'የነገው ጨዋታ ወሳኝ ነው:: የግድ 3 ነጥብ ይዘን መመለስ አለብን' ነበር ያሉት አሌክስ ፈርጉሰን ፖርቱጋላዊውን ዊንገር ሮናልዶን አጠገባቸው አስቀምጠው ዛሬ ጠዋት በሰጡት የፕሪ ማች ፕሬስ ኮንፈርንስ ላይ:: 'ከቸልሲ ጋር ሙሉ የ3 ነጥብ ቻንስ አለን:: ይህን ቻንስ መጠቀም ያለብን ለሁሉም ጨዋታዎች ክብደት ሰጥተን ስንጫወት ብቻ ነው' ያሉት ጌታ ፈርጉሰን ተጫዋቾቻቸው የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ለመውሰድ ያላቸውን ጉጉት አድንቀዋል::
በነገው ጨዋታ በብላክበርን ጨዋታ የተጎዳው አንበላችን ጋሪ ኔቭል ሀገሩ ከሆላንድ ጋር በነበራት ጨዋታ በጉዳት የተነሳ አርፎ የነበረ ሲሆን በዚህ ጨዋታ ግን ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል::
ዘንድሮ በሁሉም የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ ሪከርድ ያለው ሪዮ ፈርዲናንድ ረቡእ ምሽት እንግሊዝ ከሆላንድ ጋር በአያክስ ባደረገችው ፍሬንድሊ ማች ላይ ያሳየው ድንቅ ብቃት አስወድሶታል:: ይህም ለማንቼ ተከላካይ ክፍል ጠንካራ ግምት እንዲሰጠው አሳማኝ ምክኒያት ይሆናል::
ዋይኒ ሮኒ በዚህ የሆላንድ ጨዋታ ጎል ያስቆጠረ ሲሆን ልጃችን በጣም አስፈሪ አጥቂ መሆኑን አስመስክሩዋል:: ሚካኤል ካርሪክም የዘንድሮ ምርጥ ግዢ መሆኑን ለጌታ ፈርጉሰን በእርግጠኝነት አሳይቶዋቸዋል::
ማንቼ ከሼፍልድ ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ የሚዳኙት አልቢትር ማርክ ካትልብርግ ናቸው:: ሁለቱ ክልቦች ከዚህ ቀደም ያላቸውን ውጤት ስንቃኝ:-
በአጠቃላይ
በሊግ: Sheff United 33 wins, Man United 38, Draws 15
በፕሪምየር ሊግ: Sheff United 1 win, Man United 3, Draws 0
በሼፍልድ ሜዳ ላይ ያላቸው ውጤት
በሊግ: Sheff United 22 wins, Man United 12, Draws 9
በፕሪምየርሊግ: Sheff United 1 win, Man United 1, Draws 0
ዳረን ፍሌቸር ነገ 100ኛውን የፕሪምየር ሊግ ጨዋታውን ያከናውናል:: ቫንደርሰር በበኩሉ 50ኛውን ጨዋታ ነው ከማንቼ ጋር የሚያደርገው::
መልካም እድል ለማንቼ
የእኔ ግምታዊ አሰላለፍ
ቫንደርሳር
ጋሪ ሪዮ ቪዲች ሄንዜ
ፍሌቸር ስኮልስ ካሪክ ጊግስ
ሮኒ ሰሀ
ተጠባባቂዎች:- ኩዛክ, ሲልቨስተር, ኤቭራ, ሮናልዶ
