ቫንፐርሲ ማን.ዩናይትድ ገባ (የማን.ዩናይትድ የ2012 ሲዝን)

ስፖርት - Sport related topics

Postby ሙትቻ » Wed Jun 17, 2009 1:10 pm

ድጋሚ ፖስት :shock:
Image
ሙትቻ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2633
Joined: Fri Mar 31, 2006 7:38 am
Location: other

Postby ሙትቻ » Wed Jun 17, 2009 1:51 pm

የአዲሱን ሲዝን መርሀ ግብር ፕሪንት አውት አድርጋችሁ ማየት የምትፈልጉ ካላችሁ - የማን.ዩናይትድ ብቻ ይኸው
http://picsrv.manutd.com/?fif=/manu/img ... 2_2066.jpg
Image
ሙትቻ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2633
Joined: Fri Mar 31, 2006 7:38 am
Location: other

Postby ሰያው » Thu Jun 18, 2009 7:00 pm

thanks mutcha for your board. ግን የማንቹ ነገር በጣም የሚያሳስብ ነው: ሪበሪይ ሲል: ቪላ ሲል: ቢንዚማ ሲል: ቶሪስ ሲል: አንዴ ደግሞ ሲልቫ ሲል: ከጎን እነ ባርሳ እና ማድሪድ እየለቃቀሙ እየወሰዱአቸው ነው:: እና አሁን ማንን እንደሚገዛ እኔንጃ:: እና አረ አንድ በሉ
Q- what street did you grown up?
A- MERKATO
ሰያው
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 7
Joined: Thu May 21, 2009 2:27 am

Postby ወሮበላው » Fri Jun 19, 2009 8:36 am

ሙቴክስ እናመሰግናለን እደወትሮው ሁሉ ለተሙዋላ ኢንፎርሜሽንህ :: ማንቼ ከቸልሲ እና ከሊቨርፑል ጋር የመጀመሪያውን ዙር ከሜዳው ውጨ ስለሚያደርግ ከፕሮግራሙ ተጠቃሚ ነው ::
ማንቼ በዚህ የበጋ ወቅት ገንዘባቸውን ማፍሰስ ካለባቸው የ አውሮፓ ክለቦች መሀል የመጀመሪያው ይመስለኛል :: የዊጋኑ ኢኩዋዶሪያዊው ቫሌንሺያ በሚቀጥሉት ቀናቶች ውስጥ እንደሚፈርም እየተጠበቀ ሲሆን ሮናልዶ ከ አሜሪካው እረፍቱ ተመልሶ ከማንቺስተር ጋር ውሉን ቀዶ ሻንጣውን ጠቅልሎ እስኪወጣ ነው ሚጠበቀው :: ዊጋን በበኩሉ ብዙዎች እንደሚሉት የልጁን ስም ከተለያዩ ክለቦች ጋር በማያያዝ ማንቼን ደህና ገንዘብ ለመሞጭለፍ ፈልጎ የነበረ ቢሆንም ፈርጉሰን ባነውበት ተረጋግተዋል ::
እኔ በማንቼ ማልያ እንዳያቸው ምፈልጋቸው የቤንዛማ እና የሪቤሪ ነገር በዙም ተስፋ ሰጭ አልመሰለኝም :: ቤንዛማ ሰሞኑን ተወካዩ እንደተናገረው ልጁ ሊዮ ለመቆት እንደሚፈልግ እና ለአለም ዋንጫም ከክለቡ ጋር እንደሚዘጋጅ ተናግሮዋል:: ሪቤሪም ወደ እንግሊዝ ለመምጣት ብዙም ፍላጎት እንደሌለው ባለፈው ቴሌፉት ብሮግራም ላይ ሲናገር ሰምቼዋለው ;; ምናልባት የዚዳን ጫና እንዳለ ሆኖ ማድሪድ እና ማንቺስተር የሚያቀርቡት ገንዘብ ቁልፍ ነው ብዬ አስባለው :: ባየርንም ባቅሙ ይፍጨረጨራል :: ሮናልዶ መተካት ካለበት ሪቤርን የሚያህል ለምርጫ ተስማሚ የለም ::
ትላንት ቻሪና ውስጥ የማንቼው ሌጀንድ ቻርልተን የተናገሩት ነገር የመጨረሻ የመቺቶኛል "" ሮናልዶ ምርጡን ዘመኑን ኦልትራፎርድ ነው ያሳለፈው"" ነበረ ያሉት :: ይመቻቸው :: እንደሸንኮራ መጠን ... 93 ሚሊዮን ዩሮ ወደ ካዝና ማስገባት ይመቻል ::
Man United Forever
ወሮበላው
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 841
Joined: Sun Oct 17, 2004 10:52 pm
Location: united states

