ቫንፐርሲ ማን.ዩናይትድ ገባ (የማን.ዩናይትድ የ2012 ሲዝን)

ስፖርት - Sport related topics

Postby እኔውነኝኝ » Wed May 27, 2009 9:43 pm

ስመ ቡዙው የዚህ ቤት መስራች (ሙትቻ ወይም ሊሊ ሞገስ በሚለው ስምህ ገባ በል እና ) በ 4 ድል ዋዜማ የሚለውን ምን ብለኽ ትቀይረዋለኽ መሰለህ? ጨጓራችን እንደ ቴቬዝ አንገት ተኮሟትርዋል እና ተባበሩን ብለኽ:: :lol: :lol: ትእዛዝ ነው ይከበር:: ዲፕሎማት ጌታ ያው እንደፈረደበት ገብቶ ያጽናና:: እኔ ግን :lol: :lol:
እኔውነኝኝ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 623
Joined: Sat Jan 20, 2007 11:17 am

Postby ጌታ » Thu May 28, 2009 12:28 am

እኔውነኝኝ wrote: ዲፕሎማት ጌታ ያው እንደፈረደበት ገብቶ ያጽናና:: እኔ ግን :lol: :lol:


እኝኝ ስለሹመቱ አመሰግናለሁ:: ጠርጥር ነው 'ጌታ'ም እኮ ሙቴክስ የሊቨርፑልን ማልያ ለብሶ የሚጫወትበት ስሙ ሊሆን ይችላል :lol: :lol: :lol: :lol:

ወሮበላውን ይዘዝብህ
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby እኔውነኝኝ » Thu May 28, 2009 5:30 am

ምን ልል ነበር የገባሁት? :lol: :lol: :lol: ኤጭ የደስታ ስካር እኮ ቶሎ አይለቅም:: ጌታ:- ወሮበላን እማ ሪፈር ጻፍንለት እኮ:: :lol: :lol: ይልቅስ ማጻናናቱን አትርሳ:: የሱ ነገር የምር ያሳስበኛል:: ግድንግድ ጅል ስለሆነ በጫማው ማሰሪያ ወይም አንገቱ ላይ እናቱ ባንጠለጠሉለት የቡዳ መድሀኒት ክር ሲጥጥጥጥጥጥጥጥ እንዳይል ያስፈራል:: :lol: :lol:
እኔውነኝኝ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 623
Joined: Sat Jan 20, 2007 11:17 am

Postby ቃላት » Thu May 28, 2009 11:01 am

ለአምስት ዋንጫ የተገመተው ቡድናችን በ3 ዋንጫ መገደቡን የሚያመለክት ፊሽካ ትናንት ምሽት በ93ኛው ደቂቃ ላይ ዳኛው አብስረዋል:: እንደ ደጋፊነቴ በ3 ዋንጫ አልረካሁም:: ግን ትናንት 10 ደቂቃ በልጠን 83 ደቂቃ ተበልጠን የተሸነፍንብት ጨዋታ ስለሆነ ውጤቱን በጸጋ መቀበል ያስፈልጋል:: ለሚቀጥለው ሲዝን መበርታት ያስፈልጋል:: በተለይ በአውሮፓ መድረክ ያለንን ድል ማሳደግ ያስፈልገናል:: በፕሪሚየር ሊጉ እንክዋን ብዙ አጃቢውች እንጂ ተፎካካሪዎች እያጣን ነው:: ልክ እዚህ ቤት በዙ አጃቢዎች እንዳሉን ማለት ነው::

ግን በናታችሁ አንዳንድ ሰዎች ግን አያሳዘኗችሁም? ለጥላቻ የሚያወጡትን ኤነርጂ ምናለበት ለሌላ ነገር ቢያውሉት? እኔማ ድክም ነው የሚያደርጉኝ::

ይልቅ ሲዝኑን ሙሉ ሲያስደስቱን ለከረሙት ማንቼ ልጆቻችን ምስጋና ላቅርብ:: ብዙ ተደስተናል; እናመሰግናለን::
ቃላት
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 84
Joined: Sun Apr 23, 2006 1:46 pm

Postby ወሮበላው » Thu May 28, 2009 4:42 pm

እኔውነኝኝ wrote:ምን ልል ነበር የገባሁት? :lol: :lol: :lol: ኤጭ የደስታ ስካር እኮ ቶሎ አይለቅም:: ጌታ:- ወሮበላን እማ ሪፈር ጻፍንለት እኮ:: :lol: :lol: ይልቅስ ማጻናናቱን አትርሳ:: የሱ ነገር የምር ያሳስበኛል:: ግድንግድ ጅል ስለሆነ በጫማው ማሰሪያ ወይም አንገቱ ላይ እናቱ ባንጠለጠሉለት የቡዳ መድሀኒት ክር ሲጥጥጥጥጥጥጥጥ እንዳይል ያስፈራል:: :lol: :lol:


ማንጠግቦሽ ( ማንጤ ) ... ማንጥይዬ ... አንተን እማ እናትህ እንኩዋን የቡዳ መድሀኒት ልታስርልህ ብትቺል በቡዳ አስበልታ ብደፋህ ደስ ይላታል :: ሂድ ወዲያ ንፍጣም :: የገዛ ንፍጥህ እያዳለጠህ ምትወድቅ ጠብደል ጂል ... ለራስህ እዘን ::

ጌቾ አንተ የመቼ ዶክተር ነህ ወደ እኔ ሪፈር ምትጽፍለት :: ለማንኛውም እንኩዋን ደስ አለህ ... የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው በሚለው የጨዋታ ስልት አሸናፊ ነው ::
Man United Forever
ወሮበላው
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 841
Joined: Sun Oct 17, 2004 10:52 pm
Location: united states

Postby ወሮበላው » Thu May 28, 2009 4:53 pm

ቃላት wrote:ለአምስት ዋንጫ የተገመተው ቡድናችን በ3 ዋንጫ መገደቡን የሚያመለክት ፊሽካ ትናንት ምሽት በ93ኛው ደቂቃ ላይ ዳኛው አብስረዋል:: እንደ ደጋፊነቴ በ3 ዋንጫ አልረካሁም:: ግን ትናንት 10 ደቂቃ በልጠን 83 ደቂቃ ተበልጠን የተሸነፍንብት ጨዋታ ስለሆነ ውጤቱን በጸጋ መቀበል ያስፈልጋል:: ለሚቀጥለው ሲዝን መበርታት ያስፈልጋል:: በተለይ በአውሮፓ መድረክ ያለንን ድል ማሳደግ ያስፈልገናል:: በፕሪሚየር ሊጉ እንክዋን ብዙ አጃቢውች እንጂ ተፎካካሪዎች እያጣን ነው:: ልክ እዚህ ቤት በዙ አጃቢዎች እንዳሉን ማለት ነው::

ግን በናታችሁ አንዳንድ ሰዎች ግን አያሳዘኗችሁም? ለጥላቻ የሚያወጡትን ኤነርጂ ምናለበት ለሌላ ነገር ቢያውሉት? እኔማ ድክም ነው የሚያደርጉኝ::

ይልቅ ሲዝኑን ሙሉ ሲያስደስቱን ለከረሙት ማንቼ ልጆቻችን ምስጋና ላቅርብ:: ብዙ ተደስተናል; እናመሰግናለን::


ማንቺስተራዊው ቃላት ሰላም ሰላም ወንድሜ :: ሁሉንም በጭሩ ገልጽህዋል ... ማንቺተራዊያን በጠቅላላ ከነ ጌታ ፈርጉሰን ጭምር በበርሳ የዘንድሮ የአውሮፓ ፉትቦል አንበሳ ነት ተስማምተናል :: አንበሳው አንድ ብቻ አይደለም ለፍልሚያ ፊቱ የቆመው ቀያይ ሰራዊትም ሌላ አበሳ ነው ::
ከባርሳ ቀጥሎ ማንቼ ብዙዎቻቺን ምንስማማበት ነው ::
ፈርጉሰን ለሚቀጥለው ሲዝን የጡረታ መብታቸውን ብቻ ሳይሆን የአንበስነት ክብራቺንንም እንደሚያስመልሱ አልጠራጠርም ::
Man United Forever
ወሮበላው
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 841
Joined: Sun Oct 17, 2004 10:52 pm
Location: united states

Postby ሙትቻ » Fri Jun 12, 2009 1:38 am

ማን.ዩናይትድ ሮናልዶን በ80 ሚሊዮን ፓውንድ ለመሸጥ ተስማማ
'ሮናልዶ የልጅነት ህልሙን ሊያሳካ ነው' ሲል ነበር የዘገበው ኒውስ ኦውፍ ዘወርልድ ጋዜጣ:: ፖርቱጋላዊው የ24 አመት ወጣት ሮናልዶ ከእነ እናቱ በስፔን በተለይም በሪያል ማድሪድ መጫወትን እንደሚፈልግ በተደጋጋሚ ሲገልጽ የቆየ ሲሆን ማን.ዩናይትድ ለረዥም ጊዜ ሲቀርብለት የነበረውን የዝውውር ሂሳብ እምቢኝ ሲል ቆይቶ ዛሬ 80 ሚሊዮን ፓውንድ ከከፈላችሁኝ ውሰዱት ብሏል::
ማን.ዩናይትድ እና ሪያል ማድሪድ ባደረጉት ስምምነት መሰረት ማንቼ ሮናልዶን እንዲያግባባ ለማድሪድ ፈቃዱን ሰጥቷል:: ሁለቱም ክለቦች በግዢው ላይ በመስማማታቸው የሚጠበቀው የሮናልዶ ውሳኔ ይሆናል::
ለአለም ዋንጫ ማጣሪያ ለሀገሩ ፖርቱጋል ብሄራዊ ቡድን ሲጫወት ባለፈው ሳምንት ጉዳት የደረሰበት ሮናልዶ ከብሄራዊ ቡድኑ የተገለለ ሲሆን አሁን በሎሳንጀለስ ከተማ በመዝናናት ላይ ይገኛል::
ማን.ዩናይትድ ሮናልዶን ለመሸጥ ድንገት መወሰኑ ብዙሀኑን ያስደነገጠ ቢሆንም ለፈርጉሰን ቅርብ የሆኑ ምንጮች እንደሚሉት ፈርጊ ሮኒን በሚፈልገው የሴንትራል ቦታ ላይ ለማጫወትና ካርሎስ ቴቬዝን ለማቆየት ሮናልዶን ለመሸጥ ወስነዋል:: ሮናልዶ በተለይም ማን.ዩናይትድ ከማንቸስተር ሲቲ ጋር በተጫወተበት ወቅት ሲቀየር ያሳየው ተግባር እጅግ አሳፋሪ ነበር:: ብዙ ደጋፊዎችም አዝነውበት ነበር::
ሮናልዶ ባለፈው አፕሪል ወር ላይ በማን.ዩናይትድ መቆየትን እንደሚፈልግ የተናገረ ቢሆንም ከቀናት በኍላ ምናልባትም ከሰአታት በኍላ የልጁ ውሳኔ ከታወቀ ወደ ሪያል ማድሪድን አቅንቶ የአለማችን ውዱ ተጫዋች በመሆን ከጥቂት ቀናት በፊት ብራዚላዊው ካካ የወሰደውን
ሪከርድ ይቀበላል::
ሪያል ማድሪድ በዚህ የበጋ ወራት የዝውውር መስኮት ሪቤሪን ጭምር ማስፈረም ይፈልጋል::
ይህ በእንዲህ እንዳለ የቀድሞው የማን.ዩናይትድ አጥቂ ሩድ ቫንኒስተልሮይ በማድሪድ አንድም የተሳካ ሲዝኖች ሳያሳልፍ ዘንድሮ ቶተንሀምን በ1 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ሂሳብ እንደሚቀላቀል ተዘግቧል::
Image
ሙትቻ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2633
Joined: Fri Mar 31, 2006 7:38 am
Location: other

Postby ሙትቻ » Fri Jun 12, 2009 1:56 pm

Will United Miss Ronaldo?
"ማን.ዩናይትድ ብቻ ሳይሆን የፕሪምየር ሊግ ዳኞችም ይናፍቁታል" ነበር ያለው አንድ የአርሰናል ደጋፊ በሮናልዶ መልቀቅ ዙሪያ አስተያየቱን በሆነ ብሎግ ላይ አስተያየት ሲሰጥ:: እንደ ልጁ አባባል ሮናልዶ ችሎታውም አውቆ የሚወድቀውም ይናፈቃል; ዳኞችም አስር ጊዜ ፊሽካ እንዳይነፉ ሥራ ያቀልላቸዋል ሲል እንደ መቀለድ ብሏል:: በእርግጥ ማን.ዩናይትድ ሮናልዶን ክፉኛ አጥቶታል?
እርግጥ ነው ሮናልዶ ባለፉት 2 ሲዝኖች ወሳኝ ጎሎችን እየተነጫነጨም ቢሆን አግብቷል:: ግን ለማን.ዩናይትድ ታማኝነት እንደሌለው በተደጋጋሚ ታይቷል:: ከስፖርቲንግ ሊዝበን አንስተው ለእዚህ ያበቁትም ፈርጉሰን ናቸው:: ስለዚህ ሊያከብራቸው ይገባ ነበር:: ሆኖም በተደጋጋሚ በመልበሻ ክፍል ውስጥ እና በሜዳ ውስጥ የሚያሳያቸው "ከእኔ በላይ ሰው የለም" አይነት ባህሪይው የቡድኑን መንፈስ ሳይረብሸው በጥሩ ሰአት በጥሩ ዋጋ መሸጡ እኔን አስደስቶኛል::
በሮናልዶ ላይ ብቻ ተመስርቶ የተሰራው ቡድናችን አሁን ወደ ሁሉም ተጫዋቾች ሀላፊነቱ ይወርዳል ብዬ አስባለው:: ለቅጣት ምቶች ኦውን ሀርግሪቭስን እና አንደርሰንን ይበልጥ ማለማመድ ያስፈልጋል:: 'ናኒም እመኑኝ የሮሮናልዶን ቦታ ለመሸፈን ብቃቱ አለኝ; በሚቀጥለው ሲዝን ታዩኛላችሁ" እያለ ነው:: እንደ ናኒ አገላለጽ ሮናልዶ ለማን.ዩናይትድ ወሳኝ ተጫዋች የነበረ ቢሆንም አሁን የእርሱ መልቀቅ በብዙ ጨዋታዎች ላይ ለመስለፍ እድሉን እንደሚያስገኝለት ተስፋውን ጥሏል::
ፈርጉሰን ሮናልዶን በ80 ሚሊዮን ፓውንድ ከለቀቁት በኍላ የተለያዩ አስተያየቶች እየተደመጡ ነው:: ከነዚህ መካከል የሮናልዶ መልቀቅ ምንም ለውጥ አያመጣም ሲሉ ከዚህ በፊት በወሳኝ ሰአት ከማን.ዩናይትድ ተሸጠው የወጡ ተጫዋቾችን የሚጠቅሱ አሉ:: ለምሳሌም ፈርጉሰን ፖል ኢንስን; ያፕ ስታምን; ዴቪድ ቤካምን እና ሩድ ቫንኒስተልሮይን ሲሸጡ ማን.ዩናይትድ አበቃለት እየተባለ ነበር:: ሆኖም ግን ማን.ዩናይትድ እነዚህ ተጫዋቾች ከለቀቀ ወዲህ ይበልጥ ቅርጹን አስተካክሎ የተለያዩ ድሎችን ተጎናጽፏል::
የሮናልዶ መልቀቅ ለዋይኒ ሩኒም ጥቅም አለው እየተባለ ነው:: ዋይኒ ሩኒ በእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ውስጥ ፋብዮ ካፔሎ የሚገባውን ቦታ በመስጠታቸው እጅግ ውጤታማ ሆኗል:: በማን.ዩናይትድ ውስጥ ግን ፈርጉሰን ለሮናልዶ ቅድሚያውን መስጠታቸው ሩኒ ካለቦታው እንዲጫወት አድርገውት ልጁ ሊጠቅመን የሚችለውን ያህል ሳይጠቅመን ቀርቷል:: ሆኖም አሁን የሮናልዶ መልቀቅ ሩኒን ያጎላዋል እየተባለ ነው::
በነገራችን ላይ ካካ በሮናልዶ ዝውውር ዙሪያ ደስታውን ገልጿል:: ሆኖም አንዳንድ የስፖርት ተንታኞች "እንዴት ሮናልዶን እና ካካን በአንድ ቡድን ውስጥ ማጫወት ይቻላል?" በሚል ዙሪያ የተለያዩ መላምቶችን እያቀረቡ ይገኛል:: እኛ ምን አገባን በማድሪዶች ሥራ - በመጨረሻ ግን ባርሴሎናዎች በቪዲች ላይ የጣላችሁትን ጆፌ እዛው በሩቁ::
ማን.ዩናይትድ ሮናልዶን ለመተካትና በቀጣይ ሲዝን አዳዲስ ተጫዋቾችን ለማምጣት 100 ሚሊዮን ፓውንድ ለፈርጉሰን ተሰጥቷቸዋል:: ፈርጊ ሊያመጧቸው ካሰቧቸው ተጫዋቾች መካከል እንደ ጭምጭምታዎች ጥቆማ ሳሙኤል ኤቶ ይገኝበታል::
Image
ሙትቻ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2633
Joined: Fri Mar 31, 2006 7:38 am
Location: other

Postby ሙትቻ » Fri Jun 12, 2009 1:58 pm

ድጋሚ ፖስት ተደልዟል :wink:
Image
ሙትቻ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2633
Joined: Fri Mar 31, 2006 7:38 am
Location: other

Postby ሰያው » Fri Jun 12, 2009 11:19 pm

hi mutcha. i think if alex sell roni he has to by this 3 players to be top of english and maybe in europe.
1 FRAN RIBERY BAYERN
2 ANT.VALENCIA WIGAN
3 BENZEMA LYON
if you have any idea on this mate and the rest of you.
Q- what street did you grown up?
A- MERKATO
ሰያው
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 7
Joined: Thu May 21, 2009 2:27 am

Postby ሙትቻ » Sat Jun 13, 2009 12:23 am

ሰያው እንደምን አለህ? እንዳልከው ፈርጉሰን ሪቤሪን; ቫለንሺያን እና ቤንዜማን ለማምጣት እቅድ እንዳላቸው በተደጋጋሚ ተዘግቧል:: እኔ በሦስቱም ተጫዋቾች ደስተኛ ነኝ:: በተለይ ቫለንሺያ እና ሪቤሪ የሮናልዶን ቦታ ሊሸፍኑት ይችላሉ የሚል እምነት አለኝ:: በቤንዜማ ላይ ግን የሆነ አስተያየት አለኝ:: ፈርጉሰን ቴቬዝን በማን.ዩናይትድ የሚያቆዩት ከሆነ ቤንዜማ ቢቀርባቸው የሚሻል ይመስለኛል:: የእርሱ በውድ ዋጋ ተግዝቶ መምጣት አሁንም ቴቬዝ ላይ ጫናውን ከማሳደሩም በላይ በታዳጊዎቹ አጥቂዎቻችን ማኬዳ; ማኑቾና ዳኒ ዌልቤክ የመስለፍ እድላቸውን ያጠበዋል:: ቴቬዝ በትክክል የሚለቅ ከሆነና እንደተባለውም ወደ ሊቨርፑል የሚዘዋወር ከሆነ የቤንዜማ መምጣት አስፈላጊ ይሆናል::
አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ሮናልዶ ማን.ዩናይትድን ከለቀቀ ማንቼ በሚቀጥለው ሲዝን 3ኛ ሆኖ ነው የሚጨርሰው የሚል አስተያየታቸውን እየሰጡ ይገኛሉ:: ለእነዚህ አስተያየት ሰጪዎች "ጊዜ ሚዛን" የሚለውን የሐመልማል አባተ ዜማ ጋብዣለው::
በሌላ በኩል የአንቶን ቫለንሺያ ወደ ኦልትራፎርድ መምጣት 90 ከመቶ የሚሳካ ይመስላል:: የሪቤሪ ግን ትንሽ የሚያጠያይቅ ይመስላል:: ምክንያቱም ባየርት ሙኒክ ልጁን አልሸጥም ቢልም ሪያል ማድሪድ ራሱ ሪቤሪን የሚታፈስ ገንዘብ ይዞ ይጠብቀዋል::
Image
ሙትቻ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2633
Joined: Fri Mar 31, 2006 7:38 am
Location: other

Postby ሙትቻ » Sat Jun 13, 2009 12:26 am

ማይክል ኦውን ወደ አስቶንቪላ?
ሙሉ ስሙ ማይክል ጀምስ ኦውን ይባላል:: ዲሴምበር 14 1979 የተወለደው በአንድ ወቅት አለምን ሲያስደንቅ የነበረው ይኸው እንግሊዛዊ አጥቂ በሊቨርፑል ክለብ ውስጥ አድጎ ከ1996 አ.ም እስከ 2004 አም ተጫውቷል:: ማይክል ኦውን በሊቨርፑል በድንቅ ፐርፎርማንሱ የአውሮፓ ኮከብ ተጫዋች ተብሎ እስከመሸለም ቢደርስም በ2004 በሚያስገርም ውሳኔ ክለቡን ለቅቆ ሪያል ማድሪድ ገባ:: በማድሪድ 2 ሲዝን ብቻ የተጫወተው ኦውን የበርናቦውን የተጠባባቂ ወንበር እያሞቀ እየገባ በነዚህ ሲዝኖች ከክለቡ የወቅቱ ተመራጭ አጥቂ ብራዚላዊው ሮናልዶ የተሻለ ጎል ቢያገባም; የማድሪድን መቀመጫ ወንበር አላሞቅም በማለቱ በ2005 ለኒውካስትል ተሸጠ:: በኒውካስትል 4 አመታትን ያሳለፈው ኦውን ወደ ክለቡ ሲመጣ በክለቡ ደጋፊዎች ብዙ ተስፋ ቢጣልበትም; በጉዳት እንዲሁም በአስልጣኝና በታክቲክ ችግሮች ልጁ ብቃቱን ሳያሳይ ይባስ ብሎም ኒውካስትል ከፕሪምየር ሊጉ ሊወርድ ችሏል::
ለኒውካስትል ካደረጋቸው 71 ጨዋታዎች 26; ለማድሪድ ካደረጋቸው 35 ጨዋታዎች 13; ለሊቨርፑል ካደረጋቸው 216 ጨዋታዎች 118 ጎሎችን ማግባት የቻለው ኦውን ዘንድሮ ኒውካስትልን መልቀቅ እንደሚፈልግ አፍ አውጥቶ ተናግሯል:: የኦውን ቀጣይ ክለብም አስቶን ቪላ ይሆናል እየተባለ ሲሆን የሊቨርፑሉ አምበል ስቴቨን ዤራርድ ኦውን ወደ ቤቱ ሊቨርፑል ቢመለስ ያለውን ፍላጎት በግልጽ ተናግሯል:: እንደ ዤራርድ አባባል ኦውን ኳስ በጀመረበት አንፊልድ; የኳስ ሕይወቱም መጠናቀቅ አለበት::ž
Image
ሙትቻ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2633
Joined: Fri Mar 31, 2006 7:38 am
Location: other

Postby ሙትቻ » Sat Jun 13, 2009 12:29 am

ዋርካ አሁንስ አላበዛሽውም እንዴ? :evil: :evil:
Image
ሙትቻ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2633
Joined: Fri Mar 31, 2006 7:38 am
Location: other

Postby ቃላት » Sat Jun 13, 2009 1:25 pm

ጁን 11 ለኔም ሆነ ለብዙ የዩናይትድ ደጋፊዎች ትልቅ የሀዘን ቀን ነው:: ሮናልዶ ወደ ማድሪድ ለመሄድ የተወሰነበት ቀን ነው:: ላልፉት 6 ሲዝኖች ለማንቼ በሰራው ትልቅ ስራ የቡድኑ አይን የነበረው ሮናልዶ አሁን መልቀቁ በጣም አሳዛኝ ቢሆንም የልጁ ሙሉ ፍላጎት በመሆኑ ግን በጸጋ መቀበል ግድ ይላል:: ሮናልዶ ለቡድናችን 118 ጎሎችን ያስቆጠረ: 3 ጊዜ በተከታታይ የፕርሚየር ሊጉን ሀትትሪክ እንዲሰራ ያስቻለ: አንድ ጊዜ ኤፍ ኤ ካፕ አንድ ጊዜ ቻምፒየንስ ሊግ እንዲያገኝ ትልቅ አስተዋጾ ያበረከተ ነው::

ሮናልዶ ብዙ ጊዜ ያስጨፈረን ውድ ልጅ ስለሆነ በክብር ልንሰናበተው ይገባል:: ሮናልዶ እንደማንኛውም ሰው የራሱ የሆኑ ጉድለቶች ቢኖሩትም በችሎታው ግን ዘመን የማይሽረው ፉትቦለር መሆኑን ያስመሰከረ ነበር::

የሮናልዶን የመሄድ ጉዳይ ስሰማ የተሰማኝ ስሜት ልክ ካንቶና ጫማውን ሲሰቅል የተሰማኝን አይነት ባዶነት ነበር:: ያን ጊዜ ግን ምናልባት ልጂነትም ስለነበር ካሁን በሁአላ ማንቼ አለቀለት እኔም ቡድን አጣሁ ብዬ ነበር:: ግን ማንቼ ባንድ ሰው የቆመ ቡድን እንዳልሆነ ካንቶና ሮይ ኪን ቤካም እና ፋን ኒስተልሮይ ከለቀቁ በሁአላም እንደ ፈርጥ ያበራ ቡድን በመሆኑ አሁንም ምንም ስጋት የለም::

ሮናልዶ እናመሰግናለን:: በሄድክበት ሁሉ ይቅናህ: ከዚህ የበለጠ አብረቅርቅ: ደስተኛ ሁን:: ከማንቼ ጋር ከምታደርገው ጨዋታ በስተቀር ሁሌም ቢሆን የልብ ደጋፊህ ነኝ::
ቃላት
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 84
Joined: Sun Apr 23, 2006 1:46 pm

Postby ሙትቻ » Wed Jun 17, 2009 1:02 pm

ፕሪምየር ሊግ በ2009-10
ቃላት እንደምን አለህ? ምነው ጠፋ ጠፋ አበዛህሳ? እስኪ ብቅ ብለን ሰለማንቼ እንከስክስ:: ለማንኛውም ስላየሁህ ደስ ብሎኛል::
የ2009-10 የፕሪምየር ሊግ ሲዝን የጨዋታ መርሀ ግብር (fixtures) ተለቀቀ:: የአምናው ሲዝን ሻምፕዮን ማን.ዩናይትድ የመክፈቻውን ጨዋታ ከበርሚንግሀም ሲቲ ጋር በኦልትራፎርድ ሲያደርግ ከአርሰናል ጋርም በዚሁ ኦገስት ወር ላይ እንደሚገናኝ የወጣው ፕሮግራም ያሳያል:: ኦገስት 29 ከአርሰናል ጋር በኦልትራፎርድ የሚጫወተው ማን/ዩናይትድ ከሊቨርፑል ጋር ደግሞ ኦክቶቨር 24 በአንፊልድ ሮድ ይጫወታል::
የ2009-10 ሲዝን ከማን.ዩናይትድ ለሩኒ, ከቸልሲ ቴሪ, ከአርሰናል አርሻቪን, ከሊቨርፑል ቶሬስ ጥሩ ሲዝን ያሳልፋሉ ተብሎ ከወዲሁ ይገመታል:: የወጣው መርሀ ግብር ጨምሮም ኖቬምበር 7 ማን.ዩናይትድ ከቸልሲ በስታንፎርድ ብሪጅ ይጫወታሉ:: አርሰናል የሲዝኑን የመጀምሪያ ጨዋታ የሚያደርገው ከኤቨርተን ጋር በጉዲሰን ፓርክ ይሆናል:: ሊቨርፑልም የመጀምሪያውን ጨዋታውን ከሜዳው ውጭ በመሄድ ከቶተንሀም ሆትስፐር ጋር ያደርጋል:: ቶተንሀም ከሪያል ማድሪድ ሩበንንና ቫንኒስትልሮይን ለማምጣት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል:: ጣሊያናዊውን ካርሎ አንቸሎቲ አሰልጣኝ አድርጎ የሾመው ቸልሲ ከሁል ሲቲ ጋር ኦገስት 15 የመጀመሪያ ጨዋታውን ያደርጋል:: የቸልሲው ዲዲየር ድሮግባ ስለወደፊት ሁኔታዎች ከወዲሁ ከአሰልጣኙ ጋር መነጋገር እንደሚፈልግ ተገልጿል:: ከአርሰናል በኩል ኤቡዬ ክለቡን መልቀቅ እንደሚፈልግ ቢናገርም የቀኝ ክንፉ ሳኛ ወደሪያል ማድሪድ ሊሄድ ነው የሚባለውን ወሬ አስተባብሎ በኤመሬትስ ስታዲየም እንደሚቆይ ተናግሯል::
Image
ሙትቻ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2633
Joined: Fri Mar 31, 2006 7:38 am
Location: other

PreviousNext

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests