'የዳኛ መለዋወጥ ውጤት አይቀይርም:: በእርግጠኝነት ተዘጋጅናል አሽንፈናቸው የ6 ነጥብ እድላችንን እናሰፋለን::'
- ጌታ ፈርጉሰን
'በማንቸስተር መሸነፍ ማለት የመሬት መገልበጥ ይደርሳል ማለት አይደለም:: ማንቸስተር ትልቅ ቡድን ነው, ትልልቅ ተጫዋቾች አሉት, ጥሩ አስልጣኝ አላቸው:: እኛም ትልቅ ቡድን ነን:: በአጭሩ የእሁዱ ጨዋታ የመላውን አለም ትኩረት ይስባል:: ልናሽንፍ ነው ወደ ኦልትራፎርድ የምናመራው'
- ጆሴ ሞሪንሆ
ባለፉት አምስት ጨዋታዎች ቸልሲ እና ማንቸስተር ያላቸው ውጤት
መቼ የተጫወቱበት ቦታ ውጤት የመጀመሪያውን ጎል ያገባው
29.04.06 Away Lost 0-3 Gallas (5)
06.11.05 Home Won 1-0 Fletcher (31)
10.05.05 Home Lost 1-3 Van Nistelrooy (7)
26.01.05 Home Lost 1-2 Lampard (29)
12.01.05 Away Drew 0-0 No scorer
የእሁድ ማታውን የማንቸስተር እና የቸልሲን ጨዋታ ልዩ የሚያደርጋቸው ብዙ ነግሮች አሉ::
ከነዚህም ውስጥ ቸልሲ ማን.ዩናይትድን ካሽነፈ በነጥብ እኩል ሆኖ መሪነቱን ለመጨበጥ የጎል
ስሌት ውስጥ ይገባል:: እንዲሁም ማንቼ ካሸነፈ ከተከታዩ ቸልሲ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት
ወድ 6 ያሳድጋል:: ቻምፒዮን የመሆን እድሉንም ያሰፋል ማለት ነው::
በዚህ የቸልሲ እና የማን.ዩናይትድ ጨዋታ የሚጠበቁት ውድ ልጆች ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና
ዋይኒ ሮኒ ሲሆኑ; ሮኒ ከካራቫልሆ እንዲሁም ሮናልዶ ከአሽሊ ኮል ጋር የሚያደርጉት እልህ
አስጨራሽ ትግል ከወዲሁ የሚዲያ ትኩረትን ስበዋል::
በእኔ ግምት ጨዋታው 1-1 ይጠናቀቃል ብዬ እገምታለሁ:: እናንተስ?
እሁድ በኦልትራፎርድ ማንቸስተርን የሚገጥመው ቸልሲ