Postby ቃላት » Fri Jun 19, 2009 12:19 pm

ሙቴክስ የማንቼው እንደምን ሰነበትክ? እነ ምን እጠፋለሁ አንተ ነህ እንጂ:: እንዴ በዚህ ሲዝን እኮ በቃ አንተም ሊሊም እናትዬም ከፍተኛ የአቋም መዋዥቅ ነው ይሳያችሁት:: አሁን ብቅ ብቅ በማለትህ ደስ ብሎኛል::ወሮበላው ነው ዘንድሮ ቤታችንን ሲያደምቅ የከረመው:: ወሬክስ ዘንድሮ በኮከብ ደጋፊነት መርጨሀለሁ::

የሮናልዶ መሄድ አሳዛኝ ቢሆንም ግን መሆን ያለበት ነገር ነበር:: ስላደረገው ነገር በምስጋና ልንሸኘው ይገባል ባይ ነኝ:: ሪቤሪ በጣም ወሳኝ ልጅ ነው:: እሱን እንደምንም ፈለገው ቢያመጡት ጥሩ ነበር:: ፈረንሳዮች የፕርሚየርሊግ ፍትቦል ይመቻቸዋል:: ከነ ካንቶና እና ከነ ዴቪድ ጂኖላ ጀምሮ በፕሪሚየር ሊግ ያልተሳካለት ፈረንሳዊ አላየሁም::

እኔ የምለው ሰመሩ ግን ካሁኑ አልሰለቻችሁም:: ገና ሁለት ወር አካባቢ ያለ ማንቼ ንዴት እንደምዘልቀው እኔ እንጃ:: እስኪ አንድ አንድ ነገር እንደዚህ እየጻፋቺሁ ትንሽ እንፙፙቅ:: መልካም ዊኬንድ!
ቃላት
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 84
Joined: Sun Apr 23, 2006 1:46 pm

Postby ሙትቻ » Fri Jun 19, 2009 1:12 pm

ወሮበላው wrote: ትላንት ቻሪና ውስጥ የማንቼው ሌጀንድ ቻርልተን የተናገሩት ነገር የመጨረሻ የመቺቶኛል "" ሮናልዶ ምርጡን ዘመኑን ኦልትራፎርድ ነው ያሳለፈው"" ነበረ ያሉት :: ይመቻቸው :: እንደሸንኮራ መጠን ... 93 ሚሊዮን ዩሮ ወደ ካዝና ማስገባት ይመቻል ::

:lol: :lol: :lol: :lol: :lol: ወሮ አገላልጽህ እኮ ይደላኛል:: በሳቅ ነው የገደለኝ እንደ ሸንኮራ መጠን ያልካት :lol: :lol: ወሬክስ እና ቃሌክስ በአዲሱ ሲዝን ዋዜማ በመተያየታችን ደስ ብሎኛል:: አምና የወረደውን ፐርፎርማንሴን ለማስተካከልና ከወሬክስ; ሊሊሻ; ብናስተውል (ብኔክስ)ና እናቱ ጋር እንዲሁም ካንተና ከቻምፕዮን ጋርም ለመፎካከር ጥረቴ ነው::
ማን.ዩናይትድ በረኛ ያስፈልገዋል እንዴ?
ከሰሞኑ የሚወጡ የዝውውር ጉምጉምታዎች እንደሚጠቁሙት ማን.ዩናይትድ የበጋው ወራት የዝውውር መስኮት ከመዘጋቱ አስቀድሞ አንድ በረኛ ለማስፈረም ይፈልጋል:: በዚህ ሲዝን ኤድዊን ቫንደርሳርን ለአንድ አመት ያህል ኮንትራቱን ያራዘመው የትያትር ኦፍ ድሪምሱ ክለባችን ከባርሴሎናው በረኛ ቫልዴዝ ጋር ያደረገው የዝውውር ንግግር አልተሳካም ያሉት ዘገባዎች ከሪያል ማድሪዱ በረኛ ኤጋር ካሲያስ ጋርም ሌላ ድርድር እንደተጀመረ ተጠቁሟል::
ማን.ዩናይትድ የካርሊንግ ካፕ ሄሮው በረኛ ቤን ፎስተር; ኤድዊን ቫንደርሳር እና ቶማስ ኩዛክን በዋናው ቡድን ውስጥ 3 በረኛ አድርጎ የያዘ ሲሆን ዘንድሮ በረኛ ለመግዛት ገበያ መውጣቱ እኔን አስገርሞኛል:: በእናንተ እይታ ግን በዚህ ወቅት ማን.ዩናይትድ በረኛ የሚያስፈልገው ጊዜ ነው ወይ?
Image
ሙትቻ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2633
Joined: Fri Mar 31, 2006 7:38 am
Location: other

Postby ሙትቻ » Fri Jun 19, 2009 1:19 pm

Postby ሙትቻ » Fri Jun 19, 2009 1:33 pm

የዝውውር ተዋንያኖች

የ2009-10 ሲዝንን ለማደመቅ ወደ ኦልትራፎርድ ይመጣሉ ተብለው የሚነገርላቸው ተጫዋቾች ቁጥር እያደጉ ይገኛሉ:: በየቀኑ የምንሰማው ዜና አንዳንድ ጊዜ ውሸታም ሊያስብሉን ይችላሉ:: ስለዚህ እከሌ እዚህ ሊገባ ነው ከማለታችን በፊት ንግግር ላይ ናቸው; ድርድሩ ተጋምሷል እያልን ብናወራ መልካም ነው:: ዘንድሮ ወደ ኦልትራፎርድ ይመጣሉ ተብለው የሚናፈስላቸው ተጫዋቾች ዝርዝር የሚከተሉት ናቸው::
ካሪም ቤንዜማ አጥቂ
ፍራንክ ሪቤሪ (የመስመር ተጫዋች) 87 ሚሊዮን ፓውንድ
አሪያን ሮበን (የመስመር ተጫዋች)
አንቶንዮ ቫለንሺያ (የመስመር ተጫዋች)
ዴቪድ ሲልቫ (የመስመር ተጫዋች)
ሳሙኤል ኤቶ (አጥቂ)
ሰርጂዮ አጉዌሮ (አጥቂ)
ፈርንዳንዶ ቶሬስ (አጥቂ) 40 ሚሊዮን ፓውንድ
ዳግላስ ኮስታ (የመስመር ተጫዋች)
አሽሊ ያንግ (የመስመር ተጫዋች)
ኤጋር ካሲያስ (በረኛ)
እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት ተጫዋቾች ከማን.ዩናይትድ ዝውውር ጋር ስማቸው በሰፊው እየተነሳ ይገኛል:: እኔ በበኩሌ ማንም መጣ ማንም ቀረ የ2009-10 ሲዝን የማንቼ ቤስት XI የሚከተለው ቢሆን ውጤታማ ይሆናል የሚል እምነት አለኝ::

-----------------------------ቤን ፎስተር-------------------------------

ራፋኤል----------- ፈርዲናንድ-------------ቪዲች----------------ኤቭራ

ቫለንሺያ -----------ካሪክ--------------አንደርሰን----------------- ሪቤሪ

-----------------------------ሩኒ---------------በርባቶቭ---------------------

ቤንች:- ቫንደርሳር: ብራውን: ሀርግሪቭስ: ናኒ: ጊግስ: ኦሼ: ፍሌቸር: ቤንዜማ: ማኬዳ:
Image
ሙትቻ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2633
Joined: Fri Mar 31, 2006 7:38 am
Location: other

Postby ሙትቻ » Fri Jun 19, 2009 1:36 pm

Postby ሊሊ ሞገስ » Sat Jun 20, 2009 3:28 am

ሰላም ማንቼዎች የሲዝኑ እረፍት እንደራቀብን ይሰማኛል የቀረን ትንሽ ነውና እንታገስ:: ለዛሬው የአንገት ማስገቢያ ጀርመን ድምጽ ራዲዮ ስለሪያል ማድሪድ ቅጥ ያጣ የዝውውር ገንዘብ በሚል ያስደመጠውን ዘገባ እንካችሁ:-
ከአውሮፓ ታዋቂ የእግር ኳስ ክለቦች መካከል አንዱ ሪያል ማድሪድ፣ እጅግ ታዋቂ እግር ኳስ ተጫዋቾችን ለማሰባሰብ የሚያወጣው ቅጥ ያጣ፣ የገንዘብ መጠን የአውሮፓን ክለቦች፣ ከኤኮኖሚና ሞራል አንጻር በማነጋገር ላይ መሆኑ ተመለከተ። የአውሮፓ ክለቦች በዕዳ ተውጠው እያሉ፣ እጅግ ውድ ዋጋ እየከፈሉ ኮከብ ተጫዋቾችን መሻማታቸው፣ ፍትኀዊነት የሌለው አሠራር ነውና ፣ አውሮፓ አቀፍ ደንብ እንዲኖር የጀርመን የእግር ኳስ ፌደሬሽን እስከማሳሰብ ድርሷል። ሐያስያን እንደሚሉት፣ የጀርመን ክለቦች በአውሮፓው የክለቦች ሻምፒዮና ውድድር፣ ወደፊት ለመሳተፍ መብቃታቸው አጠራጣሪ ነው። በሌላ በኩል፣ የጀርመን የአግር ኳስ ፌደሬሽን የአስፖርት ሥራ አስኪያጅ ማትያስ ሳመር እንዳሉት ፣ እግር ኳስን ይበልጥ ለማስፋፋት ገንዘብ ሥራ ላይ ማዋል እስከሆነ ድረስ እስከዚህም ጉዳት የለውም ።

«አንድ ሰው፣ ብዙ ገንዘብ ካገኘ በኋላ፣ ስዕሎች ገዝቶ ግድግዳ ላይ በመሰቀል ቤቱን እንዳስጌጠ ቢሰማው ማለፊያ ነው። ገንዘቡን በእግር ኳስ ላይ ቢያውለውና በይበልጥ ሥራው እንዲስፋፋ ቢያደርግ እስከዚህ መጥፎ አይደለም»።

የሪያል ማድሪድ ፕሬዚዳንት ፍሎሬንቲኖ ፔሬስ፣ ፖርቱጋላዊውን ሮናልዶ በ 94 ሚልዮን ዩውሮ፣ ብራዚሊያዊውን ካካን በ 65 ሚልዮን ዩውሮ፣ ፈረንሳዊውን ሪቤሪን በ 84 ሚልዮን ዩውሮ፣ በብድር ለመግዛት ሳይወስኑ አልቀሩም። ፍሎሬንቲኖ ፣ የ FC Valencia ውን እወቅ የፊት አጥቂ David Villa ንም በውድ ዋጋ ለመግዛት ፍላጎት እንዳላቸው ተጠቅሷል። ይህ በአንዲህ እንዳለ ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ በመካሄድ ላይ ባለው የኮንፌደሬሽን የዋንጫ ውድድር፣ ትናንት ማታ ከምድብ ለ፣ ግብፅ ኢጣልያን 1-0 ስትረታ፣ ብራዚል ዩናይትድ ስቴታስን 3-0 አሸንፋለች። ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ፣ ኢጣልያ የፊታችን እሁድ ከብራዚል ጋር በምታደርገው ግጥሚያ፣ ማሸነፍ ይኖርባታል። ከቻለች!
ሊሊ ሞገስ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 574
Joined: Sun Jun 17, 2007 3:28 pm

Postby እናትዬ » Sun Jun 21, 2009 2:08 am

ሙትቻ wrote:-----------------------------ቤን ፎስተር-------------------------------

ራፋኤል----------- ፈርዲናንድ-------------ቪዲች----------------ኤቭራ

ቫለንሺያ -----------ካሪክ--------------አንደርሰን----------------- ሪቤሪ

-----------------------------ሩኒ---------------በርባቶቭ---------------------

ቤንች:- ቫንደርሳር: ብራውን: ሀርግሪቭስ: ናኒ: ጊግስ: ኦሼ: ፍሌቸር: ቤንዜማ: ማኬዳ:

አፍቃሪ ገንዘቦች ይሄዳሉ.... ማንቼ ግን ለዘል-አለሙ አለ...... ሮናልዶና ቴቬዝ እንኳን ክለባችንን በሰላም እና በጤና ለቀቁልን... በእርግጥ የቴቬዝ መልቀቅ እጅግ አስከፍቶኛል.. በሮናልዶ ልምጩ ላይ ግን ምንም ቅሬታ የለኝም... ጌታ ፈርጉሰን እንዳሉትም ሮናልዶ ሁሌ ሂያጅ ነው አሁንም መሄዱ አያስገርምም... እኔ 'ምለው ግን ደም እንደጠጣች ውሻ ሮናልዶን እንዲህ ያልከፈከፈው ምን እንደሆነ አልገባኝም... ፓሪስ ሂልተንን ለሁለት ምሽት ሲኮሞኩም አምሽቶ እሷን በሳመበት አፉ 3 ሴቶችን በአንድ ምሽት ሲያማግጥ ነበር.... ወይ ሮናልዶ እዩኝ እዩኝ ደብቁኝ እንደሚያመጣ ማን በነገራት.........
ዋናው ነገር ፈርጊ ቴቬዥን ማቆየት መቻል ነበረባቸው... እሱ ግን እንደተፈለገ ሲገባው... ደመወዜን ጣራ ካላስነካችሁ በማለቱ መሰናበቱ ግድ ነው.... በበኩሌ ፈርጊሻ በሚቀጥለው ሲዝን ማንንም ተጫዋች ባያስፈርሙ የተሻለ ነው.... ያሉት ተጫዋቾችን ከወጣቶቹ ጋር አጣምሮ ታሪክ መስራት ይቻላል.... ከምር ፈርጊ እነ "ኬፓሶን' ከሚሰበስቡ አርፈው የትም የማይከዱትን የኢንግላንድ እና የስኮትላንድ ተጫዋቾችን ቢሰበስቡ ይሻላቸዋል... ላቲኖች ልባቸው እንደቂጣቸው ሻካራ ነው....

ማን.ዩናይትድ ፍቅር ነው....... ሊቨርፑል :twisted: :twisted: ነው...
Image
እናትዬ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1286
Joined: Sat Jan 13, 2007 11:21 am
Location: ቀፊራ - ድሬደዋ

Postby ሙትቻ » Thu Jun 25, 2009 2:16 pm

ሊሊሻ እና እናቱ ናይስ ቱ ሲ ዩ አትጥፉ::
ማንቸስተር ሲቲ ስንት አጥቂ ነው የሚፈልገው?
በዘንድሮው የተጫዋች ዝውውር ገንዘብ በአካፋ እየዛቀ እየተሳተፈ ያለው ማንቸስተር ሲቲ አሁንም አጥቂዎችን ማደኑን ተያይዞታል:: ማን.ዩናይትድን የለቀቀው ካርሎስ ቴቬዝን ለመውሰድ ከጫፍ እንደደረሰ የሚነገርለት ማንቸስተር ሲቲ የባርሴሎናውን ሳሙኤል ኤቶንም እያነጋገረ ነው:: ማንቸስተር ሲቲ ከአንድ ሲዝን በፊት በፖርትስማውዝ እጅግ ተሳክቶለት የነበረውን ዙምባውቤያዊን ቤንጃኒ በዝውውር ወስዶ ችሎታውን እስኪጠፋበት ድረስ አስቀምጦታል:: በኪኤስኪ ሞስኮ ዝነኛነትን አትርፎ የነበረውን ብራዚላዊውን ጆም በከፍተኛ ገንዘብ አስመጥቶ እንዲሁ ወደ ኤቨርተን በውሰት እስከመስጠት ደርሷል:: ጆ በኤቨርተን የተሳካ ሊባል የሚችል ሲዝን በማሳለፉና የኤቨርተን ስዎችም ልጁን ለማስቀረት ሲቋምጡ ሲቲዎች እንደገና ልጁን ወደ ሲቲ ኦፍ ማንቸስተር ስታዲየም መልሰውታል::
ማንቸስተር ሲቲ እንደ ዴቪድ ቤላሚ, ሮቢንሆ, ሪኬ ሳንታክሩዝ, ዳሪየስ ቫስልን የመሳሰሉ አጥቂዎች እንዲሁም ሽዋይን ራይት ፊልፕስን, ስቴፈን አየርላንድን, ኢላኖን, ኢትሁንና ማርቲን ፔትሮቭን የመሳሰሉ አታኪንግ ሚድፊልደሮችን ይዞ እንደገና አጥቂ ሽመታ ውስጥ መገባቱ ስንት አጥቂ ነው የሚፈልገው የሚል ጥያቄ ያስነሳል:: በአሁኑ ወቅት ከአታኪንግ ሚድፊልደሮቹ ውጭ 10 አጥቂዎችን የያዘው ሲቲ ኤቶን እና ቴቬዥን የት ሊያረጋቸው ነው?
Image
ሙትቻ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2633
Joined: Fri Mar 31, 2006 7:38 am
Location: other

Postby ሙትቻ » Thu Jun 25, 2009 2:28 pm

:!: ድጋሚ ፖስት
Image
ሙትቻ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2633
Joined: Fri Mar 31, 2006 7:38 am
Location: other

Postby ሰያው » Thu Jun 25, 2009 3:01 pm

እኔማ የሚገርመኝ የዩናይትድ ነገር ነው::ማንን:ከየት እና መቼ እንደሚገዛ ሳይታወቅ ሁሉንም ሲመኝ በሌላ ክለቦች ተለቃቅመው እያለቁ ነው:: እኔማ ማንን አምጥቶ ሲዝኑን እንደሚጀምር ለማየት ነው የጠበኩት::እና በጣም አሳስቦኛል::
Q- what street did you grown up?
A- MERKATO
ሰያው
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 7
Joined: Thu May 21, 2009 2:27 am

Postby እናትዬ » Tue Jun 30, 2009 9:32 pm

ሰያው wrote:እኔማ የሚገርመኝ የዩናይትድ ነገር ነው::ማንን:ከየት እና መቼ እንደሚገዛ ሳይታወቅ ሁሉንም ሲመኝ በሌላ ክለቦች ተለቃቅመው እያለቁ ነው:: እኔማ ማንን አምጥቶ ሲዝኑን እንደሚጀምር ለማየት ነው የጠበኩት::እና በጣም አሳስቦኛል::ሰያው... ጌታ ፈርጉሰን ያንተን ጭንቀትና ስስት አይተው ፈጣኑን ቫለንሺያ አስፈረሙልህ.....
Image
እናትዬ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1286
Joined: Sat Jan 13, 2007 11:21 am
Location: ቀፊራ - ድሬደዋ

PreviousNext

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests