ቫንፐርሲ ማን.ዩናይትድ ገባ (የማን.ዩናይትድ የ2012 ሲዝን)

ስፖርት - Sport related topics

Postby ሊሊ ሞገስ » Fri Oct 24, 2008 7:18 am

Image

Birthday Boy
አሁን የተከላካዮች ዐይን ሁሉ ወደ ሩኒ...

ሰላም የማንቼ ደጋፊዎች:: ሲዝኑን አርፍጄ ተቀላቅያለው ተቀበሉኝ::
እውነት ለመጀመሪያ ጊዜ ዋይኒ ሩኒ የሚል ስም የሰማሁት ከ6 አመታት በፊት በጉዲሰን ፓርክ ነበር:: ጨዋታው አርሰናል ከኤቨርተን:: ሩኒ የ16 አመት ወጣት እንደሆነ ኮሜንታተሩ ሲዘግብ ነበር:: በዛ እድሜው በባከነ ሰአት አርሰናል ላይ ከ30 ያርድ አካባቢ ጎል አግብቶ ቡድኑ አሸናፊ እንዲሆን አስችሎት ወጥቷል:: ከዚህ ጊዜ ጀምሮ አይኔ ሲከታተለው ከርሞ እነሆ 1.78 ቁመት ያለው ሩኒ የማን.ዩናይትድ ተጫዋች ሆኖ አየሁት:: ከዛ በፊት ግን በፖርቱጋሉ የአለም ዋንጫ ላይ እስከሚጎዳ ድረስ ያሳየው እንቅስቃሴ በእውነቱ ለማንቼ የሚመጥን ተጫዋች እንደሆነ ያሳያል::
ሩኒ ለመጀመሪያ ጊዜ ለማን.ዩናይትድ ተሰልፎ የተጫወተው በቻምፕዮንስ ሊግ የቱርኩን ፌናርባቼ 6ለ2 ባሸነፍንበት ጨዋታ ላይ ነበር:: በዚህ ጨዋታ ላይ ሀትሪክ ሄሮ መሆን ችሎ ነበር:: ኦክቶበር 24 በመርሲሳይድ ሊቨርፑል ከተማ የተወለደው ዋይኒ ሩኒን አንድ የማን.ዩናይትድ ደጋፊ እንዲህ ሲል ይገልጸዋል:: ""ሁልጊዜ ደስታን ይፈጥርልኛል:: እሱ ባለበት የማን.ዩናይትድ ቡድን ውስጥ ሁልጊዜም አሸናፊ እንደምንሆን አልጠራጠርም"" ይህ የብዙዎቻችን አስተያየት ሳይሆን አይቀርም::
የማን.ዩናይትድ ደጋፊዎች ለሩኒ ከፍተኛ አክብሮት ያላቸው ልጁ ከምንም በላይ ከራሱ ዝና ይልቅ ለክለቡ ውጤት ተጨናቂ የቡድን ተጫዋች ብቻ ከመሆኑ አኳያ ሳይሆን, በኳስ ኮንትሮሉ, በቡድን ኳስ ክፍፍሉ, በአጫጭር ኳሶች ማአለፍ, የጎል እድሎችን በመፍጠር ደረጃ ተሳትፎ በማደረጉም ጭምር ነው:: Rooney is invaluable. He'll always be the first name on the teamsheet for me.
ታታሪው ሰራተኛ ሩኒ ሜዳ ውስጥ ከጎል እስከ ጎል ያለው ተሳትፎ ተነግሮ ሳይሆን ታይቶ የማይጠገብ ነው:: ተከላካዮችን ከምኔው ሲያስጨንቅ አይተነው ተቃራኒ ቡድን ሲያስጨንቀን ደግሞ ተከላካይ ሆኖ እናየዋለን:: ይህ አስገራሚ ወጣት ባለፉት ሲዝኖች እየደረሱበት ባሉት ጉዳቶች ሳቢያ ከበቂ በላይ ማንነቱን እንዳያሳየን እንቅፋት ፈጥሮበት የነበረ ቢሆንም ዘንድሮ ግን ከእግዚአብሄር ጋር ምንም ጉዳት ካላጋጠመው ማንነቱን ሊያሳየን ቆርጦ ተነስቷል:: ያሰበው ካልተሳካ ሜዳ ውስጥ እንደተኮሳተረ ፈገግታውን ሳያካፍለን ጨዋታውን የሚጨርሰው ሩኒ በዚህ ሲዝን ለእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን በ5 ጨዋታ 5 ጎል እንዲሁም ለማን.ዩናይትድ 5 ጎል አስቆጥሯል:: ካለው ስታትስቲክስ ስንረዳ ሩኒ ለብሄራዊ ቡድኑ እና ለማን.ዩናይትድ ባለፉት የመጨረሻ 6 ጨዋታዎች ላይ 7 ጎሎችን አስቆጥሯል::
Happy Birthday Wayne Rooney ! Hope you smack the 100th club at Everton where it all started. Wishing you the best.
ሊሊ ሞገስ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 574
Joined: Sun Jun 17, 2007 3:28 pm

Postby እናትዬ » Tue Oct 28, 2008 4:31 pm

ሊሊሻ እንዴት ነሽ ሀቢቢቲ... ወሮ በላው... ሙቴክስ.. አክዬ.. ቃላት... ብኔክስ... ሻምፕዮን.... ሳቂልኝ..... ማንቼ... ምነው ጠፋችሁ... ሲኑን እናሟሙቀው እንጂ..... ጀግናው የማን.ዩናይትድ ሠራዊት ቅዳሜ እለት ወደ ጉዲሰን ፓርክ ተጉዞ አቻ ወጥቶ መቷል..... ማንቼ በፍሌቸር ጎል 1ለ0 እየመራ 1ለ1 ወጥቷል... በውጤቱ ብስጭት ብዬ ወደ ዋርካ ብመጣ ዋርካም ተዘግታ ሳልተነፍስ እንደ መሬው የጨጓራ በሽተኛ ልሆን ነበር......
ማንቼ በተጫዋች ጉዳት ክፉኛ የተመታ ቡድን ነው... 4 ሚድፊልደሮችን በጉዳት አልጋ ላይ አስተኝቶ የሚጫወተው ማንቼ እንደዚህም ሆኖ ውጤት ማምጣቱ የሚያስከፋ አይደለም...... ግን ያበሳጨኝ ነገር ወትሮ በመርሲሳይድ ክለቦች በሊቨርፑል እና በኤቨርተን ላይ የነበረውን የበላይነት ዘንድሮ ማጣቱ አናዶኛል...
በነገራችን ላይ የአመቱ የፊፋ-ፕሮ ምርጥ XI ውስጥ የማን.ዩናይትድ የክፉ ቀን አንበል ሪዮ ፈርዲናንድ እና ክርስቲያኖ ሮናልዶ ተመርጠዋል.... ሮናልዶ የፊፋ ፕሮ የአመቱ የአለማችን ኮከብ ተጫዋች ሆኖ በመመረጥ አሁን ድረስ ሽልማቶችን በነሳኛና ጋላስ እያሸከመ ይገኛል..
Image
ጋላስ እና ሳኛ ይሸከሙልህ ሮኒ.... በሳቅቅቅቅቅ
በፊፋ ፕሮ የአመቱ ኮከብ በረኛ አልሙኒያ አልሆነም በሳቅቅቅቅቅ.... ኢገር ካሲያስ በረኛ... ተከላካዮች ራሞስ ቴሪ: ፈርዲናንድ እና ፒዮል ሲሆኑ ሚድፊልደሮች ጄራርድ ዣቪ እና ካካ ሲሆኑ አጥቂዎች ሜሲ... ቶሬስ እና ሮናልዶ ሆነዋል.... እኔን የገረመኝ የካካ መመረጥ ነው... ከምር ባለፈው ሲዝን ከካካ እና ከፋብሪጋስ ማን ጥሩ ሥራ ሰርቷል?.... ኤሲ ሚላን ለቻምፒዮንስ ሊግ እንኳ ማለፍ በተሳነው ሲዝን ካካ እዚህ ቲም ውስጥ መግባቱ ያጠያይቃል...
የዌስትሀሙ አጥቂ ካርልተን ኮል በነገው የማን.ዩናይትድ እና የዌስትሀም ዩናትይትድ ፍልሚያ ላይ እንደማይኖር ታወቀ..... በጃን ፍራንኮ ዞላ ቡድን ውስጥ በቋሚ የአጥቂነት ሥፍራ ተሰጥቶት እየተጫወተ የነበረው ካርልተን ኮል አርሰናል ከዌስትሀም ጋር ባደረጉት የቅዳሜ እለቱ ጨዋታ ላይ በቀይ ካርድ ከሜዳ መወገዱ ይታወሳል... በሌላ በኩል ለነገው ጨዋታ ይደርሳል ተብሎ የነበረው የማን.ዩናይትዱ ሚድፊልደር ሚካኤል ካሪክ ላይሰለፍ የሚችል ሲሆን ከዌስትሀም በኩልም የአማካይ ተጫዋቻቸው ማርክ ኖብል ከደረሰበት ጉዳት እንደማይኖር ከወዲሁ ተረጋግጧል....
Image
እናትዬ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1286
Joined: Sat Jan 13, 2007 11:21 am
Location: ቀፊራ - ድሬደዋ

Postby እናትዬ » Tue Oct 28, 2008 4:32 pm

Postby እናትዬ » Tue Oct 28, 2008 4:40 pm

Image
Image
እናትዬ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1286
Joined: Sat Jan 13, 2007 11:21 am
Location: ቀፊራ - ድሬደዋ

Postby ወሮበላው » Tue Oct 28, 2008 6:39 pm

Image

እናቱ ይሄን ዜና ጠዋት አይቼው ነበር እና እኔም ልክ እንዳንቺ ካካ ለምን ተመረጠ ባልልም ፋብሬጋስ እንዴት አልተመረጠም ብዬ ነበር :: ከዤራድ በበለጠ ጥሩ ፐርፎማንስ ላይ የነበረው በባለፍው ሲዝን ፋብሬጋስ ነበር አርሰናል ውስጥም አመቱን ሙሉ በጥሩ አቁዋም የጨረሰው እርሱ ነበር በዛ ደሞ ከስፔን ጋር የአውሮፓ ሻምፒዮን ሆኖዋል :: ፊፋ ለነገሩ ለብራዚሎች ከመጠን በላይ ያደላል ይላሉ ብዙዎች :: ሌላው ደሞ የፑዮል ነገር ብዙም አልተዋጠልኝም :: ... የሮናልዶ እንኩዋ እሱ በቃኝ እስካላለ ድረስ ሚለቁት አይመስልም ... በሰበብ ባስባቡ እርሱን መሸለም ሆኖዋል ::
Image
Man United Forever
ወሮበላው
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 841
Joined: Sun Oct 17, 2004 10:52 pm
Location: united states

Postby ወሮበላው » Wed Oct 29, 2008 12:26 am

እናትዬ wrote:ቸብ!. :lol: ቸብ!. :lol: ቸብ!. :lol: ቸብ!. :lol: ቸብ!. :lol: ቸብ!. :lol: ቸብ!. :lol: ቸብ!. :lol: ማንቼ!...Image

ሀቢቢ... አስተያየትህ መልካም ነበር ግን መጨረሻ ላይ ያልካት ነገር ትንሽ ቅር ስላለኝ ገባሁ... እንደው ይሄ አንደርሰን ከሚሉት ልጅ ይልቅ ፍሌቸር አንድ ሙቱን በዚህ ሲዝን አይሻልም?... ከምር ለብዙ ነገር ስጠብቀው የነበረው አንደርሰን እስካሁን እዚያው ነው ያለው.. በስመ ብራዚላዊ ዝም ብሎ የሚሸቅል እየመሰለኝ ነው... እስካሁን እንኳ ለማንቼ አንድ ጎል እንኳ በነጥብ ጨዋታ ይቅርና በወዳጅነት ጨዋታ እንኳ ያላገባ እንከፍ ሆኖብኛል... ፍሌቸር ግን በጣም አንበሳና ሊጨበጨብለት ይገባል..... ስለዚህ ከቴቬዝ እና ከአንደርሰን ጥምረት ይልቅ የጊግስና ፍሌቸር ቅንጅት ይሻለኛል.....

እናቱ የኔ ነገር ... ባለፍው ከላይ የጻፍሽውን አይቼ መልስ ሰጥበታለው ብዬ አስቤ ነበር :: ይህው ፎርግቼው አረፍኩት ... ብዘገይም ... የኔ አስተሳሰብ ከምን አኩዋያ እንደ ሆነ ተረጂልኝ ... እኔ ቴቬዝን ፈርጉሰን ከሚያስቀምጡት መሀል ላይ ቢያጫውቱት ይጠቅመናል የሚል ነው ... ከቴቬዝ ጋር ለመጫወት ደሞ ከ ፍሌቸር ይልቅ አንደርሰን ተመራጭ ነው :: አንቺም እንዳልሽው ፍሌቸር ባልሳሳት አራት ጎሎች (የበቀደምለታዋን ጨምሮ) አስቆጥሮዋል ;; እንዳልሽው መሀል ላይ የፍሌቸር እና የጊግስ ጥምረት ብዙም የረዳን አልመሰለኝም :: ቅዳሜ ለታ ማንቺስተር ማህእል ክፍሉ በጣም ብልጫ ተወስዶበት ነበር በተለይ ከረፈት መልስ ... :: አንደርሰን ጎል አለማግባቱ ለኔ ይህን ያህል ትርጉም የለውም ልጁ ባለፈው ሲዝን ምንም ጎል አላገባም ግን ስኮልስን ሁሉ አስረስቶን ነበር :: ልጁ በዚህ ስዝን የመድከም ነገር እያየንበት ነው .. ወጣት ነው ከልምድ ማነስ ሊሆን ይቺላል ... ደፍረቱ ና እነዛ ጥሩ ጥሩ ፓስ የሚያረጋቸው ኩዋሶቹ ከቴቬዝ ጉልበት ጋር ተደማምሮ ማንቼ ማሀሉን የተሙዋላ ያረገዋል የሚል ሀሳብ አለኝ :: ጊግስ መሀል ላይ ለመጫወት እድሜው ብቻ ያግደዋል .....
Man United Forever
ወሮበላው
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 841
Joined: Sun Oct 17, 2004 10:52 pm
Location: united states

Postby እናትዬ » Thu Oct 30, 2008 5:58 am

ቸብ.. :lol: ቸብ.. :lol: ቸብ.. :lol: ቸብ.. :lol: ቸብ.. :lol: ቸብ.. :lol: ቸብ.. :lol: ማንቼ........
ማን.ዩናይትድ ዌስትሀምን ደረመሰው...... ፓ ፓ ፓ ፓ ፓ ምንም እንኳ ጨዋታውን በእንቅልፍ የተነሳ ባላየውም በርባቶቭ አሪፍ እንደነበር ወሬ አይደበቅም ሰማሁ.... አሰልጣኝ የቀየረው ቶተንሀም ራግቤ በመሰለው ጨዋታቸው ከአርሰናል ጋር 4ለ4 በመለያየታቸው ደስታዬ ወሰን አልነበረውም... 8 ጎል በአንድ ጨዋታ ማየት ከበረኛ ውጭ ነበር እንዴ ሲጫወቱ ያመሹት ያስብላል.... በተለይ ቶተንሀም በአርሰናል 4ለ1 እየተመራ ከሗላ ተነስቶ 4ለ4 መለያየቱ ውጤቱ ለአርሰናል ደጋፊዎች ሬት ሆኖባቸዋል..............
ጀግናው ማን.ዩናይትድ አንድ ጨዋታ እየቀረው 6ኛ ላይ ቢገኝም አንዱን ጨዋታ ካሸነፈ ከአርሰናል በላይ ሆኖ 3ኛ ላይ ይቀመጣል.... ከክሪስማስ በሗላ ስኖው በረድ ሲል የመሪነቱን ሥፍራ ከሊቨርፑል እንቀበላለን... እከዛ በብርድ ይጠለዙ ከላይ..... ይሞታል ወይ ታዲያ ብሏል ዘፋኙ በሳቅቅቅቅ...
ማንቼ ዛሬ ሁለት ጎል ያገባለት ሮናልዶ ነው... ሮናልዶ በተለይ ቤርባቶቭ በሚያምር ሁኔታ ጨርሶ የሰጠውን ኳስ ጎል ሲያደርጋት ለጎሉ መገኘት በርባ ያደረገው ነገር አስደምሞኛል... ብራቮ በርባቶቭ... 30 ሚሊዮናችን አፈር አልበላውም...
Image
ሮናልዶ የአለማችን ኮከብ ተጫዋች ተብሎ በተመረጠ ማግስት 2 ጎሎችን ማግባቱ ለራሱም ክብር ሲሆን በተለይ በዚህ ሲዝን 25 ጎሎችን ያገባል ተብሎ ከወዲሁ በፈርጉሰን የተገመተለትን ግምት ሊያሰምር መንገዱን ጀምሯል..... ይመቸን ማንቼ...

ማን.ዩናይትድ ፎንቃ ነው... ጨዋታውን ያየ አስተያየቱን ያካፍለኝ....
SAY NO TO DRUGS, YES TO UNITED
Image
እናትዬ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1286
Joined: Sat Jan 13, 2007 11:21 am
Location: ቀፊራ - ድሬደዋ

Postby ወሮበላው » Fri Oct 31, 2008 12:55 am

ሀይ እናትዬ ... ማንቼ መዶሻዎቺን በራሳቸው መዶሻ ቀጥቅጦ አሳጥሮዋቸዋል :: የዛሬ አመት ከ ነውጠኛው ዌስት ፍሬንዴ ጋር ሞቅ ደመቅ አርገነው ነበር የዛሬን አያርገውና ....
የትላንቱን ጨዋታ ከእረፍት በፊት አላየሁም ነበር እረፍት ላይ ነበር የደረሰኩት ... እንዳንቺ እቅልፌን ስለጥጥ እንዳይመስልሽ ... ከእረፍት በዋላ ጨዋታው አርፍ ነበር ለማለት ብዙም አልደፍርም ... የተረጋጋ ነገር ነበር ... ሩኒ በአዲሱ መላጣው ጎል ለማስቆጠር ቢቁዋምጥም አልሆነም ... ሮናልዶ አርሪ ነበር ... ማንቼ ራፋኤልን በኔቭል ከጉዳት ተመላሹን ካሪኮን በፍሌቸር እንዲሁም ሩኒን ቀይሮ አስገብቶዋል ::

ጨዋታውን ለማየት ከፈልግሽ ደሞ ባለፈው እንዳልኩሽ
http://www.utorrent.com/download.php

እዚህች ጋር ሄደሽ መጀመሪያ utorrentን ወደ ኮምፑተርሽ ጫኚ .... ከዛ በዋላ http://www.mininova.org/እዚህ ድረ ገጽ ላይ ሄደሽ ማንችስተር ዩናይትድ ብለሽ ሰርች ስታረጊ የማንቼ አላፊ ጨዋታዎች ሳይቀር ይደረድሩልሻል ያው እየመረጥሽ የማንቼን ጨዋታዎች ለትዝታም መኮምኮም ነው .... ዳውንሎድ ስታደርጊ ባብዛኛው ከ 3 እስከ አራት ሰአታት ይወስድበሻል ...

መልካም ሌሊት (አቤት እንቅልፌ )
Man United Forever
ወሮበላው
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 841
Joined: Sun Oct 17, 2004 10:52 pm
Location: united states

Postby እናትዬ » Fri Oct 31, 2008 3:58 am

ሀቢቢ ነፍ ምስጋና ላንተ.......... ዌስትሀም እኔም ናፈቀኝ.... ከምር ጨዋታው ይደላ ነበር.... (ለካስ በዌስትሀም እና በቸልሲ እኔም እጠረጠራለው :wink: ) በሳቅቅ........... ሀቢቢ እስኪ ያልከኝን ዳውንሎድ አደርገውና እሞክራለው..... በነገራችን ላይ መሬውመራሬው የጠፋበትን ምክንያት ደርሼበታለው... ክሪዲት ካለልክ ወስዶ እዳ ውስጥ ተዘፍቆ ነው.... በሳቅቅቅቅቅ. 16 ሰአት ክሬዲት ለመክፈል እየሸቀለ እንዴት አርሰናልን አይረሳ.... :lol: :lol:
Image
እናትዬ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1286
Joined: Sat Jan 13, 2007 11:21 am
Location: ቀፊራ - ድሬደዋ

Postby ሙትቻ » Sat Nov 01, 2008 5:24 am

ሰላም ሪፐብሊክ ኦፍ ማንቹያውያን:-
ከሳምንታት በፊት ወደ ኤመሬትስ ስታዲየም ተጉዞ የነበረው ሁል ሲቲ አርሰናልን ሜዳው ላይ 2ለ1 ኩም አድርጎት መመለሱ አይዘነጋም:: ከቻሞፒዮን ሺፕ ዘንድሮ ወደላይ ካደጉት 3 ክለቦች መካከል አንዱ የሆነው ሁል ሲቲ ዛሬ በኦልትራፎርድ ከማንቼ ጋር የሞት ሽረት ትግል ያደርጋል:: በዚህ ሲዝን ኒውካስትልን: ቶተንሀምን: አርሰናልን አሸንፈው ከኤቨርተን ጋር ነጥብ የተጋሩት ሁል ሲቲዎች በቸልሲ ባለፈው ሳምንት 3ለ0 ቢገረፉም አሁንም ጥንካሬ ያላቸው ስብስብ እንደሆኑ በጌታ ፈርጉሰን ተመስክሮላቸዋል::
ትናንት ጠዋት ጌታ ፈርጉሰን የፕሪማች ፕሬስ ኮንፈረንሳቸውን ለጋዜጠኞች ሲያሽሩ ""It is a great example to anyone coming out of the Championship and shows what can be done when you are prepared to have a go at teams.
"They are playing three attackers, with Geovanni sitting behind the front two and without doubt they are a goal threat." ብለዋል::
Image
ባለፎቶው: ብራውን ከሚያምረው መላጣው ጋር ወደ አልጋ...
በአሰልጣኝ ፊል ብራውን የሚሰለጥነው ሁልሲቲ የባለፈው አመት የኮካኮላ ሻምፕዮን ሺፕ ሻምፕዮን የነበረ ሲሆን አጀማመሩን እስከመጨረሻው ካደረገ ምናልባት እስከ 10ኛ ደረጃ ዘንድሮ ይዞ ሊጨርስ ይችላል እየተባለ ነው:: እንደ ብዙሀን ተንታኞች ከዚህ ቀደም ዊጋን አትሌቲክ እና ሬዲንግን እንደምሳሌ በመጥቀስ እነዚህ ክለቦች ከኮካኮላ ሻምፒዮን ሺፕ አድገው ፕሪምየር ሊጉን በተቀላቀሉበት ሲዝን አመርቂ ውጤት ይዘው የነበር ቢሆንም የኍላ ኍላ መፈረካከሳቸው በሁልሲቲ ላይም ይደገማል ይላሉ::
በማን.ዩናይትድ በኩል ያለ ትኩስ የጉዳት ዜና ዌስ ብራውን ነው:: ዌስ ብራውን በጉዳት ኦውን ሀርግሪቭስ እና ፖል ስኮልስን ሲጠቃለል በጉዳት የተመለስው ካሪክ ""የወሩን የማንቼን ኮከብ ተጫዋች"" ፍሌቸርን ተክቶ ከአንደርሰን ጋር የመሀሉን ክፍል ይረከባሉ ተብሎ ይጠበቃል:: አምና ስኮልስ እና ሀርግሪቭስ በተጎዱበት ወቅት አንደርሰን እና ካሪክ ጥሩ ተግባብተው ውጤታማ ሥራ በማን.ዩናይትድ የመሀሉ ክፍል ላይ ሲሰሩ እንደነበር እናስታውሳለን:: ዌስ ብራውንን ወጣቱ ብራዚላዊ ራፋኤል እና ጋሪ ኔቭል ተቀያይረው ቦታውን ይሸፍኑለታል:: ጋሪ ኔቭል ነገ ከተሰለፈ ለማን.ዩናይትድ ያደረጋቸው ጨዋታዎች 550ይደርሱለታል:: እንዲሁም የአለማችን ኮከብ ተጫዋቹ ሮናልዶ ነገ በማን.ዩናይትድ ማሊያ 250ኛውን ጨዋታ ያደርጋል::
ሁልሲቲ በታሪኩ ማን.ዩናትድን ኦልትራፎርድ ላይ በፕሪምየርሊግም ሆነ በሊግ አሸንፎ አያውቅም:: እስካሁን 16 ጨዋታ አድርገው 9 ጊዜ ማን.ዩናይትድ ሲያሸንፍ 4 ጊዜ ሁልሲቲ አሸንፏል:: 3 ጊዜ ደግሞ ተከባብረው ተለያይተዋል::
Image
የዛሬውን ጨዋታ የሚዳኙት አልቢትር ማይክ ዲን ናቸው:: ከዊራል የመጡት እኚሁ አልቢትር 9 ጨዋታ ዳኝተው 2 ቀይ ካርድ ሲሰጡ 40 ቢጫ ካርዶችን ሰጥተዋል:: ይህም ወደ ሂሳብ ሲመጣ በየጨዋታው 4.67 ካርዶችን ሰጥተዋል ማለት ነው:: ማይክ ዲን ይህ ሲዝን ከተጀመረ የማን.ዩናይትድን ጨዋታ ሲዳኙ ይህ የመጀመሪያቸው ይሆናል::

ግምት:-
ማን.ዩናይትድ 3 ሁል ሲቲ 0
ግምታዊ አሰላለፍ: ቫንደርሳር:
ራፋኤል: ሪዮ: ቪዳ: ኤቭራ
ሮናልዶ ካሪክ አንደርሰን ናኒ
ቴቬዝ ሩኒ
Image
ሙትቻ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2633
Joined: Fri Mar 31, 2006 7:38 am
Location: other

Postby እናትዬ » Sat Nov 01, 2008 5:39 am

Image
የፕሪማች ዘገባም ተጀመረ.......... ዋውውውውውውውውውውውውው! ቤታችን ወዙ ተመለሰ ማለት ነው.... ሙቴክስ ይልመድብህ......

ማን.ዩናይትድ ከቫንደርሳር ይልቅ ካሁኑ ኩዛክን እና ፎስተርን በእንደዚህ ያሉት ጨዋታዎች እድል እየሰጠ ልምድ እንዲያገኙ ቢያደርግ ሀሪፍ ነው..... ቫንደርሳር ከዚህ ወዲህ እንግዲህ ከአንድ አመት በሗላ የበረኞች አሰልጣኝ እንጂ ግብ ጠባቂ የሚሆን አይመስለኝም.... አይደለም ኳስ እርጥብ ጋቢ እንኳ ቢለጋለት ላይዝ ወደሚችልበት እድሜ ላይ እየሄደ ነውና ጌታ ፈርጉሰን ያስስቡበት... ሌላው ካሪክ እና አንደርስን ላልከው አልጣመኝም... አንደርሰንን ቤንች አድርጎ ካሪክን ከፍሌቸር ጋር ማስገባት ነው እኔ የሚታየኝ... እንዲህ ስላልኩ ሀቢቢ እንዳትቆጣኝ ደግሚ በሳቅቅቅቅ....

Image

ሩኒ መላጣ... የሥላሴ ጦጣ..... :lol: :lol:
Image
እናትዬ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1286
Joined: Sat Jan 13, 2007 11:21 am
Location: ቀፊራ - ድሬደዋ

Postby ሙትቻ » Sat Nov 01, 2008 4:01 pm

እናትዬ wrote:. ቫንደርሳር ከዚህ ወዲህ እንግዲህ ከአንድ አመት በሗላ የበረኞች አሰልጣኝ እንጂ ግብ ጠባቂ የሚሆን አይመስለኝም.... አይደለም ኳስ እርጥብ ጋቢ እንኳ ቢለጋለት ላይዝ ወደሚችልበት እድሜ ላይ እየሄደ ነውና ጌታ ፈርጉሰን ያስስቡበት...ቂቂቂቂቂቂቂ አስቂኝ የሆንሽ ልጅ::

ሩኒ መላጣ... የሥላሴ ጦጣ..... :lol: :lol:

ይሄ ደግሞ ልጅነቴን አስታወሰኝ:: ቂቂቂቂቂቂቂቂ መላጣ የሥላሴ ጦጣ እያልን የተላጩ ሰዎችን መላጣ እየተማታን እንስም ነበር:: ቂቂቂቂቂቂቂ

ማንቹያውያን የማንቼ ጨዋታ ሊጀርምር 12 ደቂቃ አካባቢ ይቀረዋል:: አሰላለፉ ወጥቷል:: ኤቨርተን ፉልሀምን 1ለ0 አሸንፏል:: የማንቼ አሰላለፍ: በአጥቂ መስመር ሩኒ እና በርባቶቭ: መሀል ላይ ሮናልዶ: ካሪክ: አንደርሰን እና ናኒ: በተከላካይ ቦታ አማራው ኔቭል: ሪዮ: ቪዳ እና ኤቭራ ሲቀመጡ በረኛ ቫንደርሳር ሆኗል::
ቤንች ላይ: ቫንደርሰር ክፉ ቢነካው የሚተካው ፎስተር: ጊግስ: ፓርክ: ኦሼ: ፍሌቸር: ዳ ሲልቫ እና ቴቬዝ ዱቅ ብለዋል:: መልካም ጨዋታ ይሁንልን:
Image
ሙትቻ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2633
Joined: Fri Mar 31, 2006 7:38 am
Location: other

Postby ሙትቻ » Sat Nov 01, 2008 4:02 pm

Postby ወሮበላው » Sun Nov 02, 2008 12:12 am

Imageሰላም ዋርክስተራዊያን .... ማንቼ ዛሬ አሳቆን 3 ነጥብ ይዞ ወጥቶዋል ..... አሁን አሁን ማንቼያችን እንደ ቀድሞው ዘጠና ደቂቃ ወጥረው መጫወትን እየዘነጉት መጥተዋል ... አራት ለ አንድ ሲመራ የነበረ ቡድን ... ለዛውም ማንቼ እኩል ላለመለያየት ሲጋደል ይገርማል ... ጨዋታው አርፍ ነበር በሁለቱም በኩል ... ተከላካዮቻቺን ለገቡት 3 ጎሎች ተጠያቂዎች ናቸው .... የመጀመሪያው በ ቪዲች በርናንድ ሜንዲን ማቆም ያቃተው ኤቭራ ለሁለተኛ ጎል ሀላፊነት ሲኖርበት ፈርዲናንድ ደሞ ለሪጎሬው .... በዛሬው ጨዋታ አርሴናል ከአሁኑ በሁክ ሲቲ በደረሰባት የነበረቺበትን ቦታ ላማንቼ አስረክባ የክብር ስፍራዋን አራተኝነትን ከአሁኑ እየተለማመደቺው ትገኛለች ::

ከሁሉ ደሞ ጨካኝ እየሆኑ የመጡት ስፐርሶች ሊቨርፑልን በእንጥፍጣፊ ደቂቃ ባስቆተሩዋት ጎል 3 ነጥባቸውን ተቀብለው ወጥተዋል ... ድሮውንም አያምራቸውም ከላይ መቀመጥ ... ማንቼ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በ 21 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ ሳምንት እየተንኮታኮተች የመጣቺዎን አርሰናልን ከአሁኑ ጃዝዝዝዝ እያልናት ነው ::

ወደ ማንቼ ስመለስ ከሁሉ በፊት ከላይ ያለውን የሮናልዶን ፎቶ ትላንት ታትሞ በወጣው ከኢኪፕ ጋዜጣ ላይ በስልኬ ያነሳሁት ( ለጥራቱ ይቅርታ) እና ጋዜጣው ለሮናልዶ ልዩ እትም ያደረገው ነበር ... ሮናልዶም ጥሩ የሆነ ኢንተርቪው አርጎዋል :: ጋዜጣው ላይ እንዳለውም ለማንቺስተር ከበፊቱ የበለጠ ጎል ማግባት እንደሚፈልግ እና ለክለቡም ፍቅርና አክብሮት እንዳለው ገልፆዋል :: ከቻልኩ ኢንተርቪዎን እዚህ አቀርበዋለው ::
Man United Forever
ወሮበላው
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 841
Joined: Sun Oct 17, 2004 10:52 pm
Location: united states

PreviousNext

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests