***አርሰናልን ያላችሁ እስኪ እንያችሁ***

ስፖርት - Sport related topics

Postby Monica**** » Mon Sep 07, 2009 8:34 pm

አንበርብርዬና ማዊት
የገነርስ ታማኝ አባሎች እንዴት ከረማችሁልኝ??
እንደው እስኪ ቤቱን ጎብኝት ላድርግ ብዬ ብቅ ስል የሁለታችሁንም ስም ሳይ ደስ አለኝ!! እስኪ አልፎ አልፎ እንዲህ ብቅ በሉና የገነርስን ትዝታዎች እንጨዋወት!!!

ገነርስ ፎርኤቨር!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
Yesterday is history, tomorrow is mystery, but today is a gift and that is why they call it the present!!!
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby እንደጉድ! » Tue Sep 08, 2009 1:41 am

ገነርስ ይውደሙ!

ከጓድ አሌክስ ፈርግሰን አመራር ጋር ወደፊት!! :arrow:
«አትናገር ብዬ ብነግረው፣ አትናገር ብሎ ነገረው።»
እንደጉድ!
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 380
Joined: Fri Sep 19, 2008 4:16 pm

Postby ወሮበላው » Tue Sep 08, 2009 7:49 am

እንደጉድ! wrote:ገነርስ ይውደሙ!

ከጓድ አሌክስ ፈርግሰን አመራር ጋር ወደፊት!! :arrow:

ወደ ፊትትትትትት ..... እናሸንፋለን !
Man United Forever
ወሮበላው
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 841
Joined: Sun Oct 17, 2004 10:52 pm
Location: united states

Postby ሰማዩ » Sun Sep 20, 2009 4:01 pm

እስክናሽንፍ ድረስ ፊሽካው አይነፋም: 6 ደቂቃ ለምን አያልፍም? ኢንግላንድ ትራፎር-ዲሽ ነው!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

ወሮበላው wrote:
እንደጉድ! wrote:ገነርስ ይውደሙ!

ከጓድ አሌክስ ፈርግሰን አመራር ጋር ወደፊት!! :arrow:

ወደ ፊትትትትትት ..... እናሸንፋለን !
ሰማዩ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 4
Joined: Sat Jan 19, 2008 10:16 am

Postby አክየ » Sun Sep 20, 2009 9:43 pm

መጀመሪያ የተቃጠለ ሰአት የተጨመረው 4 ደቂቃ ነበር ግን ሁለቱም ቡድኖች ባለቀ ሰአት ጎል አግብተው ሲጨፍሩ 3 ደቂቃ አቃጥለዋል .. ዳኛው ያንን የተቃጠለውን ሰአት ነው ያጫወተው .. ቆዳው .. አንተ ደግሞ አዲሱ የ አርሰናል ደጋፊ መሆንህ ነው ወይስ ትናንት ኳስ ማየት የጀመርክ ዱባይ የምትኖር ከድር ነህ ..??

ድል ለማንቼ ...........
"Say what you have to say in the fewest possible words"
አክየ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2615
Joined: Thu Jul 28, 2005 7:43 am

Postby ወሮበላው » Mon Sep 21, 2009 12:01 am

በለው በለው በለው ... እንዲህ ነው ማንቼ ... ማንቺስተር የማሸነፍ መንፈስ ያለው ምርጥ ቡድን :: እንቢ ለ ሽንፈት ... በእግሩ ብቻ ሳይሆን በልቡ የሚጫወት አንድና ብቸኛ ቡድን ::
ለመላው ማንቺስተራዊያን ቀያይ ሰይጣኖች እንኩዋን ደስ አላቺሁ ... ኦውንን ሳመሰግነው ... ፍሌቸርን ግን አደነቀዋለው .. አንበሳ ::
ታላቁ የማንቺስተር ጦርነት በ ዩናይትድ አሸናፊነት ተጠናቆዋል .. ሲቲ እድል ብቻ ሳይሆን ብቃትም እንደሚያስፈልገው የተረዳበት ምርጥ ጨዋታ ... አሳይተን ነሳናቸው ... ማንቼ አርሰናል አይደለም ... ማንቼ እንደ አደባዮር ቴቬዝ አይጨፍርበትም ... ዝምምም ነው :: የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው ብላቺሁ ያጨበጨባቺሁ .. ዝዝዝዝምምምም ::


ከ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ቆራጥ አመራር ጋር ወደ ፊት ::
Man United Forever
ወሮበላው
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 841
Joined: Sun Oct 17, 2004 10:52 pm
Location: united states

Postby ሰማዩ » Wed Sep 23, 2009 8:11 pm

ማነህ የሆንክ ከንቱ ነገር

9 ጎል ስለገባ 9 ደቂቃ ወይም 2 ጎል ስለገባ 2 ደቂቃ: ወይም በገባ ጎል ቁጥር በሚደረግ ሴሌብሬሽን እየታሰበ ሽርፍራፊ ጊዜ አይቸመርም:: የእግር ኳስ መሀይም ካልሆንክ ይገባሀል::

ሌላው አረብ ምናምን ላልከው : አረብ አገር መሆን ትንሽ ወይም ትልቅ ሰው አያረግህም::

ግን ለአንድ አናሳ ፍጡር .. ምላሽ መስጠቴም አናሳነቱን በመርሳት እንዲደሰት ያህል ነው:

እደግ- አበቃሁ
ሰማዩ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 4
Joined: Sat Jan 19, 2008 10:16 am

Postby አክየ » Thu Sep 24, 2009 1:43 am

ሰማዩ wrote:ማነህ የሆንክ ከንቱ ነገር

9 ጎል ስለገባ 9 ደቂቃ ወይም 2 ጎል ስለገባ 2 ደቂቃ: ወይም በገባ ጎል ቁጥር በሚደረግ ሴሌብሬሽን እየታሰበ ሽርፍራፊ ጊዜ አይቸመርም:: የእግር ኳስ መሀይም ካልሆንክ ይገባሀል::

ሌላው አረብ ምናምን ላልከው : አረብ አገር መሆን ትንሽ ወይም ትልቅ ሰው አያረግህም::

ግን ለአንድ አናሳ ፍጡር .. ምላሽ መስጠቴም አናሳነቱን በመርሳት እንዲደሰት ያህል ነው:

እደግ- አበቃሁ


ጭባ አንተም ኳስ አውቃለሁ ብለህ እኔን የኳስ መሀይም ካልሆንክ አልከኝ .. እንከፍ ...... ደግሞ አንተም ሰው ሁነህ ትንሽ ሰው ብለህ ስትሳደብ ... ምን አይነቱ ዶማ ነው በናታችሁ

ሂድ ውጣ ከዚህ .. ቡችላ
"Say what you have to say in the fewest possible words"
አክየ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2615
Joined: Thu Jul 28, 2005 7:43 am

Postby Monica**** » Fri Oct 02, 2009 12:17 pm

እንዴ ይሄ ቤት ተሳስቼ ነው ወይስ የማንቼ ደጋፊዎች ቤት ነው???? :P :P
አክዬና ወሮበላው እንዴዴዴዴዴ????? በቃ እናንተ ማንቼን ያልደገፈ ስው ማናደድ ፕሮፌሽናችሁ ልታደርጉት ነው እንዴ? :lol: :lol: አበዛችሁት አንበርብር ቤት ገብታችሁማ ስማዩን አትስድቡም!!! ወሮበላውና አክየ እግዚአብሄርን ኖርዝ ለንደን ብቅ ካላችሁ ድብድብ ነው የማደርጋችሁ በአርሴናል ዱላ!!! :lol: :lol:
ስማዩ አይዞን እሽ ገነርስ ፎርኤቨር!!!!!!!!!!!!!!!
Yesterday is history, tomorrow is mystery, but today is a gift and that is why they call it the present!!!
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby አንበርብር » Sun Oct 04, 2009 7:58 am

Monica**** wrote:እንዴ ይሄ ቤት ተሳስቼ ነው ወይስ የማንቼ ደጋፊዎች ቤት ነው???? :P :P
አክዬና ወሮበላው እንዴዴዴዴዴ????? በቃ እናንተ ማንቼን ያልደገፈ ስው ማናደድ ፕሮፌሽናችሁ ልታደርጉት ነው እንዴ? :lol: :lol: አበዛችሁት አንበርብር ቤት ገብታችሁማ ስማዩን አትስድቡም!!! ወሮበላውና አክየ እግዚአብሄርን ኖርዝ ለንደን ብቅ ካላችሁ ድብድብ ነው የማደርጋችሁ በአርሴናል ዱላ!!! :lol: :lol:
ስማዩ አይዞን እሽ ገነርስ ፎርኤቨር!!!!!!!!!!!!!!!


ሞኒካ :lol: :lol: :lol: አትፍረጅባቸው ሁለተኛ ፔጅ ላይ ሂደን ከምንፈልግ ብለው ነው ከዚህ የተጠጉት........ ሙትቻ እንኳ እንዲህ ሲጠፋ!!!! አሁን ማንቹዎችን 90+ ብየ ጠርቻቸዋለሁ..... የሆኑ አዚማም ነገር ናቸው...... :lol: :lol: :lol:
Image
አንበርብር
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1278
Joined: Sat Apr 09, 2005 12:01 am
Location: everywhere

Postby Monica**** » Sun Oct 04, 2009 8:01 pm

አንበብርዬ
እንዲህ ብቅ ስትል ደስ ይላል!!!
የዛሬውን ጨዋታ አየህልኝ????? ስድስት ጎል ብላክበርኖች ላይ!!! አቤት ደስ ሲል....ሁኔታውን ሞር ሲያሳምረው ትዬሪ ሄንሪ( ኦንሬ) ስቴዲየሙ ውስጥ ገብቶ ለአርሴናል ድጋፉን ሲገልጽ ደስታውን አልቻልኩትም.....እንደመቀየም ብዬው ነበር እኛን ጥሎ ሲሄድ!!! ቪየራም ትራንስፖርቴሽን ዲሌይድ ሆኖበት ነው እንጂ ሲጠበቅ ነበር!!! ግን ግን ተመልሶ የሚመጣ አይመስልህም? ( ቬንገር ዲናይድ ቢያደርግም)!!!
አንበርብርዬ መልካም እሁድ ምሽት ይሁንልህ!!!
Yesterday is history, tomorrow is mystery, but today is a gift and that is why they call it the present!!!
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby አንበርብር » Mon Oct 05, 2009 2:15 am

Monica**** wrote:አንበብርዬ
እንዲህ ብቅ ስትል ደስ ይላል!!!
የዛሬውን ጨዋታ አየህልኝ????? ስድስት ጎል ብላክበርኖች ላይ!!! አቤት ደስ ሲል....ሁኔታውን ሞር ሲያሳምረው ትዬሪ ሄንሪ( ኦንሬ) ስቴዲየሙ ውስጥ ገብቶ ለአርሴናል ድጋፉን ሲገልጽ ደስታውን አልቻልኩትም.....እንደመቀየም ብዬው ነበር እኛን ጥሎ ሲሄድ!!! ቪየራም ትራንስፖርቴሽን ዲሌይድ ሆኖበት ነው እንጂ ሲጠበቅ ነበር!!! ግን ግን ተመልሶ የሚመጣ አይመስልህም? ( ቬንገር ዲናይድ ቢያደርግም)!!!
አንበርብርዬ መልካም እሁድ ምሽት ይሁንልህ!!!


ሞኒካየ አዎ 6 ጎል ደስ ይላል ከብዛታቸው ደግሞ ጥራታቸው የበለጠ ያረካሉ...... ፋቤ....ፋቤ.....ፋቤ ተቆጣጠረው ነው የሚባለው..... 4 አሲስት አንድ ጎል ተቀይሮ ባይወጣ ሌላም ሊጨምር ይችል ነበር..... የባልክበርኑ በር ጠባቂ ሮበርሰን አወጣቸው እንጅ ታሪኩ ሌላ ነበር የሚሆነው..... ጋነር ያደረጋቸው ጨዋታዎች 7 ሲሆኑ 3ቱ ኢምሬትስ ላይ ነበሩ.... በእነዚህ 3 ጨዋታዎች አርሰናል 14 ጎል ማስቆጠር ችለዋል...... ዋው ነው የሚባለው:: በነገራችን ላይ ቨርማለን አዲሱ ልጃችን ቀላል ተመቸኝ እንዴ...... የቆመው ሊከላከል ነበር... ልጁ ግን ጎል ማምረቱን ቀጥሎበታል..... ከአይን ያውጣው ብለናል::

አዎ ኦንሪን አየሁት :lol: :lol: ደስ ሲል.. ተመልካቹም መልካም አቀባብል አድርገውለታል..... አርሰናል አሁንም ልቤ ውስጥ ነው ይለናል.... እርሱም ልባችን ውስጥ ነው..... ስለ ፓትሪክ ቬራ ደግሞ ቬራ ወደ አርሰናል ሊመልሰን ነው ነው ከተባለ ቆይቷል..... ጃንዋሪ ላይ ለአፍሪካ ዋንጫ አሌክስ ሶንግንና ኢቦየን ስለምናጣ ቬራ መጥቶ የሶንግን ቦታ ሊሸፍን ይችላል የሚል ወሬም አለ..... እኔ ግን ቬራን በተጨዋችነት ሳይሆን በሌላ የስራ መስክ መምጣቱን እመርጣለሁ.... ፓትሪክ ቬራም እንደ ኦንሪ ለንደን ውስጥ ነበር.... የቸልሲንና የሊቨርፑልን ጨዋታ ሲከታተል አየሁት... ምናልባት ከአርሰናል ጋር የተገናኘውን የአሉባልታ ወሬዎችን ለማርገብ ይሆናል ኢምሬትስ ላይ ያልተገኘው..... ከኦንሪ ጋር ቢታይ ኑሮ ቬራ ለአርሰናል ለመፈረም ተስማማ ተብሎ በወሬ አቀጣጣይ ጋዜጠኞች ይነገረን ነበር... የውልኮት መመለስ በጣም ደስ ብሎኛል... ናስሪም በቅርቡ ይመለሳል ተብለናል.... ሁሉም ተጨዋቾች ከጉዳት ነፃ ከሆኑ አርሰናል ለዋንጫ የማይታጭበት ምንም አይነት ነገር አይታየኝም...... ጋነር ፎር ኤቨር....

ሞኒየ..... ቤትሽ መጥቸ ነበር መልዕክት ትቸልሻለሁ....
Image
አንበርብር
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1278
Joined: Sat Apr 09, 2005 12:01 am
Location: everywhere

Postby እናትዬ » Mon Oct 05, 2009 3:01 am

ታርሰናሎች በሳቅቅቅቅቅ... ምናለበት ስትሸነፉም ብትመጡ? አሁን ዘንድሮ ድክምክም ያለችው ብላክበርን ላይ 6 አገባን ብላችሁ ጮቤ ረገጣችሁ.... ከሳምንት በሗላ ስትንሸነፉ ደግሞ ሲዝኑን ሙሉ ትጠፋላችሁ :lol: :lol:
Image
እናትዬ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1286
Joined: Sat Jan 13, 2007 11:21 am
Location: ቀፊራ - ድሬደዋ

Postby አንበርብር » Mon Oct 05, 2009 5:37 am

እናትዬ wrote:ታርሰናሎች በሳቅቅቅቅቅ... ምናለበት ስትሸነፉም ብትመጡ? አሁን ዘንድሮ ድክምክም ያለችው ብላክበርን ላይ 6 አገባን ብላችሁ ጮቤ ረገጣችሁ.... ከሳምንት በሗላ ስትንሸነፉ ደግሞ ሲዝኑን ሙሉ ትጠፋላችሁ :lol: :lol:


እናቱ መጣሽልን..... የውሀ ሽታ ሆንሽብን እንኮ.... እረ እኛ አንጠፋም.... የሽንፈት በሽታ ጥፍት ይበልና... ጋነርንማ በጎል በኩል አታሚውም..... እንዴ ተይ እንጅ.... ኤቨርተንና ብላክበርን ላይ 6, 6 ፓርትስማውዝና ዊጋን ላይ 4,4 እነዚህ ቡድኖች እንኮ ቀላል የሚባሉ አይደሉም.... ያንችውም 90+ እንኮ በፈርጊ አባት ምርቃት ተይዞ እንጅ በሰንደርላንድ ተገልቦልሽ ነበር...... የፈርጊን ምላስ የፈሩ ዳኞች ደግሞ ከአርሰናልና ከሲቲ ታደጉልሽ.... ያ ተለምዶ ትናንትም ፈርጊ ዳኛ ላይ አካኪ ዘራፍ ብለው.... ፍርድን እየጠበቁ ነው.... እና እባክሽ ስትሸነፉ እየጠፋችሁ እያልሽ አትሚን... ስንሸነፍም ጎራ እንላለን.... ስናሸንፍ ደግሞ ጥፍትም እንላለን... ፍርድ አታጓድይ... ይልቅ ሚኒካን ሞኒየ ብየ ስላቆላመጥኳት ክፍት ያልሽ ትመስያለሽ ከአይኖችሽ ቅላት መገመት ይቻላል :lol: :lol: :lol: ቆይ ውሮየን ልንገረውና አንድ የቁልምጫ ስም ይዞልሽ ይምጣ..... እኔ ማግኘት አልቻልኩም..... :roll: :roll: እምምምም አሁንም ለማግኘት ተቸገርኩ ይቅርታ.. :wink: :wink:
Image
አንበርብር
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1278
Joined: Sat Apr 09, 2005 12:01 am
Location: everywhere

Postby እናትዬ » Mon Oct 05, 2009 12:21 pm

አንበርብር wrote:[ይልቅ ሚኒካን ሞኒየ ብየ ስላቆላመጥኳት ክፍት ያልሽ ትመስያለሽ ከአይኖችሽ ቅላት መገመት ይቻላል :lol: :lol: :lol: :lol:


ድንቄም ወርቄም አዲሱም ሹምዬም ተስብስበው መጡ አሉ :lol: :lol:

ቆይ ውሮየን ልንገረውና አንድ የቁልምጫ ስም ይዞልሽ ይምጣ..... እኔ ማግኘት አልቻልኩም..... :roll: :roll: እምምምም አሁንም ለማግኘት ተቸገርኩ ይቅርታ.. :wink: :wink:


አምቤው በሳቅቅቅቅቅቅቅ ገደልከኝ.... :lol:
Image
እናትዬ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1286
Joined: Sat Jan 13, 2007 11:21 am
Location: ቀፊራ - ድሬደዋ

PreviousNext

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests