ቫንፐርሲ ማን.ዩናይትድ ገባ (የማን.ዩናይትድ የ2012 ሲዝን)

ስፖርት - Sport related topics

Postby ሳቂልኝ » Sun Apr 19, 2009 3:06 pm

ማንቼ ከኤቨርተን....
በማን.ዩናይት በኩል ምንም ትኩስ የጉዳት ዜና የለም:: ምናልባት ፈርጉሰን በቻምፒዮንስ ሊግ ክተጫወተው ቡድናቸው ውስጥ አንድ 7ቱን ቀይረው እንደሚገቡ ይታወቀኛል:: ማን.ዩናይትድ ኤቨርተንን እንዳይሆን አድርጎ አሸንፎ ቸልሲን በታላቁ ዌንብሌይ እንዲበቀለው ምኞቴ ነው:: በነገራችሁ ላይ ራፋኤል ቤንቴዝ እንደዚህ ምነው ከእኔ በላይ ሰው የለም አበዛሳ? <ኤቨርተን ትንሽ ቡድን ነው> በማለት ሰሞኑን የሰጠው አስተያየት በመርሲሳይዶቹ ክለቦች ደጋፊዎች ኤቨርተን እና ሊቨርፑል ዘንድ ረግቦ የነበረውን ጥላቻ እንዳያባብሰው ከመፈራቱም በላይ የቤንቴዝን አስተያየት ፈርጉሰን እና የብላክበርኑ አስልጣኝ አላርዲስ ተቃውመዋል::
ሳቂልኝ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 47
Joined: Sat Nov 17, 2007 1:58 pm
Location: Istambul, Turkey

Postby ወሮበላው » Wed Apr 29, 2009 12:04 am

ደረሰ ሰአቱ ... አህዛባን ... ሊያለቅሱ ... ታናሽትዋ በቀያይ ሰራዊት ልትደመሰስ ሰአታት እየቀሩት ነው ::

ወዮልሽ ወዮልሽ አንቺ ታናሽ ሆይ ... አለቀልሽ ... በጎል ደም በደም .... ታናሽዋን አያርገኝ ያን ለት .......;
Man United Forever
ወሮበላው
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 841
Joined: Sun Oct 17, 2004 10:52 pm
Location: united states

Postby እናትዬ » Wed Apr 29, 2009 2:33 pm

ወዮውልሽ አደባዮር.... ከቪዲች መንጋጋ አመልጣለው ብለሽ አትፍጨርጨሪ..... ወዮውልሽ ፋጉሎ... ወዮውልሽ ፋብሪጋስ ከአንደርሰን ክርን ስር ዛሬ አመልጣለው ብለሽ ትደቆሻለሽ...... ወዮውልሽ አድሮ ጥሬ... ወዮውልሽ ሳኛ (ስሙ ሲያስቅ)....... ታናሺቷ አርሰናል ዛሬ ልትሸና.... ባለቢክ ስኪብርቶው አፍንጫ አርሰን ዌንገር በቁማቸው በጭንቀት ሱሪያቸው ሰፍቷቸው በኦልትራፎርድ ሊወልቅ ነው...... በአንጻሩ ታላቁ ማን.ዩናይትድ በድል ሳግ ይራጫል......
ቸብ!,,... :lol: ቸብ!,,... :lol:ቸብ!,,... :lol:ቸብ!,,... :lol:ቸብ!,,... :lol:ቸብ!,,... :lol: ቸብ!,,... :lol:ቸብ!,,... :lol:ቸብ!,,... :lol: ማንቼ!
Image
እናትዬ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1286
Joined: Sat Jan 13, 2007 11:21 am
Location: ቀፊራ - ድሬደዋ

Postby ጌታ » Wed Apr 29, 2009 2:58 pm

ወሬክስና እኑካ ጨዋታው እኮ ኳስ ነው:: እንኳን አርሰናልን የሚያክል ቡድን ይቅርና ሬሊጌሽን የሚያሰጋቸው ቡድኖች የቆመላቸው ቀን ትልልቅ ቡድኖችን ድራሽ ያጠፋሉ::

ለማንኛውም ይቅናቹ እንዳፋቹ ያድርግላቹ እላለሁ::
ማንቼ 2 አርሴ 1
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby እናትዬ » Wed Apr 29, 2009 9:58 pm

እልልልልልልልልልልልእልልልልልልልልልልልልእልልልልልልልልልልልልልእልልልልልልልልልልልልልልል
Image
እናትዬ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1286
Joined: Sat Jan 13, 2007 11:21 am
Location: ቀፊራ - ድሬደዋ

Postby ጓድ ዮሐንስ » Sun May 03, 2009 10:42 pm

ወሮበላው wrote:ደረሰ ሰአቱ ... አህዛባን ... ሊያለቅሱ ... ታናሽትዋ በቀያይ ሰራዊት ልትደመሰስ ሰአታት እየቀሩት ነው ::

ወዮልሽ ወዮልሽ አንቺ ታናሽ ሆይ ... አለቀልሽ ... በጎል ደም በደም .... ታናሽዋን አያርገኝ ያን ለት .......;
አቤት የፈርጉሰን ልጆች
ዘንድሮ እንዲህ ዕንዳሽላላባቹህ መብረጃቹህ ደርሱኣል!!ዶሮ በረጅም ገመድ ስትታሰር የአመለጠች ይመስልታል!!ያለዉ ማን ነበር!!ቅቅቅቅቅቅ
ልጅ ይሮጣል ዕንጂ ፋዘሩን አይቀድምም
ድል ለሊቬ!!!
ጓድ ዮሐንስ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 118
Joined: Wed Dec 19, 2007 1:16 am
Location: usa

Postby ጌታ » Mon May 04, 2009 5:59 pm

ጓድ ዮሐንስ wrote:
ወሮበላው wrote:ደረሰ ሰአቱ ... አህዛባን ... ሊያለቅሱ ... ታናሽትዋ በቀያይ ሰራዊት ልትደመሰስ ሰአታት እየቀሩት ነው ::


ወዮልሽ ወዮልሽ አንቺ ታናሽ ሆይ ... አለቀልሽ ... በጎል ደም በደም .... ታናሽዋን አያርገኝ ያን ለት .......;
አቤት የፈርጉሰን ልጆች
ዘንድሮ እንዲህ ዕንዳሽላላባቹህ መብረጃቹህ ደርሱኣል!!ዶሮ በረጅም ገመድ ስትታሰር የአመለጠች ይመስልታል!!ያለዉ ማን ነበር!!ቅቅቅቅቅቅ
ልጅ ይሮጣል ዕንጂ ፋዘሩን አይቀድምም
ድል ለሊቬ!!!


በሊቨርፑል ወንድሜ ጓድ ዮሐንስ

ማንቼዎች የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ለማጣት ካሁን በኋላ ሁለት ጊዜ መሸነፍ ሲኖርባቸው ሊቬ ደግሞ ሁሉንም ማሸነፍ አለበት:: ይህ እንዲሆን ዘንድ ሊቬ ጠንክሮ መሥራት ብቻ ሳይሆን ተግቶ መፀለይ ይህም ካልበቃ የታምራት ገለታን ሐውዛ መጠጣት ይኖርበታል:: :lol: :lol:

በበኩሌ በሊቬ የዘንድሮ አቋም እጅግ ደስተኛ ነኝ:: ባለፈው በሚድልስቦሮ ባይሸነፉ ኖሮ ምናልባት ተሥፋቸው ሰፊ ይሆን ነበር:: ለጊዜው በቅርብ ዓመታት ካየነው ሁሉ የተሻለ ውጤት በመሆኑ ልንኮራ ይገባናል:: ማንቼ ገገማውም የዋዛ አለመሆኑን አሳይቷል::

ማንቼ ገገማ
ሊቨርፑል ፍቅር ነው::
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ወሮበላው » Mon May 04, 2009 6:34 pm

ጌቾ አንተ ልክ ብለሀል ... ማንቼና የ ቀስተ ደመና ማስቲሽ ከያዙ አይለቁም ቺግሩ መያዙ ላይ ነው :: እናዳለክው ማንቼ ከእንግዲህ በዋላ የሚቀሩት ሁለት ከባድ የሚባሉትን የአርሰናል እና የ ሲቲን ጨዋታ ሜዳው ላይ እንደመጫወቱ እንደዚህ በዋዛ ለሊቬ አሳልፎ ዋንጫውን ሚበጥስላት አይመስለኝም :: እናትዬ ወዳ መስለህ ከማንቼ ዋንጫ መውሰድ ከ አንበሳ አፍ ስጋ እንጠመቀማት ይቆጠራል ያለቺው እቺ የልጅ ቡዳ ....
ጉዋድ ዮሀንስ ደሞ ለየት አልክብኝ ... እኛ ስናቅ የሊቨርፑል ደጋፊ ሰከን ያለ ጸጉሩ ገባ ገባ ያለ ( የ ጌቾ መለጥ ያለ ነው) .. ከ አነጋገሩ ረጋ ያለ ምናምን እድሜ ጠገብ ደጋፊዎቺን ነው ምናውቀው ... አንቺ እንዴት ነው ፈንዳ ፈንዳ ያልሽው ?
ቆይ ሲዝኑ ልያልቅ 4 ጨዋታ ቀርቶት አንተ እንዲህ ማናፋት ምን ይሉታል ... በርጂሙ ቢያስሩዋት .. ገመድ ዶሮ ምናምን ምትልበን ... አንተ እና ፍሬንዲህ ቤኔቴዝ እንዲሁ እንደቁዋመጣቺሁ ትቀራላጩ እንጂ የማንቼ እጅ በቀላሉ አይጠመዘዝም ....
ገና ሀያ ምናምን አመታት ይቀራቺዋል ....መጣንልሽ ታናሽቱ .... ወዮልሽ ... ወዮልሽ ... አንቺ ሻኛ .. አንቺ ኩሬ ... ወዮልሽ አለቀልሽሽ ...
Man United Forever
ወሮበላው
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 841
Joined: Sun Oct 17, 2004 10:52 pm
Location: united states

Postby አዋሳው » Mon May 04, 2009 11:27 pm

የማ ደጋፊ ልሁን ?
የማንቼ ለሁን ሊቨርፑል?
አርሴናል ይሻላል?
አቦ ግራ ገባኝ ኤጭ አርፌ ሌብሮን ጄምስ አትላንታዎች ላይ ሲጨፍር አርፌ ባይ ይሻላል
ግን አገር ቤት ስሄድ የማን ልሆን ነው? የግድ እራሴን ማመሳሰል አለበኝ
እምምም አለች እናትዬ
ባለፈው እናትዬ(ማንቼ :D )ከቶትንሀም ጋር ያደረጉተን ጫወታ አይቼ ጉድ ነው ያልኩት
ለመሆኑ አገር ቤት የማን ደጋፊ ይበዛል?

አዋሳው
አዋሳው
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 646
Joined: Tue Apr 19, 2005 11:03 pm
Location: ethiopia

Postby እናትዬ » Tue May 05, 2009 3:56 pm

አዋሳው wrote:የማ ደጋፊ ልሁን ?
የማንቼ ለሁን ሊቨርፑል?
አርሴናል ይሻላል?
አቦ ግራ ገባኝ ኤጭ አርፌ ሌብሮን ጄምስ አትላንታዎች ላይ ሲጨፍር አርፌ ባይ ይሻላል
ግን አገር ቤት ስሄድ የማን ልሆን ነው? የግድ እራሴን ማመሳሰል አለበኝ
እምምም አለች እናትዬ
ባለፈው እናትዬ(ማንቼ :D )ከቶትንሀም ጋር ያደረጉተን ጫወታ አይቼ ጉድ ነው ያልኩት
ለመሆኑ አገር ቤት የማን ደጋፊ ይበዛል?

አዋሳው
አዋስቾ...... አማን ነው የአዳዲስ ሙዚቃዎች ባለቤት..... እኔና ማንቼ እንዳማረብን ይሄው ይህንንም አመት በደስታ እያሳለፍን ነው....

ለጠየቅከኝ ጥያቄ ወደ ኢትዮጵያ ልትሄድ እንደሆነ ተረዳሁኝ..... መልካም መንገድ ይሁንልህ ታዲያ ኢትዮጵያ ስትገባ ከ'መ' ሕጎች መካከል አንዱን ምረጥ.... መጠቀም? መታቀብ?... መወሰን?..... የእናት ምክር ነው.....

ኢትዮጵያ ውስጥ የማን ደጋፊ ይበዛል? ከምር ለመገመት አስቸጋሪ ነው... ከሰው ጋር እንዳዋዋልህ ለመደገፍ ከፈለክ ደግሞ አዋዋልህን ማሳመር ነው... ከዱርዬና ፍንዳታ ጋር የምትውል ከሆነ አርሰናልን ትደግፋለህ..... ከኩል ሰዎችና ኳስን ከሚያውቁ ሰዎች ጋር የምትውል ከሆነ የውበት ምልክቶቹን ማን.ዩናይትድን ትደግፋለህ.... ከአሮጊቶችና ሽማግሌዎች ጋር የምትውል ከሆነ ሊቨርፑል አለልህ..... በሳቅቅቅቅቅ....

አዋሳው የዛሬው የማን.ዩናይትድ እና የአርሰናል ጨዋታ እንዳያመልጥህ............


ሐቢቢ መሬው ሳኛውን ሰላም በልልኝ... አንበርብር ሼባው ታውቆታል መሰለኝ ጠፋ.... አቤት ሰው ግን በጣም ነው ለካስ የሚጠገረረው? በሳቅቅቅቅቅ....... ታየኝ እኮ አንቤና መሬው 2 ስራ እየተጠገረሩ ለኳስ ብቻ ሳይሆን ለእንቅልፍ እንኳ ሰአት ሲያጡ..... ምጭ! :(
Image
እናትዬ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1286
Joined: Sat Jan 13, 2007 11:21 am
Location: ቀፊራ - ድሬደዋ

Postby ሙትቻ » Wed May 13, 2009 10:31 pm

1 ነጥብ ብቻ ቀረን....
የሪፐብሊክ ኦፍ ማን.ዩናይትድ ደጋፊዎች ሰላም ብያለው በአጭሩ - ለአንገት ማስገቢያ ያህል:: ተወዳጁ ቡድናችን ዛሬ በጄጂቢ ስታዲየም በቀድሞው የማን.ዩናይትድ ተጫዋች ስቲቭ ብሩስ የሚሰለጥነውን ዊጋንን 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፎ በ6 ነጥብ ፕሪምየር ሊጉን በመምራት ላይ ይገኛል:: ከማንቸስተር ከተማ በሰሜን ምእራብ ውስጥ ተመስርቶ የሚገኘው የዊጋን ክለብ ዘንድሮ ከፕሪምየር ሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ ክለቦች መካከል አንዱ ነበረ:: ዛሬም እንደተለመደው ለማን.ዩናይትድ አልበገሬነቱን አሳይቶ 1ለ0 እየመራ ለሊቨርፑል ደጋፊዎች ካርሎስ ቴቬዝ ተቀይሮ ገብቶ የአቻነቷን ጎል እስከሚያገባ ድረስ ተስፋን ጥሎላቸው ነበር:: የሊቨርፑል ደጋፊዎች ዊጋኖች ወደ ጎል በደረሱ ቁጥር ሲቁነጠነጡ ቢያመሹም በ85ኛው ደቂቃ ሚካኤል ካሪክ የማሸነፊያዋን ጎል ለማንቼ አግብቶ ቡድናችን በ6 ነጥብ ርቀት ላይ ተቀመጧል::
አሁን ባለው ሁኔታ ማን.ዩናይትድ የፕሪምየር ሊጉን ድል አሳክቷል ለማለት ያስደፍራል:: ከእንግዲህ ማንቼ ከሚቀሩት ጨዋታዎች 1 ነጥብ ብቻ ካገኘ ሻምፒዮን ይሆናል::
ከሳምንት በፊት በማን.ዩናይትድ 3ለ1 ቀምሶ ቀልቡ የተገፈፈው የአርሰን ዌንገር ቡድን ባለፈው ሳምንት በቸልሲ 4ለ1 ተሸንፎ ተሰናክሎ ወደ ኦልትራፎርድ ቅዳሜ ይመጣል:: በተለይ ለማን.ዩናይትድ ደጋፊዎች ደስታን እና ምርጥ ስሜትን የሚሰጠው አርሰናልን ማሸነፍ ሲሆን አርሰናልን ቅዳሜ አሸንፈን ሻምፒዮን መሆናችንን ማረጋገጣችን ቅዳሜን ልዩ ቀን ያደርጋታል::

ከፕሪምየር ሊጉ ይልቅ (የተበላ እቁብ በመሆኑ) ስለ ቻምፕዮንስ ሊጉ ፋይናል ብናወራስ?
Image
ሙትቻ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2633
Joined: Fri Mar 31, 2006 7:38 am
Location: other

Postby ሊሊ ሞገስ » Wed May 13, 2009 10:49 pm

[color=darkblue]ሙቴክስ እንኳን በሰላም ተመለስክ! ማንቸስተር ዩናይትድ ከባርሴሎና ጋር ስለሚያደርገው ጨዋታ ብዙ ልንል እንችላለን:: በቅድሚያ ግን የ2008/09 የፕሪምየር ሊጉ ሻምፕዮን ለመሆን አፋፍ ላይ በመድረሳችን እንኳን አብሮ ደስ ያለን ብያለው::
ይገርምሀል "ዘ-ሐበሻ" ጋዜጣ ላይ ስለ ባርሴሎና እና ስለ ዩናይትድ ጨዋታ ነበር አንድ ሙሉ ገጽ የጻፍኩት:: በርካታ ሰዎች ዘገባውን እንደወደዱት ከመልእክቶቻቸው ተረድቻለው:: ዘገባውን በትንሽ በትንሹም ቢሆን ላቅርበው እዚሁ::
የመጨረሻው መጀመሪያ:-ባርሴሎና Vs ማን.ዩናይትድ
'እንዴት ክርስቲያኖ ሮናልዶን ለሪያል ማድሪድ ሸጦ; ካካን ከኤሲ ሚላን አምጥቶ ማን.ዩናይትድ ለማስገባት ያስባል?" ሲል የጻፈው የእንግሊዙ ታብሎይድ (ጋዜጣ) ዘ-ሰን ነበር:: ታብሎይዱ ይህን ያለው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአርሰናል ላይ ከ40 ያርድ አካባቢ በቻምፒዮንስ ሊግ ላይ ያገባውን ጎል እንደእማኝ በመጥቀስ ነበር:: በማን.ዩናይትድ እንዳልተረጋጋ የሚነገርለትና የዝውውር መስኮቶች በተከፈቱ ቁጥር ስሙ ከሪያል ማድሪድ ጋር ዘወትር የሚነሳው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በዚህ ሲዝን ብቻ ከ40 ያርድ አካባቢ ጎል ሲያስቆጥር 8 ጊዜያት አልፈዋል::
'I can't wait" ሲል መግለጫ የሰጠው ደግሞ የቀድሞው የማን.ዩናይትድ ተከላካይ የአሁኑ የባርሴሎና ደጀን ስፔናዊው ዤራርድ ፒውኬ ነው:: ባርሴሎና በላሊጋው ሪያል ማድሪድን በሜዳው 6ለ2 ባሸነፈበት የኤል ክላሲኮ ፍልሚያ; ጨዋታውን በቲቪ ሲያስተላለፍ የነበረው ኮሜንታተር 'ዤራርድ ፒውኬ እንኳ በሪያል ማድሪድ ላይ አገባ" ሲል በማድሪድ ፐርፎርማንስ ላይ ሊሳለቅበት ሞክሯል:: ይህ ተከላካይ ከማን.ዩናይትድ ወደ ባርሴሎና ከተዘዋወረ ወዲህ በማድሪድ ላይ ያገባት ጎል የመጀመሪያው ሆና ስትመዘግብለት በቻምፕዮንስ ሊግ ፋይናል ከባርሴሎና ጋር በመሆን የቀድሞ ክለቡን ማን.ዩናይትድን ለመግጠም ተዘጋጅቷል:: ለዚህም ነው ፒውኬ "ማን.ዩናይትድን ለመግጠም ተዘጋጅቻለው:: የጨዋታው ቀን እስከሚደረስ ድረስ መቆየት እንኳን አልቻልኩም' ሲል የሮም ኦሎምፒክ ስታዲየሙን ፍልሚያ በመጠባበቅ ላይ እንደሆነ አብስሯል::ከቀድሞ የክለብ ጓደኞቹ ዋይኒ ሩኒና ክርስቲያኖ ሮናልዶ ጋር በሚያደርገው ትንቅንቅ በባርሳው አሰልጣኝ ጆሴፍ ጋርዲዮና እነዚህን ሁለት አጥቂዎች የማቆም ሀላፊነት የሚሰጠው ፒውኬ በቻምፕዮንስ ሊጉ ፋይናል ከማን.ዩናይትድ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ልዩ ስሜት እንደሚፈጥርበት; አምና ከዩናይትድ ጋር ያገኘውን የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ዘንድሮ ከኑካምፑ ክለብ ጋር ማግኘትን ይመኛል::
በዓለም የእግር ኳስ ተመልካቾች ዘንድ ከዓለም ዋንጫ በላይ የሚወደደው ቻምፒዮንስ ሊግ ከአፍሪካም, ከአውሮፓም, ከኤሽያም, ከአሜሪካም, ከላቲንም, ከአውስትራሊያም; በአጠቃላይ ከሁሉም የዓለም ክፍሎች የመጡ ምርጥ የእግር ኳስ ፈርጦች ይሳተፉበታል:: የያዝነው የ2008/09 የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ በአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ስር ያሉ ከ52 አገራት የተወጣጡ 76 ክለቦች ተወዳድረውበታል:: እስከ ፍጻሜው ድረስ በተደረጉ 124 ጨዋታዎች በአጠቃላይ 327 ግቦች ተቆጥረው በአማካይ በአንድ ጨዋታ እስከ 2.89 ጎሎች የሚመዘገቡበት የውድድር ዘመን ሆኗል:: በአማካይ እነዚህን ጨዋታዎች በስታዲየም ተገኝቶ የሚመለከተው ተመልካች 40 ሺህ መሆኑ ምን ያህል ውድድሩ ተወዳጅ እንደሆነ ያመላከተ ነው::
ሜይ 27/2009 ፍጻሜውን በሮም ኦሎምፒክ ስታዲየም የሚያገኘውን የቻምፒዮንስ ሊግ ፋይናል ጨዋታ በሚመለከት የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ግንዛቤ አስጨባጭ ዘገባዎችን በአጫጭሩ ይዞ ቀርቧል:: ተከታተሉት::[/quote]
ሊሊ ሞገስ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 574
Joined: Sun Jun 17, 2007 3:28 pm

Postby ሙትቻ » Wed May 13, 2009 10:57 pm

ሊሊሻ አሪፍ ጽሑፍ ነው:: ግን እኔ ክርስቲያኖ ሮናልዶን ፈርጉሰን ከቡድናችን ውስጥ ቢያስወግዱልኝ ደስታዬን አልችለውም:: ልጁ ችሎታ ሳያንሰው የሚያሳየው ባህርይ ግን አልጥመኝ እያለ መጥቷል:: በሲቲ ደርቢ ጨዋታ ሲቀየር ላይ ያሳየውን አስጸያፊ ተግባር እንኳን እኔ የቀድሞው የማን.ዩናይትድ ተጫዋቾች ሁሉ ተችተዋል:: ልጁ በዚህ ከቀጠለ ባህርይው የሌሎቹኑም በካምፕ ውስጥ ያሉትን ልጆች ጸባይ ስለሚበክል ከወዲሁ ማሰናበቱ ተገቢ ነው:: እዛው ሪያል ማድሪድ ሄዶ እንደነሮበን እና ቫንኒስተልሮይ ሲነፍስበት ብናይ መልካም ነው::
Image
ሙትቻ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2633
Joined: Fri Mar 31, 2006 7:38 am
Location: other

Postby ሊሊ ሞገስ » Wed May 13, 2009 11:49 pm

ከባርሴሎና እና ከማን.ዩናይትድ ማን ይበልጣል?
ባርሴሎና እና ማን.ዩናይትድ በቻምፒዮንስ ሊግ ፋይናል ላይ ሲገናኙ የመጀመሪያቸው ይሁን እንጂ; በሌሎች ዋንጫ ፋይናሎች እንዲሁም በቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች በደርሶ መልስ ለ10 ጊዜያት ያህል ተገናኝተ ዋል:: በተገናኙበት የ10 ጊዜ ጨዋታዎች ማን የበላይ ነበር? ቀጥሎ ያለው ስታትስቲክስ መልሱን ይሰጠናል::
የኑካምፑ ክለብ እና የኦልትራፎርዱ ክለብ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፓ የነጥብ ጨዋታዎች መድረክ ላይ የተገናኙት በ1983/84 የውድድር ዘመን ነበር:: የአውሮፓ Cup Winner's Cup ተብሎ በሚታወቀው ውድድር ላይ ባርሴሎና በኑካምፕ ቀያዮቹን ሰይጣኖች ጋብዞ 2ለ0 ቢያሸንፍም በመልሱ ጨዋታ ማን.ዩናይትድ በትያትር ኦፍ ድሪምስ 3ለ0 በማሸነፍ ባርሴሎናን ጥሎ ለዋንጫ በ3ለ2 ውጤት አሸንፎ አልፏል::
ለሁለተኛ ጊዜ ሁለቱ ክለቦች የተገናኙት ደግሞ በ1991 በአውሮፓ Cup Winner's Cup ፋይናል ጨዋታ ላይ ነበር:: በወቅቱ በጆን ክሩፍ የሚሰለጥነው የባርሴሎና ቡድን ከአውሮፓ አስፈሪ ቡድኖች መካከል አንዱ የነበረ ቢሆንም; በዚህ የፋይናል ጨዋታ ላይ በአሁኑ ወቅት ማንቸስተር ሲቲን እያሰለጠነ በሚገኘው የቀድሞው የማን.ዩናይትድ ተጫዋች ማርክ ሂውጅስ አማካኝነት 2 ጎል ገብቶበት በ2ለ1 ውጤት ተሸንፎ Cup Winner's Cup ድልን አጥቷል:: ይህ የማን.ዩናይትድ ድል የእንግሊዝ ክለቦችን ወደ አውሮፓ ውድድሮች ድል በር የከፈተ ተብሎ ሲታወስ ይኖራል:: በነገራችን ላይ ማርክ ሂውጅስ በባርሴሎናም ተጫውቷል::
ለ3ተኛ ጊዜ ባርሳ እና ማንቼ የተገናኙት ደግሞ በ1994/95 ሲዝን በቻምፕዮንስ ሊግ በምድብ ማጣሪያ ላይ ነበር:: በዚህ ውድድር ዘመን ክሩፍ ይዞ የቀረበው ባርሴሎና ማን.ዩናይትድን ያርበደበደ ነበር:: በመጀመሪያው ጨዋታ በትያትር ኦፍ ድሪምስ 2ለ2 የተለያየው የክሩፍ ቡድን በኑካምፕ ደግሞ 4ለ0 አቅምሶታል:: በዚህ ቡድን ውስጥ የአሁኑ የባርሴሎና አሰልጣኝ ጆሴፍ ጋርዲዮላ የነበረ ሲሆን ሪያን ጊግስ እና ፖል ስኮልስም ነበሩ:: ለባርሴሎና 4ቱን ጎሎች ማን.ዩናይትድ ላይ ያገቡት 2ቱን ስቶችኮቭ, ሮማርዮና አልበርት ፌሬራ ነበሩ::
ማን.ዩናይትድ የአውሮፓን ሻምፒዮንነት ክብር በተቀዳጀበት 1998/99 ሲዝን ሁለቱ ክለቦች በማጣሪያ ላይ ተገናኝተው ነበር:: በምድብ ማጣሪያው በኦልትራፎርድም ሆነ በኑካምፕ በተደረገው ጨዋታ 3ለ3 በሆነ ተመሳሳይ አቻ ውጤት የተለያዩበት ጨዋታ የሁለቱ ክለቦች የምንጊዜውም ምርጥ ፍልሚያ ተብሎ ይዘከራል:: በዚህ በ1998/99ኙ የባርሴሎና ቡድን ውስጥ አሁን ድረስ እየተጫወተ የሚገኘው ዣቪ ሄርናንዴዝ የነበረ ሲሆን ከማን.ዩናይትድ በኩል; ጊግስ, ስኮልስ እና ጋሪ ኔቭል እስካሁንም አብረው ናቸው::
አምስተኛው ባለፈው ሲዝን በቻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍጻሜ የተገናኙበት ነው:: በዚህ ጨዋታ በኑካምፕ 0ለ0 ተለያይቶ የመጣው ማን.ዩናይትድ በኦልትራፎርድ 1ለ0 አሸንፎ ለቻምፕዮንስ ሊግ ፋይናል ደርሷል:: 
ሊሊ ሞገስ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 574
Joined: Sun Jun 17, 2007 3:28 pm

Postby ወሮበላው » Thu May 14, 2009 12:19 am

ዊጋንም ተወጋ ... ተወጋ...እተተተተ... ተጠጋ ..... ቬንገር እየሰጋ....እፎይይይይ ... በረጂሙ ተነፈስኩ ... ጨዋታውን ቀድቼ አይቼ አሁን መጨረሴ ነው ... ውጋንን ወወጋጋናት ... ደስ ብሎኛን ሁላቺሁንም እንኩዋን ደስ አላቺሁ ... ማንቼ አርሴ ላይ የሞራል ጥሰት ፈጽሞባት ዋንጫ ሊስም ቀናት ቀሩ ... እፎይይይ... ቴቬዝ ክፉ አይንካህ ... ቤርባቶቭም አሁን ቦታውን አግኝቶዋል ማራኪ ጨዋታ ምርጥ ፓሶቹን እየረካንባቸው ነው ... ሩኒ ዛሬም እንደ ሁሌው ኮስተር ያለ ጨዋታውን አሾፈን ... ሮናልዶ ... ንካውውውው ... አንተን አስመርሸው ሪቤሪን (ፌራሪቤሪ) ሰባትዋን ፈርጂ እንደሚያለብሱት አልጠራጠርም ... የአራቱ ጥምረት ደስ ሲል :: ባርሳን አያርገኝ ...
ሙቴክስ እና ሊሊዬ እናት ቤታቺሁ ውስጥ ስላየሁዋቺሁ ደስ ብሎኛል ... እናተም ስትጠፉ የዋርካ ስፖርት እልም ብሎ ነበር ... አሁን መጣ መጣ እያላቺሁ ሞቅ ሞቅ አርጉልን ... ሊሊዬ ጽሁፎቺሽን እየተጠባበቅሁ ነውና ለጠፍ ለጠፍ አርጊሊን ... ይመቻቺሁ ...
Man United Forever
ወሮበላው
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 841
Joined: Sun Oct 17, 2004 10:52 pm
Location: united states

PreviousNext

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest