የኢትዮጵያ የአትሌቲክስ:- 2005 የተስፋ ዘመን

ስፖርት - Sport related topics

የኢትዮጵያ የአትሌቲክስ:- 2005 የተስፋ ዘመን

Postby ተድላ ሀይሉ » Tue Apr 22, 2008 12:05 am

ሰላም ወገኖቼ :-

ዛሬ ቦስተን በተደረገ የማራቶን ሩጫ ውድድር በሴቶች ኢትዮጵያዊቷ ድሬ ቱኔ 2 ሰዓት 25.25 ደቂቃ በመግባት 1ኛ ወጥታለች ::

የዚችን ልጅ አሯሯጥ ለተመለከተ እግዚአብሔር ጤናውን ይስጣት እንጂ በቤጂንግ የወርቅ ሜዳሊያ ለማጥለቅ ተስፋ ያላት ናት ::

ምንጭ :-
http://www.bostonmarathon.org/
http://www.youtube.com/watch?v=LyYJiKxHZz0

ዘወትር ለሚያኮሩን ለመላ አትሌቶቻችን መልካም ዕድል እመኛለሁ ::

ተድላ
Last edited by ተድላ ሀይሉ on Mon Sep 10, 2012 7:39 pm, edited 16 times in total.
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ሙትቻ » Tue Apr 22, 2008 12:40 am

Image
ድሬ ቱኔ ከድል በኍላ....

ተድላ ስለመልካሙ ዜናህ እናመሰግናለን::
ጃንዋሪ 31 በሂውስተን ማራቶን በማሸነፍ 2:24:40 ገብታ የነበረችው አትሌት ድሬ ቱኔ ዛሬ ቦስተን ላይ ያሸነፈችበት 2 ሰዓት 25.25 ከባለፈው ሰአቱ ትንሽ ዘግየት ያለ ቢሆንም መልካም ውጤት ነው::
በ3 ሺህ ሜትር ሩጫ ጀምራ እስከ 10 ሺህ ሜትር ባሉት ርቀቶች ትሮጥ የነበረችው አትሌት ድሬ ቱኔ ጁን 19 1985 እንደአወሮፓውያን ቀመር ነው የተወለደችው:: አትሌቷ በግማሽ ማራቶን እና በ25 እና 30 ኪሎ ሜትር ሩጫዎች ላይ ጥሩ ውጤት አላት:: እንግዲህ ለቤጂንጉ ኦሎምፒክ መልካም ውጤት ከእርሷ: ብርሀኔ አደሬ: ጌጤ ዋሚና ሌሎችም በቡድን ሥራ እንጠብቃለን::

እንኳን ደስ ያለን::
Image
ሙትቻ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2633
Joined: Fri Mar 31, 2006 7:38 am
Location: other

Postby ብናስተውል » Tue Apr 22, 2008 8:06 am

ዋውውውውውውውውው
በጣም እናመሰግናለን ስለሊንኩ ተድላ ሃይሉ::
ዋውውውው .... እጅግ በጣም አስደሳች ውጤት ነው ድሬ ያስመዘገበችው:: ዋው አጨራረስ!!!!! ማራቶን ሳይሆን ገና 10 ኪሜ የሮጡም አይመስሉም መጨረሻ ላይ ያደረጉት ፉክክር:: በጣም የሚያስደስትና ተስፋ የሚሰጥ ውጤት::
በርችልን ድሬዋ! ኮርተንብሻል!!!!!
አለ ገና .... ገና ....... ቤጅንግ ላይ ..... አነ ገና .... ተስፋ አለን ዘንድሮ ..... ሙቴክስ እንዳለውም: ብርሃኔና ጌጥሻም አሉልን ...... ይቅናን ዘንድሮ ኦሎምፒክስ

ድል ለአትሌቶቻችን!!!!
Selam le-Ethiopia
ብናስተውል
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1115
Joined: Tue Jan 31, 2006 11:33 pm

Re: የቦስተን '2008' ማራቶን

Postby ወርቅሰው1 » Tue Apr 22, 2008 1:36 pm

ተድላ ኃይሉ!
ድንቅ አቀራረብ ነው:: ቪዲዮው በትክክል ሁሉንም የሚያሳይ የሷንና የራሻዊቷንም ፍክክር አስገራሚ ነው:: ኢትዮጵያዊቷ ልጅ ሲበዛ ጀግና ነች:. ሊንከባከቧትም ይገባል:: ድንቅ ልጅነች:: የቤይጂንጉን የማራቶችን ወርቅ የግዴታ ኢትዮጵያዊያኖች በ2 ቱም ሥፍራ ሊቆጣጠሩት ይገባል:: ማራቶችን ስሙ ነው ኦሎምፒያ በመሆኑም?

ሙትቻም!!! ጥሩ ነው ከፎቶጋር የተደገፈውን ማቅረብህ:: ብናስተውልም እንዲሁ ቶሎብለህ ገጹን መክፈትህ ልትመሰገን ይገባል::

ወርቅሰው1
ከ(ሰሐሊን)ተድላ ሀይሉ wrote:ሰላም ወገኖቼ :-

ዛሬ ቦስተን በተደረገ የማራቶን ሩጫ ውድድር በሴቶች ኢትዮጵያዊቷ ድሬ ቱኔ 2 ሰዓት 25.25 ደቂቃ በመግባት 1ኛ ወጥታለች ::

የዚችን ልጅ አሯሯጥ ለተመለከተ እግዚአብሔር ጤናውን ይስጣት እንጂ በቤጂንግ የወርቅ ሜዳሊያ ለማጥለቅ ተስፋ ያላት ናት ::

ምንጭ :-
http://www.bostonmarathon.org/
http://www.youtube.com/watch?v=LyYJiKxHZz0

ዘወትር ለሚያኮሩን ለመላ አትሌቶቻችን መልካም ዕድል እመኛለሁ ::

ተድላ
ወርቅሰው1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4075
Joined: Wed Nov 05, 2003 9:49 pm
Location: Sehalin

Postby ተድላ ሀይሉ » Sat Aug 02, 2008 4:40 am

ሰላም ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

የዛሬ ሣምንት አርብ ነሐሴ 2 ቀን 2000 ዓ.ም. (Friday August 8, 2008) በቤጂንግ : ቻይና በሚጀመረው እና ለሁለት ሣምንታት በሚካሄደው የ29ኛው የበጋ ኦሎምፒክ ለአገራችን ለኢትዮጵያ ምን ውጤት እንጠብቅ ?

ዘንድሮ ከ800 ሜትር እስከ ማራቶን በሴትም : በወንድም ሜዳሊያ በሜዳሊያ እንሆናለን ብየ እገምታለሁ ::

እናንተስ?

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby 777 » Sat Aug 09, 2008 7:45 am

በውነት እንደትላንት ወሽመጤ እንደተበጠሰ መቼም የሚሆን አይመስለኝም::

አትሌቶችን ለማየት ጉዋጉቼ ተጎልቼ ጉድ ሆንከ::
ከምሩጵ በቀር ቅራቅምቦ የተሰበስበበት:: ኮመንታተር ኢትዮጵያውያን ሲያልፉ ከአሁን አሁን ምን ይናገራል ስል ስለማን ያውራ:: አንድ እንኩዋን አትሌት የለ::

ኦሎምፒክ ዋናው አላማ ሀገር ማስተዋወቂያ ነበር:: ግን መልካም መንግስት ሲኖር እኮ ነው: ግን የህዝብን መደስት የማይፍልግ የህዝብ ሞራል መግደል የሚፈልግ መንግስት ነው:: ብቻ ለዚህ መንግስት ፍጻሜውን ያሳየን::

አትሌቶቻችን ሞራላችሁ እንዳይነካ አይዟአችሁ::
መልካም ውጤት ለአትሌቶቻችን::

እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን:::
777
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 45
Joined: Mon Jul 14, 2008 2:29 pm
Location: Darmar

Postby ጩጉዳ » Sat Aug 09, 2008 8:57 am

777 wrote:በውነት እንደትላንት ወሽመጤ እንደተበጠሰ መቼም የሚሆን አይመስለኝም::

አትሌቶችን ለማየት ጉዋጉቼ ተጎልቼ ጉድ ሆንከ::
ከምሩጵ በቀር ቅራቅምቦ የተሰበስበበት:: ኮመንታተር ኢትዮጵያውያን ሲያልፉ ከአሁን አሁን ምን ይናገራል ስል ስለማን ያውራ:: አንድ እንኩዋን አትሌት የለ::

ኦሎምፒክ ዋናው አላማ ሀገር ማስተዋወቂያ ነበር:: ግን መልካም መንግስት ሲኖር እኮ ነው: ግን የህዝብን መደስት የማይፍልግ የህዝብ ሞራል መግደል የሚፈልግ መንግስት ነው:: ብቻ ለዚህ መንግስት ፍጻሜውን ያሳየን::

አትሌቶቻችን ሞራላችሁ እንዳይነካ አይዟአችሁ::
መልካም ውጤት ለአትሌቶቻችን::

እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን:::


ሰላም 777

ይመስለኛል አሜሪካ ውስጥ ካለህ NBC ነው ያየሄው:: እኔም እንዳንተው በግኛለሁ:: 2 ሰዐትሙሉ ተጎልቼ እነ ቀነኒሳ በባንዲራ አሸብርቀው ብዙ ይባልላቸዋል ብዬ ስጠብቅ ምሩጽንና 3 ቦርጫም ሸበቶ ሰዎች ለ 10 ሰከንድ ያህል አሳይቶ አለፈ:: የሚገርመው ቡድኑ እንደወትሮ የአገር ባህል ልብስ አለመልበሱ ነው:: ይሁና >>>>> ደግሞ ኦሊምፒክ ዌብሳይት ገብቼ ፕሮፋይላቸውን ሳይ ምንም የማይታወቁ ሯጮች ሞልተውበታል:: ለመሆኑ ዐመቱን ሙሉ በየከተማው እያሸነፉ ስማቸው ሄድላይን ያጣበበ ልጆች የት ገቡ ወይስ ኦሊምፒክም በችሎታ ሳይሆን በብሄር ብህረሰብና በክልል ሆነ::
መታገስንና መቻልን የመሰለ ብቀላ የለም ::
ጩጉዳ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1267
Joined: Mon Jan 31, 2005 6:40 am
Location: Studio City, Wilson Republic

Postby እህምም » Sat Aug 09, 2008 9:07 am

777 wrote:ኦሎምፒክ ዋናው አላማ ሀገር ማስተዋወቂያ ነበር:: ግን መልካም መንግስት ሲኖር እኮ ነው: ግን የህዝብን መደስት የማይፍልግ የህዝብ ሞራል መግደል የሚፈልግ መንግስት ነው:: ብቻ ለዚህ መንግስት ፍጻሜውን ያሳየን::

:::


:lol: በለው........እውነት እምትሉትን አጣችሁ! በዚህ መንግስት ስር እትዮ 21 ሜዳሎች አግኝታለች (17 አመት)! በሀይለስላሴ እና በደርግ ተደምሮ 10 ነው ያላት(60+ yrs) ! እና እስቲ ኮምፕሌይን ስናረግ አት ሊስት ምክንያት ይሁረን ምናለበት! we should give credit where it's due!
Homage to darkness : http://yekolotemari.blog.com/2010/02/09 ... -darkness/


"Is it stealing
if I take
the pains of others

and make it my healing?"
http://elicitbeauty.blogspot.com/
እህምም
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2509
Joined: Mon Dec 19, 2005 10:36 pm
Location: on a small rock; between an ocean and a sea.

Postby 777 » Sat Aug 09, 2008 9:51 am

አይ እህህም

ድግሞ በዚህ መንግስት ያገኘንው እያልሽ ሜዳልያ መቁጠር ጀመርሽ???? ቅቅቅቅ ቂቂቂ :D :D

እንደዚህ መንግስት ቢሆን ኖሮ ሜዳልያ አይደለም የወርቅ የብር የነሐስ የኮርኪም አታገኝም ነበር:: የበረኪና ዋንጫስ ታቂያለሽ ቂቂቂቂቂ :lol: :lol: :lol:

ቀልጂ ብቻ አንቺ:: የቆጠርሻቸው ሜዳልያዎች ሁሉ የተገኙት በአትሌቶች ብርታት እንጂ መንግስት የሚያደርገውን ድጋፍ እንኩአን ተይው ቂቂ ቀልድ ብቻ

የኔ እህት አትሳሳቺ ለዛሬዎቹ አትሌቶች ምሳሌ የሆኑት አንቺ ሜዳልያዎቻቸውን በጣት የቆጠርሻቸውን በባዶ እግራቸው ሮጠው የወርቅ ሜዳልያ ያመጡልን እነ አበበ ቢቂላና ማሞ ወልዴን ታሪክ ማናናቅ ዋጋ የለውም::

መንግስት ያልፋል ሀገርና ታሪክ ግን ለዘላለም ህያው ሆኖ ይኖራል::
777
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 45
Joined: Mon Jul 14, 2008 2:29 pm
Location: Darmar

Postby ጩጉዳ » Sat Aug 09, 2008 2:32 pm

እህምም wrote: :lol: በለው........እውነት እምትሉትን አጣችሁ! በዚህ መንግስት ስር እትዮ 21 ሜዳሎች አግኝታለች (17 አመት)! በሀይለስላሴ እና በደርግ ተደምሮ 10 ነው ያላት(60+ yrs) ! እና እስቲ ኮምፕሌይን ስናረግ አት ሊስት ምክንያት ይሁረን ምናለበት! we should give credit where it's due!


በለው መለስ ዜናዊ ሯጮቹ ሜዳሊያ እንዲያገኙ አስደረገ ሊባልለት ነው እዚህ ጋ! :wink: :roll:

በወያኔ አገዛዝ 21 ሜዳሊያ ማግኘታችን አገዛዙ በስልጣን ላይ ስለሻገተ ከጊዜ ብዛት አንጻር ምንም አያስደንቅም::

የመንግስት ነገር ካነሳን ዐለማችን አሁን ከድረሰበትና አገራችን ያሏት ታለንትድ ስፖርተኞች አንጻር ሲታይ ግን ወያኔ ምንም የጨመረው አነገር የለም:: ድሮም በሩጫ ነው የምንሳተፈው አሁንም ያው ሩጫ ነው:: እንዲያውም በደርግ ጊዜ ብስክሌትና በዛ ያሉቦእኞች እናሳትፍ ነበር አሁን አንድ ቦክሰኛ ቢኖር ነው የብስክሌቱ ጉዳይ አይወራ

በእግር ኳስ የት ደረስን ጃንሆይ ባሰሩት ሜዳ አይደለም ወይ እስካሁን የሚራገጡበት? ደሮም በደርግ ተጫዋች ይከዳል አሁንም በወያኔ ይከዳል ድሮም በግብጽና በካሜሩን 4 ለ 0 እንሸነፋለን አሁንም እንደዚያው እንዲያውም በ2002 በ ኤርትራ 2 ለ 0 መሸነፋችንን ታውቀው ይሁን? ምንድ ነው ልዩነቱ ?

ኢትዮጵያ በታሪክ ከፊፋ በታሪክ የታደገደችበት ጊዜ ቢኖር በወያኔ ዘመነ መንግሥትት መሆኑንስ ታውቀዋለህ? ለዚህ መንግስት ነው ክሬዲት ኡእሚሰጠው? ለመሆኑ በቫሊቦል በሀንድ ቦል ስለ በባስኬት ቦል በአፍሪካ ዋንጫ እንካፈላለን ወይ? መልሱን ለታዛቢ እንተወው >>>
መታገስንና መቻልን የመሰለ ብቀላ የለም ::
ጩጉዳ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1267
Joined: Mon Jan 31, 2005 6:40 am
Location: Studio City, Wilson Republic

Postby ተድላ ሀይሉ » Sat Aug 09, 2008 5:56 pm

እህምም wrote: :lol: በለው........እውነት እምትሉትን አጣችሁ! በዚህ መንግስት ስር እትዮ 21 ሜዳሎች አግኝታለች (17 አመት)! በሀይለስላሴ እና በደርግ ተደምሮ 10 ነው ያላት(60+ yrs) ! እና እስቲ ኮምፕሌይን ስናረግ አት ሊስት ምክንያት ይሁረን ምናለበት! we should give credit where it's due!


ያንን ዓይነት ፕሮፓጋንዳ በፋና ሬድዮ ማቅረብ አይሻልሽም ? አትሌቶቹ በምን ዓይነት ፈተና አልፈው ወደ ኦሎምፒክ ውድድር እንደሚሄዱ እናውቃለን እኮ :: በሲድኒ ኦሎምፒክ ምን ነበር የተደረገው ? ወያኔዎቹ 25 የትግራይ ክልል አትሌቶች ብቻ ናቸው የሚሄዱት ብለው ስንት ሙግት ነበር !! ወያኔዎች ያ እንደማይቻል ሲያውቁ ከመንግሥት ምንም ዓይነት ድጎማ አይደረግም ብለው አትሌቶቹ በህዝብ መዋጮ ነበር የሄዱት :: እንግዲህ በኦሎምፒክ ታሪክ ኢትዮጵያ ከፍተኛውን የሜዳሊያ ቁጥር (4 ወርቅ : 1 ብር : 3 ነሐስ) ያገኘችው በዚያ የሲድኒ ኦሎምፒክ መሆኑ ይህንን የወያኔዎችን መከራከሪያ ነጥብ የሚደግፍ ነው ?

ሥለ ትላንቱ የመክፈቻ ዝግጅት :-
የኢትዮጵያ አትሌቶች ውድድር የሚጀምሩት ሣምንት አርብ ነሕሴ 9 : 2000 ዓ.ም. (Friday August 15, 2008) በወንዶች 1,500 ሜትር የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ : በሴቶች 3,000 ሜትር መሠናክል ሩጫ የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ እና በሴቶች 10,000 ሜትር የፍፃሜ ውድድር ሥለሆነ ውድድሩ እስኪቃረብ ቤጂንግ መሄድ አያስፈልጋቸውም :: ምክንያቱም የቤጅንግ የአየር ፀባይ ወበቃማና በአየር ብክለት የተሞላ ሥለሆነና የእኛም አትሌቶች በከፍተኛ ሥፍራ በመለማመድ መቆየቱ ለውጤታቸው ጠቃሚ በመሆኑ ::

መልካም ውጤት ዘወትር ለሚያኮሩን አትሌቶቻችን ::

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby 777 » Sun Aug 10, 2008 6:03 am

ለወንድማችን ተድላ

ስለሰጠህኝ በቂና ቅንነት ያለው ማብራሪያ ከልብ አመሰግናለሁ::

ምነው ቀደም ብዬ ባወቅሁና ሦስት ሠኣት ሙሉ ቲቪ ላይ ከማፍጠጥ በተረፍኩ ኖሮ::

ሦስት ሠአት ስንት ይሸቀል ነበር????????????
ወይ ነዶ
777
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 45
Joined: Mon Jul 14, 2008 2:29 pm
Location: Darmar

አስተሳሰብ!

Postby ልጁነኝ1 » Sun Aug 10, 2008 4:42 pm

አስተሳሰብ!
በውነቱ ወደ ቤይጂንግ በዚህ ጊዜ ፈጥነው ያለመሄዳቸው ይወደድ ነበር:: ግን ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ እንደአነበብኩት ከሆነ የመላኒየሙ በዓል አዘጋጆች ምን ሲያደርጉ በስፖርት ደረጃው ላይ ሄደው ሊካፈሉ ቻሉ?ያየሚያበሽቅ ተግባር ነው:: ስፖርተኞቻችን ከማንም ከምንም በፊት ከፍተኛ ክብካቤ ከራሳቸው መንግሥት ሊያገኙ ይገባል:: ምክንያቱም የሠፊው ሕዝብ ልጆች ናቸውና:: የስድኒውን ኦሎምፒክ አሻጥር አላውቅም ነበር ዛሬ መስማቴ ነው:: አስገራሚ ነገር ለዝያም ነው ለካ ሲሸለሙ ጀግኖቻቺን ያለቅሱ የነበሩት? አሁንም ድጋሜ ማበላሸት እንዳይፈጠር:: ከዚያም የስፖርትና የባህል ሚኒስትር ስራቸው ምን ይሆን? ስፖርቱን መገንባት ነበር? ነገር ግን የግርኳስ ተጫዋቾቹ ለምን እስከዚያ ተሄዶ ከዓለም ፌዴሬሽን ሊሰረዙ በቁ? ቀጥሎም አባይና ጣና አዋሳና ጎዶውሃ ኦሞና ገናሌ ባሏት ከፍተኛ ባሕሮችን ምክንያት አድርጎ ዋና ዋኝዎችን የስፖርት ሚኒስትሩ ወጣት ሕጻናትን ቀደም ብሎ ለምን ለማሰልጠን አልሞከረም? በባሊቦልና ባስኬጽ በጠመንጃ ተኩሶችና በሽጉጥ ተኩሶች በአሎሎ ውርወራዎችና በጦር ውርወራዎች በ100 ሜትርና እስከ 800 ሜትር ፍጣን ሯጮችን እየመለመሉ ለምን በረጅም ጊዜ ስልጠናና ማስተማር አላገኙም ከዚያም በዓለም ደረጃ እንዲካፈሉ አልተደረገም? ያን ያን ሲያስቡት አገራችን እስካሁንም ድረስ እያንቀላፋች ነው:: ፖለቲካውንና ስፖርቱን ማቀላቀል አይገባቸውም የኢሕአዴግ ሰውዎች:: ከፍተኛ ልባዊ ወዳጅነትና ብሎም ማዕረግ በሰራዊቱ ውስጥ ለሚሮጡ ሊሰጥ ይገባል? ኃይሌ እስከዛሬ ድረስ ሻለቃ እንደሆነ ቆይቷል? ቦታው ግን ሜ/ጄኔራል ነው:: በተለይ ጥሩነሽ:: ከፍተኛ ማዕረግ ሊሰጣት ይገባል:: ወጣት ነች ብ/ጄኔራል ብትሆን እድሜዋን ደስ ብሏት እንድትኖር ይገባል:: ማዕረግ የማይፈልጉትን ወይም የማይገባቸውንም በቂ የኤኮኖሚ መዳበር እድኒያገኙ በአገራቸው ላይ ደስተኛ እንዲሆኑ ወጣቱን ትውልድ የነሱ ማጝነትና ደስተኛ መሆን ወደውድድሮች ስለሚጋብዝም::የስፖርትና ... ሚኒስቴር ይስራ ወይም ይዘጋ አዲስ አስተሳሰብ እያወጡ ህዝቡን ከድሮጋ ወደ እስፖርተኛነት ወጣቱን ለመቀየር ያደረጉት ክብካቤ እስከዛሬ ያልነበረና ያልታየም ስለሆነ? የመዋኛ ስፍራዎች:: የስፖርት መገናኛ አዳራሾች ብሎም የስፖርት ጂምናዚየሞችን በየክልሎቹ ሳይቀር አውራጃና ወረዳዎች ሁሉ እንዲሰሩ መንግስት መተባበርና ማስፈጸም ይገባዋል? ታዲያ ያን ያደርጋሉ ወይ በአገራችን ነጋ ጠባ የነገር አረቄ እያወጡ ለራሳቸው እንዲመች እያደረጉ ከመኖር በስተቀር?

ልጁነኝ1
ልጁነኝ1
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 641
Joined: Tue Dec 30, 2003 2:17 pm
Location: united states

Postby አንበርብር » Mon Aug 11, 2008 3:03 am

ሰላም ወገኖቸ?
አትሌቶቻችን ቤጅንግ ያልገቡት በአየሩ ብክለት ምክንያት ስለሆነ ነው ስለተባለው ትንሽ ግራ የሚያጋባ ነገር ነው...... በእርግጥ የአየር ብክለት እንዳለ ሁሉም የሚያምንበት ነው ነገር ግን የሚሮጡት ቤጅንግ ውስጥ እስከሆነ ድረስ ከዚያው በመሆን ከአየሩ ጋር በመጋፍት ልምምዳቸውን ቢያደርጉ አይሻልም ነበር ወይ? ቆይታቸውን ከቤጅንግ ውጭ አድርገው በመሮጫቸው ሰሀት ካለመዱትና ካልጠበቁት weather ጋር ለውድድር መቅረቡ ሳይድ ኢፌክት አይኖረውም ወይ?

ሀይሌና ቀነኒሳን የመሰሉ ስመ ጥር አትሌቶች በመክፈቻው ሰሀት ከባንዲራቸው ጋር አለመታየታቸው በጣም ያስከፋል:: ለውድድሩ ወደ ቤጅንግ የተጓዙት ተወዳዳሪዎች ቁጥር 32 ነው ተብሎ ነበር የታዩት ግን በጣት የሚቆጠሩ ነበሩ:: እነርሱም በጡረታ የተገለሉ አትሌቶችና ቤተሰቦቻቸውን የሚመስሉ............ ባንዲራው እስከነ አንባሻው.........

በቦክስ ውድድር ሀገራችንን ለመወከል ወደ ቤጅንግ ተጎዞ የነበረው ሞላ ጌታቸው ከውድድር ታገደ:: ምክንያት ክብደት ጨምሮ ስለተገኘ........... የሞላ እጣ ፈንታው ወደ ሀገሩ መመለስ ወይም ለእነ ሀይሌ... ቀነኒሳ ጥሩነሽ እንዲሁም ለተቀሩት አትሌቶች በቦታው ተገኝቶ ድጋፉን መለገስ::

Image

Runner's World የተባለው አለም አቀፍ መፅሄት በቤጀንጉ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ 4 የወር ሜዳሊያዎችን እንደምታገኝ ግምቱን ሰጥቷል:: ይህ መፅሄት ሀገራችን በሴቶች 1500M ገለቴ ቡርካ ወርቅን ታጠልቃለች ሲል በሴቶች 5000M ደግሞ ያለምንም ማቅማማት አትሌቶቻችን ከ1-3 ያለውን ደርጃ ይቆጣጠሩታል ካለ በኌላ በደረጃ መሰራት ደፋርን 1ኛ... ጥሩነሽ ዲባባን 2ኛ መሰለች መልካሙን 3ኛ አድርጓቸዋል:: ሌላው የወርቅ ባለቤት እንሆንበታለን የተባለው የወንዶች የ10000M ውድድር ሲሆን ይህ መፅሄት ቀነኒሳን 1ኛ ይወጣል ብሎ ሲገምት ስለሺን ደግሞ 2ኛ ላይ በማስቀመጥ ኤርትራዊውን ዘርሰናይ ታደሰን 3ኛ አድርጎታል....... ሀይሌ ከግምቱ ውስጥ አልገባም :roll: :roll: :roll: በሴቶች 10000M ደግሞ ጥሩነሽ ዲባባን ወርቅን ትመነትፋለች ሲል ከእርሷ ውጭ ማንንም አትሌት ከኢትዮጵያውያን አላካተተም:: መጽሄቱ አትሌቶቻችን በማራቶኑ ምንም አይነት ሜዳሊያ እንደማናገኝ ግምቱን ሲሰጥ በወንዶች 5000 M ውጤታማ እንደማንሆን የተሰማውን ስሜት ጀባ ብሎናል:: እንደ ግምቱ ሀገራችን የ4 ወርቅና የ2 ብር ባለቤት ትሆናለች ማለት ነው:: አያንስም :?: :?: :?: ቢያንስ ከማራቶኑ አንድ ወርቅ በ5000 M ደግሞ 1 ወርቅ ቢጨመርበት መልካም ነው............ በወንዶች 5000M ላይ ቀነኒሳ ከታናሽ ወንድሙ ታሪኩ በቀለ ጋር ተሰላፊ ነው........... እናም በዚህ ውድድር አንድ ወርቅ ካልሆነ ብር ይታየኛል..........

መልካም እድል ለጀግኖች አትለቶቻችን.............
Image
አንበርብር
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1278
Joined: Sat Apr 09, 2005 12:01 am
Location: everywhere

Postby ተድላ ሀይሉ » Mon Aug 11, 2008 5:21 am

አንበርብር wrote:ሰላም ወገኖቸ?
አትሌቶቻችን ቤጅንግ ያልገቡት በአየሩ ብክለት ምክንያት ስለሆነ ነው ስለተባለው ትንሽ ግራ የሚያጋባ ነገር ነው...... በእርግጥ የአየር ብክለት እንዳለ ሁሉም የሚያምንበት ነው ነገር ግን የሚሮጡት ቤጅንግ ውስጥ እስከሆነ ድረስ ከዚያው በመሆን ከአየሩ ጋር በመጋፍት ልምምዳቸውን ቢያደርጉ አይሻልም ነበር ወይ? ቆይታቸውን ከቤጅንግ ውጭ አድርገው በመሮጫቸው ሰሀት ካለመዱትና ካልጠበቁት weather ጋር ለውድድር መቅረቡ ሳይድ ኢፌክት አይኖረውም ወይ?

ሰላም አንበርብር :-
የቤጅንግ የአየር ፀባይ በአየር ብክለት ችግር ብቻ ሣይሆን ቤጅንግ ያለበት ከፍታ ጭምር ለሯጮች ልምምድ መልካም አጋጣሚ አይፈጥርም :: ብዙ ጊዜ በከፍተኛ ሥፍራ ልምምድ የሚያደርጉ አትሌቶች ለውድድር ወደ ዝቅተኛ ሥፍራ ሲሄዱ በተሻለ ሁኔታ ውድድሩን ማሸነፍ ይችላሉ :: ስለዚህ ጉዳይ 'Google' ላይ 'Advantages of high altitude training for athletes' ብለህ ብትፈልግ ብዙ ማብራሪያ ታገኛለህ ::

ሀይሌና ቀነኒሳን የመሰሉ ስመ ጥር አትሌቶች በመክፈቻው ሰሀት ከባንዲራቸው ጋር አለመታየታቸው በጣም ያስከፋል:: ለውድድሩ ወደ ቤጅንግ የተጓዙት ተወዳዳሪዎች ቁጥር 32 ነው ተብሎ ነበር የታዩት ግን በጣት የሚቆጠሩ ነበሩ:: እነርሱም በጡረታ የተገለሉ አትሌቶችና ቤተሰቦቻቸውን የሚመስሉ............ ባንዲራው እስከነ አንባሻው..

በእርግጥ አትሌቶቻችንን በመክፈቻው ዕለት ብናያቸው ጥሩ ነበር :: የመክፈቻውን ሥነ-ሥርዓት ተካፍለው ወደ ልምምድ ማድረጊያ መሄድ ይችሉም ነበር :: ነገር ግን በኢትዮጵያ ስፖርት አመራር ውስጥ ይህንን ሊያከናውን የሚችል : ኃላፊነት የሚሰማው : አገሩን የሚወድ እንደ አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ዓይነት የስፖርት መሪ ያስፈልጋል እኮ :: ዋናው ነገር አሁን እነዚህ ብዙ የወያኔን መሠናክል አልፈው ለውድድር የደረሱት አትሌቶቻችን መልካም ውጤት እንዲያስገኙልን ፈጣሪያችንን እንለምን ::

ይኼ ኢትዮጵያ ከ 4 ወርቅ በላይ አታገኝም የሚለውን ቱሪናፋ ተወው :: ያንንማ በሲድኒ ኦሎምፒክ ያገኘነው ውጤት ነው ::

መልካም ዕድል ለአትሌቶቻችን

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Next

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests