by ሙትቻ » Tue Oct 24, 2006 9:53 am
ሰላም የማንቼ ደጋፊ ወንድሞቼ እንደምን አላችሁ?
በቡድናችን ውጤት እርካታችንን እየተወጣን የ1998ቱን ድል እንድንናፍቅ አድርጎናል:: አሁንም ይህ ጊዜ እንዲደገም መልካም ምኞቴ ነው::
ማንቼ የባለፈው ሲዝን የካርሊንግ ካፕ አሽናፊ እንደነበር ይታወሳል:: ዘንድሮም ይህ ድል ወደ አኦልትራፎርድ መመለስ አለበት::
አሌክስ ፈርጉስን በነገው ምሽት (ረቡእ) ወደ ሲ ጂ ፎይ ስታዲየም ተጉዘው ክሪው አሌክሳንደሪያን ለካርሊንግ ካፕ 3ኛውን ዙር ለማለፍ ቀለል ያለ ግጥሚያ ይጠብቃቸዋል::
እንደተለመደው ካርሊንግ ካፕ ሶስትኛው ዙር በመሆኑ ፈርጊ አሰላለፋቸው የሚሆነው ሲኒየር ቲማችን አይደለም::
በዚህ ጨዋታ ይሰለፋሉ ብዬ የምገምታቸው ተጫዋቾች:-
በረኛ:- ቶማስ ኩዛክ
ተከላካዮች:- ብራውን, ሲልቨስተር, አዳም ኤከርስኪ, ሄንዜ
አማካዮች:- ሪቻርድሰን, ዴቪድ ጆንስ, ሪቼ ጆንስ, ፍሎርበርት,
አጥቂዎች:- ሶልሻየር, ስሚዝ
ተጠባባቂ በረኛ:- ቶም ሂተን
ተጠባባቂ ተከላካይ, ኤቭራ, ፈርዲናንድ
ተጠባባቂ አማካይ, ሮናልዶ, ካሪክ
ተጠባባቂ አጥቂ, ሰሀ
ይሆናል ብዬ እገምታለሁ:: ማንቼ ክሪው አሌክሳንደሪያን እንድሚያሽንፍ ሙሉ እምነት አለኝ::
በነገራችን ላይ የመልካም ልደት ምኞት አልኝ::
ባለፈው እሁድ ቪዲች 25ኛ አምቱን ሊቭርፑልን ስናሽንፍ አክብሮዋል:: ሪቻርድስን ደግሞ 22ኛ አመቱን አክብሮዋል::
ዛሬ ማክስኞ ደግሞ ዋይኒ ሮኒ 21ኛ አመት ልደቱን ያከብራል:: በዛሬው እለት ለሮኒ አሌክስ ፈርጉስን ያዘጋጁለት ስጦታ የ10 አመት የማን.ዩናይትድ ቆይታ ፊርማ እና ለዚህም ፊርማው 80 ሚሊዮን ፓውንድ ነው:; ሮኒ ለቀጣዮ 10 አመት ለማን.ዮናይትድ ለመጫወት የተስማማ ሲሆን ልደቱን ሲያከብር ፊርማውን ያኖራል::
ድል ለማንቼ!!