ነገ ምሽት ቅዳሜ ወደሪቨር ሳይድ ስታዲየም እንጉዋዛለን:: በዚህ ስታዲየም ባለፈው ሲዝን የማይረሳ አሳዛኝ ሽንፈት በሚድልስ ቦሮ ደርሶብናል:: 4 ለ 1:: 'የነገው ጨዋታ ያለፈውን ሽንፈት የምንበቀልበት ነው' ሲል አርጀንቲናዊው ተከላካይ ሄንዜ ከአሌክስ ፈርጉሰን ጋር ዛሬ ጠዋት በማን.ዩናይትድ ሬድዮ ጣቢያ መግለጫ ሰጥቱዋል::

ይህ ጨዋታ ለማንቼ ወሳኝ ነው:: ከዚህ ቀጥሎም ከማን.ሲቲ ጋር ያለብን ግጥሚያ እንዲሁ የዘንድሮውን ድል ለማሳካት ወሳኝ መሆናቸውን ጌታ ፈርጉሰን ተናግረዋል;:
በማንቼ በኩል የክንፍ ተጫዋች እና የአጥቂ ችግር እየጎላ ይመስለኛል:: ይህም በጉዳት የተነሳ ነው;: እናም ኮሪያዊው ጂ ሱንግ ፓርክ እና ሶሻ መዳናቸውና ልምምድ መጀመራቸው አበረታች ነው::
በሌላ በኩል ፌብሩዋሪ 2 ፈርናንዶ ቶሬስ ወደ ኦልትራፎርድ ይመጣል:: ስፔን እና እንግሊዝ የወዳጅነት ግጥሚያ አላቸው:: ቶሬስ የማንችስተርን የልምምድ ሜዳ ካርሊንግተንን የማየት እድልም ያገኛል:: ይህም ልጁ ኦልትራፎርድን እንዲመርጥ ይገፋፋዋል የሚል ግምት አለ:: እንዲሁም አሜሪካዊው አጥቂ ፍሬዲ ኤዱ 15 ቀን በካርሊንግተን ከማንቼ ተጫዋቾች ጋር ልምምድ ሲሰራ ስንብቶ ወደ ዲሲ ዩናይትድ ተመልሷል:: ይህ ወጣት ጉደኛ አጥቂ በጃንዋሪ የዝውውር መስኮት ከባየር ሙኒኩ ሚድፊልደር ሀርግሪቭስ ጋር ኦልትራፎርድ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል::
እንግዲህ ረቡእ ምሽት ኤቨርተንን በረታንበት ጨዋታ ያልተሰለፉት ሪያን ጊግስ, ቪዲች, ስኮልስ እና ሰሀ በሚድልስ ቦሮው ጨዋታ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል::
የቸልሲ ጨዋታ ኮከብ የነበረው ካሪክ እንዲሁም በኤቨርተን ጨዋታ ስታር የነበረው እስከ አሁን ፕሪምየር ሊጉ ከተጀመረ ምንም ያልተቀየረው ብቸኛው ተጫዋቻችን ሪዮ ፈርዲናንድ በጥሩ አቁዋም ላይ መገኘታቸው ለጌታ ፈርጉሰን እፎይታ ሆኖላቸዋል:: ቢሆንም ሮናልዶና ጊግስ ጉዳት እያለባቸው መሰለፋቸው ሌላው ራስ ምታት ነው:: አሁን ፓርክ እና ሶሻ ደርሰዋል:: ተስፋ ይኖራል::

የቦሮን እና የማንቼን ጨዋታ የሚዳኙት አልቢተር ክሪስ ፎይ ናቸው::
ሮኒ በዚህ ጨዋታ አንድ ጎል ይፈልጋል:: ይህን ማሳካት ከቻለ በፕሪምየር ሊጉ ያገባቸውን ጎሎች ብዛት 50 ያደርሳል:
ሰሀም እንዲሁ አንድ ጎል ካገባ 100ኛው የፕሪምየር ሊግ ጎሉ ትሆናልች::
ሁለቱ ክለቦች ከዚህ ቀደም ያላቸው ውጤት
በአጠቃላይ
በሊግ: Middlesbro 29 አሽነፈ, Man United አሽነፈ, አቻ 20
በፕሪምየር ሊግ: Middlesbro 5 አሽነፈ, Man United 12, አቻ 5
atበሚድልስ ቦሮ ሜዳ ላይ ያላቸው ውጤት
በሊግ: Middlesbro 18 አሸነፈ, Man United 19, አቻ 11
በፕሪምየር ሊግ: Middlesbro 2 ሲያሸንፍ, Man United 7 አሸንፎ 2 ጊዜ አቻ ወጥተዋል::