የኢትዮጵያ የአትሌቲክስ:- 2005 የተስፋ ዘመን

ስፖርት - Sport related topics

Postby ተድላ ሀይሉ » Mon Sep 10, 2012 8:49 pm

ሰላም ነገደ-አርበኛ ዘዋርካ :-

በመገባደድ ላይ የሚገኘው 2004 ዓ.ም. ካሠሙን አስገራሚና አሣዛኝ ጉዳዮች አንዱ ታዋቂው አትሌት የኃይሌ ገብረሥላሤ ለበላዔሰቡ ለለገሠ [መለስ] ዜናዊ ያሠማው የዘቀጠ የሐዘን መግለጫ ነበር :: ስለዚህ 2004 ዓ.ም. የምንሠናበተው በኃይሌ ገብረሥላሤ ላይ በቀረበው በሚከተለው የሠላ ትችት ይሆናል::

ምንጭ:- ECADF, Aug 27, 2012. Ethiopia: Comment on Haile Gebrselassie.

ፈጣሪ ሆይ በጭንቅላታቸው ሣይሆን በእግራቸው ከሚያስቡ ስፖርተኞች ሠውረን :: መጪው የ2005 ዓ.ም. በስፖርቱ መስክ ለኅሊናቸውና ለአገር ታማኝ የሆኑ አዳዲስ አትሌቶችን የምናይበት ዘመን ይሁንልን ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Mon Sep 17, 2012 12:40 pm

ሰላም ለአትሌቲክስ ስፖርት አፍቃሪዎች :-

ከሎንዶን ኦሎምፒክ መልስ ጥሩነሽ ዲባባ የ2005 ዓ.ም. የመጀመሪያውን ውድድሯን በአሸናፊነት አሃዱ ብላለች :: ትላንት እሑድ በኒውካስል (እንግሊዝ) በተደረገ ውድድር ጥሩነሽ ከዚህ በፊት ኃያልነቷን ባሥመሠከረችባቸው የረዥም ርቀት የትራክ ውድድሮች ብቻ ሣይሆን በግማሽ ማራቶን ሩጫም የወደፊት ተስፋዋን የሚያለመለም ውጤት አስመዝግባለች:: በዚህ ውድድር የአገሯ ልጅና ያለፈው የሎንዶን ማራቶን ባለ ወርቅ ሜዳሊያ ቲኪ ገላና በ3ኛነት አጠናቃለች ::

ምንጭ:- IAAF, Sunday, September 16, 2012. Dibaba and Kipsang take Great North Run victories.

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Tue Oct 09, 2012 3:57 pm

ሰላም ለአትሌቲክስ ስፖርት አፍቃሪዎች :-

የጀመርነው 2005 ዓ.ም. በአትሌቲክስ መሥክ ለኢትዮጵያውያን አትሌቶች የታላላቅ ድሎች የብሥራት ዘመን ሆኗል :: እሑድ ዕለት በቺጋጎ በየዓመቱ በሚደረገው የታላቁ የቺጋጎ የወርቅ ደረጃ ማራቶን ውድድር የወንዶቹን ምድብ ፀጋዬ ከበደ የሥፍራውን የርቀቱን ሬኮርድ በመሥበር አሸንፏል - የገባበት ሰዓት 2:04:38:: ከፀጋዬ እግር ሥር ተከታትለው የገቡት የአገሩ ልጆች ሌሊሣ ፈይሣና ጥላሁን ረጋሣ ናቸው :: በቦስተን ማራቶን ታሪክ በወንዶች ምድብ ከአንድ አገር ተወዳዳሪዎች መካከል ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተከታትሎ በመግባት ለማሸነፍ እነ ፀጋዬ የመጀመሪያዎቹ በመሆን አርማውን ከፍ አድርገዋል :: በሴቶች ምድብ ደግሞ አፀደ ባይሣ የቦስተንን ማራቶን ለሦሥት ተከታታይ ጊዜ በማሸነፍና በዓለም በሴቶች ማራቶን ሁለተኛውን ሁለተኛውን ፈጣን ሰዓት ያስመዘገበችው ሊሊያ ሹቡኮቫን በመቅደም አሸናፊ ሆናለች ::

ምንጭ:-
1 ..... Jon Gugala for the IAAF, Sunday, October 07, 2012. Course record for Kebede, Baysa dethrones Shobukhova – Chicago Marathon report.

2 ..... Chicago Marathon Men's Results.

3 ...... Chicago Women's Marathon Results.

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ወርቅነች » Tue Oct 16, 2012 9:12 am

ፈጣሪ ሆይ በጭንቅላታቸው ሣይሆን በእግራቸው ከሚያስቡ ስፖርተኞች ሠውረን :: መጪው የ2005 ዓ.ም. በስፖርቱ መስክ ለኅሊናቸውና ለአገር ታማኝ የሆኑ አዳዲስ አትሌቶችን የምናይበት ዘመን ይሁንልን ::

ፈጣሪ ሆይ ደብተራዎች ጭንቅላታቸውን ተጠቅመው እንዳይሰሩ ምነው እንዲህ አርገህ ፈጠርካቸው አሁንም እኔ የምልህ ጌታ ድንጋይ አድርጋቸው በ2005 ዓ.ም እትዮጵያን ከደብተራዎች ነጻ አርጋት ደብተራ የረጋጣት መሬት ትደርቃለች ትላልች ጀሚላ ከቸርችል ጎዳና :lol: :lol:ተድላ ሀይሉ wrote:ሰላም ነገደ-አርበኛ ዘዋርካ :-

በመገባደድ ላይ የሚገኘው 2004 ዓ.ም. ካሠሙን አስገራሚና አሣዛኝ ጉዳዮች አንዱ ታዋቂው አትሌት የኃይሌ ገብረሥላሤ ለበላዔሰቡ ለለገሠ [መለስ] ዜናዊ ያሠማው የዘቀጠ የሐዘን መግለጫ ነበር :: ስለዚህ 2004 ዓ.ም. የምንሠናበተው በኃይሌ ገብረሥላሤ ላይ በቀረበው በሚከተለው የሠላ ትችት ይሆናል::

ምንጭ:- ECADF, Aug 27, 2012. Ethiopia: Comment on Haile Gebrselassie.

ፈጣሪ ሆይ በጭንቅላታቸው ሣይሆን በእግራቸው ከሚያስቡ ስፖርተኞች ሠውረን :: መጪው የ2005 ዓ.ም. በስፖርቱ መስክ ለኅሊናቸውና ለአገር ታማኝ የሆኑ አዳዲስ አትሌቶችን የምናይበት ዘመን ይሁንልን ::

ተድላ
ወርቅነች
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 967
Joined: Sun Oct 03, 2010 10:05 am

Postby ከንቲባ. » Tue Oct 16, 2012 11:30 am

ወርቅነች አንደበትህን የተከራየው ሰይጣን መች ነው የሚለቅህ ?አንድም ቀን መልካም ነገር ተናግረህ የማታቅበትን አፍህን ማለቴ ነው::
ክፋቱ ሰይጣን ግን ወንዳገረዶች (ጌዮች) የራሱ ስለሆኑ አይለቃቸውም:
በስመ አብ ብለናል ሰይጣን ከዚህ ቤት ጥፋ !
Ethiopia tikdem
ከንቲባ.
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 50
Joined: Fri Jan 08, 2010 10:12 pm
Location: Roma

Postby ወርቅነች » Thu Oct 18, 2012 8:15 am

ከንቲባው የት ነው ያደርከው :lol: ሸንት ቤት ነው እንዴ ያደርከው እንዴት ሰይጣን ይለቀሀል :lol: .ራሰህ ስይጣን መሆንህ እወቀው ለመሆኑ ሸንት ቤቱን መጠህ ጨርሰሀዋል እንዴ :lol: ለዚህ ነው እንዴ አመድ የነፋብህ ሰይጣኖች እያገላበጡህ ነው ለካሰ ሸንት ቤት ውሰጥ :lol: :lol: ..

ወርቅነች አንደበትህን የተከራየው ሰይጣን መች ነው የሚለቅህ ?

ያንተን ብጤ ና ደብተራዎችን ነው ሰይጣን አንደበታችሁን የያዘው...ወርቅነች እንደሆነ መላክት ሰለሆነች ስይጣን አይጠጋትም.... ሰይጣን እንዲለቃችሁ ከፈለጋችሁ የወርቅነሸን ሸንት ጠጡ አንተን አዛባ :lol: :lol:

አንድም ቀን መልካም ነገር ተናግረህ የማታቅበትን አፍህን ማለቴ ነው::

አፌ እንደሆነ ማር ነው የሚተፋው ያንተ አፍ ግን አር ነው የሚተፋው :lol:

ክፋቱ ሰይጣን ግን ወንዳገረዶች (ጌዮች) የራሱ ስለሆኑ አይለቃቸውም:

እውነትህን ነው ያንተ ጎደኞት ሰለሆኑ ነው...ሁሌ ይከታተሉሀል ጠብቃቸው..እኔ የሚመሰለኝ ወደፊት ቡሼ ሳይወትፉልህ አይቀሩም :lol: :lol: :lol:

በስመ አብ ብለናል ሰይጣን ከዚህ ቤት ጥፋ

አንተ እያለህ ሰይጣን ከየት ይጥፋል..ትልቁ ሰይጣን አንተ ነህ ያልታወቀብህ ትለሀለች ጀሚላ ከቸርችል ጎዳና :lol: :lol:

ከንቲባ. wrote:ወርቅነች አንደበትህን የተከራየው ሰይጣን መች ነው የሚለቅህ ?አንድም ቀን መልካም ነገር ተናግረህ የማታቅበትን አፍህን ማለቴ ነው::
ክፋቱ ሰይጣን ግን ወንዳገረዶች (ጌዮች) የራሱ ስለሆኑ አይለቃቸውም:
በስመ አብ ብለናል ሰይጣን ከዚህ ቤት ጥፋ !
ወርቅነች
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 967
Joined: Sun Oct 03, 2010 10:05 am

Postby ተድላ ሀይሉ » Mon Oct 29, 2012 3:51 pm

ሰኞ ኅዳር 19 ቀን 2005 ዓ.ም.

ሰላም የአትሌቲክስ ስፖርት አፍቃሪዎች

ከረዥም ርቀት የሩጫ ውድድሮች መካከል የ10,000 ሜትር የዙር ሩጫ ውድድርን አውሮፓውያን እና አሜሪካውያን የሩጫ ውድድር አዘጋጆች ተባብረው ከውድድሮች ዝርዝር ውጭ ለማድረግ ባካሄዱት የተቀነባበረ ሤራ ምክንያት ውጤቱ እንደምናየው ሆኗል :: በዚህም ምክንያት በዚህ ርቀት ታዋቂና አይበገሬ የነበሩት ኢትዮጵያውያን እና ኬንያውያን ሯጮች ተቆጣጥረው ከኖሩት የሩጫ ውድድር ወጣ እያሉ ወደ ሌሎች የሩጫ ውድድር ዓይነቶች እንዲሣቡ ተገድደዋል :: ለዚህም ይመስላል ባለፈው በመስከረም ወር ጥሩነሽ ዲባባ በኒውካስል (እንግሊዝ) በግማሽ ማራቶን ውድድር የተካፈለችው:: በዚያ ውድድር ጥሩነሽ አዲሱን የውድድር ዘመኗን በአሸናፊነት አሃዱ ብላ ጀምራለች:: ትላንት ደግሞ እንደ ጥሩነሽ የ10,000 ሜትር የዙር ሩጫ ምርጥ አትሌት የሆነችው መሠለች መልካሙ አንድ ደረጃ ከፍ ብላ በፍራንክፈርት ማራቶን ለመጀመሪያ ጊዜ ተወዳድራ ያለፈውን የሎንዶንን ኦሎምፒክ ባለወርቅ ሜዳሊያ ቲኪ ገላናን ሣይቀር በመቅደም በጥሩ ሰዓት 1ኛ ሆናለች :: መሠለች አምና በማሚቱ ደስቃ ተይዞ የነበረውን የሥፍራውን የሴቶች የማራቶች ሬኮርድ (2:21:59) በ58 ሴኮንድ አሻሽላለች:: ዘንድሮ ማሚቱ ከኬንያዊቷ ጆርጂና ሮኖ ተከትላ 3ኛ ሆናለች::

ምንጭ:- Pat Butcher (organisers for the IAAF). Sunday, October 28, 2012. Patience pays for Makau in Frankfurt, debut win for Melkamu.

በሌላ የማራቶን ውድድር በቬኒስ (ጣሊያን) በተደረገ ፉክክር እመቤት ኢታ የአገሯን ልጆች ሐሊማ ሐሰንን እና ፋንቱ ኢተቻን አስከትላ አሸንፋለች:: እመቤት የገባችበት ሰዓት 2:38:11 ነበር::

ምንጭ:- Diego Sampaolo for the IAAF, Monday, October 29, 2012. Kisang and Bedada prevail over difficult conditions in Venice.

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ሞፊቲ » Thu Nov 01, 2012 8:15 pm

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን::

ጃፓናዊያን ሴቶች በፍቅር ያበዱለት የማራቶን ጀግና
October 31, 2012By Fisseha Tegegn

Podcast: Play in new window
Download

የማራቶኑ ንጉስ አበበ ቢቂላ የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያዎችን ባሸነፈባቸው ሮም እና ቶኪዮ ኦሎምፒክ እንዲሁም በሜክሲኮ ኦሎምፒክ አብሮት ከሮጠው ማሞ ወልዴ ጋር ተቃቅፈው
በአንድ ወቅት ጃፓናውያን ሴቶች አብረውት ለመሆን በቁጥር አንድነት የሚመኙት ጎረምሳ ነበር። እሱ ያለበትን ሁኔታ በንቃት ይከታተላሉ፣ ባዩት ቁጥር በደስታ ይጮሀሉ። ስለ ብራድ ፒት ወይም ዴቪድ ቤካም እያወራሁ አይደለም፤ ስለ አበበ ቢቂላ እንጂ። እ.አ.አ በ1961 ዓ.ም በጃፓኗ ኦሳካ ከተማ በተካሄደው የማራቶን ውድድር ላይ ተሳትፎ በአሸናፊነት ካጠናቀቀ በኋላ በጃፓናውያን ሴቶች ልብ ውስጥ መግባት የጀመረው አበበ ቢቂላ በ1964ቱ የቶኪዮ ኦሎምፒክ ለመሳተፍ ወደጃፓን ሲሄድ በሰውነት አቋማቸው ከሚበልጡትና በእድሜ ከሱ ከሚያንሱት ፈርጣማና ጡንቸኛ አሜሪካዊን የኦሎምፒኩ ተሳታፊዎች ቦክሰኛው ጆን ፍሬዠርና ዋናተኛው ዶናልድ አርቱር ሾላንደር ይልቅ የሀገሪቷን ሴቶች ቀልብና ልብ መስረቅ ችሏል።

አበበና አሰልጣኙ ኦኒ ኒስከነን
እ.አ.አ በ1932 ዓ.ም ሰሜን ሸዋ ጃቶ ውስጥ የተወለደው አበበ፤ ከእናቱ ጋር ለመኖር በሚል የትውልድ ቦታውን ትቶ ወደ አዲስ አበባ ከሄደ በኋላ በቅድሚያ ከከተማዋ የወደደው ነግር ቢኖር ጥርት ያለና ስርአት ያለው የደንብ ልብስ የሚለብሱት የአጼ ኃይለ ስላሴ ክቡር ዘበኛ አባሎች ነው። እናም በ1956 ዓ.ም አበበ ክቡር ዘበኛን ተቀልቀለ። ክቡር ዘበኛ ውስጥ በጥሩ ዋናተኛነት፣ በጎበዝ ፈረስ ጋላቢነትና በገና ተጨዋችነት ከመታወቁ በስተቀር በሩጫ ማንም ግምት አይሰጠውም ነበር።

በጊዜው የአበበ ቢቂላ አሰልጣኝ የነበሩት ሲውዲናዊው ኦኒ ኒስከነን አበበን አስመልክተው ሲናገሩ “ከ1959 ዓ.ም በፊት አበበን በጭራሽ አላውቀውም ነበር። የኦሎምፒክ የመጀመሪያ ማጣሪያ ውድድር ላይ ሶስተኛ ቢወጣም የሩጫ ብቃቱ አሳማኝ አልነበረም። ምክንያቱም እጆቹ እዛና እዚህ ሲወራጩ ማየትና የሚዛን አጠባበቅ ችግር አበበ ላይ ማየት የተለመደ በመሆኑ አንዳንድ ጊዜ እጮህበት ነበር። በርግጥ መስዋእትነት መክፈልንና ጠንክሮ መስራትን ከእሱ ጋር የሚስተካከል ማንም አልነበረም። ታላቁ አበበን የፈጠረው እራሱ አበበ ነው። እኔ ለእርሱ ታላቅነት ምንም አስተውጾ አላበረከትኩም” አሉ።

ወደሮም ለ1960ው ኦሎምፒክ ከመሄዱ በፊት ከኢትዮጵያ ውጪ አንድም ውድድር ያላደረገውና ሩጫን ዘግይቶ የጀመረው አበበ፤ ለኦሎምፒኩም የመጀመሪያ ተመራጭ አልነበረም። የመጀመሪያ ተመራጭ የነበረው ዋሚ ቢራቱ ጉዳት ደረሰበትና አበበ ዋሚን ተክቶ ቡድኑን ተቀላቀለና ጉዞ ወደ ሮም ሆነ።

የኦሎምፒኩ የማራቶን ውድድር ከመጀመሩ ሁለት ሰአታት በፊት አበበ ሌላ አስገራሚ ክስተት አጋጣመው። በውድድሩ ለአትሌቶች ጫማዎችን ሲያቀርብ የነበረው አዲዳስ በቂ ጫማዎች ስላልነበሩት ለአበበ እግር ይበቃሉ ተብለው የተገመቱ የተለያዩ ጫማዎች ቢሞከሩም ሊገኙ አልቻሉም፤ የተቃረቡትም ያበረከቱት አስተዋጾ ቢኖር አለመመቸትና እግሩን ማቁሰል ነበር። ሀገሩ በልምምድ ወቅት በአብዛኛው ያለጫማ ይሮጥ የነበረው አበበም “በባዶ እግሬ እሮጣለሁ” የሚል ሀሳብ አቀረበና አሰልጣኙም በሀሳቡ ተስማሙ።

ውድድሩ ተጀመሮ የርቀቱን ሩብ ያህል እንደሮጡ ከመሪዎቹ በትንሽ የሚርቀው አበበ ፍጥነቱን ጨመረና ቤልጄማዊው ኦውሬል ቫን ዴን ሬሽኽ፣ ብሪታኒያዊው አርቱር ኬሊ እና ሞሮኳዊው ራህዲ ቤን አብዲሰላም የሚገኙበትን የመሪዎቹን ቡድን ተቀላቀለ። የ42.196 ኪሎ ሜትሩን ግማሽ ካለፉ በኋላ አበበና ራህዲ ከሌሎች ተገንጥለው በመውጣት መሪነቱን ለብቻቸው ተቆጣጠሩ።

አበበ በሮም ጎዳናዎች ላይ በባዶ እግሩ ሲገሰግስ
ውድድሩ ከመጀመሩ በፊት አሰልጣኝ ኦነኒስከን የአበበ ተፎካካሪ 26 ቁጥር የተጻፈበት መለያ የሚለብሰው ሞሮኳዊው ራህዲ ሊሆን እንደሚችል በመገንዘባቸው ለአበበ “26 ቁጥር የለበሰው አትሌት ላይ ትኩረትህን አድርግ” የሚል መለክት አስተላልፈው ነበር። በሚገርም ሁኔታ ታዲያ ውድድሩ ከተጀመረ በኋላ ራህዲ የለበሰው 26 ቁጥር ሳይሆን 10 ሺህ ሜትር ሲሮጥ የለበሰው 185 ቁጥር የተጻፈበት ማሊያን መሆኑ ነው። ውድድሩ እየተጋመሰ ሲሄድ አበበ ወደ ግራና ቀኝ፣ እንዲሁም ወደኋላ ዘውር እያለ 26 ቁጥር የለበሰ ሲፈልግ ሊያየውና ሊያገኘው አልቻለም። ለካ ራህዲ አብሮት ከአበበ ቢቂላ አጠገብ በመሪነት እየሮጠ የነበረው 185 ቁጥር የለበሰው አትሌት ሆኗል።

ማራቶኑ ሊጠናቀቅ ሶስት ኪሎ ሜትሮች ያህል እስኪቀሩት ድረስ አበበና ራህዲ ጎን ለጎን አብረው ከሮጡ በኋላ፤ አበበ ፍጥነቱን ጨመረና ራህዲን በ200 ሜትሮች ያህል በመቅደም አንደኛ ወጥቶ ለኢትዮጵያና ለጥቁር አፍሪካ በኦሎምፒክ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኘ። በስታዲዬሙ የተገኘውን ተመልካችና አለም አቀፉን መገነኛ ብዙሃን ያስገረመው ሌሎቹ ሯጮች ሲያለክልኩና ጥቂቶቹም ራሳቸውን መቆጣጠር አቅቷቸው ሲውድቁ፤ በባዶ እግሩ ማራቶኑን የሮጠው አበበ ስታዲየሙ ውስጥ ሲያሟሙቅና ሰውነቱን ሲያፍታታ ማየታቸው ነበር።

ከውድድሩ በኋላ የአበበ በባዶ እግር ሮጦ ማሸነፍ ያስገረማቸው ጋዜጠኞች አሰልጣኝ ኦኒ ኒስካነን ሁኔታውን እንዲያብራሩላቸው ሲጠይቋቸው “በባዶ እግሩ መሮጡ ምንም አያስገርምም። ልምምድ ላይ በባዶ እግሩ ሲሮጥ አንድ ደቂቃን በ98 ርምጃዎች ሲሸፍን፤ በጫማ ሲሮጥ ደግሞ ደቂቃን በ96 ርምጃዎች ሲሸፍን አይቻለሁ። እናም ብዙ ልዩነት አይኖረውም ብዬ ስላሰብኩ በባዶ እግሩ ተመችቶት እንዲሮጥ ወሰንን። ምን አልባት ጫማ በኮረኮንቻማ ቦታዎች ላይ ሊጠቅምህ ይችላል፤ ብዙ እግርህን ሊያቆስሉህ የሚችሉ ነገሮች ይኖራሉና። የሮም ጎዳናዎች ግን እንደዛ አይደሉም። ስለዚህ አበበ ‘በባዶ እግሬ ልሩጥና ለአፍሪካ ታሪክ እንስራ አለኝ፤ እኔም ተስማማሁ።’ በጣም አርበኝነት የሚሰማው ሰው ነው” የሚል ነበር መልሳቸው።

የአበበ ቢቂላ ወርቅ ሜዳሊያና የሞሮኳዊው ራህዲ ብር ሜዳሊያ በወደፊት የኦሎምፒክና የተለያዩ አለም አቀፍ ውድድሮች ላይ አፍሪካዊያን ሩጫን በበላይነት ሊቆጣጠሩ እንደሚችሉ ምልክት የሰጠ ነበር።

ቁጥር አንዱ አበበ ቢቂላ
በሮም የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ከሆነ በኋላ በግሪክ፣ ጃፓንና ቼኮዝሎቫኪያ ላይ የተካሄዱ የማራቶን ውድድሮችን ያሸነፈው አበበ ቢቂላ እስከ ቶኪዮ ኦሎምፒክ መቃረቢያ ድረስ ያሉትን ጊዜያት በጥሩ ሁኔታ አላሰለፈም ማለት ይቻላል። የአበበን በጥሩ አቁም ላይ አለመገኘት የተገነዘቡት በርካታ የዘርፉ ባለሞያዎችና መገናኛ ብዙሀን ከኦሎምፒኩ መጀመር አራት ወር ቀደም ብሎ አዲስ የአለም የማራቶን ክብረወሰንን 2 ሰአት ከ13 ደቂቃ 55 ሰከንድ በሆነ ጊዜ ያስመዘገበው ብሪታኒያዊው ቤንጃሚን ባሲል ሄትሊ የቶኪዮው ኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ይሆናል የሚል ግምት ሰጡ። ይባስ ብሎ አበበ ጠንካራ ልምምዶችን በማድረግ ድክመቱን ለማካካስ ጥረት እያደረገ እያለ የትርፍ አንጀት ህመም አጋጠመውና ኦሎምፒኩ ከመጀመሩ ከአራት እስከ ስድስት ሳምንታት ቀደም ብሎ የቀዶ ጥገና ህክምና በማድረጉ ልምምዱ ተሰናከለ። ሆኖም ልክ ሀኪሞቹ ለአሰልጣኝ ኒስከነን እንደነገሯቸው አበበ በቶሎ አገገመና የቀዶ ጥገና ህክምናውን ካደረገ ከሁለት ሳምንታት ቆይታ በኋላ ልምምድ መስራት ጀመረ።

ለኦሎምፒኩ ማሟሟቂያና ማጣሪያ እንዲሆን አዲስ አበባ ውስጥ በተካሄደ የማራቶን ሩጫ ውድድር ማሞ ወልዴን በአንድ ሰከንድ ቀድሞ አንደኛ የወጣው አበበ ያስመዘገበው 2 ሰአት ከ16 ደቂቃ 18.8 ሰከንድ የሆነ ጊዜ ምን አልባትም ሁለተኛ የወርቅ ሜዳሊያውን ለማግኘት እድል እንዳለው ያሳየ ነበር።

64 ተወዳዳሪዎች በተሳተፉበት የ1964ቱ የቶኪዮ ኦሎምፒክ የማራቶን ውድድር ሻምበል አበበ ቢቂላ ርቀቱን ለማጠናቀቅ 10 ኪሎ ሜትሮች እስኪቀሩ ድረስ መሪነቱን በተረጋጋ ሁኔታ ለመያዝ ቻለ። ብዙም ሳይቆይ ታዲያ አበበ ከሌሎቹ አትሌቶች ተገንጥሎ ወጣና ለብቻው መሪነቱን በመቆጣጠር ብሪታኒያዊውን የአለም ክብረወሰን ባለቤት ባሲል ሄትሊን በአራት ደቂቃዎች ልዩነት ቀድሞ 2 ሰአት ከ12 ደቂቃ 12.2 ሰከንድ በሆነ ጊዜ የአለም ክብረወሰንን በመስበር አንደኛ ወጥቶ ለሁለተኛ ጊዜ የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ሆነ።

አሶሺዬትድ ፕሬስ ሁኔታውን እንዲህ በማለት ነበር የዘገበው። “አበበ ተከታዩን በሰፊ ልዩነት በመቅደም ወደቶኪዮ ስታዲዬም ከገባ በኋላ ሁለት እጆቹን ወደላይ አንስቶ የመጨረሻውን ገመድ በደረቱ በጥሶ አንደኛ ወጣ። ከዛም ወደሜዳው መሀል ገባና ሳሩ ላይ በጀርባው ተኝቶ እግሮቹን ልክ የብስክሌት ፔዳል እንደሚመታ ሰው አይነት እያወራጨ በማፍታታት ስታዲዬም የተገኘው ተመልካችን አስደመመ።”

ከቶኪዮው ወርቅ ሜዳሊያ በኋላ አበበ በ1965 ዓ.ም ወደ ጃፓን በመመለስ የኦትሱ ማራቶንን አሸነፈ። በቀጣዩ አመት ደግሞ የባርሴሎናው ዛራውትዝ ማራቶንን በማሸነፍ ለ1968ቱ የሜክሲኮ ኦሎምፒክ ዝግጁ መሆኑን ለአለም አረጋገጠ። የ36 አመቱ አበበ ቢቂላ ለሶስተኛ ተከታታይ ጊዜ የማራቶን ወርቅ ሜዳሊያን ለማግኘት ሜክሲኮ ሲገባ በጥሩ አቋም ላይ ይገኝ ነበር። እሱ እራሱ በጊዜው በሰጠው አስተያየት “በጣም በጥሩ አቋም ላይ ስለምገኝ አሸንፋለሁ ብዬ እጠብቃለሁ። ነገር ግን በእንደዚህ አይነት ረጅም ሩጫ ያልተጠበቀ ነገር ሊፈጠር ይችላል። ያልተጠበቀው ተከስቶ የምሸነፍ ከሆነ በሀገሬ ልጆች ማሞ ወልዴና መርሀዊ ገብሩ ብሸነፍ ይሻለኛል” አለ።

የሜክሲኮው ኦሎምፒክ የማራቶን ውድድር ከመጀመሩ በፊት የነበሩት አራት ቀኖች ለአበበ መጥፎ ጊዜዎች ነበሩና ቀናቶቹን በህመም አሳለፈ። ውድድሩ ተጀምሮ 10 ኪሎ ሜትሮች ያህል እንደሮጠ ታላቁ አትሌት ውድድሩን አቋርጦ ወጣና ሌላው ኢትዮጵያዊ ማሞ ወልዴ አንደኛ በመውጣት አሸንፎ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት በመሆን ለኢትዮጵያ ሶስተኛውን ተከታታይ የማራቶን ወርቅ ሜዳሊያዎች አገኘ።

ቀስተኛው አቤ ለድል ሲያነጣጥር
መጋቢት ወር አጋማሽ 1969 ዓ.ም ላይ ይነዳት የነበረችው ፎልስቫገን መኪና ተገልብጣ አደጋ የደረሰበትና እግሮቹ ፓራላይዝ የሆኑት ሻምበል አበበ ቢቂላ፤ እነዛ የወርቅ ሜዳሊያዎች ያስገኙለት አስደናቂ እግሮቹን ወደስራ እንደገና ለመመለስ ህክምናዎችን ቢያደርግም የተደረገው የህክምና ጥረት ውጤታም አልሆነም። የመጨረሻ አማራጭና ተስፋ በሚል ወደእንግሊዝ ተወስዶ በስቶክ ማንዴቪል ሆስፒታል ህክምና ቢደረግለትም አበበን እንደገና ወደሩጫው መመለስ ሳይቻል ቀረ። ታዲያ ተስፋ የማይቆርጠው አበበ “መሮጥ አልችልም” ብሎ ከስፖርቱ አለም ከመራቅ ይልቅ ራሱን ወደቀስት ወርዋሪነት አሸጋገረና በእግሮቹ ያገኛቸውን ድሎች በእጆቹም ለመድገም ወሰነ። ምንም እንኳን እንዳሰበው ውጤታማ ባይሆንም በ1969 ዓ.ም በተካሄደው የዊልቸር ኦሎምፒክ በጀማሪ ቀስት ወርዋሪዎች ክፍል ተወዳድሮ ዘጠነኛ ደረጃን አግኝቶን ጨረሰ።

የሚያሳዝነው ነገር ታላቁ አበበ ቢቂላ ገና በ41 አመቱ በ1973 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለየና የአትሌቲክስ ስፖርት አፍቃሪው አለምና ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው አጡ።

በቅርቡ የአለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር መቶኛ አመት ምስረታን አስመልክቶ የስፖርቱ የታላቆች ታላቅ ተብለው ከተመረጡት ቀዳሚ 12 አትሌቶች መካከል ኢትዮጵያዊው ጀግና አበበ ቢቂላ አንዱ ነበር። ወረቀት ላይ ከተነደፉ እቅዶች ይልቅ የራሱን የተፈጥሮ የሩጫ ችሎታን እና ነገሮችን እንደየአመጣጣቸው የማንበብ ብቃቱን በመጠቀም ታላቅ ታሪክን የሰራው የአበበ ቢቂላን ሩጫዎች ያላዩ ታሪኩን ሲሰሙ የአፈታሪክ ያህል ነው የሚሆንባቸው። “ማራቶንን በባዶ እግሩ ሮጦ መጨረስ ብቻ ሳይሆን አንደኛ ወጥቶ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት የሆነ አትሌት አለ” ብሎ አንድ ሰው ጎዳና ላይ ላገኘው ሰው ቢያወራ “አብደሀል ወይ፤ ለምን የማይሆን ነገር ታወራለህ” ነው የሚባለው። አበበ ግን ተአምረኛ ነበርና አድርጎታል፤ ለሰሚ እውነት የማይመስል እውነትን ያውም በታላቁ ኦሎምፒክ ላይ ፈጽሟል።

ቸር እንሰንብት::
ሞፊቲ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 837
Joined: Thu Dec 15, 2005 9:18 pm

Postby ኮሎኔል » Fri Nov 02, 2012 1:33 am

ሞፊቲ እጅህ ይባረክ ጥሩ ታሪክ ነች
ኖሬ ያየሁትንም ታሪክ ማንበብ በጣም ደስ ይለኛል:
ባገራችን ካበበ ቢቂላ ቀጥሎ ትልቅ ታሪክ የሰራ ምሩጽ ይፍጠር ነው :
በሮማ የአለም ሻምፒዮና ላይ አብዲ ቢሌ በ1500 ሜትር ካሸነፈ በሁዋላ ከእንግዲህ ምሩጽ የለም ብሎ መናገሩ ትዝ ይለኛል::
ከዚያ በሁዋላ ግን እንዳለው ሳይሆን ከ3000 ሜትር አላለፈም::
በሞስኮ ኦሎምፒክ ትልቅ ታሪክ የሰራ ማኒንካ የሚባል የፊንላንድ ዜጋ ነው በ5000 ሜትር ሶስተኛ ሲወጣ በ10,000 ሜትር ሁለተኛ ወጣ:
ከሩጫው በሁዋላ ሲናገር አሰልጣኙ ኢትዮጵያን ተከትለህ ሩጥ እነሱ ሚያረጉትን ብቻ አርግ ማለቱን መስክሯል::
አሰልጣኙም ጥሩ ትንፋሽ ስለነበረው የመከርኩትን አድርጎ አሸነፈ ነው ያለው::
ኢትዮጵያን ተከትሎ መግባት ማሸነፍ ነበረ ::
ብዙ ብዙ አስታወስከኝ ሞፊቲ
የልጅ ተድላ ቁምነገረኛነት ላገሩ ውለታ ነው
አክባሪያችሁ ኮሎኔል
Ethiopia
ኮሎኔል
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 229
Joined: Fri Apr 07, 2006 7:19 pm
Location: zimbabwe

Postby ተድላ ሀይሉ » Fri Nov 02, 2012 1:44 am

ሞፊቲ wrote:ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን::

ጃፓናዊያን ሴቶች በፍቅር ያበዱለት የማራቶን ጀግና
October 31, 2012By Fisseha Tegegn

Podcast: Play in new window
Download

የማራቶኑ ንጉስ አበበ ቢቂላ የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያዎችን ባሸነፈባቸው ሮም እና ቶኪዮ ኦሎምፒክ እንዲሁም በሜክሲኮ ኦሎምፒክ አብሮት ከሮጠው ማሞ ወልዴ ጋር ተቃቅፈው
በአንድ ወቅት ጃፓናውያን ሴቶች አብረውት ለመሆን በቁጥር አንድነት የሚመኙት ጎረምሳ ነበር። እሱ ያለበትን ሁኔታ በንቃት ይከታተላሉ፣ ባዩት ቁጥር በደስታ ይጮሀሉ። ስለ ብራድ ፒት ወይም ዴቪድ ቤካም እያወራሁ አይደለም፤ ስለ አበበ ቢቂላ እንጂ። እ.አ.አ በ1961 ዓ.ም በጃፓኗ ኦሳካ ከተማ በተካሄደው የማራቶን ውድድር ላይ ተሳትፎ በአሸናፊነት ካጠናቀቀ በኋላ በጃፓናውያን ሴቶች ልብ ውስጥ መግባት የጀመረው አበበ ቢቂላ በ1964ቱ የቶኪዮ ኦሎምፒክ ለመሳተፍ ወደጃፓን ሲሄድ በሰውነት አቋማቸው ከሚበልጡትና በእድሜ ከሱ ከሚያንሱት ፈርጣማና ጡንቸኛ አሜሪካዊን የኦሎምፒኩ ተሳታፊዎች ቦክሰኛው ጆን ፍሬዠርና ዋናተኛው ዶናልድ አርቱር ሾላንደር ይልቅ የሀገሪቷን ሴቶች ቀልብና ልብ መስረቅ ችሏል።

አበበና አሰልጣኙ ኦኒ ኒስከነን
እ.አ.አ በ1932 ዓ.ም ሰሜን ሸዋ ጃቶ ውስጥ የተወለደው አበበ፤ ከእናቱ ጋር ለመኖር በሚል የትውልድ ቦታውን ትቶ ወደ አዲስ አበባ ከሄደ በኋላ በቅድሚያ ከከተማዋ የወደደው ነግር ቢኖር ጥርት ያለና ስርአት ያለው የደንብ ልብስ የሚለብሱት የአጼ ኃይለ ስላሴ ክቡር ዘበኛ አባሎች ነው። እናም በ1956 ዓ.ም አበበ ክቡር ዘበኛን ተቀልቀለ። ክቡር ዘበኛ ውስጥ በጥሩ ዋናተኛነት፣ በጎበዝ ፈረስ ጋላቢነትና በገና ተጨዋችነት ከመታወቁ በስተቀር በሩጫ ማንም ግምት አይሰጠውም ነበር።

በጊዜው የአበበ ቢቂላ አሰልጣኝ የነበሩት ሲውዲናዊው ኦኒ ኒስከነን አበበን አስመልክተው ሲናገሩ “ከ1959 ዓ.ም በፊት አበበን በጭራሽ አላውቀውም ነበር። የኦሎምፒክ የመጀመሪያ ማጣሪያ ውድድር ላይ ሶስተኛ ቢወጣም የሩጫ ብቃቱ አሳማኝ አልነበረም። ምክንያቱም እጆቹ እዛና እዚህ ሲወራጩ ማየትና የሚዛን አጠባበቅ ችግር አበበ ላይ ማየት የተለመደ በመሆኑ አንዳንድ ጊዜ እጮህበት ነበር። በርግጥ መስዋእትነት መክፈልንና ጠንክሮ መስራትን ከእሱ ጋር የሚስተካከል ማንም አልነበረም። ታላቁ አበበን የፈጠረው እራሱ አበበ ነው። እኔ ለእርሱ ታላቅነት ምንም አስተውጾ አላበረከትኩም” አሉ።

ወደሮም ለ1960ው ኦሎምፒክ ከመሄዱ በፊት ከኢትዮጵያ ውጪ አንድም ውድድር ያላደረገውና ሩጫን ዘግይቶ የጀመረው አበበ፤ ለኦሎምፒኩም የመጀመሪያ ተመራጭ አልነበረም። የመጀመሪያ ተመራጭ የነበረው ዋሚ ቢራቱ ጉዳት ደረሰበትና አበበ ዋሚን ተክቶ ቡድኑን ተቀላቀለና ጉዞ ወደ ሮም ሆነ።

የኦሎምፒኩ የማራቶን ውድድር ከመጀመሩ ሁለት ሰአታት በፊት አበበ ሌላ አስገራሚ ክስተት አጋጣመው። በውድድሩ ለአትሌቶች ጫማዎችን ሲያቀርብ የነበረው አዲዳስ በቂ ጫማዎች ስላልነበሩት ለአበበ እግር ይበቃሉ ተብለው የተገመቱ የተለያዩ ጫማዎች ቢሞከሩም ሊገኙ አልቻሉም፤ የተቃረቡትም ያበረከቱት አስተዋጾ ቢኖር አለመመቸትና እግሩን ማቁሰል ነበር። ሀገሩ በልምምድ ወቅት በአብዛኛው ያለጫማ ይሮጥ የነበረው አበበም “በባዶ እግሬ እሮጣለሁ” የሚል ሀሳብ አቀረበና አሰልጣኙም በሀሳቡ ተስማሙ።

ውድድሩ ተጀመሮ የርቀቱን ሩብ ያህል እንደሮጡ ከመሪዎቹ በትንሽ የሚርቀው አበበ ፍጥነቱን ጨመረና ቤልጄማዊው ኦውሬል ቫን ዴን ሬሽኽ፣ ብሪታኒያዊው አርቱር ኬሊ እና ሞሮኳዊው ራህዲ ቤን አብዲሰላም የሚገኙበትን የመሪዎቹን ቡድን ተቀላቀለ። የ42.196 ኪሎ ሜትሩን ግማሽ ካለፉ በኋላ አበበና ራህዲ ከሌሎች ተገንጥለው በመውጣት መሪነቱን ለብቻቸው ተቆጣጠሩ።

አበበ በሮም ጎዳናዎች ላይ በባዶ እግሩ ሲገሰግስ
ውድድሩ ከመጀመሩ በፊት አሰልጣኝ ኦነኒስከን የአበበ ተፎካካሪ 26 ቁጥር የተጻፈበት መለያ የሚለብሰው ሞሮኳዊው ራህዲ ሊሆን እንደሚችል በመገንዘባቸው ለአበበ “26 ቁጥር የለበሰው አትሌት ላይ ትኩረትህን አድርግ” የሚል መለክት አስተላልፈው ነበር። በሚገርም ሁኔታ ታዲያ ውድድሩ ከተጀመረ በኋላ ራህዲ የለበሰው 26 ቁጥር ሳይሆን 10 ሺህ ሜትር ሲሮጥ የለበሰው 185 ቁጥር የተጻፈበት ማሊያን መሆኑ ነው። ውድድሩ እየተጋመሰ ሲሄድ አበበ ወደ ግራና ቀኝ፣ እንዲሁም ወደኋላ ዘውር እያለ 26 ቁጥር የለበሰ ሲፈልግ ሊያየውና ሊያገኘው አልቻለም። ለካ ራህዲ አብሮት ከአበበ ቢቂላ አጠገብ በመሪነት እየሮጠ የነበረው 185 ቁጥር የለበሰው አትሌት ሆኗል።

ማራቶኑ ሊጠናቀቅ ሶስት ኪሎ ሜትሮች ያህል እስኪቀሩት ድረስ አበበና ራህዲ ጎን ለጎን አብረው ከሮጡ በኋላ፤ አበበ ፍጥነቱን ጨመረና ራህዲን በ200 ሜትሮች ያህል በመቅደም አንደኛ ወጥቶ ለኢትዮጵያና ለጥቁር አፍሪካ በኦሎምፒክ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኘ። በስታዲዬሙ የተገኘውን ተመልካችና አለም አቀፉን መገነኛ ብዙሃን ያስገረመው ሌሎቹ ሯጮች ሲያለክልኩና ጥቂቶቹም ራሳቸውን መቆጣጠር አቅቷቸው ሲውድቁ፤ በባዶ እግሩ ማራቶኑን የሮጠው አበበ ስታዲየሙ ውስጥ ሲያሟሙቅና ሰውነቱን ሲያፍታታ ማየታቸው ነበር።

ከውድድሩ በኋላ የአበበ በባዶ እግር ሮጦ ማሸነፍ ያስገረማቸው ጋዜጠኞች አሰልጣኝ ኦኒ ኒስካነን ሁኔታውን እንዲያብራሩላቸው ሲጠይቋቸው “በባዶ እግሩ መሮጡ ምንም አያስገርምም። ልምምድ ላይ በባዶ እግሩ ሲሮጥ አንድ ደቂቃን በ98 ርምጃዎች ሲሸፍን፤ በጫማ ሲሮጥ ደግሞ ደቂቃን በ96 ርምጃዎች ሲሸፍን አይቻለሁ። እናም ብዙ ልዩነት አይኖረውም ብዬ ስላሰብኩ በባዶ እግሩ ተመችቶት እንዲሮጥ ወሰንን። ምን አልባት ጫማ በኮረኮንቻማ ቦታዎች ላይ ሊጠቅምህ ይችላል፤ ብዙ እግርህን ሊያቆስሉህ የሚችሉ ነገሮች ይኖራሉና። የሮም ጎዳናዎች ግን እንደዛ አይደሉም። ስለዚህ አበበ ‘በባዶ እግሬ ልሩጥና ለአፍሪካ ታሪክ እንስራ አለኝ፤ እኔም ተስማማሁ።’ በጣም አርበኝነት የሚሰማው ሰው ነው” የሚል ነበር መልሳቸው።

የአበበ ቢቂላ ወርቅ ሜዳሊያና የሞሮኳዊው ራህዲ ብር ሜዳሊያ በወደፊት የኦሎምፒክና የተለያዩ አለም አቀፍ ውድድሮች ላይ አፍሪካዊያን ሩጫን በበላይነት ሊቆጣጠሩ እንደሚችሉ ምልክት የሰጠ ነበር።

ቁጥር አንዱ አበበ ቢቂላ
በሮም የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ከሆነ በኋላ በግሪክ፣ ጃፓንና ቼኮዝሎቫኪያ ላይ የተካሄዱ የማራቶን ውድድሮችን ያሸነፈው አበበ ቢቂላ እስከ ቶኪዮ ኦሎምፒክ መቃረቢያ ድረስ ያሉትን ጊዜያት በጥሩ ሁኔታ አላሰለፈም ማለት ይቻላል። የአበበን በጥሩ አቁም ላይ አለመገኘት የተገነዘቡት በርካታ የዘርፉ ባለሞያዎችና መገናኛ ብዙሀን ከኦሎምፒኩ መጀመር አራት ወር ቀደም ብሎ አዲስ የአለም የማራቶን ክብረወሰንን 2 ሰአት ከ13 ደቂቃ 55 ሰከንድ በሆነ ጊዜ ያስመዘገበው ብሪታኒያዊው ቤንጃሚን ባሲል ሄትሊ የቶኪዮው ኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ይሆናል የሚል ግምት ሰጡ። ይባስ ብሎ አበበ ጠንካራ ልምምዶችን በማድረግ ድክመቱን ለማካካስ ጥረት እያደረገ እያለ የትርፍ አንጀት ህመም አጋጠመውና ኦሎምፒኩ ከመጀመሩ ከአራት እስከ ስድስት ሳምንታት ቀደም ብሎ የቀዶ ጥገና ህክምና በማድረጉ ልምምዱ ተሰናከለ። ሆኖም ልክ ሀኪሞቹ ለአሰልጣኝ ኒስከነን እንደነገሯቸው አበበ በቶሎ አገገመና የቀዶ ጥገና ህክምናውን ካደረገ ከሁለት ሳምንታት ቆይታ በኋላ ልምምድ መስራት ጀመረ።

ለኦሎምፒኩ ማሟሟቂያና ማጣሪያ እንዲሆን አዲስ አበባ ውስጥ በተካሄደ የማራቶን ሩጫ ውድድር ማሞ ወልዴን በአንድ ሰከንድ ቀድሞ አንደኛ የወጣው አበበ ያስመዘገበው 2 ሰአት ከ16 ደቂቃ 18.8 ሰከንድ የሆነ ጊዜ ምን አልባትም ሁለተኛ የወርቅ ሜዳሊያውን ለማግኘት እድል እንዳለው ያሳየ ነበር።

64 ተወዳዳሪዎች በተሳተፉበት የ1964ቱ የቶኪዮ ኦሎምፒክ የማራቶን ውድድር ሻምበል አበበ ቢቂላ ርቀቱን ለማጠናቀቅ 10 ኪሎ ሜትሮች እስኪቀሩ ድረስ መሪነቱን በተረጋጋ ሁኔታ ለመያዝ ቻለ። ብዙም ሳይቆይ ታዲያ አበበ ከሌሎቹ አትሌቶች ተገንጥሎ ወጣና ለብቻው መሪነቱን በመቆጣጠር ብሪታኒያዊውን የአለም ክብረወሰን ባለቤት ባሲል ሄትሊን በአራት ደቂቃዎች ልዩነት ቀድሞ 2 ሰአት ከ12 ደቂቃ 12.2 ሰከንድ በሆነ ጊዜ የአለም ክብረወሰንን በመስበር አንደኛ ወጥቶ ለሁለተኛ ጊዜ የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ሆነ።

አሶሺዬትድ ፕሬስ ሁኔታውን እንዲህ በማለት ነበር የዘገበው። “አበበ ተከታዩን በሰፊ ልዩነት በመቅደም ወደቶኪዮ ስታዲዬም ከገባ በኋላ ሁለት እጆቹን ወደላይ አንስቶ የመጨረሻውን ገመድ በደረቱ በጥሶ አንደኛ ወጣ። ከዛም ወደሜዳው መሀል ገባና ሳሩ ላይ በጀርባው ተኝቶ እግሮቹን ልክ የብስክሌት ፔዳል እንደሚመታ ሰው አይነት እያወራጨ በማፍታታት ስታዲዬም የተገኘው ተመልካችን አስደመመ።”

ከቶኪዮው ወርቅ ሜዳሊያ በኋላ አበበ በ1965 ዓ.ም ወደ ጃፓን በመመለስ የኦትሱ ማራቶንን አሸነፈ። በቀጣዩ አመት ደግሞ የባርሴሎናው ዛራውትዝ ማራቶንን በማሸነፍ ለ1968ቱ የሜክሲኮ ኦሎምፒክ ዝግጁ መሆኑን ለአለም አረጋገጠ። የ36 አመቱ አበበ ቢቂላ ለሶስተኛ ተከታታይ ጊዜ የማራቶን ወርቅ ሜዳሊያን ለማግኘት ሜክሲኮ ሲገባ በጥሩ አቋም ላይ ይገኝ ነበር። እሱ እራሱ በጊዜው በሰጠው አስተያየት “በጣም በጥሩ አቋም ላይ ስለምገኝ አሸንፋለሁ ብዬ እጠብቃለሁ። ነገር ግን በእንደዚህ አይነት ረጅም ሩጫ ያልተጠበቀ ነገር ሊፈጠር ይችላል። ያልተጠበቀው ተከስቶ የምሸነፍ ከሆነ በሀገሬ ልጆች ማሞ ወልዴና መርሀዊ ገብሩ ብሸነፍ ይሻለኛል” አለ።

የሜክሲኮው ኦሎምፒክ የማራቶን ውድድር ከመጀመሩ በፊት የነበሩት አራት ቀኖች ለአበበ መጥፎ ጊዜዎች ነበሩና ቀናቶቹን በህመም አሳለፈ። ውድድሩ ተጀምሮ 10 ኪሎ ሜትሮች ያህል እንደሮጠ ታላቁ አትሌት ውድድሩን አቋርጦ ወጣና ሌላው ኢትዮጵያዊ ማሞ ወልዴ አንደኛ በመውጣት አሸንፎ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት በመሆን ለኢትዮጵያ ሶስተኛውን ተከታታይ የማራቶን ወርቅ ሜዳሊያዎች አገኘ።

ቀስተኛው አቤ ለድል ሲያነጣጥር
መጋቢት ወር አጋማሽ 1969 ዓ.ም ላይ ይነዳት የነበረችው ፎልስቫገን መኪና ተገልብጣ አደጋ የደረሰበትና እግሮቹ ፓራላይዝ የሆኑት ሻምበል አበበ ቢቂላ፤ እነዛ የወርቅ ሜዳሊያዎች ያስገኙለት አስደናቂ እግሮቹን ወደስራ እንደገና ለመመለስ ህክምናዎችን ቢያደርግም የተደረገው የህክምና ጥረት ውጤታም አልሆነም። የመጨረሻ አማራጭና ተስፋ በሚል ወደእንግሊዝ ተወስዶ በስቶክ ማንዴቪል ሆስፒታል ህክምና ቢደረግለትም አበበን እንደገና ወደሩጫው መመለስ ሳይቻል ቀረ። ታዲያ ተስፋ የማይቆርጠው አበበ “መሮጥ አልችልም” ብሎ ከስፖርቱ አለም ከመራቅ ይልቅ ራሱን ወደቀስት ወርዋሪነት አሸጋገረና በእግሮቹ ያገኛቸውን ድሎች በእጆቹም ለመድገም ወሰነ። ምንም እንኳን እንዳሰበው ውጤታማ ባይሆንም በ1969 ዓ.ም በተካሄደው የዊልቸር ኦሎምፒክ በጀማሪ ቀስት ወርዋሪዎች ክፍል ተወዳድሮ ዘጠነኛ ደረጃን አግኝቶን ጨረሰ።

የሚያሳዝነው ነገር ታላቁ አበበ ቢቂላ ገና በ41 አመቱ በ1973 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለየና የአትሌቲክስ ስፖርት አፍቃሪው አለምና ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው አጡ።

በቅርቡ የአለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር መቶኛ አመት ምስረታን አስመልክቶ የስፖርቱ የታላቆች ታላቅ ተብለው ከተመረጡት ቀዳሚ 12 አትሌቶች መካከል ኢትዮጵያዊው ጀግና አበበ ቢቂላ አንዱ ነበር። ወረቀት ላይ ከተነደፉ እቅዶች ይልቅ የራሱን የተፈጥሮ የሩጫ ችሎታን እና ነገሮችን እንደየአመጣጣቸው የማንበብ ብቃቱን በመጠቀም ታላቅ ታሪክን የሰራው የአበበ ቢቂላን ሩጫዎች ያላዩ ታሪኩን ሲሰሙ የአፈታሪክ ያህል ነው የሚሆንባቸው። “ማራቶንን በባዶ እግሩ ሮጦ መጨረስ ብቻ ሳይሆን አንደኛ ወጥቶ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት የሆነ አትሌት አለ” ብሎ አንድ ሰው ጎዳና ላይ ላገኘው ሰው ቢያወራ “አብደሀል ወይ፤ ለምን የማይሆን ነገር ታወራለህ” ነው የሚባለው። አበበ ግን ተአምረኛ ነበርና አድርጎታል፤ ለሰሚ እውነት የማይመስል እውነትን ያውም በታላቁ ኦሎምፒክ ላይ ፈጽሟል።

ቸር እንሰንብት::

ሰላም ሞፊቲ :-

እንዴት ነህ ወንድሜ? ወይዘሮ ስንዱ (Hurricane Sandy) እናንተ አካባቢ ጎራ ብላ ነበር? መቼም ከአደጋ ብትተርፍ ነው ዋርካን የጎበኘሃት :roll:

የምንጊዜም የማራቶን ጀግና : የኢትዮጵያ : የአፍሪቃ እና የመላው ጥቁር ሕዝብ መኩሪያ የሆነውን የሻምበል አበበ ቢቂላን ታሪክ ፍስሃ ተገኝ ጥሩ አቀናብሮታል :: ነገር ግን የቀን አቆጣጠሩ እንደ አውሮፓውያን እንጂ በእኛ በኢትዮጵያውያን የቀን አቆጣጠር አይደለም :: ምነው ልጄ እንዲያው ሰው ሁሉ ማንነቱን ሸጦ በላው? ውጭ አገር የሚኖረው ሰው ምን ነካው? ሥልጣኔ መሆኑ ነው :cry: :cry: :cry:

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Mon Nov 12, 2012 8:41 am

ሰላም የአትሌቲክስ ስፖርት አፍቃሪዎች:-

ያሣለፍነው የሣምንት መጨረሻ ለኢትዮጵያውያን አትሌቶች የድል ቀናት ነበሩ:: እሑድ ዕለት ከተደረጉት ውድድሮች ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Mon Nov 26, 2012 4:49 am

ሰላም ለአትሌቲክስ ስፖርት አፍቃሪዎች:-

የሣምንቱ መጨረሻ የስፖርት ዜናዎች

ሃይድራባድ (ሕንድ)

በየዓመቱ በሕንድ ደቡባዊ ከተማ በሃይድራባድ በሚካሄደው የ10 ኪ.ሜ. የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር በሴቶችም : በወንዶችም ምድቦች ኢትዮጵያውያን የድል አክሊል ተቀዳጅተዋል:: በሴቶቹ የብርጓል መለሰ በ33 ደቂቃ 21 ሴኮንዶች ስታጠናቅቅ ሞስነት ገረመው ደግሞ የወንዶቹን ምድብ ውድድር በ27 ደቂቃ 36 ሴኮንድ ጨርሶ አሸናፊዎች ሆነዋል::

ምንጭ:- Press Trust of India (PTI), Sunday 25 November 2011. Ethiopians clean sweep at Hyderabad 10K Run.

ቤጂንግ (ቻይና)
በሌላዋ የእስያ ኃያል አገር በቻይና ዋና ከተማ በቤጂንግ በተደረገው ዓመታዊው የማራቶን ውድድር ኃብቴ ጅፋር በ2 ሰዓት 9 ደቂቃ 39 ሴኮንድ ጨርሶ አንደኛ ሆኗል::

ምንጭ:- Mirko Jalava (for the IAAF), 25 November 2012. Jufar and Jia Chaofeng triumph in Beijing.

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Sat Dec 22, 2012 10:40 pm

ሰላም የአትሌቲክስ ስፖርት አፍቃሪዎች:-

የሎንዶን ኦሎምፒክ ሽልማት ጉዳይ ውዝግብ ቀስቅሷል:: አትሌት ገብረእግዚአብሔር ገብረማርያም የሚለው አለና እስኪ ኃሣቡን እናንብብለት::

ምንጭ:- ደረጀ ጠገናው : እሑድ ታኅሣሥ 14 ቀን 2005 ዓ.ም.:: “በመንግሥት ሽፋን ሽልማት እየሰጠን የሚመስለንን ልንጠቅምበት የማይመስለንን ደግሞ የምንጎዳበት ሊሆን አይገባም” አትሌት ገብረእግዚአብሔር ገብረማርያም::

የለንደን ኦሊምፒክ ከተጠናቀቀ መንፈቅ ገደማ ቢያስቆጥርም እዚህ ያልተጠናቀቁ አነጋጋሪ ጉዳዮች አሁንም ከፍተኛ አለመግባባትን ፈጥረዋል፡፡

መንግሥት ለአትሌቶች የሰጠው ሽልማትን ተከትሎ አትሌቶቹ ከፍተኛ ቅሬታ አድሮባቸዋል፡፡ የሽልማቱ መሥፈርት ግልፅ ካለመሆኑም በላይ ጥረትን ማዕከል እንዳላደረገም የሚሉ አትሌቶች አሉ፡፡ የሽልማቱን ሥነ ሥርዓት ያስተባበረው አካል ለዚህ ጉዳይ ማብራርያ እንዲሰጣቸው ይጠይቃሉ፡፡ ለመሆኑ አትሌቶቹ የሚያነሱት ጥያቄ ምንድን ነው? ይኼን ጥያቄ የሚመልስልን የአትሌቶቹ ተወካይ ገብረእግዚአብሔር ገብረማርያም ሲሆን፣ ደረጀ ጠገናው አነጋግሮታል፡፡

- የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በውድድር ዓመቱ የአመራር ለውጥ አድርጓል፡፡ በዚሁም አንዳንድ ከብሔራዊ ዝግጅት ጋር ተያይዞ ቅድሚያ የሚያስፈልጋቸው ሥራዎች እንዲጓተቱ ማድረጉን የሚናገሩ አሉ፡፡ አንተ ደግሞ አትሌቶችን ወክለህ የፌዴሬሽን አመራር አካል ነህና የምትለው ይኖርሃል?

o ምርጫውን ተከትሎ አንዳንድ መቀዛቀዞች እንዳሉ ይሰማኛል፡፡ ምክንያቱም አሁን የምንገኝበት ወቅት የውድድር ዓመቱ ሩብ ዓመት የተገባደደበት ነው፡፡ የዓለም አገር አቋራጭ ውድድር የቀረው ከሁለትና ሦስት ወር ያልበለጠ ጊዜ ነው፡፡ እስካሁን ብሔራዊ ቡድኑ መሰባሰብ ቀርቶ አሰልጣኝና ተያያዥ ሙያተኞች ምርጫና ምደባ እየተከናወነ አይደለም፡፡ ይህንኑ አዲሱ አመራር ያጣዋል የሚል እምነት የለኝም፡፡

- አትሌቶችን በመወከል የአመራሩ አንዱ አካል አንተ መሆንህ ይታወቃል፡፡ ከዚህ አኳያ ጥያቄውን የምትቀበል ከሆነ ከአመራር ጋር በጉዳዩ ለመወያየት አልሞከርክም?

o ጥያቄውን እጋራለሁ፣ በተወሰነ መልኩም ቢሆን ተነጋግረንበታል፡፡ በግሌ በአንድ ነገር እስማማለሁ፡፡ ምክንያቱም ፌዴሬሽኑን ለዓመታት ከመሩ በኋላ በአዲስ የተተካው አመራር ያከናወናቸው ሥራዎች በተወሰነ መልኩም ቢሆን ጥገና እየተደረገላቸው መቀጠል ያለባቸው እንጂ እንደገና ከዜሮ መጀመር እንደሌለበት ግልፅ ነው፡፡ መጀመር ያለበት ከነበረው ነው፡፡ መቀየር አለበት ከተባለም አሁንም ምናልባት የማያሠራ ነገር ካለ ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ውጭ መሠረቱን መንቀል ተገቢ ነው የሚል እምነት የለኝም፡፡ ይህ ሲባል ግን የነበረው አመራር አደረጃጀቱ ማለትም ተቋሙን መምራት የሚችሉ ሙያተኞችን ከማብቃት አኳያ ከስፖርት ቤተሰቡም ሆነ ከሚመለከተው ባለድርሻ ሲቀርቡ የሚደመጡ ክፍተቶች አሉ፡፡ እነዚያን ወደ ትክክለኛው መስመር እንዲገቡ ማድረግ ለዚያ ደግሞ ተገቢውን የአሠራር ሥርዓት መፍጠር ያስፈልጋል፡፡

- አትሌቶችና አሰልጣኞች ሲመረጡ ሁሌ ከስፖርት ቤተሰቡም ሆነ ከእናንተ ከአትሌቶቹ ሳይቀር የሚቀርቡ ቅሬታዎች እንደነበሩ ይታወቃል?

o እነዚህ ነገሮች እንቅስቃሴ እስካለ ድረስ ወደፊትም የሚኖር ነው፡፡ ምክንያቱም የብዙ ሰዎች ፍላጎት ያለበት አትሌቲክስ ቀርቶ በቤተሰብ ውስጥ ፍፁም ነገር አይኖርም፡፡ በዚህ መነሻነት ይመስለኛል አትሌቶችም ሆነ አሰልጣኞች ሲመረጡ አስተያየቶችና ቅሬታዎች የሚቀርቡት፡፡ ጥያቄው ለምን ይቀርባል ብሎ ድርቅ ማለትም ትክክል አይመስለኝም፡፡ ቅንነት በተመላበት መንገድ ሁሉንም ሊያሳምን የሚችል ሥርዓት መፍጠር ይቻላል ብዬ አስባለሁ፡፡ ከምርጫ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመድፈን ፌዴሬሽኑ ጉዳዩን የሚመለከተውን ክፍል አቅምና ብቃት ባላቸው ሙያተኞች አደራጅቶ፣ ተገቢውን ሰው በተገቢው ቦታ ማስቀመጥ ነው፡፡

ያን ጊዜ ከስፖርት ቤተሰቡም፣ ከስፖርተኛውም ሆነ ከሙያተኛው ለሚቀርቡ ቅሬታዎች ተቋሙ አሳማኝ መልስ ለመስጠት የሚቸገርበት ምክንያት አይኖርም፡፡ ቢኖር የግል ፍላጎቱ ያልተሟላለት አካል ቅሬታ ነው፡፡ የእስካሁኑ አሠራር ግን ከብዙ ሰዎች ሐሳብ ይልቅ የአንድ ግለሰብ ሐሳብ የሚደመጥበት በመሆኑ የቱንም ያህል ጥሩ ሥራዎች ቢሠሩ ጎልቶ የሚወጣው መጥፎው ነው፡፡ ሰዎችን ማብቃት እነዚህን ክፍተቶች መቶ በመቶም ባይሆን ቅድሚያ እንደሚያስፈልገው ግን ለአፍታም መዘንጋት ያለብን አይመስለኝም፡፡ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለበት አሠራር ለተቋምም ሆነ ተቋማትን ለሚመሩ ሰዎች ዋስትና እንጂ ጉዳት ያለው አይመስለኝም፡፡

- የአትሌቶች ተወካይ በመሆንህ ፌዴሬሽኑን ከሚመሩ አካላት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ለመነጋገር ዕድሉ አለህና የሚነሱ ቅሬታዎችን ለአመራሩ አቅርበህ የተከራከርክበት ጊዜ የለም?

o በራሴ ምክንያት ካልሆነ እንደተባለው የፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈጻሚ ስብሰባዎች ላይ እገኛለሁ፡፡ በሥራ ጫና በተወሰኑት ስብሰባዎች ላይ ያልተገኘሁበት አጋጣሚም ቢኖርም ግን ግዴታዬ ነው፡፡ ምክንያቱም አትሌቱ የወከለኝ የእሱን ድምፅና ፍላጎት ማንጸባረቅ እንድችል ነው፡፡ የማቀርባቸው ሐሳቦች ተቀባይነት የሚያገኙም አሉ የሚወድቁም አሉ፡፡ እንደ አሠራር ተገቢም ይመስለኛል፡፡

- የፌዴሬሽኑ የቀድሞ አመራር በአዲስ አመራር ተተክቷል፡፡ እንደ አትሌት ተወካይነትህ የአዲሱ አመራር የመጀመሪያ አጀንዳ ሊሆን ይገባል የምትለው ምንድነው?

o የአመራሩ የፌዴሬሽኑን የዕለት ዕለት እንቅስቃሴ ከመጀመሩ በፊት ለአትሌቲክስ ዋነኛ የጀርባ አጥንት ከሆኑት አትሌቶችና በዙሪያቸው ከሚገኙ ሙያተኞችና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር መድረክ ፈጥሮ መነጋገር እንዲችል ነው፡፡ በግሌም የአትሌቶች ተወካይ እንደመሆኔ መጠን ይኼው እውን ይሆን ዘንድ እየተንቀሳቀስኩ ነው፡፡ ምክንያቱም ወደ ኃላፊነት የመጣው ሥራ አስፈፃሚም ሆነ ለማንኛውም የስፖርት ቤተሰብ የሚታወቅ ነገር አለ፡፡ ከዚህ በፊት ከውጤት ጋርም ሆነ በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ሚዲያውን በመጠቀም ሲደመጡ የቆዩ ቅሬታዎች፣ የአደረጃጀትና የአሠራር ጉድለቶችን የተመለከቱ ናቸው፡፡ እነዚህን አዲሱ አመራር ያጣቸዋል የሚል እምነት የለኝም፡፡ ስለዚህ በአዲስ መንፈስ፣ በአዲስ ጉልበትና አመለካከት ወደ ሥራ ለመግባት ደግሞ የነበሩ ክፍተቶችን በቅድሚያ መድፈን የሚያስፈልግ ይመስለኛል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ጉድለቶቹን ተጠቅመው ተጨማሪ ጉደለቶችን ለመፍጠር የሚችሉ እድሎች ላለመኖራቸው ዋስትና አይኖርም፡፡ ለዚሁ ደግሞ አሁንም ደግሜ ደጋግሜ መናገር የምፈልገው የፌዴሬሽኑን አጠቃላይ እንቅስቃሴ በተገቢው ወቅትና ጊዜ መቆጣጠርና መከታተል ይቻል ዘንድ ተአማኒነት ያለው ሥርዓት መፍጠር የግድ ነው፡፡ አንድ ተቋም ግልፅነትና ተጠያቂነትን የሚያሰፍን ሥርዓት ካለው ሰዎች ሄዱ፣ ሰዎች መጡ የሚፈጠር ችግር አይኖርም፡፡ ይኼ ከሆነ እስከዛሬ የምንነታረክበት ሁሉ ሰዎች ከሰዎች ጋር መሆኑ ይቀርና ከሥርዓት ጋር ይሆናል፡፡ የቻለ ይቀጥላል ያልቻለው ደግሞ በሥርዓቱ ይወገዳል፡፡

- በቅርቡ በፌዴራሉ ስፖርት ኮሚሽን የአትሌቲክሱን ውጤት ተከትሎ በቀረበው “ዳሰሳ ጥናት” አትሌቶች ከአገራዊ ውድድር ይልቅ የግል ውድድር እያስቀደሙ ስለመሆኑ ይፋ አድርጓል፡፡ እንደ አትሌት ተወካይነትህ “ዳሰሳ ጥናቱ” በቀረበው ዕለት ነበርክ እንዴት አገኘኸው?

o ዳሰሳ ጥናት ሲባል ለመፍትሔ መነሻ ሐሳብ መሆኑ ቢገባኝም፣ ነገር ግን ጥናቱ እንደ ጥናት ከሚመለከተን ባለድርሻ አካል ተገቢውን ግብዓት ያላካተተ በመሆኑ ጥናቱን እንደ ጥናት ለመቀበል እቸገራለሁ፡፡ ምክንያቱም በግሌ የአትሌቶች ተወካይ ብቻ ሳልሆን፣ አትሌትም በመሆኔ ስሜቱ ይሰማኛል፡፡ ማንኛውም አትሌት በግሉ ተወዳድሮ 300 ሺሕ ዶላር ከሚያገኘው ይልቅ በዓለም ሻምፒዮና አልያም ኦሊምፒክ ላይ ቢያሸንፍ ይመርጣል፡፡ በሚፈጠሩ የአሠራር ችግሮች ካልሆነ በስተቀር ደግሜ ደጋግሜ መናገር የምችለው የዓለም ሻምፒዮና ወይም ኦሊምፒክ ለአንድ አትሌት ትልቅ ሕልሙና ስኬቱ ነው፡፡ ከትልልቆቹ ብንጀምር ኃይሌ ገብረሥላሴ በዓለም ላይ የሚዘመርለት ሰው ነው፡፡ ኃይሌን የሚያስደስተው አድናቆቱ ብቻ ሳይሆን በሲድኒ ኦሊምፒክ ወቅት ከኬንያዊው ፖል ቴርጋት ጋር አንገት ለአንገት ተናንቆ ያስመዘገበው ድል ነው፡፡ ኃይሌን እንደምሳሌ አነሳሁ እንጂ ገብረ እግዚአብሔርን የሚያስደስተው በኒዮርክ ማራቶን ድል ያገኘው በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ዶላር ሳይሆን፣ በኦሊምፒክ አልያም ዓለም ሻምፒዮና ከተቻለ ወርቅ ካልተቻለ ደግሞ የብርና ነሐስ ሜዳሊያዎችን ቢያገኝ ነው፡፡ ይኼ የማንኛውም አትሌት እምነት ነው፡፡ የቀነኒሳ፣ የጥሩነሽ፣ የመሠረትና የሌሎችም እምነት ነው፡፡

እኔን ጨምሮ የዴጉን የዓለም ዋንጫ ውጤት ተከትሎ የደረሰብን የሞራል ውድቀት በገንዘብ አይለውጥም፡፡ የሚያከብረን የስፖርት ቤተሰብ በሔድንበት ሁሉ ምን አትሌት አለ? አትሌት ቀረ የሚሉና ለሎችም በርካታ ስሜትን የሚነኩ አስተያየቶች ሲቀርቡብን ነበር፡፡ ይሁንና እውነቱ ግን የአገርን ባንዲራ ወክሎ በሚሊዮን ተመልካች ፊት ከመታየት የበለጠ ክብር አለ የሚል ካለ ለመከራከር ዝግጁ ነኝ፡፡ ከዚህ አንጻር ኮሚሽኑ ያቀረበው ጥናት እንደ ጥናት ብቀበለውም፣ ነገር ግን ማካተት ከሚገባው ግብዓት አኳያ ጎደሎ በመሆኑ እንደገና ሊታይ ይገባዋል፡፡

- የጥናቱ አቅራቢ ከሚመለከታቸው ግብዓት አላካተተም እያልክ ነው?

o ጥናት እስከሚገባኝ የሰዎች ሐሳብ ስብስብ ነው፡፡ ለችግሮች መፍትሔ አመላካች አቅጣጫዎችን ጠቋሚ ነው፡፡ ስለዚህ ገብረ እግዚአብሔር እንደ አትሌት ተወካይነቱ ብቻ ሳይሆን እንደ አንድ ባለድርሻ መጠየቅ ነበረብኝ ብሎ ያምናል፡፡ ግን አልሆነም፡፡ በጥናቱ ልመንበትም፣ አልመንበትም ጥናት ነውና አስተያየትህ ምንድነው መባል ያስፈልግ ነበር ብዬ አምናለሁ፡፡ ስለዚህ እኔ ስለምመራው አካል የእኔን ሐሳብ ሳያካትት ሦስተኛ ወገን የሰጠውን አስተያየት መሠረት ያደረገ ጥናት፤ ጥናት ነው ብዬ ለመቀበል እቸገራለሁ፡፡ እንደሰማሁት ይኼው ጥናት የብሔራዊ ፌዴሬሽኑንም አስተያየት ያካተተ አልመሰለኝም፡፡

- ምክንያት ያለው ይመስልሃል?

o ችግሩ የራስን ፍላጎት ለማስፈጸም የሚመነጭ ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም ስፖርት በምንም መመዘኛ በምስጢር የሚከወን ሳይሆን፣ ከውጤቱ ጀምሮ ሜዳ ላይ የሚታይ ነው፡፡ ይኼ ከሆነ ደግሞ ለዘርፉ ይመለከታቸዋል ተብለው የሚታሰቡ አካላት የጥናቱ ጥቅም ለጋራ እስከሆነ ድረስ ማለት ያለባቸውን እንዲሉ እድሉ ሊሰጣቸው ይገባል የሚል እምነት ነው ያለኝ፡፡ በአገሪቱ በተለይ በስፖርቱ የዚህ ተመሳሳይ ጥናቶች ሲቀርቡ የመጀመርያ አይደለም፡፡ ብዙዎቹ ያለ ውጤት የሚቀሩትም ሰዎች ለአገሪቱ ስፖርት የሚገባውን ትኩረት ሳይሰጡ የግል ፍላጎታቸውን በሌሎች ላይ ለመጫን በሚፈልጉበት ጊዜ ነው፡፡ አንዱን ለመከላከል፤ ሌላውን ለመወንጀል፣ አንዱን ለማሾም ሌላውን ለማፈናቀል ታሳቢ ያደረጉ ጥናቶች መቼም ለፍሬ አይበቁም፡፡ ይህም ለስፖርቱም ለአገርም፣ ለራሱ ለጥናቱ አቅራቢም ይጠቅማል የሚል እምነት የለኝም፡፡ ጥናት የመፍትሔ አካል ነው ከተባለ ቢያንስ ቀና አመለካከትን ማካተት አለበት፡፡

- ይኼ እንደተጠበቀ የለንደን ኦሊምፒክ ሽልማትን ተከትሎ አትሌቶች በአንተ በኩል ስለሽልማቱ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው የጠየቁ መኖራቸው ተሰምቷል፡፡ የችግሩ መንስኤ ምንድነው?

o ሲጀመር ለንደን ኦሊምፒክ ከዝግጅቱ ጀምሮ አትሌቶች እጅግ በርካታ ውስብስብና አስቸጋሪ ውጣ ውረዶችን አልፈው እውን የሆነ ክንውን ነው፡፡ አትሌቶች በለንደን ኦሊምፒክ ውጤት ያገኙም ሆነ ያላገኙ እውነተኛ መስዋዕትነት ከፍለዋል፡፡ አትሌት ቀነኒሳ ከስንት ትግል በኋላ ነው የለንደን ኦሊምፒክ ሚኒማ አሟልቶ ወደ ለንደን ያመራው፡፡ አገሪቱ በእሱ የለመደችውን ድል ለማስመዝገብ ጭምር ማለት ነው፡፡ ሌሎቻችንም ከሕመም ጋር እየታገልን ውድድር ላይ የታየነው የወከልነውን ሕዝብ ለማስደሰት ነው፡፡ አሰልጣኞችም ከአትሌቱ ጋር የደከሙት ለዚሁ ዓላማ ነው፡፡ ያም ሆኖ አቅማቸው የፈቀደውን ሁሉ አድርገው አንዳንዶች በጥቃቅን ስሕተት አንዳንዶች ደግሞ ከአቅም በላይ ሆኖባቸው ውጤት ያልቀናቸውም አሉ፡፡ ውጤታማዎቹ አንደተጠበቁ ሆኖ ማለት ነው፡፡ ይኼ ሁሉ አልፎ አጥጋቢ ነው ተብሎ ባይታመንም፣ ከዴጉ ዓለም ሻምፒዮና የተሻለ ውጤት መጣ፡፡ ነገር ግን እንደተለመደው ለለንደን ኦሊምፒክ ማበረታቻ ተብሎ የተሰጠው ሽልማት ከመሥፈርቱ ጀምሮ ትርጉም አልባ ሆኖ መጠናቀቁ ግን እኔን ጨምሮ ለአትሌቶች እንቆቅልሽ ሆኖብናል፡፡ የተሰጠው ሽልማት የብዙ አትሌቶችን ሞራል የሰበረ ነው፡፡ በስሕተት ነው የሚሉ ሊኖሩ ይችሉ ይሆናል፡፡ እንደ እኔ ግን አልስማማም፡፡

- ምክንያት ብለህ የምታቀርበው ይኖራል?

o በግሌ የሥነ ሥርዓቱ ትርጉም የሕዝብን ቦታ ይዞ የግል ፍላጎትን ለማሟላት እንደተሠራ ይሰማኛል፡፡ ሕዝብና መንግሥት ወንበሩን ሲሰጠኝ የሚፈለግብንን ሥራ እንድሠራ እንጂ፣ በመንግሥት ሽፋን የሚመስለንን ልንጠቅምበት የማይመስለንን ደግሞ ልንጎዳበት አይደለም፡፡ በመሠረቱ ሽልማት አነሰ በዛ ተብሎ ቅሬታን ሊያስከትል የሚችል ሳይሆን፣ አንድ ሰው ለደከመበትና ወደፊትም የተሻለ እንዲሠራ ማበረታቻ ነው፡፡ በሌላ በኩል ሽልማት ሦስት ነገሮችን ታሳቢ አድርጎ የሚከወን ነው፡፡ የመጀመርያው አንድ ሰው በጉልበቱ አልያም አእምሮው ለሠራው ዋጋ ነው፡፡ ሁለተኛው ሰው ለሠራው ሥራና ላጠፋው ጉልበት የማካካሻ ማበረታቻ ነው፡፡ የመጨረሻው ደግሞ ሸክም ነው፡፡ ሸክም ሲባል ዓላማው ለወደፊቱ የበለጠ እንዲሠራ አደራ ጭምር ነው፡፡ ማንኛውም አትሌት እሸለማለሁ ብሎ አይደለም ለውድድር የሚቀርበው፡፡ አእምሮውና አቅሙ የፈቀደውን አድርጎ የሠራውን ውጤት ለማግኘት ነው፡፡ እነዚህን ሁሉ መነሻ አድርገን ወደ ሽልማቱ ስንመለስ እያንዳንዱ ክንውን አሳዛኝና አስተዛዛቢ ነው፡፡ ከሽልማቱ መሥፈርት ስንነሳ በአንደኛውና በሁለተኛው መካከል በምንም መመዘኛ ያንን ያህል ልዩነት ሊኖር አይገባም፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከናወኑ የሽልማት መሥፈርቶችን ብናይ አንደኛው መቶ ፐርሰንት ሲሆን፣ ሁለተኛው የፈለገው ነገር ቢፈጠር እንኳ በሃምሳ ፐርሰንት አይወርድም፡፡ የእኛዎቹ ሸላሚዎች ይህንን አያውቁም ማለት የዋህነት ነው፡፡ ይህም ይቅር በአገራችን ከሃምሳ ዓመት በላይ ያስቆጠረው ብሔራዊ ሎተሪ ለአንደኛው ሁለት ሚሊዮን ቢሆን፣ ለሁለተኛው አንድ ሚሊዮን ስለመሆኑ የማያውቅ የለም፡፡ በአሰልጣኝ ደረጃም ቢሆን ለአንዳንዱ የእንኳን ደህና መጣህ እንጂ፣ በሥራው ተመዝኖ አይመስልም፡፡ በኦሊምፒክ በሦስት ሺሕ ሜትር መሰናክል በሴት በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያውን የነሐስ ሜዳሊያ ነው ያገኘችው፡፡ አትሌቷ የተሰጣት ሽልማት ግን እጅግ የሚገርምና የሚያሳዝን ነው፡፡

በአጠቃላይ የሽልማቱ አሠራር በአንድ ሰው ፍላጎትና እምነት የተከናወነ እንጂ፣ እውነት የብዙ ሰዎች አስተያየት ኖሮበት ነው ለማለት አያስደፍርም፡፡ ሽልማቱን የተከታተለው ኅብረተሰብ ራሱ ሳይቀር ጥያቄ አቅርቧል፡፡ ምናልባትም አትሌቶቹ ሽልማቱን እንዲወስዱ ምክንያት የሆናቸው የኅብረተሰቡ አስተዋይነት እንጂ እንደ ኮሚሽኑ ላለመውሰድ ውሳኔ ላይ ደርሰው ነበር፡፡ ያም ሆኖ ግን መሥፈርቱን አስመልክቶ ከሚመለከተው አካል ማብራርያ እየጠበቁ ነው፡፡ የሚመለከተው አካልም መድረክ አመቻችቶ ማብራሪያ ይሰጣል ብለንም እንጠብቃለን፡፡
ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Sun Dec 23, 2012 11:46 pm

እሑድ ታኅሣሥ 14 ቀን 2005 ዓ.ም.

የብራስልስ (ቤልጅግ) ዓመታዊ የአገር አቋራጭ የሩጫ ውድድር

ሩቲ አጋ የሴቶችን ምድብ በአሸናፊነት አጠናቃለች:: በዚህ ውድድር ሩቲ ቀዳሚ የሆነቸው በአገር አቋራጭ የሩጫ ውድድር ለሁለት ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒዮና ከሆነቸው ከፊዮኑላ ብሪተን የገጠማትን ከባድ ፉክክር ተቋቁማ በመቅደም ነበር:: የአገሯ ልጅ እሌኒ ገብረሕይወት ሦሥተኛ ወጥታለች::

ምንጭ:- IAAF, 23 DEC 2012. Report Brussels, Belgium: Teenagers Kirui and Aga show off their prodigious talent in Brussels.

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Tue Jan 01, 2013 6:13 pm

ሰላም ለአትሌቲክስ ስፖርት አፍቃሪዎች:-

ያለፈው የፈረንጆቹ 2012 ሲጠናቀቅ ኢማኒ መርጋ በአገር አቋራጭ ውድድር የማይበገር ሯጭ መሆኑን አስመሥክሮ ዓመቱን አጠናቅቋል:: ጣሊያን አገር ቦላንዞ ከተማ ለ38ኛ ጊዜ በተዘጋጀው የአገር አቋራጭ የሩጫ ውድድር ኢማኒ የአገሩን ልጅ ሙክታር እድሪስን በአገባብ ብቻ ቀድሞ (ሁለቱም የገቡበት ሰዓት 29 ደቂቃ 12 ሴኮንድ ነው) አሸንፏል:: በሴቶች ምድብ የ5 ኪ.ሜ. ርቀት በሚሸፍነው ውድድር አፈራ ጎደፋይ በኬንያዊቷ ሲልቪያ ኪቤት በአንድ ደቂቃ ተቀድማ ሁለተኛ ስትሆን ሌላዋ የአገሯ ልጅ ወርቅነሽ ደገፋ በ16 ደቂቃ 24 ሴኮንድ ሦሥተኛ ሆና ጨርሣለች::

ምንጭ:- Diego Sampaolo (for the IAAF), Tue Jan 1, 2012. Favourites Merga and Kibet win in Bolzano.

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

PreviousNext

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest