ቫንፐርሲ ማን.ዩናይትድ ገባ (የማን.ዩናይትድ የ2012 ሲዝን)

ስፖርት - Sport related topics

Postby አክየ » Thu Aug 24, 2006 10:30 am

ማንቼ 3 ቻርልተን 0

ድል ለማንቸ እና ፈርጉሰን
"Say what you have to say in the fewest possible words"
አክየ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2615
Joined: Thu Jul 28, 2005 7:43 am

Postby ቃላት » Thu Aug 24, 2006 6:19 pm

ማንቼ ወደ ድሮው ብቃቱ እየተመለሰ ለመሆኑ ፍንጭ እየሰጠ ነው:: ዘንድሮስ ተፈጥሮም ህጓን ቀየረች መሰለኝ:: ሰው እያረጀ ሲሄድ ነው የምናውቀው: ጊግስ ግን እንደገና እየተወለደ ነው:: ማንቼ ያለፉትን ሁለት ጨዋታዎች የሚያስደንቅ ብቃት ነው ያሳየው:: እንግዲህ ያዝልቅላችሁ ቀዮቹ ሰይጣኖች!
ቃላት
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 84
Joined: Sun Apr 23, 2006 1:46 pm

Postby ወሮበላው » Fri Aug 25, 2006 7:48 am

....ማንቼ አሁን ጂምሩን እንዳሰመረለት ያዝልቅለት አሁን ነው ነጥብ መሰብሰቢያ ጊዜ ....ቼልሲ ሊጉ እየተጠናቀቀ ሲመጣ እየተዳከመ እንደሚመጣ የባለፈው ሲዝን ምስክር ነው
...ከሁሉ ግን የሚያስደሰተው በቡድን ውስጥ ያለው መናበብ እና ፍጥነት የተሞላበት አጨዋወት በተገኘው ክፍተት መጠቀም መቻል ማንቼ ከ አምናው ስህተቱ የተማረበት ይመስለኛል
ዘንድሮ ማንቼ ውስጥ ያላሻሻለ የለም ብል ያጋነንኩ አይመስለኝም ...ሳሀ ብዙ ተስፋ የምንጥልበት እንደሆነ እያስመሰከረ ነው
የበቀደምለታው የ ቻርልተን ድል ማንቼ ካለ ሮኒ ዋጋ የለውም ለሚሉ
ወገኖች ትልቅ ትምህርት የሰጠ ነው ብዬ አምናለው


ደል ለማንቼ
ወሮበላው
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 841
Joined: Sun Oct 17, 2004 10:52 pm
Location: united states

Postby ቢኖ. » Fri Aug 25, 2006 11:34 am

ማንቼ ብዙውን ጊዜ በውድድር ዘመን የሚጎዳው ምክንያቱን ባላውቅም በሲዝኑ መጀመሪያ የሚጥላቸው ነጥቦች ናቸው:: ዘንድሮ ግን ይሄን ነገር በደንብ ያሰቡበት ይመስላል መቸም ገና በሁለት ጨዋታ ምንም ማለት ባይቻም ረጅሙን ጉዞ በጥሩ ሁኔታ ለመጓዝ የተዘጋጁ ይመስላሉ ፍጻሜአቸውን ያሳምር::
As for me. however, I will boast only about the cross of our Lord Jesus christ. Gela 6:14
ቢኖ.
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 529
Joined: Mon Oct 17, 2005 2:20 pm
Location: ethiopia

Postby አፍሪክ » Thu Aug 31, 2006 6:58 pm

ማልዶ መገመቱ ብዙም ባያዋጣም ካለፉስ ሶስት ሲዝኖች የዘንድሮው ማን ዩናይትድ የማሸነፍ ወኔው ላቅ ያለበትን ሁኔታ ነው የታዘብኩት በሶስቱ ጨዋታዎች:: ከሁሉም ግን ጥሩ የሆነላቸው ቁልፍ ተጫዋቾች በዚዝኑ መጀመሪያ የሚጎዱት ነገር ዘንድሮ ባለመከሰቱ አመርቂ አጀማመር አሳይተዋል:: በዚህ ላይ መገንባቱ እንግዲ የነሱ ስራ ይሆናል:: ግን ቅር ያለኝ በግሩም አጀማመራቸው ተመስጠው በዝውውር ገበያው ላይ ቸልተኝነት ማሳየታቸው አልወደድኩትም:: አንድ የረባ አጥቂና ሠንትራል ሚድፊልደር መገዛት ነበረበት የሚል አመኔታ ነበረኝ:: በተለይ ለቻምፒየንስ ሊግ ግብግቡ ማለቴ ነው:: የሆነው ሆነና መልካም ሲዝን ለማንዩ እመኛለሁ::
አፍሪክ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 505
Joined: Fri Feb 18, 2005 9:05 pm
Location: united states

Postby ሙትቻ » Fri Sep 01, 2006 10:18 am

አፍሪክ ትክክል ነህ ግን አሁን ያለው የማን.ዩናይትድ ስብስብ ጥሩ ነው:: የሁዋላ ደጀን ሆኖ እያገለገለ ያለው ጆን ኦሼ ጋሪ ኔቭል እና ጋብርኤል ሄንዜ ሲድኑ በትክክል ከፖል ስኮልስ እና ከጊግስ ጋር የሚካኤል ካሪክ ምትክ ሆኖ ሚድ ፊልዱን የመምራት ብቃት እንዳለሁ ባለፈው ሲዝን መጨረሻ ላይ አርስናልን ካሽነፍንበት ጨዋታ በሁዋላ በትክክል አሳይቱዋል::

በሌላ በኩል ደግሞ ትናንትና ማን.ዩናይትድ ከብላክበርን ሮቨርስ ጋር ሪዘርቭ ቲሙ ጨዋታ ነበረው:: ቡድናችን በዚህ ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ሲያሽንፍ ደም እና ሞራል ያለው የቀድሞው ሚድፊልራችን አለን ስሚዝ ሙሉ ዘጠና ደቂቃ በአጥቂነት መጫወቱ ሌላው የምስራች ነው::

ቡድናችን በአጥቂ በኩል ችግር የለበትም:: ከማን.ዩናይትድ ጋር ለዘላለም እንደሚሆን የገልጠው ዋይኒ ሮኒ; የምንጊዜም ምርጫችን ሶሻ (ሶልሻየር), የቫን ምትክ ሰሀ እንዲሁም ለቡድናችን ደም የሆነው አለን ስሚዝ ዘንድሮ ብቃታቸው 'ወርልድ ክላስ' አስብሎዋቸዋልና አልሰጋም:: በሌላ በኩል ጂሱንግ ፓርክ, ኮከባችን ሮናልዶና አለኝታችን ሪያን ጊግስ በአስፈላጊው ጊዜ አጥቂ መሆን እንደሚችሉ አትጠራጠር::

የአሜሪካው ተወላጅ ጣሊያናዊው የ19 አመት አጥቂያችን ጉሴፒ ሮሲ ለማግፓይስ (ኒውካስትል) በውሰት እስከ ጃንዋሪ ድረስ የተሰጠ ሲሆን ከጃንዋሪ በሁዋላ በአውሮፓ የስራ ፓስፖርቱን ከሚያገኘው ቻይናዊው ዶንግ ጋር የቡድናችን አለኝታ እንድሚሆኑ ተስፋ አለኝ::

እስከአሁን ቡድናችንን ስገመግመው የሮናልዶ ብቃት እና የፓትሪክ ኢቭራ ማደግ በጣም የሚግርም ነው:: ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ከፉልሀምና ከቻርልተን ጋር በነበረው ማለት ነው ኮከብ የነበረው ፓትሪክ ኢቭራ ነው::

በጋዜጠኞች ምርጫ
1- ከፉልሀም ጋር - ሮኒ
2 - ከቻርልተን ጋር - ሮናልዶ
3 - ከዋትፎርድ ጋር - ጊግስ ኮከቦች ነበሩ::

ሁላችንም ጠቅለል ያለ እውቀት እንድናገኝ ስለማንቼ እናውራ::


ማንቸስተር ፍቅር ነው:::
Image
ሙትቻ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2633
Joined: Fri Mar 31, 2006 7:38 am
Location: other

Postby አፍሪክ » Fri Sep 01, 2006 7:22 pm

ጥሩ አድርገህ አስቀምጠሀል ሙትቻ
በኔ አመለካከት አሁንም ቡድኑ ጎል አነፍናፊ የምንለው አጥቂ የለም:: አሁን ያለው የጠቅላላ ሙዱ ጥሩ ስለሆነ ይህ ጉዳይ ተድበስብሶ ያለፈ ይመስላል::ብዙም አልጣሩም እንጂ ትሬዚጌን ማምጣት ይችሉ እንደነበር ነው:: ሩኒ ጎን የሚጫወት ጎል አምራች የክፉ ወቅት ደራሽ አጥቂ ያለመኖሩን ጎልቶ የሚወጣው እንደ አምናው የቤኔፊካ ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ አይነቱ ላይ ነው:: ታስታውስ እንደሆነ ሩኒ ብቻውን ያለረዳት ሲንከላወስ ሲሯሯጥ ተሸንፈው ወተዋል:: ሳሀ ጎበዝ ነው ግን ቫን ኒስትልሮይን ያህል ግብ ያገባልናል ማለት ዘበት ነው:: ሶልስሻየር እድሜውን super sub ሲባል የጨረሰ ሲሆን ስሚዝም ችሎታው ጣራ ነካ የተባለበት የሊድስ ቆይታው እንኳ በግብ ሀያ ቤት ሲገባ አላየንም:: አማካዩ as long as scholes and giggs are on top of thier form, i wouldnt worry much. because they are still two of the best midfielders in the premiership. but, what if their form dips? do we have the depth to go and replace them effectively? this bothers me, specially when i recall giggs's potential to get injured atleast once in a season. Man utd suffered greately in the midfield for the past few seasons, which cost us three consecutive P-league titles. in my opinion that department is not addressed as properly as it should be. ለማኛውም መልካሙን ለ ቀያይ ሰይጣኖች::
አፍሪክ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 505
Joined: Fri Feb 18, 2005 9:05 pm
Location: united states

Postby አንበርብር » Sat Sep 02, 2006 8:31 am

ሙትቻና አፍሪክ ቡድናችሁ አጀማመሩን ያሳመረ ይመስላል..........ነገር ግን በአሁኑ የገበያ ዝውውር ማንቸስተር ቸል ባለበት ሰሀት ከታች ያሉት እንደነ ዌስትሀም ቶትንሀም ፖርትስማውዝ እና ሌሎች ከመሰሉ ክለቦች ከባድ ፍክክር እንደሚጠብቃቸው የታወቀ ነው ስለዚህ ከአሁኑ ነጥብ መሰብሰብ ጠቃሚ የሚመስልበት ወቅት ነው
አንበርብር
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1278
Joined: Sat Apr 09, 2005 12:01 am
Location: everywhere

Postby ሙትቻ » Tue Sep 05, 2006 5:28 pm

ማንቸስተር ከቶተንሀም ጋር በመጪው ቅዳሜ ይፋለማል::

በዚህ ጨዋታ ኮከባችን ዋይኒ ሮኒ እና ስኮልስ ባይሰለፉም
አሁንም ውጤታማ ክለባችን እንደሚሆን አንጠራጠርም::

የቶተንሀሙ አሰልጣኝ ለማን.ዩትድ ጨዋታ እንደተዘጋጁ
ቢገልጡም ፈርጉስን ሥራ በልብ ነው ያሉ ይመስላሉ::

ቶተንሀሞች ከባየር ሊቨርኩሰን በ10.3 ሚሊዮን ፓውንድ የገዙት ሩማንያዊው አጥቂያቸው
ቤትሮቭ በሙሉ ጤንነት ላይ በመሆኑ በአጥቂያቸው ላይ ተስፋን ጥለዋል::
እንዲሁም ጀርሚን ዴፎ ለአውሮፓ ዋንጫ ማጣሪያ
ኢንግላንድ ሜቄዶንያን 5 ለ 0 ስታሽንፍ 2 ጎሎችን
በማግባቱ በአጥቂ መስመራቸው ተማምነዋል::

ድል ለማንቼ!!
Image
ሙትቻ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2633
Joined: Fri Mar 31, 2006 7:38 am
Location: other

Postby ሙትቻ » Tue Sep 05, 2006 5:30 pm

ማን.ዩትድ ከ አርሰናል

ከ1 ሳምንት በሁዋላ

የፕሪምየር ሊጉ ወሳኝ ጨዋታ


ማን ያሽንፋል?
Image
ሙትቻ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2633
Joined: Fri Mar 31, 2006 7:38 am
Location: other

Postby አፍሪክ » Sun Sep 10, 2006 8:31 pm

ስፐርስ በወረቀት ላይ የፕሪምየርሊጉአምስቱ ትልቅ ቡድኖች the big five አንዱ ነው:: ከነሱ ጋር ተጫውተን ሙሉ 3 ነጥብ ይዞ መውጣት እሰየው ሆኖ ሳለ ማንቼ ያደረገው እንቅስቃሴ ብዙም የሚጥም አልነበረም:: በመጀመርያ 3 ጨዋታዎች ያሳዩትን ወረራ ትናንት በኦልድ ትራፎርድ ላይ ለመድገም ሲሳናቸው ከመስተዋሉም በላይ ቶተንሀሞች ደጋግመው አደጋ እንዲፈጥሩ እድሎችን ከፍተውላቸዋል:: በተለይ ዴፎ እና ሚዶ በጭንቅላት ገጭተው የሳቱስ ኳሶች በነሱ ስታንዳርድ የማይይጠበቅ ማንቼንም እድለኛ አድርጋዋለች:: አጥቂያችን ልዊስ ሳሀም ያለቁ እድሎችን ሲያመክን መዋሉ ጎል አይምሬ አጥቂ መፈረም ነበረበት ሚለውን አቋሜን አጠናክሮልኝ አልፏል::
ብቻ ለሁሉም መልካም ዜናው የቡድኑ ሞተሮች ስኮልስ እና ሩኒ መመለስ አጨዋወቱን rythem የሚመጣለትና ፈጠን እንደሚያረገው አምናለሁ::

በ ቀድሞ red devil ጎርደን ስትራካን ከሚሰለጥነው ሴልቲክ( hoops) ጋር ላለብን የቻምፒየንስ ሊግ መክፈቻ እንዲሁም አርሰናልን በምናስተናግድበት የመጪ እሁድ ፍልሚያ ለታላቁ ማን ዩናይትድ መልካም እድል::
አፍሪክ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 505
Joined: Fri Feb 18, 2005 9:05 pm
Location: united states

Postby ሙትቻ » Mon Sep 11, 2006 12:59 pm

አፍሪክና ሌሎች የማንቼ ወዳጆች በቡድናችን ውጤት እየተዝናናን ነው::
ልዊስ ሰሀ በቶተንሀም ጨዋታ እድለኛ አልነበረም:: እንዳልከው አሁን አምበሳችን ሮኒ ደርሶልናል::
አለን ስሚዝም በፊት መስመር እንዲሰለፍ
የክለባችን ደጋፊዎች በቶተንሀሙ ጨዋታ ላይ አስተያየታቸውን
እየዘመሩ ስጥተዋል:: በዚህም መሰረት ስሚዝ ረቡእ ለቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ከ7ቱ ተቀያሪ ተጫዋቾቸ
መካከል አንዱ ይሆናል:: ይህ ሰበር ዜና ነው::

ሌላው በቅርቡ ኤቨርተንን የተቀላቀለው የቀድሞው የክሪስታል ፓላስ የጎል ማሽን አንዲ ጆንሰን በጃንዋሪ
የዝውውር መስኮት ላይ ኦልትራፎርድ እንደሚደርስ እርግጥ
ሆኑዋል:: ጆንሰን ኤቨርተን ሊቨርፑልን 3ለ0 ባሸነፈበት ጨዋታ 2 ጎሎችን አግብቶዋል::

ቀጣዩ ከሴልቲክ ጋር ከተጫወትን በሁዋላ እሁድ አመሻሹ ላይ ከአርሰናል ጋር እንፋለማለን:;

ከአርሰናል ወቅታዊ ብቃት አንጣር ለማንቼ የሚያስፈራ ነገር ባይኖርም
ሮኒ, ስኮልስ, ቪዲችና ሄንዜይ ለዚህ ጨዋታ መድረሳቸው ሙሉ 15 ነጥብ እንደምንይዝ ሀሳብ አይግባህ::

የሮናልዶ ወቅታዊ ብቃት ያስድስታል:: ሆኖም የሳሀ አቁዋም መዋዠቅ ፈርጊን ቆም ብለው እንዲያስቡ የሚያስገድዳቸው ይሆናል::

ቀጣይ ጨዋታዎቻችን
ዋናው ቡድናችን
ረቡእ ከ ሴልቲክ ቻምፒዮንስ ሊግ - 3:45
እሁድ ከአርሰናል ፕሪምየር ሊግ - 12:00
ነው:: ቀጣዩን እንመለስበታለን::

ድል ለማንቼ::
Image
ሙትቻ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2633
Joined: Fri Mar 31, 2006 7:38 am
Location: other

Postby ሙትቻ » Thu Sep 14, 2006 4:05 pm

http://news.bbc.co.uk/sport1/hi/footbal ... 330298.stm

ታዋቂው የስፖርት ኤክስፐርት ማርክ ላውረንሰን የእሁዱን የማን.ዩናይትድና አርሰናል ጨዋታን በተመለከተ ውጤቱ ምን እንደሚሆን ተንብዮዋል::

በዚህም መሠረት ማን.ዩናይትድ 1 አርስናል 0 ተገምቱዋል::

በእኔ ግምት ጨዋታው 3ለ0 በማን.ዩናይትድ አሽናፊነት ይጠናቀቃል::

እስከአሁን ማንቼና አርሰናል ያላቸው ውጤት
HEAD TO HEAD TOTALS
አጠቃላይ በአርሰናልም በማን.ዩናይትድ ሜዳም ያላቸው ውጤት
League: Man Utd 71 wins, Arsenal 63, Draws 40
Prem: Man Utd 12 wins, Arsenal 7, Draws 9

በማንቼ ሜዳ
League: Man Utd 49 wins, Arsenal 14, Draws 24
Prem: Man Utd 8 wins, Arsenal 2, Draws 4

ጨዋታውን የሚመራው ዳኛ ግርሀም ፖል ነው::

አጠቃላይ የሁለቱን የእሁድ ምሽቱን ጨዋታ ልዩ የሚያደርገው

ከማንቼ በኩል
MANCHESTER UNITED and old adversaries Arsenal face up to each other at Old Trafford in their 199th competitive meeting and 175th in the League. The all-conquering Red Devils have made their best ever start to a Premiership season, while the Gunners have made their worst.

The eight times former Premiership champions are coming off a midweek odd goal in five victory over Celtic in the Champions League. They've not won five League games from the outset of the season since reeling off 10 successive victories in 1985, when Arsenal were beaten 2-1 at Old Trafford in the third match of that sequence.

United hold an eight match unbeaten Premiership string against the Gunners of four wins and four draws.

ከአርሰናል በኩል

ARSENAL go to the Theatre of Dreams eager not to lose a 50th League match on enemy territory. The managers stand all square in their 31-match head-to-head standings at 11 wins a piece with nine draws. But of those drawn encounters, United won the 2003 Community Shield on penalties, and Arsenal the 2005 FA Cup final on penalties.

Like United, the Londoners were victorious in their midweek Champions League match (1-2 at Hamburg). They have never failed to win at least one of the first four matches in the Premiership era, and go back 24 years since last failing to win any of their opening quartet of League fixtures.

The Gunners have failed to score in five of the last six meetings with United in all competitions, including both last season's Premiership meetings. They last beat the Red Devils in the Premiership 0-1 at Old Trafford on 8 May 2002, when Sylvain Wiltord got the winner.


መልካም ውጤት በ74 ሺህ ደጋፊዎቹ ፊት ለሚጫወተው ማንቼ:
Image
ሙትቻ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2633
Joined: Fri Mar 31, 2006 7:38 am
Location: other

Postby ሙትቻ » Sun Oct 15, 2006 2:07 pm

ማንቼ ብቃቱን ባስመሰከረበት ጨዋታ ከጄጂቢ ስታዲየም ከዊጋን ሶስት ነጥብ ቀምቶ መጥቶ የመሪነት ደረጃውን አስጠብቁዋል::

የዋይኒ ሩኒ ድንቅ ብቃት በታየበት በዚህ ጨዋታ ማንቼ ዊጋን አትሌቲክን 3ለ1 አሽንፎዋል::
Image
ሙትቻ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2633
Joined: Fri Mar 31, 2006 7:38 am
Location: other

Postby ወሮበላው » Sun Oct 15, 2006 6:08 pm

ሙትቻ ትላንት በጣም ደስ የሚል ቀን ነበር ..ደስ ያለኝ ማንቼ ማሸነፉ ብቻ አንበሳው ሩኒ ወደ ቀድሞ ብቃቱ መመለሱ እና ጠቅላላው የማንቼ ደጋፊ ናፍቆት የነበረውን በልበሙሉነት መጫወት መውደቅ መነሳት በማይታመን ፍጥነት ኩዋስ መቀማት(ማስጣል) 3እና4 ተጫዋቾቺን ደርምሶ መሆድን እና ፍትፍት የሆኑ ፓሶቹን ማየታቺን በራሱ ከ ድል አይተናነስም ጊግስም ጠቃሚ አሁንም ጠቃሚ መሆኑን ያየኝ ይመስለኛል...
ሙትቻ....በአሁኑ የማንቼ ብድን ውስጥ ትልቅ የሆነ ለውጥ ያየን ይመስለናል...ትልቅ ደረጃ የሚደርስም ይመስለኛል...ግን ምን አልባት አንተም ታዝበህ ከሆነ በግራ የተከላካይ ቦታ ላይ ትልቅ ቺግር ያለ ይመስለኛል...ታስታውስ እንደሆነ ጋብሪኤል ሄንዚ በገባባቸው 2 ጨዋታዎች ላይ ቦታው ተከብሮ ነበር ግን ፈርጂ እርሱን የሚተካ ተጫዋች አላገኙም ፓትሪክ ኤቭራ በታምር በፊዚካልም ሆነ በብቃት ቦታውን ሊያስከብር አልቻለም...ሲልቨስተርም እንዲሁ...ትላንት እንኩዋ አስተውለህ እንደሆነ ሄስኪ ኤቭራን እየጨፈለቃት ነበር ሲሄድ የመበረው....አንተ አንተም ሆነ ሌሎች ማንቼዎች የምትሉትን በሉ...

ድል ለማንቼ
ወሮበላው
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 841
Joined: Sun Oct 17, 2004 10:52 pm
Location: united states

PreviousNext

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest