***አርሰናልን ያላችሁ እስኪ እንያችሁ***

ስፖርት - Sport related topics

Postby ሀሪከን2 » Tue Oct 06, 2009 1:08 am

አንቺ ላባ ቀረሽ በደህና ነው የጠፋሽው
each mind is a different world
ሀሪከን2
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1039
Joined: Fri Oct 31, 2008 3:59 am

Postby አንበርብር » Sat Oct 17, 2009 10:26 am

ቀኑ ይለፍ እንጅ ዛሬም ከመተከዝ ወደ ኌላ አላልኩም... አሳዛኝና አስደንጋጭ ክስተትን በአይኔ ከእግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ያየሁበት ስለነበረ:: ቀኑን ባልሳሳት የካቲት 23 2008....... ቦታው ሴንት አንድሪው ስታዲየም ነበር:: አርሰናል በበርሚንግሀም ለፕሪምየር ሊጉ ጨዋታ የተጋበዘበት:: ሁሉም የእግር ኳስ አፍቃሪ ከታሪኩ ተቋዳሽ ስለነበረ ታሪኩን አሁን መድገሙ አሰለች ስለሆነ ሙሉ ታሪኩን ትተን ዋና ዋናዎችን እንዳስስ:: አርሰናል በርሚንግሀምን ከማግኘቱ በፊት ሊጉን በመምራት የነበረ ከመሆኑም በላይ ለዋንጫ ከታጩት ክለቦችም ውስጥ አንዱ ነበር:: ሆኖም ግን በዚያች ምፅዐት ቀን ሁሉም ነገር ተበለሻሸ:: አርሰናል ወደ ኌላ አፈገፈገ:: ወደ ሰባት የሚሆኑ ቀጣዩን ጨዋታዎች ማሸነፍ ተሳነው:: ችግሩ የት ላይ ተነሳ? ከዚሁ ሴንት አንድሪው ሜዳ የኢድዋርዶ ሲሊቫ እግር በማርቲን ቴለር ከተቀነጠሰ በኌላ:: ኢድዋርዶ ያ አሰቃቂ አደጋ ሲደርስበት በአይኔ በብረቱ የተመለከትኩ ቢሆንም ጉዳቱ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ግን ማየት አልቻልኩም ነበር:: ጨዋታውን በቀጥታ የሚያስተላልፈው የስካይ ስፓርት ጋዜጠኞች የኢድዋርዶ ጉዳት አሰቃቂ ስለሆነ እንዳናስተላልፈው ተከልክለናል ያሉትን መልዕክት አረሳሁም:: እናም በዚያች ቀን ያጣነው ኢድዋርዶን ብቻ ሳይሆን ወርቃማ 2 ነጥብ: የጋላስን ትዕግስት እንዲሁም በተጨዋቾች መካከል የነበረውን ፍቅር ጭምር ነበር:: እናም ቀኗ የአርሰናል ደንቀራ ቀን ሆነችና ጋነር ኢድዋርዶንና መሪነቱን አጥቶ ሊጉን በሶስተኛነት ለመጨረስ ተገደደ:: ዛሬ አርሰናል ይህንን ሸካራ ታሪክ ያፃፈውን በርሚንግሀምን ኢምሬትስ ሜዳ ላይ ጋብዞታል:: እንደ አጋጣሚ ሁኖ በዛሬው ጨዋታ ላይ ኢድዋርዶና ቴለር አይኖሩም...... ቢኖሩ ኑሮ የጨዋታው ይዘት ይቀየር እንደነበር ግን ለመገመት ይቻላል:: ክስተቱ ታሪክ ሁኖ አለፈና ዛሬ አርሰናልና በርሚንግሀም የተለመደውን የ 90 ደቂቃ ጨዋታ ያደርጋሉ:: በርሚንግሀም ከአርሰናል ደጋፊዎች መራራ አቀባበል እንደሚገጥማቸው ብገምትም ጨዋታውም ብቀላ እንደሚቀላቀልበት ግምቴ ነው:: መልካም እድል ለአርሰናል...........
Image
አንበርብር
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1278
Joined: Sat Apr 09, 2005 12:01 am
Location: everywhere

Postby ፓራጎን33 » Sat Oct 17, 2009 5:00 pm

አንበርብር ልክ ነህ:: ያችን ቀን ማን ይረሳታል ብለህ ነው? አሁንም ጨዋታውን እያየሁት ነው:: አርሰናል 3:1 እየመራ ነው:: የዘንድሮ አያያዙ ጥሩ ይመስላል:: ዋንጫ ያገኝ ይሆን? ሁሉንም ጊዜ ያሳየናል::

ድል ለአርሰናል!
Never follow the path may lead, go instead where there is no path and leave the trail!
ፓራጎን33
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 29
Joined: Wed May 20, 2009 10:03 pm

Postby አንበርብር » Fri Oct 30, 2009 4:33 am

ፓራጎን33 wrote:አንበርብር ልክ ነህ:: ያችን ቀን ማን ይረሳታል ብለህ ነው? አሁንም ጨዋታውን እያየሁት ነው:: አርሰናል 3:1 እየመራ ነው:: የዘንድሮ አያያዙ ጥሩ ይመስላል:: ዋንጫ ያገኝ ይሆን? ሁሉንም ጊዜ ያሳየናል::

ድል ለአርሰናል!


ሰላም ፓራጎን... አርሰናል በማጥቃቱ በኩል ዘንድሮ ጥሩ ይመስላል:: ጎል የማስቆጠር ችግር ብዙም ያለበት አይመስልም:: ከተከላካዮች ጀምረው እስከ መሀል ተጨዋቾች እንዲሁም አጥቂዎች ድረስ ጎል የማስቆጠር ብቃት አላቸው:: አሁንም አልፈታ ያለ ችግር ግን መዘናጋት የሚባለው ነው:: ውጤትን እስከ መጨረሻው ሰሀት አስጠብቆ የመውጣቱ ጉዳይ ደካማ ጎን ተብሎ ሊጠቀስ የሚችል ነገር ነው:: ይህ ድክመት ባለፈው በቻምፒወን ሊጉና ከዌስትሀም ጋር ባደረግነው ጨዋታ ተከስቷል:: በተለይ የዌስትሀሙ ጨዋታ አናዳጅና አሳባጅ ነበር:: በሁለት ጎል ልዩነት እስከ 70ኛው ደቂቃ ድረስ ሲመሩ ቆይተው እንዴት 3 ነጥብ ይዘው መመለስ ይቸግራቸዋል? ከስተታቸው መታረም ካልቻሉ አሁን ባሉበት ቦታ መቆየት አይችሉም:: አንተስ ምን ይመስልሀል? እስካሁን ባደረጉት እንቅስቃሴ ምን አስተያየት አለህ?
Image
አንበርብር
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1278
Joined: Sat Apr 09, 2005 12:01 am
Location: everywhere

Postby አንበርብር » Fri Oct 30, 2009 5:12 am

አርሰናል ከ ቶትንሀም.... ይህንን ጨዋታ ታሪክ እያጣቀሰ ከቀልድ ጋር የሚያቀርብልን የድሮው መሬው ነበር:: ሳይታሰብ የውሀ ሽታ ሁኖ ቀረ እንጅ? Vann መሬው ነው እያሉ ምልክትን የሰጡኝ ነበሩ... ማረጋገጥ ግን አልቻልኩም:: መሬው ምናልባት ይህችንን የምታነብ ከሆነ ከጀርባ ነካ አድርገኝና መኖርህን አረጋግጥልኝ::

ለሁሉም ነገ ብዙዎች የለንደን ኗሪዎች ሙትቻንና ሞኒካን ጨምሮ ምሳቸውን የማይበሉበት ቀን ነው:: መብላት ካማራቸው ከ12:45 pm ቀደም ብለው ካልቻሉ ግን መክሰስ ያደርጉታል:: በሁለቶች ክለብ መካከል በሊጉ ታሪክ የሰፋ ልዩነት ቢኖርም እስካሁን ድረስ ግን አርሰናል ከ ቶትንሀም የሚያደርገው የዳርቢ ጨዋታ የሁሉንም ትኩረት ከመሳብ ወደ ኌላ አላለም:: የአርሰናል ደጋፊ ጋነር ዩናይትድን ወይም ቸልሲን ከሚያሸንፍ ይልቅ ቶትንሀምን ቢያሸነፍ ደስታን ይሰጠዋል ( እኔን ሳይጨምር):: የቶትንሀም ደጋፊም ስሜት ተመሳሳይ ነው:: ይህ ስሜት የሁለቱንም ክለቦች ተጨዋቾች ያካትታል:: ምን ተጨዋቾችን ብቻ.... ከተጨዋች ደላላዎች እስከ ውሀ አቀባይ ህፃናቶች ድረስ የአርሰናልና የቶትንሀም ጨዋታ ከፍተኛ ቦታ ይሰጡታል:: አርሻቪን ምን እንዳለ አንብቡትማ...... "I found out about the importance of these matches almost immediately after I signed for Arsenal.

"People who work for the club told me about it and about the most memorable clashes with Spurs.
"They told me that after some defeats they couldn't even speak to each other for a long time."

እንግዲህ ለዚህ ጨዋታ ይህን ያህል ትኩረት ነው የሚሰጡት.... በዚህ ጨዋታ መሸነፍ አፍን ይለጉማል..... ቅቅቅ.... ታዲያ ነገ የሚለጎመው አፍ የማን ይሆን??? የእኔን አያድርገው... ወደ ተጨዋቾች አቋም ስንመጣ ቪንገር የተለመደውን አሰላልፍ 4-3-3 ይዞ የሚገባ ሲመስለኝ.... በረኛ ምናልባት አልሙኒያ ሳይሆን አይቀርም:: ክሊቺ... ቨርማላን....ጋላስና.... ሳኒያ ከኌላ ሶንግ.... ፋበርጋስና ድያቢ መሀል ላይ አርሻቪንና ቤንትነር(ኢቦየ) በክንፍ ቫንፐርሲ መሀል ላይ ይሆናሉ የሚል ግምት አለኝ:: ቤንች ላይ ናስሪና ኢድዋርዶ መኖራቸው ለቪንገር ጥሩ እድልን ሰጥቶታል:: የአምናውን ጨዋታ ታስታወሳላችሁ?? 4-4 የተለያዩበት ቅቅቅቅ ዘንድሮ 3-0 ነው..... ጋነር ስፑድስን ያቀምሰዋል:: መልካም እድል ለአርሰናል........... ጋነር ፎር ኤቨር......
Image
አንበርብር
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1278
Joined: Sat Apr 09, 2005 12:01 am
Location: everywhere

Postby እኔውነኝኝ » Sat Oct 31, 2009 6:08 pm

ልጅ አንበርብር: የ አንተው አርሰናል ቶትንሀምን ብቃት በተሞላበት መልኩ አሸንፎ 3 ነጥቡን ላፍ አድርጓል እንኳን ደስ አላችሁ ጋነርሶች:: የኔው ሊቨርፑል ደግሞ በ ፉልሀም አይሆኑ ሽንፈት ተሸንፎ እና ሁለት ቀይ ካርዱን ጎርሶ ተመልሧል: አይጣል ነው!! ጭጓራዬ :? :? :? :?
እኔውነኝኝ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 623
Joined: Sat Jan 20, 2007 11:17 am

Postby አንበርብር » Tue Nov 03, 2009 1:56 am

እኔውነኝኝ wrote:ልጅ አንበርብር: የ አንተው አርሰናል ቶትንሀምን ብቃት በተሞላበት መልኩ አሸንፎ 3 ነጥቡን ላፍ አድርጓል እንኳን ደስ አላችሁ ጋነርሶች:: የኔው ሊቨርፑል ደግሞ በ ፉልሀም አይሆኑ ሽንፈት ተሸንፎ እና ሁለት ቀይ ካርዱን ጎርሶ ተመልሧል: አይጣል ነው!! ጭጓራዬ :? :? :? :?


ታዲያስ እኔው ነኝ.... ሰላም ነህ ወይ? የሊቬ መውረድ በጣም አሳሳቢ ነገር ነው... የአምናው ሊቨርፑል የ3 ሰዎች ክልብ ብቻ እንደነበረ ያመላከተ ይመስለኛል:: ጀራልድ..... አሎንሶና ቶሬዝ አሎንሶን ደግመው ላያገኙት አንዴ አጥተውታል ጀራልድና ቶሬዝን ደግሞ በጉዳት ሲያጧቸው አቋማቸው ምን እንደሚመስል ታይተዋል እናም ክለቡ አጣብቂኝ ውስጥ ያለ ይመስላል:: ሊቬ የቻምፒወን ሊጉን ማጣሪያ ካላለፈ የቤንቴዝ መቆየትም አጠያያቂ ነው :roll: :roll:

የእኛዋ አርሱካም ጥሩ ተፎካካሪ ትመስለኛለች..... ግምቴም ሰርቶ 3 ነጥብ ከ3 ጎል ጋር ከስፑድስ ቸርፍሰናል... በዚህ አቋም ለመቆየት ቪንገር አንድ ነገር ማድረግ ያለበት ይመስለኛል..... ድያቢን ወርውሮ አንድ ጥሩ ዲፌንሲፍ ሚድፊልደር መግዛት....... ሶንግን ካጣነው ጣጣ ውስጥ እንደምንገባ ይታየኛል....... ድያቢ እንዴት እንዳስጠላኝ... ከአቋሙ ወረደ ሳይሆን ዘቀጠ ነው የሚባለው ቅቅቅቅ በተረፈ....... ሊቨርፑል ከወደቀበት የአቋም መዋዠቅ በተሎ እንዲመለስ ምኞቴ ነው...... ሊቬ ለጌታ ከዋርካ ስፓርት መጥፋትም ተጠያቂ ነው....... ጋነር ፎር ኤቨር.... ሊቨርፑል ለግዜው :lol: :lol: ዩናይትድ ኔቨር ኤቨር :evil: :evil:
Image
አንበርብር
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1278
Joined: Sat Apr 09, 2005 12:01 am
Location: everywhere

Postby Monica**** » Wed Dec 23, 2009 3:09 pm

አንበርብርዬ በቃ የዚህ ቤት ነገር እንዲህ ሆኖ ይቅር መጨረሻው????
ሁሉም በስላም ከሆነ ሲመችህ ብቅ በል!!!
መልካም የፈርንጆች ገናና አዲሳመት እና የአበሻ ገና ሁሉም በጅምላ ይሁንልህ!!!
ሞኒካ ነኝ ከኤምሬት ስቴዲየም!!!
Yesterday is history, tomorrow is mystery, but today is a gift and that is why they call it the present!!!
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby Monica**** » Thu Dec 31, 2009 12:40 am

አንበብርዬ
አሁንም አልተመለስክም አይደል???
እኔ እንክዋን ብቅ ያልኩት የዛሬው ድላችንን ሴሌብሬት ለማድረግ ነበር....የለህም :oops: ፖርትስመዝን 4 ለ 1 ቀጣናችው.....ምንም እንክዋን እንደምናሽንፍ ባውቀውም አንዳንደ የተናቀ ቲም.....ለማንኛውም ቀጣናችው!!!!!!
እረ አንተ ወይም ማዊት ብቅ በሉና እናውራ እንደድሮው!!
ገነርስ ፎርኤቨር!!!!!!!!!!
Yesterday is history, tomorrow is mystery, but today is a gift and that is why they call it the present!!!
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby Monica**** » Thu Dec 31, 2009 12:42 am

በነገራችን ላይ መልካም የፈረንጆች አዲስ አመትና የአበሻ ገና ለገነርስ አፍቃሪዎች በሙሉ እመኝላችህዋለሁ!!!! ሆፕፉሊ ለአርስናልም ጥሩ 2010 እንዲሆን ምኞቴ ነው!!!
Yesterday is history, tomorrow is mystery, but today is a gift and that is why they call it the present!!!
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby Monica**** » Wed Jan 13, 2010 8:48 am

ዛሬ ኢማኑኤል አዲባዮር ኢንተርቪው ሲደረግ መጀመሪያ ያየሁት ነገር የለበስው ቲሽርት የማንችስተር ሲቲ ሳይሆን የኛን የገነርሶችን ነበር :lol: :lol: ልቡ ውስጥ ያለውን መሆን አለበት......በነገራችን ላይ በቶጎ ስፖርተኞች ላይ የደረስው ተኩስ አደጋ በጣም ያሳዝናል!!!!
Yesterday is history, tomorrow is mystery, but today is a gift and that is why they call it the present!!!
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby ኤስመር » Fri Apr 16, 2010 1:19 pm

ይሄ ቤት እንደዚህ ተረስቶ ይቅር :( :( :?
አንበርብር..ቻው ሳይል ቤቱን ክፍት ትቶ ጠፋ.... ሞኒካም ተጣርታ ተጣርታ..መልስ ስታጣ ጠፋች:: ከዋርካ በጡረታ ተገለው ይሆን :?: ...
ባሩክ ዮዳሄ እስኪ እኛ የሸረሪት ድሩን እያራገፍን እንጫወትበት:: :wink:
.........................................................................
Opinions are like assholes... everybody's got one, and they're often full of shit. :D (from some forum)
.......................................................................
ኤስመር
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 95
Joined: Sat Jan 23, 2010 10:17 pm
Location: ኤድሪያን ሲቲ (somewhere in estern Europe!)

ሰላም ለዚህ ቤት

Postby ethiomawit » Fri May 07, 2010 4:27 pm

ሰላም አርሰናሎች... እንዴት ከረማችሁ....


የናንተው ማዊት
ከአርሰናል ሜዳ
ethiomawit
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 157
Joined: Fri Oct 03, 2003 10:31 am
Location: united states

Postby Monica**** » Thu Jun 17, 2010 10:23 am

ወይ ጉድ ይሄ ቤት እንክዋን ተገፍቶ ተገፍቶ 2ኛ ገጽ ላይ ይድረስ???
ወይኔ ወንድሜ አምበርብር ይሄኔ የዛሬን አያድርገውና ስለአለም ዋንጫ ስንት የምትጽፋችው ወርቅ ጽሁፎች ይኖሩህ ነበር!!!
ግዴለም መቼም አንድ ቀን እንደድሮው እንደሚመለስ ተስፋ አለኝ!!!!
ስላም እንክረም
Yesterday is history, tomorrow is mystery, but today is a gift and that is why they call it the present!!!
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby ተድላ ሀይሉ » Mon Jun 27, 2011 9:14 pm

Monica**** wrote:ወይ ጉድ ይሄ ቤት እንክዋን ተገፍቶ ተገፍቶ 2ኛ ገጽ ላይ ይድረስ???
ወይኔ ወንድሜ አምበርብር ይሄኔ የዛሬን አያድርገውና ስለአለም ዋንጫ ስንት የምትጽፋችው ወርቅ ጽሁፎች ይኖሩህ ነበር!!!
ግዴለም መቼም አንድ ቀን እንደድሮው እንደሚመለስ ተስፋ አለኝ!!!!
ስላም እንክረም


የቤቱ አድባር ቢጠፋም እኛ አንረሣውም :: እስኪ ወደመጀመሪያ ገፅ ይመለስ ::

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

PreviousNext

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests

cron