ቫንፐርሲ ማን.ዩናይትድ ገባ (የማን.ዩናይትድ የ2012 ሲዝን)

ስፖርት - Sport related topics

Postby ወሮበላው » Sun Nov 02, 2008 10:07 am

ማንቼዎች ምነው ጠፋ አላቺሁ ... ለሊቱን ሞቅ አርጋቺሁት ታድራላቺሁ ብዬ ነበር ... :: እናንተ እስክትመልሱ እና የትላንቱ ጨዋታ ላይ አስተያየታቺሁን እስክሰነዝሩ ድረስ የትናንቱን ቡድን በተናጠል በኔ እይታ ምን ይመስል እንደ ነበር ላስቀምጠው .....

ቫንደርሳር ... ብዙም ከባድ የግብ ሙከራዎች አላጋጠመውም ... ለገቡትም ጎሎች ተጠያቂ ሊሆን አይቺልም መካከለኛ የሚባል ጨዋታ አሳይቶዋል ::

ኔቭል ...... ብዙም አላየሁትም ... ቦታውን አስጠብቆ ወጥቶዋል ... ከዛ ባለፈ ይህን ያህል ክንፍ ላይ አጥቂዎቺን ሲያግዝ አላስተዋልኩትም ... በቦታው ራፋኤልን ባይ ደስ ይለኝ ነበር ...

ፈርዲናንድ .... በመጀመሪያው አጋማሽ በጥም አርፍ የሆነ ጨዋታ ነበር ያሳየው .... ጥሩ ጥሩ ኩዋሶች እየያዘ ይወጣ ነበር ... ለፔናሊቲውም መገኘት ተጠያቂው እርሱ ነው .. ብዙም በዳኛው ውሳኔ ባልስማማም ::

ቪዲች .... ለመጀመሪያው ጎል መቆጠር ያርሱ ጥፋት ቢሆንም ጎል አስቆጥሮ አካክሶዋል ... ብድር በምድር ብሎ ማለት ነው ... ከዛ ባለፈ ቪዳ እንደ ሁሌውም ቪዳ ነበር ::

ኤቭራ .... እሮብ ለታ ሚገርም ጨዋታ ነበር ያሳየው ... ጀት ነገር ሆኖ ነበር .... ትላንትም ቢሆን ከረፍት በፊት አሪም ነበር ... እንደ ሌላው ቀን በማጥቃት ላይ የዘነበለ ጨዋታውን ቀንሶ ነበር ... ብዙም ወደ ፊት አካባባቢ አልታየም ... የቀድሞው ተጫዋች የፓሪስ ሳን ዥርማ ክለብ በርናንድ ሜንዲ ተቀይሮ ከገባ በዋላ ኤቭራ ተፈትኖ ነበር ... አልቀረም ሁለተኛው ጎል የርሱ ጥፋት ነበር ::

ካሪክ ..... ለትላንትናው ጨዋታ ኮከቡ እርሱ ነበር ለኔ ... በአስፈላጊው ሰአት ሁለተኛዋን ጎል አግብቶ ቡድኑ እና ደጋፊው እንዲረጋጋ አድርጎዋል ... እንደምናውቀው የመጀመሪያው ጨዋታ ነው የመጀመሪያ ተመራጭ ሆኖ ሲገባ ... ከዛ ባለፈ ከጉዳት ተመላሽ እንደ መሆኑ ብዙ ነገር አልጠብቅ ነበር ከርሱ ... ግን የሚጠበቅበት በላይ ሰርቶ ነበር የወጣው ... ቡድኑም መሀል ሜዳ ላይ የነበረው ግርማ ሞገስ እንዲመለስ እረድቶዋል ...

አንደርሰን ( አንዲ) .... ቁልምጫዋ እናትዬን ለማነደድ እንደሆነ ይታወቅልኝ ... :lol: :lol: :lol: ... ትላንት በለፈው አመት የምናቀውን አንደርሰንን አይተናል ብል ብዙዎቻቹ ምትስማሙ ይመስለኛል :: ጥሩ ጥሩ ፓሶቺን ያደርግ ነበር ... መሀል ሜዳ ላይ ተጋዳይነቱ እንዳለ ሆኖ ... ድሮ ምትትሮሽ ተጫውቶ እንዳላደገ ያስታውቃል ... ከአያ ሜትር እርቀት ላይ የመታው ኩዋስ ስታዲየሙን አልፎ ይሄዳል ... ያንን ማስተካከል ይገባዋል በተረፈ ከካሪክ ጋር ድንቅ ጨዋታ ነበር ያሳየው ;;

ናኒ ... በጣም ጥሩ ነበር ማለት ይቻላል ... የወትሮው አቁሳዩ ናኒ እቺን ሰሞን እየናፈቀኝ ነው ... እየተረጋጋ መጥአኦዋል :: ለምን ተቀይሮ እንደወጣ አልገባኝ ??

ሮናልዶ ..... አሁንም ሁለት ጎል ... ፈርጉሰን እዚህ ልጅ ላይ ካላቸውን ጥገኝነት ለመላቀቅ አንድ ነገር ማረግ አለባቸው :: ሮናልዶ ያው ሮናልዶ ነበር ምን ማለት ይቻላል :: የርሱ ጎሎች ለ ሶስት ነጥቦች እረድተውናል

ሩኒ ..... ጥሩ ነበር ማለት አልቺልም ... ደካማ የሆነ እንቅስቃሴ ነበር ያረገው ... ከዛ ባለፈ በራሱ ስህተት ቢጫ ካርድ አይቶዋል ... ሩኒ አንዳንዴ ሚያደርጋቸው ነግሮች አሁንም መብሰል እንዳለብት ይጠቁማሉ ... ምናልባት ያ ቢጫ ኦልትራፎርድ ላይ ባይሆን ቀይም ሊሆን ይቺል ነበር ::

ቤርባቶቭ .... ምርጥ ጨዋታ ነበር ያሳየው ... ሁለት ለጎል የሚሆኑ ጎሎቺን አቀብሎዋል ...ተከላካዮችን ግራ ሲያጋባ ነበር ... ያለቀላቸውን ኩዋሶች መረብ ላይ ስጠብቅ አበላሽቶዋቸዋል ... ባጠቃላይ በርሱ ጨዋታ ደስተኛ ነበርኩ ::


ጊግስ ... የቱ ጋር እንደነበረም አላየሁትም ...
ቴቬዝ ... ያው ተጋዳይነቱ እንዳለ ሆኖ ... የርሱ መግባት አልታየኝ ነበር ... ምናልባት ፈርጉሰን አንድ ተጫዋች መጫወት ስላለበት ብቻ መቀየራቸውን አቁመው ቡድኑን ይጠቅማል ወይ ማለት አለባቸው ...
ኦሼም ... ያው ኦሼ ነው ... ብዙም ባላየውም ... ደህና ነበር

እንንግዴ ይህ የኔ የትላንትናውን ማንቼ ያየሁበት አይታ ነበር ... መልካም እሁድ ማንቼዎች ::
Man United Forever
ወሮበላው
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 841
Joined: Sun Oct 17, 2004 10:52 pm
Location: united states

Postby ወሮበላው » Wed Nov 12, 2008 6:10 pm

ሰላም ሰላም ማንቼዎች .... ሰሞኑን እንዴት ነው ... ማንቼያቺን በሽታው አልታወቅ ብሎዋል ... ቺግሩ እዚህ ጋር ነው ለማለት አልተቻለም እኮ ... ጠንካራው የተከላካይ ክፍላቺን እንኩዋ እድሜ ሽማግሌ ሰብሳቢው ፈርጉስን እነ ናስሪ ሲያሽከረክሩት ዋሉ ... ማሀሉ እንዲሁ እንትና ከ እንትና ስንል ሁሉም ዜሮ ሆኑ ... አጥቂዎቹ መግባባት አልቻሉ አንዱ ሲጠልዝ አንዱ ይንቀራፈፋል .... መቺ ይሆን እውነተኛውን ማንቼ የምናየው ???
ማታ የካርሊግ ካፕ አራተኛ ዙር ጨዋታን ለማየት ፈልጌ በምንም መልኩ አልተቻለም ማንቼ ሳይት ላይ ሄጄ ላይቭ ሬድዮ የተላለፍ ስለነበር ተከታተልኩ ... ከሁለተኛ ዲቪዝዮን የመጣው ኩይንስ ፓርክ ሬንጀርስ ጎሉን አላስደፍርም ብሎ ነበር ያመሸው ዌምብሌክ ተጠልፎ የተገኘውን ፔናሊቲ ቴቬዝ አግብቶ በጠባብ በር ለቀጣዩ ዙር አልፈናል ... ተጫዋቾቻቺን ዝም ብሎ አሰቃቂ ሙከራ ከመሞከር ውጭ ያገኙዋቸውን የግብ እድሎች ሳይጠቀሙ መውጣት በጣም እየለመድነው መጥተናል ... በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደሚባለው ... ከነገ ዛሬ ተመለሰ እያልን ስንጠብቀው የነበረው ሀርግሬቭሥ ይህን ሲዝን እንደማይጫወት ተነገረ ... መሀል ሜዳው ባዶ ሆኖዋል ... ስኮልስ እና ፍሌቸርም እንዲሁ ጉዳት ላይ ናቸው ... ምናልባት ሮድሬጎ ፖስቦን ከጉዳት ስላገገመ መሀል ላይ ይረዳን እንደሆን እንጂ ቡድናቺን አጥሩ ሁኔታ ላይ አይደለም ያለው ... ምን ይበጃል ትላላቺሁ ማንቼዎች ???
ፈርጉሰን የፊቱን ክፍል ለቴቬዝ እና ለሩኒ ሰጥተው ያ ከሮናልዶ ጋር የነበራቸው ቅንጂት ለምን መልሶ እንዲመጣ አይሞከርም ??? ቤርባም ምናልባት ተቀምጦ ቡድኑን ሲያይ ምናልባት ለመዋሀድ ይጠቅመው ይሆናል ....
Man United Forever
ወሮበላው
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 841
Joined: Sun Oct 17, 2004 10:52 pm
Location: united states

Postby ወሮበላው » Mon Nov 17, 2008 3:51 pm

5 ጎሎች ለ ጌታ ፈርጉሰን 50ኛው አመት የኳስ ሂወት ስጦታ

ይህ ሳምንት አሪፍ ነበር ... ማንቼ አርሰናልን አወናብዶ ያሸንፈውን ስቶክ ሲቲ ደም በደም ሲያደርገው አርሰናል ደሞ አንድ ወደ ፊት አንድ ወደ ሁዋላ ነው ጫወታዋ ... ባለፈው ሳምንት ፈርጉሰን በሰሩት ጥቃቅን ስህተት አረብ ሜዳ ላይ ከኛ ሶስት ነጥብ እና ሶስተኛ ደረጃ ደረጃውን ማስረከባቺን ይታወሳል ... ቅዳሜ በሜዳቸው ተልከስክሰው ሶስተኛ ደረጃዋን አጥበው ተኩሰው አሳምረው መልሰውልናል :: ሌላው ደሞ ትላንት የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ ነበር እና ኤልፓ ጊዮርጊስን አሸንፎ ዋንጫ ውስዶዋል ... የገረመኝ ኤልፓን የሚያስለጥነው የቀድሞው የቢራ አሰልጣኝ አስራት ሀይሌ መሆኑ ነበር :: ባጠቃላይ
ሳምንቱ የተሳካ ነበር ::
Image
......))) ወደ ቅዳሜው ጨዋታ ስንመለስ ... ሁሌም ለማየት የምንጉዋጉዋለትን ትክክለኛውን ማንቼን ያየን ይመስለኛል .. በእንግሊዝ ብሄራዊ ብድን ውስጥ ተሰላፊ የሆኑት ዋይን ሩኒ እና ተከላካዩ ፈርዲናንድ ባይሆኑም ወጣቱ ኤቫንስ ከሚጠበቅበት በላይ ሀላፊነቱን በሚገባ ተወጥቶዋል ... ሮናልዶን በቅጣት ምቶቹ ተማርሬበት ነበር በቀደም ግን አስደናቂ አስደናቂ ጎሎቺን ነበር ያስቆጠረው ... ከሁሉ ወኔው እና ደስታውን አገላለጹ ተመቺቶኛል .... የተከላካይ መስረራቺን እና በረኛቺን በዙም ስራ አልበዛባቸውም .. መሀል ላይ ካሪክ እና ፍሌቸር ምገረም ቅንጂት ነበር ያደረጉት ... በተለይ ፍሌቸር ከለት ወደ እለት ጨዋታው እየበሰለ ነው የመጠው .. በጣም ሰፊ ቦታን ሸፍኖ ነበር ሲጫወት የነበረው ... ካሪክም እንዲሁ ጥሩ ጨዋታ እና ጥሩ ጎል አግብቶ ወጥቶዋል ... ቴቬዝ ብዙም አልተሳካለትም ጎሉ ላይ .. ግን አጥቂ ቦታ ጥሩ ትግል ሲያደረግ ተስተውሎውዋል .. ቤርባቶቭም እስከ ተከላካይ ቦታ ድረስ መጥቶ እስከመጫወት ደርሶ ነበር ..ፓርክም ውር ውር ስትል ነበር ... ከሁሉም የ ወጣቱ ዌልብሌክ ፍጥነቱ እና ቦታ የመቀያየር ብቃቱ ብቻ ያስገረመኝ ያን የመሰለ ጎል ከረጂም እረቀት ላይ መትቶ ማስቆጠርሙ ነበረ :: ፈርጉሰን በወጣት ተጫዋቾቻቸው እንደሚተማመኑ የተናገሩት እውነት እንደሆነ አስመስክረዋል .. ማኑቾ ዙም ደቂቃ ያልተጫወተ ሲሆን በገባበትም ጊዜ ብዙ የፍጥነት ቺግር ታይቶበታል ::
Man United Forever
ወሮበላው
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 841
Joined: Sun Oct 17, 2004 10:52 pm
Location: united states

Postby ሙትቻ » Tue Nov 18, 2008 8:07 am

Image
ወሮበላው ዘ - ብሔረ ማንቼ! እንደምን አለህ ወንድሜ:: ቅዳሜ እለት ጨዋታውን አይቼዋለው:: በተለይ በወጣት ልጆች ላይ የተመሠረተ ጨዋታ መሆኑ በጣም አርክቶኛል:: ይገርምሀል ለጆን ኦሼ እና ለፍሌቸር ለምን እንደሆነ አላውቅም ጥሎብኝ ፍቅር አለኝ:: ከምንም በላይ ታማኝነታቸው (ለክለቡ) ስለሚታየኝ ይሆን አላውቅም ብቻ ይመቹኛል:: ቤንች ሆኑም አልሆኑም ጫጫታ አያበዙም:: በገቡበት ጊዜ ግን ቦታቸውን አስከብረው ይወጣሉ:: አሁን ፖል ስኮልስ እየተመለሰ ቢሆንም ፈርጉሰን አሁንም ለፍሌቸር ቦታ መስጠት አለባቸው:: ለፍሌቸር ብቻ ሳይሆን ለነዳኒም ሆነ ማኑቾ ቦታ ሊሰጣቸው ይገባል:: እንደዚህ ከሆነ ለመሰለፍ የሚደረገው ትንቅንቅ ክለባችንን ውጤታማ ያደርገዋል:: በተለይ አሁን የቦክሲንግ ደይ ፈታኝ ጨዋታዎች የሚመጡበት ጊዜዎች በመሆናቸው ፈርጊ ሁለት ቡድን አዘጋጅተው የገናን ሳምንት 12ቱን ነጥቦች በሙሉ አግኝተው እንደተለመደው የሻምፕዮኖንነት ሩጫችንን ከጃንዋሪ ጀምሮ ወፈር ፈር ያለ ጃኬትም ቢሆን ለብርዱ ለብሰን መጀመር አለብን::
ፍሌቸር በዚህ ሲዝን የማንቼ ኮከብ ተጫዋች ነው ብል አላጋነንኩም:: በጣም እየሳበኝ ያለ ተጫዋች ነው:: ትዝ ይልህ ከነበረ ጌታ ፈርጉሰን ከ3 አመት በፊት ""ሩኒ; ሮናልዶ እና ፍሌቸር ተስፋዎቼ ናቸው"" ሲሉ ይደመጡ ነበር:: ዛሬ እውን እየሆነላቸው ይመስላል:: ልጁ አንዳንድ ጊዜ የሀገሩን ሶኮትላንድ ብሄራዊ ቡድን ሳይቀር በአንበልነት እየመራ በመግባት ሀላፊነት የሚሰማው በመሆኑ ፈርጉሰን ከ16ቱ ልጆቻቸው ውስጥ ባያወጡት እመርጣለው:: የናኒ; የአንደርሰን እና የቫንደርሳር ነገር ግን ሊታሰብበት ይገባል:: ሦስቱን በዚህ ሲዝን ወርደውብኛል:: ሌላው አየርላንዳዊው ጆኒ ኢቫንስ እንኳንም ፒውኬ ተሸጠ የሚያስብል ብቃት እያሳየን ነው:: ፈርዲናንድ ወይም ቪዳ ስለተጎዱ ብቻ መሰለፍ የማይኖርበት በሳል ተጫዋች ነው::
ሌላው ፈርጉሰን ሰሞኑን ብልህ ከሰው ይማራል የሚባለውን ተረት መከተል ጀምረዋል:: ይበል ይበል ያሰኛል:: በካርሊንግ ካፕ ቸልሲ እና ሊቨርፑል በአንካሳ ቡድኖች ተኮላሽተው መውደቃቸው ለማንቼ ትምህርት እንደሆነና ማንንም ቡድን ንቀው እንዳይገቡ እንደሚያደርጋቸው አስታውቀዋል:: ፈርጊ በካርሊንግ ካፕ ከብላክበርን ጋር ኦልትራፎርድ ላይ በሚያደርጉት ጨዋታ ላይ ወጣቶቹን ሊጠቀሙ ቢችሉም ባሉት ላይ አንጋፋዎቹን ሊያክሉባቸው ይችላሉ:: አርሰናል ቸልሲን ካባረረው በርነሊ ጋር ከሜዳው ውጭ ይጋጠማል:: ይህችን የ''በረኪና ዋንጫ'' ለወጣት ልጆቻችን ሞራል መውሰድ ይኖርብናል::
Image
የማን.ዩናይትድ የብረት አጥር ቪዲች በሁለተኛው ዙር ማን.ዩናይትድ ምን አይነት የዋንጫ ተፎካካሪ ቡድን እንደሆነ ታዩታላችሁ ሲል ከወዲሁ አስጠነቀቀ:: ቪዳ ማን.ዩናይትድ የዘንድሮውን የፕሪምየር ሊጉ ሻምፕዮን የመሆን እድሉ በእጁ ነው ሲል የቸልሲው ምክትል አንበል ፍራንክ ላምፓርድ በበኩል ማን.ዩናይትድን ልንፈራው ይገባል ብሏል:: የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ ራፋኤል ቤንቴዝ በኩላቸው ማን.ዩናይትድን በ20 ነጥብ ርቀት እስካልመራነው ድረስ መኩራራት አንችልም ብለዋል:: ማንቹካ አስመስጋኝ ቡድን እኮ ነው!...
ጥያቄ:- ማኑቾ ኳስ አያያዙ ሰሀን የመሰለው ሰው አለ??

ለሮናልዶ ወፍራሙ አድናቂዎች መልካም ዜና:: ሮናልዶ ወደ ሜዳ ተመልሷል:: Brazilian legend Ronaldo made a return to football earlier tonight, as he took part in a charity match in Morocco.
A visibly overweight and unfit Ronaldo took part in a charity match earlier tonight, which was played to benefit the “Against Poverty” cause.

The contest was organized by the United Nations and was held in Morocco, in front of a packed stadium.

The match was played between the “Friends of Ronaldo”, and the “Friends of Zidane”, which proved to be a great battle.

The Brazilian played just 22 minutes, before being substituted to a rousing reception by the star of the Brazilian national women’s team, Marta.

For the record, Ronaldo’s side ran out 6-5 winners, in a thrilling contest for a great cause.

Image
አሚጎስ በስፓኒሽ ጓደኞች ማለት ነው?... ከስእሉ መማር ቻልኩ:: ቅቂቂቂቂቂቂ::
Image
ሙትቻ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2633
Joined: Fri Mar 31, 2006 7:38 am
Location: other

Postby ቃላት » Tue Dec 09, 2008 4:00 pm

የታላቁ ማንቸስተር ደጋፊዎች ምነው እንዲህ ጠፋችሁ? የማንቼ ስም ወደታች ሲወርድ ደስ ስለማይለኝ ጎትቼ አመጣሁት...


ዩናይትድ! ዩናይትድ!! ዩናይትድ!!!
ማንቼ! ማንቼ!! ማንቼ!!!

ማንቸስተር ፍቅር ነው
ቃላት
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 84
Joined: Sun Apr 23, 2006 1:46 pm

Postby ቃላት » Tue Dec 09, 2008 4:02 pm

ዩናይትድ ፍቅር ነው
ቃላት
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 84
Joined: Sun Apr 23, 2006 1:46 pm

Postby ብናስተውል » Wed Dec 10, 2008 11:09 am

ሰላም ማንችስተራዊያን:

ሰላም ከረማቹህ ወይ? ምነው ዘንድሮ የስፖርት አምድ ቀዘቀዘ? እኔ ደግሞ ከጠፋሁበት አለም ስለ ማንቸ ብዙ ለማንበብ ብቅ ስል ሁሉም ቅዝቅዝ ብሎ ሳገኘው ገረመኝ::

ጊዜውና የመዘገብ ችሎታው ያላቹህ አስነብቡን እስቲ::

ድል ሁሌም ለንጉሱ ማንቼ!!!
Selam le-Ethiopia
ብናስተውል
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1115
Joined: Tue Jan 31, 2006 11:33 pm

Postby ጌታ » Mon Dec 22, 2008 6:23 pm

ዋርካ ስፖርት ያለ ሙትቻ?..............ኤ ጭ!!!!
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby አፍሪክ » Sat Jan 03, 2009 2:09 am

ገና ጃንዋሪን አሀዱ ብለን ከመጀመራችንና የዝውውር መስኮት መከፈቱን ተከትሎ ላለፉት ወራት በድርድር ላይ የሰነበቱትን ሰርቢያዊ ወጣቶችን ከ ፓርቲዛን ቤልግሬድ ላይ ባፋችን አድርገናል:: ስማቸው
1. zoran tosic
2. adem ljajic ይባላሉ::
በበኩሌ ገና ጭምጭምታውን ስሰማ የልጆቹን ኳሊቲ ለማየት በዩትዩብን በጎበኘሁበት ወቅት በ ljajic ክህሎት ተማርኬ ነበር:: ነገር ግን የዞራን tosic በቂ እንቅስቃሴ ስላላየሁ ይህ ነው ማለት ባልችልም በአንዳንድ ፎረሞች ላይ ግን የሰርብያን ፉትቦል እንከታተላለን የሚሉ ሰዎች እንደጻፉት ልጁ እምብዛም የሚያመረቃ ችሎታን እንደሌለው ነው:: እስኪ ጠብቀን ማየት ነው:: እንግዲ የሁለቱ መምጣት የሚያመለክተው በግራ በኩል ናኒ እና ፓርክ ጊግስን መተካት ቀርቶ በስተርጅና የሚያረግውን እንኳን ማድረግ ስላልቻሉ የግራ እግር ተጫዋቹን tosic በስተቀኝ ደሞ የሮናልዶ ነገር ምኑም ስላልጣማቸው ፈርጊ የ 17 አመቱ liajicን ለክፉም ለደጉም አስፈርመዋል:: እንግዲ በ ቪዲች አመርቂ የሆነልን የሰርቢያው ገበያ በታዳጊዎቹም ቢሳካ እመኛለሁ::
p.s. ቶሲች አሁኑኑ ቡድኑን እንደሚቀላቀል ሲታወቅ የ17 አመቱ አደም ሊያጂች ግን እስከሲዝኑ ማብቅያ ድረስ እዛው ፓርቲዛን ይቆያል::


የሁለቱን እንቅስቃሴ የሚያሳየውን የዩትዩብ ቪድዮ አምጥቼዋለሁ

http://www.youtube.com/watch?v=oH0XFSDPzzs

መልካም ግዜ
አፍሪክ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 505
Joined: Fri Feb 18, 2005 9:05 pm
Location: united states

Postby ወሮበላው » Sun Jan 11, 2009 4:27 pm

መላ ማንቺስተራዊያን ... ሙቴክስ - እናትዬ - ሊሊዬ - አፍሪክ - ብናስተውል - ሻምፒዮን - ቃላት እንዲሁም ለጠላት ደጋፊዎች ከአርሰናል አንበርብር ከ ሊቨርፑል ጌታው እንኩዋን ለፈረንጆች አዲስ አመትና ለገና በአለ አደረሳቺሁ እላለሁ በዘገይም እንኩዋ ::
Man United Forever
ወሮበላው
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 841
Joined: Sun Oct 17, 2004 10:52 pm
Location: united states

Postby ጌታ » Sun Jan 11, 2009 7:37 pm

ወሮበላው wrote:መላ ማንቺስተራዊያን ... ሙቴክስ - እናትዬ - ሊሊዬ - አፍሪክ - ብናስተውል - ሻምፒዮን - ቃላት እንዲሁም ለጠላት ደጋፊዎች ከአርሰናል አንበርብር ከ ሊቨርፑል ጌታው እንኩዋን ለፈረንጆች አዲስ አመትና ለገና በአለ አደረሳቺሁ እላለሁ በዘገይም እንኩዋ ::


እንኳን አብሮ አደረሰን ወሬክስ:

በጉጉት ስጠብቀው የነበረው የማንቼና ቸልሲ ጨዋታ የናንተው ማንቹ የምንጊዜም የበላይነቱን ያረጋገጠበት በመሆኑ እንኳን ዴስ አላቹ ልል ነበር አመጣጤ:: የኔዎቹ ከላይ ሆነው ብርዱን ቢሞቁም ማንቼ ቀሪዎቹን ተስተካካይ ጨዋታዎች ከበረታ መሪነቱን ማንም አይቀማውም:: ይህንንም የምለው ትናንት ሊቬዎች ለማይረባ ቡድን ነጥብ ጥለው ስላናደዱኝ ነው::

ሊቨርፑል ፍቅር
ማንቼ ባለድል ነው:: አርሴ ተረስቷል::
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby አፍሪክ » Sun Jan 11, 2009 8:02 pm

ወሮበላው ስለመልካም ምኞትክ አመሰግናለሁ:: በተጨማሪም እግረ እርጥብ ነክ መሰለኝ ቼልሲን 3-0 አሸንፈናል:: ቀሪ ጨዋታዎቻችንን ሙሉ ስድስት ነጥብ ካገኘን ሊቨርፑል አናት ላይ በአንድ ነጥብ ልዩነት ቁብ ማለታችን ነው:: ቤኒቴዝም ይህ ታውቆት ነው መሰለኝ የፈርጊን የሳይኮሎጂ ጦርነት ስታይል ካሁኑ ጀምሮታል:: በሁለት ቀን ውስጥ ሁለቴ ስለሰር አሌክስ ጠንካራ አስተያየቶችን መስጠቱ የጤናው ያርግለት:: እስኪ ካዘለቀው እናያለን::
አፍሪክ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 505
Joined: Fri Feb 18, 2005 9:05 pm
Location: united states

Postby ወሮበላው » Mon Jan 12, 2009 12:55 am

ሰላም በድጋሚ .... አፍሪካቺን እንኩዋን ደስ አለን ::
ጌቾ አለቃህ ጋሼ ቤኔቴዝ ከአሁኑ ልቡ ድው ድው ድው ማለት መጀመሩን የሰሞኑ ንግግሮቹ አሳብቀውበታል ... ማንቼያቺን በድል ጎዳና ላይ እየተረማመደ ነው :: ዛሬ ቸልሲን ቸልሶታል ... በዛሬው ጨዋታ ቡድናቺን ለማንኛውም ድል ብቃት እንዳለው አስመስክሮዋል :: ሁሌም ልናይለት የምንጉዋጉዋለት እውነተኛው ማንቺስተር ሆኖ ነበር የዋለው ::
ማንቼ ከሁለት ቀሪዎቹ ጨዋታዎች እሮብ ከዊጋን ጋር በመሜዳቺን እንጫወታለን ... 6 ነጥባቺንን ላፍ ላፍ አርገን ከላይ ጉብ ማለት ነው ::
ዛሬ ፈርጉሰን ከጨዋታው በዋላ እንዳሉት ተፎካካሪያቺን ቸልሲ ብቻ ነው ብለው ሰሞኑን ቀልቀል ያሉትን ቤኔቴዝን የትም አትደርስም ለማለት ያህል ነበር ::
Man United Forever
ወሮበላው
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 841
Joined: Sun Oct 17, 2004 10:52 pm
Location: united states

Postby ብናስተውል » Mon Jan 12, 2009 3:27 pm

አይይይይ ጽፌ ጽፌ የማይከሰሰው ዋርካ ዋጥ አደረገው::

በሉ በድጋሜ የመጻፍ ሞራሉ እስኪመጣ ድረስ እንኳን ደስ ያለን ማንችስተራዊያን:: የትናንትናው ጨዋታና ውጤት እጅግ በጣም አስደስቶኛል::

በሉ ፈጠን ብለን ለሊቬ ያዋስነውን ቦታችንን መረከብና ማሟሟቅ አለብን ..... እነሱ ብርድ እያስመቱት ነው ያን ይክብር ወንበር::
Selam le-Ethiopia
ብናስተውል
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1115
Joined: Tue Jan 31, 2006 11:33 pm

Postby ወሮበላው » Fri Jan 16, 2009 9:34 am

ማንቼ በወሳኝ ሰአት ወሳኝ ተጫዋቾቹ ጉዳት

በእሮብ ምሽት ማንቼ ጨዋታው በተጀመረ የመጀመሪያዎቹ ሰከንዶች ላይ ሮኒ ባስቆጠራት ጎል ከታላቅ ትግል በዋላ ሶስት ነጥብ ይዞ ሊወጣ ቺሎዋል ::
ማንቼ ቸልሲን እንደዛ ዝብርቅርቁን አወጥቶ ካሸንፈ በዋላ የአብዛኞቹ ግምት ዋንጫው ከማንቼ እንደማያመልጥ እየተናገሩበት ባሉበት ሰአት ማንቼ ቀስ በቀስ ወሳኝ ተጫዋቾቹ በጉዳት እየተለዩት ነው .... ይህም ለዋንጫው ለሚያደርገውን ግስጋሴ እንቅፋት እንዳይሆንበት ሰግቻለው::
ፓትሪስ ኤቭራ ... ዋይን ሩኒ ... ሪዮ ፈርዲናንድ ... ፈርዲናድን በጥሩ ሁኔታ ወጣቱ ኤቫንስ ተክቶት እየተጫወተ ቢሆንም .... አጥቂ ቦታ ግን የቴቬዝ ብቃት በጣም ወርዶዋል ... የሩኒን ቦታ ተክቶ የመጫወት የቀድሞ ብቃት ከድቶታል ዝም ብሎ ትግል ብቻ ሆኖዋል ::
የኤቭራን ጥቅም በተለይ ከ4 ሳምንታታ እገዳ በዋላ በቸልሲ ጨዋታ ላይ ምን ያህል ወሳኝ እንደነበረ አይተናል ..አሁንም ኤቭራችን አለመኖሩ ማንቼን በጣምን ይጎዳዋል ብዬ አስባለው :: አሁን ጉዳትን ያርቅልን እያልኩን የማንቼን ስኬት ያብዛልን እላለው ::

የነገውን የማንቺስተርን እና የቦልተንን ጨዋታ ለቡዳንቺን ከወዲሁ በአሸናፊነት ተወጥቶ ከ ዘብዛባው ቤኔቴዝ የክብር ዙፋኑን እንዲቀበል ምኞቴ ነው ::

መልካም እድል ለዩናትድ
Man United Forever
ወሮበላው
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 841
Joined: Sun Oct 17, 2004 10:52 pm
Location: united states

PreviousNext

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: Bing [Bot] and 2 guests

cron