by ሙትቻ » Fri Oct 20, 2006 8:52 am
'ጦረኛ ተከላካይ ነው' - አሌክስ ፈርጉሰን ናቸው ዛሬ ጠዋት ስለ እሁዱ
የሊቨርፑል ግጥሚያ ስለደረሰው ጀግና ተከላካያችን ጋብሬኤል ሔንዜይ
ድንቅ ብቃት ሲመሰክሩ:: እውነተኛ የተከላካይ ባህርይ ያለው ሄንዜ
ለእሁዱ የሁለቱ ሬድ ዴቭልሶች ፍልሚያ ደርሶዋል:: ሰበር ዜና ነው::
በሌላ በኩል ሪዮ እና ጋሪ የሁዋላ መስመራችንን ይቆጣጠራሉ::
ሪያን ጊግስ እና ሮናልዶ በክንፍ በኩል ጂሚ ካራገርን ሲያሰቃዩ ያመሻሉ::
ሮኒ.. ሰሀና ሶሻ ሆዜ ሬናን ሲያሰቃዩ ያመሻሉ::
የሊቨርፑል የቁርጥ ቀን ልጅ ስቴቨን ዥራርድ ሊቨርፑል ረቡእ ምሽት
ለቻምፒዮንስ ሊግ ከቦርዶ ጋር በነበረው ጨዋታ ያልተሰለፈ ሲሆን
አሁን ስካይ ስፖርት ቲቪ ባስተላለፈው ዜና በእሁዱ ጨዋታ ይገባል::
የማንቼን እና የሊቨርፑልን የእሁድ ግጥሚያ ልዩ የሚያደርገው ኒሚጃ ቪዲክ (ቪዳ)
እና ከረን ሪቻርድሰን 25ኛ እና 22 ዓመት የልደት በአላቸውን በዚሁ ጨዋታ
እለት ያከብራሉ:: ፈርጊ ለሁለቱ ተጫዋቾች የመሰለፍ እድል ከሰጡዋቸው
ታሪካዊ አጋጣሚው ልዩ ይሆናል::
ሊቭርፑል እና ማንቼ እስከ አሁን ባላቸው ውጤት መሠረት
በኦልትራፎርድና አንፊልድ ላይ ተገናኝተው
League: Man United 54 wins, Liverpool 49, Draws 43
Prem: Man United 14 wins, Liverpool 7, Draws 7
በማንቼ ሜዳ
League: Man United 34 wins, Liverpool 14, Draws 25
Prem: Man United 7 wins, Liverpool 3, Draws 4
ውጤት አላቸው::
መልካም እድል ለማንቼ እየተመኘሁ ከዛ በፊት ግን:-
ፈርጊ ሮቴሽን ሲስተም
ሊጀምሩ ነው:: ይህን ተግባራዊ እንድሚያደርጉም ዛሬ ጠዋት በፕሬስ
ኮንፈረንሳቸው ላይ ይፋ አድርገዋል:: ይህን ሲስተም ባርሴሎና እንዲሁም
ሊቭርፑል ይጠቀሙበታል:: ቸልሲ ሞክሮት አልተሳካለትም::
እንዴት ነው የማንቼ ደጋፊዎች ይህን የፈርጊ አዲስ እቅድ እንዴት
ትመለከቱታላችሁ?.. እንወያይበት::
'ዘ ጌም ኮምፖዘር' - የሚል ስያሜ ያገኙት ሰር አሌክስ ፈርጉሰን 20
አመት ማንቼን በማሰልጠን ታሪካዊ ሰው ናቸው:: ኖቬምበር 1
20ኛ አመታቸውን በማንቼ ያከብራሉ::
ለሰር አሌክስ ፈርጉሰን መልካም እድሜን ይስጥልን!!
