የኢትዮጵያ የአትሌቲክስ:- 2005 የተስፋ ዘመን

ስፖርት - Sport related topics

Postby እንሰት » Sat Aug 11, 2012 6:41 pm

ደጀን ገብረ መስቀል 5000 ብር ሜዳሊያ በ 13:41:93
ሀጎስ 11ኛ የኔው 12ኛ ወጥተዋል::

ተድላ ሀይሉ wrote:ሰላም ጌታ እና እንሰት :-

ግምቴ ብዙም ሥህተት የለውም :: ምክንያቱም የዘነበች ቶላ (መሪማ የሱፍ ጀማል) ሜዳሊያ ሲደመር ዛሬ ያገኘነው ሜዳሊያ ብዛት 3 ይሆናል :) እንግዲህ 'geremew' ቅር እንዳይልህ :lol: :lol: :lol:

እንዲያው ለመሆኑ እኒህ የቱርክ ሴቶች የ1,500 ሜትር ርቀት ሩጫን እንዴት ቢሮጡት ነው ተከታትለው መግባት የቻሉት? ፊልሙን ፈልጌ ማዬት ይኖርብኛል ::

እንሰት :- በሜዳሊያ ግምትህ ብዙም ከትክክለኛው የምትርቅ አይመስለኝም :: ከእንግዲህ ቢበዛ 3 ሜዳሊያዎች ብናገኝ ነው ::

ተድላ

ወንድም ተድላ
መጀመሪያ ይህንን አምድ በመክፈትህ ምስጋና አቀርባለሁ:: የኔ ግምት ከነበረው እና ካለው ሁኔታ ተነስቼ ነው:: 5000 የወንዶች እየጠበቅን ነው::
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ወርቅነች » Sun Aug 12, 2012 1:50 pm

እንዲያው ለመሆኑ እኒህ የቱርክ ሴቶች የ1,500 ሜትር ርቀት ሩጫን እንዴት ቢሮጡት ነው ተከታትለው መግባት የቻሉት? ፊልሙን ፈልጌ ማዬት ይኖርብኛል ::

ቅቅቅቅቅቅቅ...ፈዛዛው ደግሞ ፊልሙን ለምን ፈለከው... በቃ ጭንቅላትህ መሰራቱን አቆመ ... ጠላና ጠጅ ደባልቀው እየጠጡ ነው ተከታትለው መግባት የቻሉት ትለሀለች ጀሚላ ከቸርችል ጎዳና :lol: :lol: :lol:

ተድላ ሀይሉ wrote:ሰላም ጌታ እና እንሰት :-

ግምቴ ብዙም ሥህተት የለውም :: ምክንያቱም የዘነበች ቶላ (መሪማ የሱፍ ጀማል) ሜዳሊያ ሲደመር ዛሬ ያገኘነው ሜዳሊያ ብዛት 3 ይሆናል :) እንግዲህ 'geremew' ቅር እንዳይልህ :lol: :lol: :lol:

እንዲያው ለመሆኑ እኒህ የቱርክ ሴቶች የ1,500 ሜትር ርቀት ሩጫን እንዴት ቢሮጡት ነው ተከታትለው መግባት የቻሉት? ፊልሙን ፈልጌ ማዬት ይኖርብኛል ::

እንሰት :- በሜዳሊያ ግምትህ ብዙም ከትክክለኛው የምትርቅ አይመስለኝም :: ከእንግዲህ ቢበዛ 3 ሜዳሊያዎች ብናገኝ ነው ::

ተድላ
ወርቅነች
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 967
Joined: Sun Oct 03, 2010 10:05 am

Postby እንሰት » Sun Aug 12, 2012 9:10 pm

እንደምን ሰነበታችሁ ወገኖች
የማራቶኑን ርእሰ ዜና "ሜዳሊያውን ኡጋንዳ እና ኬንያ ተቀራመቱት" የሰማሁት ከስድስት ሰአት በፊት ነበር:: እስኪ እነ አየለ አብሽሮ እነ ዲኖ ሰፈር ምን ደረሱ? ደረጃ ውስጥ ገብተው ይሆን? የሚለው ጉጉቴ DNF በሚል ምህጻረ ቃል ታጅቦ 62ኛ, 92ኛ, እና 97ኛ መሆናቸውን አንድ ድረ ገጽ አስነበበኝ:: ይቺ DNF ምን ትሆን? ሁዋላ እንደተረዳሁት did not finish የምትል ሆና አገኘሁዋት አየለ 35 ኪሎ ሜትር ዲኖ 25 ኪሎሜትር እንዲሁም ጌቱ 23 ኪሎሜትር ሮጠው መውጣታቸውን ሰማሁ::

እንደ ወንድማችን ቱርቦ ቱሞ በሴት ሰአት መግባት ስላልፈለግን እንዳይሉ እነ ቲኪ ማ ሬከርድ ሰባብረዋል::

ሎንዶን መጠው ኮንትሮባንድ ለመነገድ ከሆነ ቢያሸንፉ ነበር የሚሻላቸው::

አሳፋሪዎች ከማለቴ በፊት ምን እንደሆኑ ቢያሰሙን ደግኛ ነው::

ነባሩ የማራቶን አሰልጣኝ ዶክተር ይልማ በርታስ ምን ይሉ ይሆን?

የናቴ መቀነት ዘንድሮ አልሰራም አናብስት እናቶቻችን እህቶቻችንማ ወርቅ አንበሽብሽውናል::

የብራዚሉም ኦሎምፒክ ነገ ይደርሳል:: ኬንያ ተፎካካሪያችን የሚባለው ወሬም አልሰራም:: እነሱ ቤጂንግ 14 ሜዳሊያ እኛ 7 እነሱ ሎንዶን 11? ሜዳሊያ እኛ 7 ቀድመውናል::

በጊዜ ስልጠናውንም የአትሌቶች አመራረጥ መስፈርቱንም መላ ቢሉ ይሻላል:: ነገ 7 ሜዳሊያም አይኖርም::
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ቀደምት » Mon Aug 13, 2012 12:28 am

እንሰት wrote:እንደምን ሰነበታችሁ ወገኖች

አትሌቶቹ አይመስሉኝም አሳፋሪዎቹ ያሰለፋቸው የማኔጅመትንት ክፍል ነው:: ኃይሌን እድል ቢሰጡት ኖሮ እስከ 10ኛ ድረስ መጨረስ የሚያቅተው ስፖርተኛ አልነበረም:: የስፖርት ተንታኞች እንዳሉት የተሰላፊነት ብቃት መለኪያቸው የተምታታና ግራ የሆነ ነበር::

በአሰልጣኞቹ በኩልም አንዳንዶቹ አትሌቶች እንዴት ከሜዳሊያ ውጪ እንደሆኑ ስናይ በጣም ኢለመንታሪ የሆኑ የውድድር ስልቶችን የሚሰጣቸው እንደሌለ ነው የሚያረጋግጠው:: ካሸነፉትም ውስጥ ቢሆን ለምሣሌ መሠረት ስታስረዳ ለድል የበቃችበትን ታክቲክ የነገራት ባለቤቷ መሆኑን ነው የተናገረችው:: ስለዚህ አትሌቶቻችን በግል ባላቸው ችሎታና የማሸነፍ እልህ ከሚያደርጉት ጥረት በስተቀር በስልጠና በኩል የሚደረግላቸው እገዛ ብዙ ችግር ያለበት ይመስላል::
ቀደምት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 761
Joined: Mon Feb 20, 2006 3:22 pm

Postby ተድላ ሀይሉ » Mon Aug 13, 2012 4:05 am

ሰላም የአትሌቲክስ ስፖርት አፍቃሪዎች :-

የሎንዶን ኦሎምፒክ ተጠናቀቀ :: እንግዲህ ቀሪው ታሪኩ ብቻ ነው :: በዚህ የኦሎምፒክ ውድድር ከወራት በፊት በተደጋጋሚ ሥናነሣው የነበረው ሥጋት ሥጋና ደም ለብሶ : ሕይወት ዘርቶ በገሃድ ለመታዬት በቅቷል :: በሙሥና በተዘፈቁና አገር በሚንዱ ሹሞች የተሞላው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ እንዲሁም ዋና አስፈፃሚ የሆነው የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሹሞች አሣፋሪ የሆነውን የሥራ ፍሬያቸውን ሰብስበዋል ::

በዚህ የኦሎምፒክ መድረክ ቆራጥና ጠንካራ ሴት አትሌቶች ባይኖሩን ኖሮ በአጠቃላዩ የሜዳሊያ ሠንጠረዥ በ1 የብር እና በ1 የነሐስ ሜዳሊያ ብቻ እንቀር ነበር :: ከዚህ ያነሠ ውጤት የተገኘው ደግሞ ያኔ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ስፖርት አዲስ በነበረበት ዘመን ከ40 ዓመታት በፊት በተደረገው በሙኒክ ኦሎምፒክ 2 የነሐስ ሜዳሊያዎች ባገኘንበት ጊዜ ነበር (ምንጭ:- ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ ጨዋታዎች ያስመዘገበችው ውጤት::)::

የሚችሉትን ያህል ጥረት ላደረጉት አትሌቶቻችን ትልቅ አክብሮት አለኝ :: የኦሎምፒክ ኮሚቴ እና የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሹሞች ግን ከሾማቸው አካል ጋር በአንድ ላይ ለፍርድ የሚቀርቡበት ጊዜ ሩቅ አይደለም ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ሞፊቲ » Mon Aug 13, 2012 5:25 am

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን::

እንዳየነው ኦሎምፒክ በርግጥም ተጠናቋል::ቀደም ሲል በነበሩን ውድድሮችም የተለየያዩ አስተያየቶች ሲስተናገዱ
ተመሳሳይ ሀሳቦች እንዳይሆኑ በመስጋት ማለት የፈለኩትን ሀሳብ ወይም ስሜት ለመጋራት ውስጤ ቀዝቃዛ ነበር::
አሁንም መናገር ቢያስፈልግ እንኳ ቀደም ካሉት ግዜያቶችና
ከተነሱት ቆራጥ ሀሳቦች ውጪ የምለው ነገር አይኖርም::
ከቤጂንግ ማግስት ጀምሮ የዲያጉን የአለም ሻምፒዮና አልፈን እስካሁን ሊደረጉ ስለሚገባቸው
እርምቶች ተወርቷል;ተነግሯል;ተሰምቷል::
ግን ምንም እርምት አልነበረም::አሁንም እኔ በራሴ የምስማማበት ነገር ለዚች ለበቃናት ድል እንኳ የሁጤቱ ባለቤቶች የሀገር ፍቅር የተላበሱትና ሀላፊነት የወደቀባቸው ብርቅ አትሌቶቻችን እንጂ
በእርግጥም የአሰልጣኞቻችን ወይም የቴክኒክ ክፍሉና የስፖርት ባለስልጣኖች እጅ ሳይሆን ጣት እንኳ እንደማይኖርበት እርግጥ የሆነ ነው::
በጣም የሚገርመው ከ 25 ሚሊየን ብር በላይ ለ ኦሎምፒክ ልኡካኑ የተዋጣ በቂ ገንዘብ እያለ ተጠባባቂ አትሌቶችን ይዞ መሄድ
ያቃተው አመራር እና በስፓርተኞቹ ቁጥር ልክ ለሽርሽር የተጓዙ አላስፈላጊ ሰዎችን በሎንዶን ኦሎምፒክ አንደላቆ ያኖረ
ቡድን ቢኖር የኢትዮጵያ ልኡክ ብቻ እንደነበር ምስክር የሚያስፈልገው አይመስለኝም::
ምንም መናገር አያስፈልግም::ነገም ብራዚል ላይ ይሄው ነው የሚገጥመን::እመኑኝ ..እዛ ቤት የሚጠራና የሚሻሻል
ነገር አይኖርም::
አትሌቶቻችን ግን በራሳቸው ጥረት አንዲትም ትሁን ሁለቴ ባንዲራችንን ከፍ ማረጋቸው አይቀርም!!!

ቸር እንሰንብት!!!
ሞፊቲ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 837
Joined: Thu Dec 15, 2005 9:18 pm

Postby ወርቅነች » Mon Aug 13, 2012 12:21 pm

በሙሥና በተዘፈቁና አገር በሚንዱ ሹሞች የተሞላው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ እንዲሁም ዋና አስፈፃሚ የሆነው የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሹሞች አሣፋሪ የሆነውን የሥራ ፍሬያቸውን ሰብስበዋል ::

ቅቅቅቅቅ..ፈዛዛው ችግሩ በሙሰና የተዘፈቁና አገር በሚነዱት ሹሞች ሳይሆን የአትሌቶቹ የቲም ዎርክ ጉድለት መሆኑን በሴቶችም ሆነ በወንዶቹም ጎልቶ የታየ ሰለሆነ ዳውላ ፈልጋህን አቁም :P አንዴ ውቃው የሚሉት ዋርካዊ ዳውላ ነህ ብሎ ሲያወራ ሰምቼው ነበር ዳሩ ግን አህያ ሆነህ አግኝቼሀለሁ ትለሀለች ጀሚላ ከቸርችል ጎዳና :lol: :lol: :lol:

ተድላ ሀይሉ wrote:ሰላም የአትሌቲክስ ስፖርት አፍቃሪዎች :-

የሎንዶን ኦሎምፒክ ተጠናቀቀ :: እንግዲህ ቀሪው ታሪኩ ብቻ ነው :: በዚህ የኦሎምፒክ ውድድር ከወራት በፊት በተደጋጋሚ ሥናነሣው የነበረው ሥጋት ሥጋና ደም ለብሶ : ሕይወት ዘርቶ በገሃድ ለመታዬት በቅቷል :: በሙሥና በተዘፈቁና አገር በሚንዱ ሹሞች የተሞላው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ እንዲሁም ዋና አስፈፃሚ የሆነው የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሹሞች አሣፋሪ የሆነውን የሥራ ፍሬያቸውን ሰብስበዋል ::

በዚህ የኦሎምፒክ መድረክ ቆራጥና ጠንካራ ሴት አትሌቶች ባይኖሩን ኖሮ በአጠቃላዩ የሜዳሊያ ሠንጠረዥ በ1 የብር እና በ1 የነሐስ ሜዳሊያ ብቻ እንቀር ነበር :: ከዚህ ያነሠ ውጤት የተገኘው ደግሞ ያኔ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ስፖርት አዲስ በነበረበት ዘመን ከ40 ዓመታት በፊት በተደረገው በሙኒክ ኦሎምፒክ 2 የነሐስ ሜዳሊያዎች ባገኘንበት ጊዜ ነበር (ምንጭ:- ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ ጨዋታዎች ያስመዘገበችው ውጤት::)::

የሚችሉትን ያህል ጥረት ላደረጉት አትሌቶቻችን ትልቅ አክብሮት አለኝ :: የኦሎምፒክ ኮሚቴ እና የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሹሞች ግን ከሾማቸው አካል ጋር በአንድ ላይ ለፍርድ የሚቀርቡበት ጊዜ ሩቅ አይደለም ::

ተድላ
ወርቅነች
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 967
Joined: Sun Oct 03, 2010 10:05 am

Postby ሞፊቲ » Wed Aug 15, 2012 6:20 pm

ሰላም ለዚህ ቤት ይህን::

እስከመቼ ከባለድል አትሌቶች ጀርባ ተደብቀው ያጭበረብራሉ?
August 14, 2012
By Fisseha Tegegn

አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን ሀላፊዎችና የፕሬስ አታሼ ከባለድል አትሌቶች ጀርባ ተደብቀው እስከመቼ ያጭበረብራሉ?

“ፊሽ – የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን ፕሬስ አታሼን አነጋግርና አትሌቶችን ለቃለ መጠይቅ የምናገኝበትን መንገድ እስቲ አመቻች” የሚለው ጥያቄ የመጣው የ2012 የለንደን ኦሎምፒክ ጨዋታዎች የኦሎምፒክ ዜና አገልግሎት (Olympic News Service) ውስጥ በምሰራበት ወቅት የአትሌቲክስ ቡድን ስፖርት ባለሞያ ከሆነው ባልደረባዬ ነበር። የዜና አገልግሎቱ ስራውን ሲጀምር ወደለንደን የሚመጡት የኦሎምፒክ ቡድኖች ህዝብ ግንኙነት ወይም ፕሬስ አታሼ ሀላፊዎች የብሪታኒያ ተንቀሳቃሽ ስልኮች ቁጥር መረጃ ከሀላፊዎቹ ስም አጠገብ የሰፈረበት የመገናኛ ብዙሀን መመሪያ አነስተኛ መጽሀፍ ተሰጥቶን ነበር። ታዲያ ባልደረቦቼ የእኔን የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪነት እና ቀድሞ ኢትዮጵያ ውስጥ በነበረኝ የሬድዮ ጋዜጠኝነት ሞያን ከግምት ውስጥ በማስገባት የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድንን በተመለከተ መረጃዎችን የማሰባሰብ ሀላፊነቱን ለእኔ ሰጡኝ። ባልደረቦቼ ያላወቁት ነገር ቢኖር ከኢትዮጵያ የመንግስት ድርጅቶች መረጃ ለማግኘት ከመሞከር ይልቅ ነዳጅ ማውጣት የሚቀል መሆኑን ነው።

የመጀመሪያው ስራዬ የነበረው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን ፕሬስ አታሼ ማን እንደሆነ መፈለግ ነበር። ከጥቂት አሰሳዎች በኋላ ገበያው ታከለ የሚል ስም የተሰጠን የመገናኛ ብዙሀን የግንኙነት መረጃ መመሪያ ላይ ተጽፎ አየሁ። ገበያው ታከለ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የገንዘብ ያዥ እንደነበሩ ስለማውቅ ‘እውነት ከሰውዬው ጋር ትክክለኛ የሚዲያ ስራ መስራት ይቻላለን?’ የሚል ጥያቄ እንዳነሳ አስገደደኝ። ሌላኛው የአእምሮዬ ክፍል ደግሞ ‘ምንአልባት ነገሮች ተለውጠውና ተሻሽለው ይሆናል’ የሚል ሀሳብ አነሳና በሁለት ሀሳብ ተወጥሬ ለማንኛውም ሰውዬውን ላግኛቸውና የግንኙነት መስመራችንን ላመቻች በሚል ስልክ ለመደወል ስዘጋጅ ከገበያው ታከለ ስም አጠገብ የስልክ ቁጥር እንደሌለ ተገነዘብኩ። ቀጣዩ አማራጭ የነበረው ከሀገርቤት የሚመጡ ጋዜጠኞችን በመገናኘት የአቶ ገበያው ታከለን አድራሻ ለማግኘት መሞከር ቢሆንም የቀድሞ ባልደረቦቼም ተመሳሳይ ችግር እንደገጠማቸው ለማወቅ ሰከንዶች አልወሰደበኝም። በሮች ሁሉ ዝግ የነበሩ ከመሆናቸው በተጨማሪ ከኦሎምፒክ ስታዲዬሙ አጠገብ የሚገኘው የአትሌቶች መለማመጃ ቦታ ላይ ያገኘሁት የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ቡድን አባል ስለቡድኑ አንዳንድ ዝግጅቶች እንዲነግረኝ ስጠይቀው “ለቃለምልልስ ከላይ ትእዛዝ ማግኘት አለብኝ” የሚል መልስ ከመስጠቱ በተጨማሪ “የፕሬስ አታሼውን ስልክ ቁጥር ነገ አመጣልሀለሁ” ብሎኝ ከተለያየን በኋላ እንደተደበቀኝ የለንደን ኦሎምፒክ ተጠናቀቀ።

በኦሎምፒኩ የፕሬስ አታሼው ቀዳሚ ስራ ከመገናኛ ብዙሀን ጋር ግንኙነቶችን በመፍጥር ለሚመለከተው አንባቢ፣ ተመልካችና አድማጭ ስለሚፈልጋቸው ሰዎች መረጃዎችን እንዲያገኝ ማስቻል ቢሆንም ገበያው ታከለ ግን አይደለም የኢትዮጵያ አትሌቶችን ሊያገናኝ እራሱም ሳይገናኝ ቀርቷል።

የለንደን ኦሎምፒክ ከመጀመሩ ቀደም ብሎ ወደከተማዋ የመጡት የተለያዩ ሀገሮች ኦሎምፒክ ቡድኖች ፕሬስ አታሼዎች የሚሰሩትን ውጤታማ እንቅስቃሴ አንባቢዎቼ ብታዩ ኖሮ በኢትዮጵያ ቡድን ሀላፊዎች እጅግ በጣም ነበር የምታፍሩት። የአሜሪካ ቡድን ፕሬስ አታሼ “በዚህ ቀን ሎሎ ጆንስ፣ ሳኒያ ሪቻርድስ፣ አሊሰን ፊሊክስ፣ አሽተን ኢተን እና ትሬይ ሀርዲ ጋዜጣዊ መግለጫ ይኖራቸዋል” የሚል መልእክት ለመገናኛ ብዙሀን ሲበትኑ፤ የቦትስዋናው ወኪል ደግሞ አማንትሌ ሞንሾ መቼ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚኖራት የሚያሳይ መረጃ ይልክልናል። ጀርመናዊኑ አትሌቶች መቼ ለጋዜጠኞች ክፍት የሆነ የልምምድ ጊዜ እንደሚኖራቸው ፕሬስ አታሼው ሲነግራችሁ፣ የደቡብ አፍሪካው ፕሬስ አታሼ ደግሞ “ኦስካር ፒስቶሪዬስ በዚህ ቀን እና በዚህ ቦታ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል” ይላችኋል። የጣሊያን ፕሬስ አታሼ ከሀገሩ አትሌቶች ጋር የተገናኙ መረጃዎችን በተለያዩ መንገዶች ሲልክላችሁ፣ የኬኒያው ደግሞ ዴቪድ ሩዲሻ፣ ቪቪዬን ቼሪዮት እና ሳሊ ኪፕዬጎ ከጋዜጠኞች ጋር ውስን ደቂቃዎች ያሉት የቃለመጠይቅ ፕሮግራም እንደሚያደርጉ አስቀድሞ ይነግራችኋል። ገበያው ታከለ እና ባልደረቦቹ ታዲያ ይሄንን ከማድረግ ይልቅ በየሀበሻ ሬስቶራንቱ እየዙሩ ክትፏቸውን መብላት፣ ቸኮሌት መሰብሰብ፣ ፌስታል ሞልቶ ወደአረፉበት ቦታ አምሽቶ መግባት እና ወደሀገራቸው ሲመለሱ አትሌቶቹ ለፍተው ባገኙት ውጤት ምክንያት የሚሸለማቸውን ነገር ምን እንደሆነ ማሰላሰል ነበር ስራቸው።

አትሌቶች ከተወዳደሩ በኋላ ወደመልበሻ ቤታቸው ከመመለሳቸው በፊታ የሚያልፉት የመገናኛ ብዙሀን በቆሙበት “ሚክስድ ዞን” ተብሎ በሚጠራው ቦታ ሲሆን ይህ ቦታ ጋዜጠኞች አትሌቶቹን ስለውድድሩና ስለብቃታቸው የሚጠይቁበት ቦታ ነው። እዚህ ቦታ ላይ አትሌቶቹ ለጥያቄ መልስ ያለምስጠት መብት ቢኖራቸውም አብዛኞቹ ለማውራት ፈቃደኞች ናቸው፤ በተለይ ለየሀገሮቻቸው መገናኛ ብዙሀን። ሚክስድ ዞኑ መግቢያ ላይ ውድድር ያላቸው አትሌቶች ሀገሮች ፕሬስ አታሼዎችን ማየት የተለመደ ነው። የእነሱ ቀዳሚ ስራ አትሌቶቻቸው ልክ ውድድራቸውን እንደጨረሱ ወደሚክስድ ዙኑ ሲመጡ አትሌቶቹን ይዘው የሀገሮቻቸው መገናኛ ብዙሀን ጋዜጠኞች ወደቆሙበት ቦታ መውሰድ እና ለሌላ ቋንቋ ተናጋሪ መገናኛ ብዙሀን የአትሌቱ አስተርጓሚ ሆኖ ማገልገል ሲሆን፣ እኔም ሆንኩ የሌላ ሀገር ጋዜጠኛ አትሌቶቹን ለማናገር ከፈለገ ሊያቆሙለትም ዝግጁ ናቸው። ታዲያ እዛ ሚክስድ ዞን ያልነበረና በጭራሽም ያልታየ የፕሬስ አታሼ ቢኖር የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን ተወካዩ ገበያው ታከለ ብቻ ነበር ብል እያጋነንኩ አይደለም።

ለነገሩ ኢትዮጵያዊያኑ አትሌቶች በአስተሳሰባቸው ከአብዛኞቹ የቡድኑ ሀላፊዎች ፍጹም በተሻለ መልኩ የሰለጥኑ እና ቅኖች በመሆናቸው ወደ ሚክስድ ዞኑ ሲመጡ ለጥያቂ ሳስቆማቸው ሁሉም ለመቆም ፈቃደኞች እና ደስተኞች ነበሩ። ነገር ግን እንግሊዘኛ ቋንቋን አቀላጥፈው መናገር የሚችሉት እጅግ በጣም ጥቂቶች በመሆናቸው ፕሬስ አታሼያቸው አጠገባቸው አለመኖሩ በአስተርጓሚነት እንኳን እንዳይረዱ አድርጓቸዋል። ኢትዮጵያዊያኖቹ ታላላቅ አትሌቶች ለእኔ ሲቆሙ ያዩ የኦሎምፒክ ዜና አገልግሎት ባልደረቦቼ እጅግ በጣም ከመገረማቸው በተጨማሪ የሌሎች አገሮች ጋዜጠኞች ልክ አትሌቶቹን ከጠየኩ በኋላ ቶሎ ወደቢሮ ገብቼ የተናገሩትን የመረጃ መሰብሰቢያው ውስጥ ከማስገባቴ በፊት እንድተረጉምላቸው ይጠይቁኝ እና መረጃዎቹን በዚህ መልኩ ያገኙ ነበር። በተለይ ከሴቶች 5 ሺህ ሜትር ማጣሪያ በኋላ በመጀመሪያው የማጣሪያ ቡድን ውስጥ የነበሩት ጥሩነሽ ዲባባ እና መሰረት ደፋር አብረው ወደ ሚክስድ ዞኑ ሲመጡ “መቼም የደከማቸው ሯጮችን በተራ ለመጠየቅ በሚል ብዙ አላቆማቸውም” ብዬ እያሰብኩ እንዳለ ሁለቱም ፈቃደኛ መሆናቸውን ከተለመደው በእጅ የመጨባበጥ ሰላምታችን በኋል ገልጸውልኝ ፊት ለፊቴ የነበረችው መሰረትን እየጠየኩ ጥሩነሽ ቆማ ስትጠብቀኝ “ምን አለ የቡድኑ ሀላፊዎችም እንደእንዚህ አትሌቶች ቅኖች በሆኑ” የሚለው ሀሳብ ውስጤ ይመላለስ ነበር። አጠገቤ የነበሩት የሮይተርስ፣ ኤ.ኤፍ.ፒ እና ኤ.ፒ ጋዜጠኞች የፎቶ ካሜራቸውን አውጥተው ሁለቱን ድንቅ አትሌቶች ያነሱ ነበር። ልክ ሁለቱንም ቃለምልልስ አድርጌ እንደጨረስኩ የጋዜጠኞቹ የመጀመሪያ አስተያየት “እንዴት ትእግስተኞች ናቸው” የሚል ነበር። ታዲያ ቃለምልልሱን በፍጥነት እየተረጎምኩላቸው እያለ አንደኛው ጋዜጠኛ “ፕሬስ አታሼያቸው የታለ?” የሚል ጥያቄ አነሳ። ‘እዚህ ድርሽ ብሎ አያውቅም’ የሚል መልስ ሥሰጥ፤ እነሱም ሊያገኙት ሞክረው እንዳልተሳካላቸውና ቢያንስ ሚክስድ ዞን እንኳን ሲመጣ እናገኘዋለን ብለው ጠብቀው እንደነበር ነገሩኝ።

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን ፕሬስ አታሼ ሚክስድ ዞን ውስጥ ብቻ ሳይሆን በአንዱም ኢትዮጵያዊያን የሜዳሊያ ባለቤቶች በተገኙባቸው የፕሬስ/ሚዲያ ኮንፍረንሶች ላይ አልተገኙም። ኢትዮጵያዊያን የሜዳሊያ ባለቤቶች ያደረጓቸውን ፕሬስ ኮንፍረንሶች ላይ በሙሉ ስገኝ የመጀመሪያው ስራዬ ገበያው ታከለን መፈለግ ነበርና ሰውዬው የትም ሊታዩ አልቻሉም። “የት ናቸው?” ምን አልባት ከኦሎምፒክ ስታዲዬሙ ይልቅ በርካታ የሀበሻ ምግቤቶች በሚገኙባቸው የለንደን ጎዳናዎች ካሊዶኒያን ሮድ፣ ፊንስበሪ ፓርክ እና ሸፐርድስቡሽ አካባቢ እያውደለደሉ ይሆናል የሚል ነበር ለራሴ የምሰጠው መልስ።

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን ሀላፊዎች እና የሀገሪቷ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በድንቆቹ አትሌቶች ብርታትና ጥንካሬ በሚገኙ ውጤቶች ጀርባ ተደብቀው እያጭበረበሩ ሲኖሩ ቆይተዋል። አትሌቶች ላይ ጫናን እና ጭንቀትን ከመፍጠር እና የህዝብን ገንዘብ ከማጭበርበር ውጪ ሌላ ስራ የላቸውም። የኦሎምፒክ ስታዲዬሞች የሚያስገባቸው አጋጣሚው ተመቻችቶላቸው እያለ የሀገራቸው አትሌቶች ያደረጓቸውን ውድድሮች በሙሉ ቁጭ ብለው የተመለከቱ የኢትዮጵያ ቡድን ሀላፊዎች እጅግ በጣም ጥቂቶች ናቸው። ልክ የፍጻሜ ውድድሮች ሲኖሩ ብቻ ስታዲዬም በመገኘት የፉገራ አርበኝነታቸውን ባንዲራ በማውለብለብ ለማሳየት ከመሞከር ውጪ አትሌቶቻቸው ድጋፍ ሲጠይቋቸው “አለሁ” ብለው አይገኙም ነበር።

ወደሀገራቸው ሲመለሱ ከባለድሎቹ አትሌቶች ቀድመው ከአውሮፕላኑ ደረታቸውን በመንፋት የቦሌ አውሮፕላን ማረፊያን መሬትን የሚረግጡት እነዚህ ስራ-ፈት የቡድን ሀላፊዎችና ከህዝብ በተዋጣ ገንዘብ የተገዙ የለንደን እቃዎች የወጠሯቸው ሻንጣዎቻቸው ናቸው። ከዛ በኋላ ያለምንም እፍረት “የገንዘቡና የተለያዩ ሽልማቶች ተካፋይ ካልሆንን” ይላሉ። እነዚህ የማያፍሩ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን ሀላፊዎች እና አባላት ከጋዜጠኞች “ለምንድነው የተጠበቀውን ያህል ሜዳሊያዎች ያላገኘነው?” የሚል ጥያቄ ከቀረበላቸው ያለምንም እፍረት ወጣቶቹን እና አቅማቸው በሚችለው መጠን የለፉ አትሌቶችን ከመተቸት ወደኋላ እንደማይሉ አልጠራጠርም፤ ምክንያቱም ከዚህ በፊት አድርገውታልና።
ሞፊቲ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 837
Joined: Thu Dec 15, 2005 9:18 pm

Postby ተድላ ሀይሉ » Wed Aug 15, 2012 9:30 pm

ሰላም ሞፊቲ :-

'የኦሎምፒክ ኮሚቴ' ተብየው ሹሞች ድርጊት ከተራ የአሜሪካን ግቢ ኪስ አውላቂዎች ሥርቆት ጋር ሲወዳደር እንኳን እጅግ የወረደ ነው :: እነርሱ እና ልጆቻቸው ነገ በየትኛው አገር ሊኖሩ እንዳሠቡ አይገባኝም :: በሥደት ዓለም ለመንከራተት ቢያስቡ እንኳን አሣፋሪ ታሪካቸው ተከትሏቸው እንደሚሄድ የማይገነዘቡ ድንጋይ-ራሶች ናቸው:: በወንዶች የ10 ሺህ : 5ሺህ እና ማራቶን ውድድሮች ሜዳሊያ ያጣንበትን የሤራ ድር እንዴት እንደጎነጎኑት ጉዳቸው ውሎ አድሮ ይፋ መሆኑ አይቀርም ::

ቸር እንሠንብት ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

ሀይሌ ብራዚል 2008

Postby እንሰት » Tue Aug 28, 2012 7:40 pm

ሰላም ለዋርካ ኦሎምፒክ ዜና ተከታታዮች
ይቺን አዝናኝ ንባብ ላካፍላችሁ ብዬ አመጣሁዋት

Brazil 2016. Haile Are you serious?
These days a journalist wrote from London that, with his perennial smile on your face, you never really know if Haile Gebreselassie is serious or joking. Has a sense of humor, no doubt, but not usually frivolous when it comes to his career. is case is the journalist who said that he attended a meeting of the athlete with a small group of journalists in which he reiterated that his life is still the athletics and are considering competing in the Olympic Games in Brazil in 2016, with 43 years. And you still thinking to go into politics when I leave the shoes.

http://www.mamaetiopia.blogspot.ca/
FRIDAY, AUGUST 3, 2012 Google translation
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Re: ሀይሌ ብራዚል 2008

Postby ተድላ ሀይሉ » Wed Aug 29, 2012 7:41 pm

እንሰት wrote:ሰላም ለዋርካ ኦሎምፒክ ዜና ተከታታዮች
ይቺን አዝናኝ ንባብ ላካፍላችሁ ብዬ አመጣሁዋት

Brazil 2016. Haile Are you serious?
These days a journalist wrote from London that, with his perennial smile on your face, you never really know if Haile Gebreselassie is serious or joking. Has a sense of humor, no doubt, but not usually frivolous when it comes to his career. is case is the journalist who said that he attended a meeting of the athlete with a small group of journalists in which he reiterated that his life is still the athletics and are considering competing in the Olympic Games in Brazil in 2016, with 43 years. And you still thinking to go into politics when I leave the shoes.

http://www.mamaetiopia.blogspot.ca/
FRIDAY, AUGUST 3, 2012 Google translation

ሰላም እንሰት :-

እ.ኤ.አ. በ2016 በሬኦ-ዴ-ጃኔሮ (ብራዚል) የሚካሄደው 31ኛው ኦሎምፒያድ ገና በዓለም እና በተለይም በኢትዮጵያችንም ላይ ብዙ ተዓምር ከታዬ በኋላ የሚመጣ ዝግጅት ነው :: ሌላውን እንተወውና ኃይሌ ገብረሥላሤ እስከዚያ ድረስ በምን ሁኔታ ላይ ሊቆይ እንደሚችል መገመት ከባድ ነው :: እርሱ [ኃይሌ] ምኞቱን ሊገልፅ ይችላል : ሊመጣ የሚችለውን ነገር የሚያውቀው ሁሉን አዋቂው ፈጣሪ ብቻ ነው :: ትዕቢት ወጥሮት አልታዬውም እንጂ ኃይሌ ከወያኔዎች ጋር አብሮ እንጣጥ : እንጣጥ ማለት ማለት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍቅር ርቆታል :: ስለሆነም የወያኔን ባለሥልጣኖች ድጋፍ ተማምኖና የእነርሱ ጫማ ላሽ ሆኖ ሊያገኝ የሞከረው ዝናና ክብር ሁሉ የማይጨበጥ ጉም ሲሆንበት እያየ እንዲህ ከአቅሙ በላይ ባይንጠራራ ጥሩ ነው ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby geremew » Mon Sep 03, 2012 10:32 pm

ተድላ ሀይሉ wrote:ሰላም ሞፊቲ :-

'የኦሎምፒክ ኮሚቴ' ተብየው ሹሞች ድርጊት ከተራ የአሜሪካን ግቢ ኪስ አውላቂዎች ሥርቆት ጋር ሲወዳደር እንኳን እጅግ የወረደ ነው :: እነርሱ እና ልጆቻቸው ነገ በየትኛው አገር ሊኖሩ እንዳሠቡ አይገባኝም :: በሥደት ዓለም ለመንከራተት ቢያስቡ እንኳን አሣፋሪ ታሪካቸው ተከትሏቸው እንደሚሄድ የማይገነዘቡ ድንጋይ-ራሶች ናቸው:: በወንዶች የ10 ሺህ : 5ሺህ እና ማራቶን ውድድሮች ሜዳሊያ ያጣንበትን የሤራ ድር እንዴት እንደጎነጎኑት ጉዳቸው ውሎ አድሮ ይፋ መሆኑ አይቀርም ::

ቸር እንሠንብት ::

ተድላ

Everybody is innocent until they are proven guilty. ይላሉ በዲሞክራሲን የሚያምኑ ማህበረሰቦች:: ማራቶን ለመጨረሻ ጊዜ ወርቅ ሜዳልያ ያገኘነው በገዛኅኝ አበራ በሲድኒ ኦሊምፒክ ነበር:: ከሲድኒ በፊት ሌላ 3 ኦሊምፒኮች ተሳትፈን ነበር:: ባርሴሎና : አትላንታ : ሞስኮ (በነምሩጽ ዘመን) ነገር ግን በማራቶን ወርቅ አላገኘንም:: ከሲድኒ በሁዋላ አቴንስ እና ቤጂንግ ተሳትፈናል:: ወርቅ አልነበረንም:: ነሀስ ነበር ያገኘነው:: ዘንድሮ ማግኘት ሲገባን ወንጀለኞቹ አሳጡን ያልከውን ከነማስረጃው እስቲ አቅርብልን::

5,000 ሜ ወርቅ ያገኘነው ከሞስኮ ቀጥሎ ሲድኒ ላይ በሚሊዮን ወልዴ እና ቤጂንግ ላይ በቀነኒሳ ነበር:: ሌላ ታሪክ የለንም:: አሁንም ወርቅ ይገባን ነበር ግን አሳጡን ያልክበትን ማስረጃ አቅርብልን::

10,000ሜ ሚኒማ አምዋልተው በወቅታዊ አቅዋማቸው አሁን ከተሰለፉት ልጆች ይሻሉ ነበር የምትላቸው ካሉ እስቲ ጥቀስልን እና እንወያይ:: ማስረጃን በማስረጃ መመከት ይቻላል:: ከንቱ እና ጭፍን ጥላቻን ግን እንዴት?

ለወደፊቱ ማስረጃዎችን ብቻ አቅርብ እና ፍርዱን ላንባቢ ተው:: አንተን ወደድምዳሜ ያደረሰህን ማስረጃ ግን አትንፈገን:: በሰለጠኑት አለም ያሉ ሰዎች የሚከተሉት ስነምግባር ይሄ ነው::
geremew
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 285
Joined: Tue Dec 28, 2004 8:43 pm
Location: united states

Postby ተድላ ሀይሉ » Fri Sep 07, 2012 8:34 pm

ሰላም ለአትሌቲክስ ስፖርት አፍቃሪዎች :-

ዘንድሮ በኢትዮጵያ ምድር እና በኢትዮጵያውያን ያልተጠበቁ ውጤቶችን እናያለን :: ኢትዮጵያ በፓራኦሎምፒክ አትሌቶችን ማሣተፍ ከጀመረችበት ከሜክሲኮው የ1960 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. 1968) ጀምሮ ምንም ዓይነት ሜዳሊያ አሸንፋ አታውቅም ነበር::
ምንጭ:- Official Website of the Paralympic Movement: Ethiopia's Results until 2008.::

በዘንድሮው የሎንዶን ፓራኦሎምፒክ ወንድዬ ፍቅሬ እንደልቡ በ1,500 ሜትር ርቀት የሩጫ ውድድር የብር ሜዳሊያ በማግኘቱ አገራችንም ከ44 ዓመታት ተሣትፎ በኋላ በሜዳሊያ ሠንጠረዥ ላይ ለመመዝገብ አብቅቷታል ::
ምንጭ:- London Paralympics 2012: Men's 1500m - T46 Results.

እስከዛሬ ድረስ በፓራኦሎምፒክ ኢትዮጵያን ወክለው የተሣተፉ አትሌቶች ቁጥር በጣም ጥቂት ነው (7 ብቻ ናቸው):: እነርሱም የሚከተሉት ናቸው:-
  1 ..... አብርሃም ኃብቴ (እ.ኤ.አ. በ1968 : 1976 እና 1980 በጦርና መዶሻ ውርወራ ውድድሮች)

  2 ..... ንጋቱ (እ.ኤ.አ. በ1968 :- በመዶሻና ጦር ውርወራዎች እንዲሁም በተሽከርካሪ ወንበር ተቀምጦ መጋለብ ውድድሮች)

  3 ..... ኪሮስ ተክሌ ረዴ (እ.ኤ.አ. በ2004 እና 2012 :- በ100 እና 200 ሜትር ርቀት የሩጫ ውድድሮች)

  4 ..... ፈረጅ መሐመድ ሂቡ (እ.ኤ.አ. በ2008 :- በ1,500 ሜትር ርቀት የሩጫ ውድድር)

  5 ..... ተስፋዓለም ገብሩ ከበደ (እ.ኤ.አ. በ2008 እና 2012 :- በ800 እና 1,500 ሜትር ርቀት የሩጫ ውድድሮች)

  6 ..... የንጉሥ ደሴ አዘናው (እ.ኤ.አ. በ2012 :- የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት የፓራኦሎምፒክ ተወዳዳሪ : በ100 : 200 እና 400 ሜትር ርቀት የሩጫ ውድድሮች)

  7 ..... ወንድዬ ፍቅሬ እንደልቡ (እ.ኤ.አ. በ2012 :- የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የፓራኦሎምፒክ ባለሜዳሊያ : በ1,500 ሜትር ርቀት የሩጫ ውድድር)

ምንጮች:-
1 ..... በፓራኦሎምፒክ ታሪክ ኢትዮጵያን ወክለው የተሣተፉ አትሌቶች ዝርዝር::

2 ..... በሎንዶን ፓራኦሎምፒክ የሚሣተፉ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ዝርዝር::

በሴቶች ምድብ ብቸኛ ኢትዮጵያዊቷ ተወዳዳሪ የንጉሥ ነገ ቅዳሜ በ400 ሜትር የፍፃሜ ውድድር ይጠብቃታል :: እስካሁን በማጣሪያ ውድድሮች ያስመዘገበችው ሰዓት ለሜዳሊያ ተፎካካሪነት የሚያበቃት ባይሆንም ነገ በምታደርገው ውድድር አንድ ተዓምር ታሣየን ይሆናል ::

መልካም ዕድል ለየንጉሥ !

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ወርቅነች » Mon Sep 10, 2012 9:45 am

እነርሱ እና ልጆቻቸው ነገ በየትኛው አገር ሊኖሩ እንዳሠቡ አይገባኝም ::

ሀገራቸው ነው እሚኖሩት እንዳንተ ሀገር ጥለው አይፈርጥጡም.... ቢበዛ ጀግኖች ናቸውና ባገራቸው ጫካ ይኖራሉ... ፈዛዛው ቄሰ ነህና አይገባህም ትላላእች ጀሚላ ከቸርችል ጎዳና :lol: :lol: :lol:

ተድላ ሀይሉ wrote:ሰላም ሞፊቲ :-

'የኦሎምፒክ ኮሚቴ' ተብየው ሹሞች ድርጊት ከተራ የአሜሪካን ግቢ ኪስ አውላቂዎች ሥርቆት ጋር ሲወዳደር እንኳን እጅግ የወረደ ነው :: እነርሱ እና ልጆቻቸው ነገ በየትኛው አገር ሊኖሩ እንዳሠቡ አይገባኝም :: በሥደት ዓለም ለመንከራተት ቢያስቡ እንኳን አሣፋሪ ታሪካቸው ተከትሏቸው እንደሚሄድ የማይገነዘቡ ድንጋይ-ራሶች ናቸው:: በወንዶች የ10 ሺህ : 5ሺህ እና ማራቶን ውድድሮች ሜዳሊያ ያጣንበትን የሤራ ድር እንዴት እንደጎነጎኑት ጉዳቸው ውሎ አድሮ ይፋ መሆኑ አይቀርም ::

ቸር እንሠንብት ::

ተድላ
ወርቅነች
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 967
Joined: Sun Oct 03, 2010 10:05 am

Re: ሀይሌ ብራዚል 2008

Postby ወርቅነች » Mon Sep 10, 2012 9:51 am

ፈዛዛው ቄስ እስፖርተኛ... ከ ኢትዮጵያዊያን ጀኖች ጋር ችግርህ ምን ድነው.... የግድ እኮ ቄሶች መሆን የለባቸው ትለሀለች ጀሚላ ከቸርችል ጎዳና :lol: :lol: :lol:

ተድላ ሀይሉ wrote:
እንሰት wrote:ሰላም ለዋርካ ኦሎምፒክ ዜና ተከታታዮች
ይቺን አዝናኝ ንባብ ላካፍላችሁ ብዬ አመጣሁዋት

Brazil 2016. Haile Are you serious?
These days a journalist wrote from London that, with his perennial smile on your face, you never really know if Haile Gebreselassie is serious or joking. Has a sense of humor, no doubt, but not usually frivolous when it comes to his career. is case is the journalist who said that he attended a meeting of the athlete with a small group of journalists in which he reiterated that his life is still the athletics and are considering competing in the Olympic Games in Brazil in 2016, with 43 years. And you still thinking to go into politics when I leave the shoes.

http://www.mamaetiopia.blogspot.ca/
FRIDAY, AUGUST 3, 2012 Google translation

ሰላም እንሰት :-

እ.ኤ.አ. በ2016 በሬኦ-ዴ-ጃኔሮ (ብራዚል) የሚካሄደው 31ኛው ኦሎምፒያድ ገና በዓለም እና በተለይም በኢትዮጵያችንም ላይ ብዙ ተዓምር ከታዬ በኋላ የሚመጣ ዝግጅት ነው :: ሌላውን እንተወውና ኃይሌ ገብረሥላሤ እስከዚያ ድረስ በምን ሁኔታ ላይ ሊቆይ እንደሚችል መገመት ከባድ ነው :: እርሱ [ኃይሌ] ምኞቱን ሊገልፅ ይችላል : ሊመጣ የሚችለውን ነገር የሚያውቀው ሁሉን አዋቂው ፈጣሪ ብቻ ነው :: ትዕቢት ወጥሮት አልታዬውም እንጂ ኃይሌ ከወያኔዎች ጋር አብሮ እንጣጥ : እንጣጥ ማለት ማለት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍቅር ርቆታል :: ስለሆነም የወያኔን ባለሥልጣኖች ድጋፍ ተማምኖና የእነርሱ ጫማ ላሽ ሆኖ ሊያገኝ የሞከረው ዝናና ክብር ሁሉ የማይጨበጥ ጉም ሲሆንበት እያየ እንዲህ ከአቅሙ በላይ ባይንጠራራ ጥሩ ነው ::

ተድላ
ወርቅነች
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 967
Joined: Sun Oct 03, 2010 10:05 am

PreviousNext

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest