, 2005 5:28 pm

ድብዳቦ

ኢትዮጵያ ሶማሌን 3 - 1, ሱዳንን 3 - 0 ጅቡቲን 7 - 0 በማሽነፍ ከምድቧ አልፋለች:: ቀጣይ የምድብ 1 አሸናፊ ተጋጣሚዋ ዛንዚባር ትሆናለች::

ኢትዮጵያ መቼ ያለም ዋንጫ ትካፈላለች? ለሚለው ግምትህ ብዙ ነገሮችን ታሳቢ ማድረግ አለብህ:: እግር ኳስና የኢኮኖሚ እድገት አብረው ይሄዳሉ:: ከአለም በድህነት አንደኛ የሆነች ሀገር ያለም ዋንጫ ባለመካፈሏ አይገርመኝም:: እንደውም ብታልፍ ይገርመኛል:: ምን ያህል ሀብት ያላግባብ እየባከን እንደሆነ የማስብ ይመስልኛል:: ፉትቦል ኢንቨስትመንት ነው:: ባንድ ቀን የምታደርሰው ነገር አይደለም:: የኢትዮጵያ ድህነት በዚሁ ከቀጠለ አንተ የገመትከው ቀን በጣም ቅርብ እኮ ነው:: ከኬንያ ጋር ማውዳደርህም ይገርማል:: ኬንያ እኮ ከኛ በጅጉ የተሻለች አገር ናት:: እስኪ የፊፋን ሰንጠርዥ እየው http://fifa.com/en/mens/statistics/inde ... 05,00.html ኬንያ የት እንዳለች ተመልከት /92ኛ/, ሱዳንን እይ /93ኛ/ ታዲያ እነዚህ ከኛ አይሻሉም ትላለህ::

ለግንዛቤ ያህል ካቻምና ላፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ በመጨረሻዋ የጊኒ ጨዋታ ተሸንፋ ከውድድር መውጣቷን አይዘነጋም:: ጊኒን ብታሸንፍ ኖሮ ለአፍሪካ ዋንጫ እናልፍ ነበር::

ቸር ይግጠምህ..
ጊዮርጊስ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 45
Joined: Sun Oct 16, 2005 2:36 pm
Location: ethiopia

Postby ጊዮርጊስ » Wed Dec 07, 2005 5:50 pm

አ.አ. ስቴዲየም ከናፈቀህ ደግሞ ይችን ቪዲዮ እያት::

አክባሪህ
http://nazret.com/blog/index.php?title= ... &tb=1&pb=1
ጊዮርጊስ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 45
Joined: Sun Oct 16, 2005 2:36 pm
Location: ethiopia

Postby ደባደቦ » Wed Dec 07, 2005 11:20 pm

የማይገባው ድንጋይ ራስ:: ምን ታቃለህ ሀብትማ ቢሆን እንግሊዝ ስንት ዋንጫ በልታ ነበር:: በተለይ ደሞ አሜሪካ:: ምሳሌ ልስጥህ እንግሊዝ በጣም አሪፍ አሪፍ ኮኮብ ተጫዋች አላት ነገር ግን ዋንጫ ትበላለች ወይ ብትል መብላት ቀርቶ ማሸነፍም በግድ:: እና አስብ ዝም ብሎ ሁል ጊዜ ድህነታችን ድህነታችን አንበል:: ደሞ ድህነት ከሆነ ሩጫስ ለምን እናሸንፋለን? ይህንን ላንተ እንድትመልስልኝ ትቸዋለው:: ግን ማን ዋጋአለው ሰበብ አታጣ ምክንያት ትፈጥራለህ:: ግን እሱንም ቢሆን መልስልኝ
HTML
ደባደቦ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 467
Joined: Mon Feb 28, 2005 11:27 am
Location: ETHIOPIA

Postby ጊዮርጊስ » Thu Dec 08, 2005 11:27 am

የማይገባው ማነ ነው:: እውነቴ ነው የምልህ ስል እግር ኳስ ምንም አታቅም:: ሩጫንና እግር ኳስን ማመሳሰልህ ብቻ ማስረጃ ነው:: ኢትዮጵያንና እንግሊዝን ማውዳደርህ ጭራሽ ከትምህርት ጎዳና ብዙ ሺ ማይል መራቅህን አውኩ አንተን ኳስ, ኢኮኖሚክስ, ዲሲፕሊን...ማስተማር ስለሚከብድ የተካንክባትን የስድት ሙያህን ወጥረህ ያዝ...እስዋን ካጣህ አገርህ ስትገባ አዝማሪ ቤት ውስዱኝ ማለቱም ይቀራል:: መቼም ኮሌጅ ልክፈት አትልም::

ግን አሳዘንከኝ:: አንብብ እንጂ...
ጊዮርጊስ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 45
Joined: Sun Oct 16, 2005 2:36 pm
Location: ethiopia

Postby ወጭባራው » Thu Dec 08, 2005 11:34 am

ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ ሱዳንን 3-0 አይደለም ያሸነፈቻት

3-1 ነው ተሳስተሀልጊዮርጊስ wrote:ድብዳቦ

ኢትዮጵያ ሶማሌን 3 - 1, ሱዳንን 3 - 0 ጅቡቲን 7 - 0 በማሽነፍ ከምድቧ አልፋለች:: ቀጣይ የምድብ 1 አሸናፊ ተጋጣሚዋ ዛንዚባር ትሆናለች::

ኢትዮጵያ መቼ ያለም ዋንጫ ትካፈላለች? ለሚለው ግምትህ ብዙ ነገሮችን ታሳቢ ማድረግ አለብህ:: እግር ኳስና የኢኮኖሚ እድገት አብረው ይሄዳሉ:: ከአለም በድህነት አንደኛ የሆነች ሀገር ያለም ዋንጫ ባለመካፈሏ አይገርመኝም:: እንደውም ብታልፍ ይገርመኛል:: ምን ያህል ሀብት ያላግባብ እየባከን እንደሆነ የማስብ ይመስልኛል:: ፉትቦል ኢንቨስትመንት ነው:: ባንድ ቀን የምታደርሰው ነገር አይደለም:: የኢትዮጵያ ድህነት በዚሁ ከቀጠለ አንተ የገመትከው ቀን በጣም ቅርብ እኮ ነው:: ከኬንያ ጋር ማውዳደርህም ይገርማል:: ኬንያ እኮ ከኛ በጅጉ የተሻለች አገር ናት:: እስኪ የፊፋን ሰንጠርዥ እየው http://fifa.com/en/mens/statistics/inde ... 05,00.html ኬንያ የት እንዳለች ተመልከት /92ኛ/, ሱዳንን እይ /93ኛ/ ታዲያ እነዚህ ከኛ አይሻሉም ትላለህ::

ለግንዛቤ ያህል ካቻምና ላፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ በመጨረሻዋ የጊኒ ጨዋታ ተሸንፋ ከውድድር መውጣቷን አይዘነጋም:: ጊኒን ብታሸንፍ ኖሮ ለአፍሪካ ዋንጫ እናልፍ ነበር::

ቸር ይግጠምህ..
ወጭባራው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 102
Joined: Sun Sep 25, 2005 1:13 pm
Location: australia

Postby አምባሳደር » Thu Dec 08, 2005 11:00 pm

8/12/05: Ethiopia 4-0 Zanzibar

good Ethiopian boys.
What is next?
አምባሳደር
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 37
Joined: Fri Nov 12, 2004 5:41 pm
Location: united states

Postby ጊዮርጊስ » Sun Dec 11, 2005 7:57 pm

እንኳን ደስ ያላችሁ:: አሁንም የዋንጫው ባለቤት ሆነናል::
ጊዮርጊስ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 45
Joined: Sun Oct 16, 2005 2:36 pm
Location: ethiopia

Postby አምባሳደር » Mon Dec 12, 2005 9:55 am

2006 Champions: Ethiopia

Even at this worst time of our history (so many depressing events at home) our boys have proven that we are still regional supper powers. Thank you boys! good work.
What is next?
አምባሳደር
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 37
Joined: Fri Nov 12, 2004 5:41 pm
Location: united states

Re: ይምስራቅ አፍሪካ ዋንጫ

Postby እንቁየ » Tue Dec 13, 2005 5:26 am

ደባደቦ wrote:ሰላም ወገኖቼ መቼም ቀን አይደርስ የለ ደረስ :: አሁን ሰሞኑን የሀገራችን ቡድን ከሱማሌው አቻው ጋር ግጥሚያ ያደርጋል :: አይ ውርደት አይ ውርደት እኔ ብቻ ሀገራችን ተሸነፈ ቢባል ......... (የምለው የለም ): እነ ኬንያ አሁን አድገው ለአፍሪካ ዋንጫ እንኳን ትፋለች የኛዋ ግን በጣም ጎበዝ ከሆኑ ጊዜ የምስራቅ አፍሪካን ማጣሪያ ያልፋሉ ደሞ ይችም ውጤት ሆኖ ይጎርራሉ :: አይ መጥኔ የፋራ ነገር :: እዚህ አምድ ላይ ባለፈው ጊዜ አንድ ነገር ፅፌ ነበር :: ታዳሚው ሁሉ ተናዶቢኝ ነበር :: ግን ይህ ሀቅ ነው :: እኛ የአለም ዋንጫ ይምንበላው ሳይሆን የምንሳተፈው ይህ እኛ ያለንበት ጀኔሬሽን ሲያልቅ ነው እሱም ድንገት ከተቀየረ ለመብላት ሳይሆን ለመሳተፍና ለመመለስ :: ይህ ማለት ደሞ ምናልባት 2099 አመትምህረት ለመብላት ግን 5000 አመተምህረትም እንጃ ያደሞ
_________________
ስላም ወዳጀ ስለ አገራችን ብዙ ተብሏል ነገር ግን ያልተረዳህው ነገር ቢኖር እንደ እድል ሆኖ በአገራችን ያለው የእርስ በእርስ ጦርነት እንደ ደግ ነገር ከአባት ወደ ልጅ ከትውልድ ወደትውልድ እንደ ተስቦ እየተላለፈ እየህውና ያሁኑን ትውልድ ያሽ ሞደምደዋል ::
ይቅርታ እኒ እንካ ቦተሊካ ለቦተሊከኛች እንተወእና ስለአገራችን የእግርካስ እድገት ያለስ አስተሳስብ ምን አልባት ካለህ የካስ ፍቅር አካያ እና ፍቅርህን ምኞትህን መግለጽ የፈለክ ይመስለናል :; ግን እስቲ ምን አልባት ትዝታው ካለህ በአለቀ ሳአት ግብ አስቆጥረን የዝንባቢ ቡድን በቅታት ምት አሽንፈን የዋንጫ ባለቢት በሆንበት ወቅ ት የነበሩን ጥሩ ተጫዋቾች ስለ 1990 ለተደረገው የአለም ዋንጫ ማጣሪ ደርስን የመጨረሳው ጭዋታ የመጀመሪያው ዙር ከግብጽ ጋር አ.አ እስትዶኢዩ 1 ለባዶ አሽንፈን መልስ ካይሮ እኩል በመውጣት ማለፍ የምንችልበት እድል ነበር ግን ... 5 ለባዶ በሆነ ውጠት ተሽንፈን ግማሾቹ ተጫወቾች ጥገኝነት ጠይቀው ግብጽ ቀሩ:;...... ከዚያም ብዙ አመርቂ ውጠት ባይታይም ግን ጅምሩ ጥሩ ይመስላል ከጥቂት አመታት በፊት በተደረገው የታዳጊወች ውድድር በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዚ አገራችን አፍሪካን ወክላ በአርጀንቲና በተደረገው ውድድር ተሳትፋለች ሆላንድ ኮስተሪካ እና.... ጎል አስቆጥረው ቢሽነፉም ያስደስታል እና

የተስፈ ምርኮኛ በተስፋ ይኖራል እና "' በተስፈ ጥሩ ነገር ተመኝ ጊዝው እሩቅ አይደለም እና

መልካም ቆይታ
እንቁየ
እንቁየ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 111
Joined: Tue Feb 03, 2004 6:49 am

Postby ሰበቡ » Tue Dec 13, 2005 9:29 pm

ወንድም ጊዜው በጣም ሩቅ ነው:: አሁን ሁሉም የችን የምስራቅ አፍሪካ ዋንጫ አግኝተን እንደሰታለን ግን ይች ምንም ተስፋ የምትሰጥ አደለም እኔ ይህንን ከሰፈር ዋንጫ ጋር ነው የምመድበው: የናንተን አላውቅም...
እኔ ሀገሬ ዋንጫ ብታገኝ በጣም ደስተኛነኝ ግን ውጤቱን ለማግኘት በጣም ሩቅ ነው:: አሁን ዋንጫ ብንበላ ነገ ደሞ ይህንኑ እንጂ ሌላ አዲስ ለውጥ የለውም ወይም የባሰበት ይሆናል እኔ ግን ሱማሌንታ ኤርትራን ሱዳንን አሽነፍን ብዬ አልጨፍርም አዝናለው እንጂ
አመሰግናለው
ሰበቡ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 127
Joined: Thu Oct 13, 2005 5:01 pm
Location: UK


Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest