የኢትዮጵያ የአትሌቲክስ:- 2005 የተስፋ ዘመን

ስፖርት - Sport related topics

Postby ተድላ ሀይሉ » Wed Jan 02, 2013 5:54 pm

ሰላም ለአትሌቲክስ ስፖርት አፍቃሪዎች:-

አንዳንዴ "ዘግይቶ በደረሠን ዜና" ተብሎ ወሬ ይጀመራል:: እናም ከትላንት ወዲያ ሰኞ በሣን-ሲልቬስተር ቫሌካና (ማድሪድ : እስፓኝ) ለ48ኛ ጊዜ በተደረገው የአገር አቋራጭ የሩጫ ውድድር በሴቶችም ሆነ በወንዶች ምድቦች ኢትዮጵያውያኑ ቀዳሚዎች በመሆን አጠናቅቀዋል::

በሴቶች ምድብ ገለቴ ቡርቃ የውድድሩን ሬኮርድ በ23 ሴኮንዶች በማሻሻል 2ኛ ሆና የተከተለቻትን ኬንያዊቷን ሊኔት ማሣይን በ1 ደቂቃ 14 ሴኮንድ ቀድማ በ30 ደቂቃ 59 ሴኮንድ ውድድሩን አሸንፋለች::

ታሪኩ በቀለ ደግሞ በአውሮፓውያኑ የዘመን መለወጫ ዋዜማ የሚዘጋጁትን የሣዖ-ፖሎ (ብራዚል) እና የማድሪድ አገር አቋራጭ የሩጫ ውድድሮች በተለያዩ ጊዜያት በሁለቱም አሸናፊ በመሆን 3ኛው ሰው ለመሆን በቅቷል:: ከታሪኩ በቀለ በፊት እኒህን ውድድሮች ለማሸነፍ የቻሉት የቀድሞው የዓለም የ10 ሺህ ሜትር ርቀት የሩጫ ውድድር ሬኮርድ ባለቤት የነበረው ሜክሲኳዊው አሩቶ ባሪዮስ እና የዓለም የአገር አቋራጭ ሩጫ ፉክክርን ለሦሥት ጊዜያት ያሸነፈው ፖርቱጋላዊው ካርሎስ ሎፔዝ ናቸው::

ምንጭ:- IAAF, Jan 1, 2013. Bekele and Burka triumph at San Silvestre Vallecana in Madrid.

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Sun Jan 06, 2013 2:02 am

ሰላም የአትሌቲክስ ስፖርት አፍቃሪዎች:-

መቼም የዘመናችንን የዓለምን የመካከለኛና የረዥም ርቀት የሩጫ ውድድሮች እንደ አቶ ዲባባ ልጆች የተቆጣጠረው የለም:: የታላላቆቿን ፈለግ የተከተለችው ገንዘቤ ዲባባ ዛሬ ቅዳሜ ታኅሣሥ 27 ቀን 2005 ዓ.ም. በኤደንብራ (ስኮትላንድ) በተካሄደው የቡፓ የ3ሺህ ሜትር የአገር አቋራጭ የሩጫ ውድድር አሸናፊ ሆናለች:: ሁለተኛ የወጣችው መሠረት ደፋር ስትሆን በመሠናክል ሩጫ የገነነ ስም ያላት ሶፍያ አሠፋ በኬንያዊቷ ሌኔት ማሣይ ተቀድማ 4ኛ ሆናለች::

ምችጭ:- Organisers for the IAAF, Jan 5, 2013. Dibaba dashes Defar’s hopes with speedy finish in Edinburgh.

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Sun Jan 06, 2013 5:34 pm

እሑድ ታኅሣሥ 28 ቀን 2005 ዓ.ም.

ትላንት ቅዳሜ በዢያንሜን (ደቡባዊ ቻይና) በተደረገው የ11ኛው ዓመታዊ የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያኑ ነገሪ ተርፋ እና ፋጡማ ሣዶ የወንዶችንና የሴቶችን ምድቦች አሸናፊዎች ሆነዋል:: ነገሪ አምና በኬንያዊው ፒተር ካሚያስ ተይዞ የነበረውን የሥፍራውን ሬኮርድ በ5 ሴኮንዶች ያሻሻለ ሲሆን ፋጡማ ደግሞ ሁለተኛ የሆነችዋን ኬንያዊት ኢውኒስ ጄፕኪሩይን በ2 ደቂቃ 25 ሴኮንዶች ቀድማታለች::

ምንጭ:- Mirko Jalava (for the IAAF), Sat Jan 5, 2013. Terfa breaks course record in Xiamen.

ዝርዝር ውጤቱ ይህንን ይመስላል::

የሴቶች ምድብ
1. ፋጡማ ሣዶ (ኢትዮጵያ) _______ 2:27:35
2. ኢውኒስ ጄፕኪሩይ (ኬንያ) ______2:30:00
3. እየሩሣሌም ኩማ (ኢትዮጵያ) ___ 2:34:31
4. ዋንግ ዡኪን (ቻይና) _________ 2:34:56
5. ወርቅነሽ ቶላ (ኢትዮጵያ) ______ 2:37:49

የወንዶች ምድብ
1. ነገሪ ተርፋ (ኢትዮጵያ) _______ 2:07:32
2. ፖል ሎንያንጋት (ኬንያ) _______ 2:07:44
3. ሣህሌ ዋርጋ (ኢትዮጵያ) ______ 2:08:39
4. ገብረጻዲቅ አድኃና __________ 2:09:00

ለክርስትና ኃይማኖት ተከታዮች መልካም የልደት በዓል !

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Tue Jan 15, 2013 4:39 pm

ሰላም የአትሌቲክስ ስፖርት አፍቃሪዎች:-

ያለፈው ሣምንት መጨረሻ ኢትዮጵያውያን ሯጮች የደመቁበት ሆኖ አልፏል:: በሒውስተን (ቴክሣሥ ግዛት : አሜሪካ) : ኢልጎይባር (እስፓኝ) እንዲሁም በሣን ጂኦርጂዎ ሱ ሌኛኖ (San Giorgio su Legnano : ጣሊያን) በተለያዩ ርቀቶች በተደረጉት ፉክክሮች ኢትዮጵያውያን አሸናፊዎች ሆነዋል:: በተለይም በሒውስተን በግማሽ እና ሙሉ የማራቶን ውድድሮች ኢትዮጵያውያን ያስመዘገቧቸው ውጤቶች እጅግ አስደናቂዎች ናቸው::

ዝርዝር ውጤቶቹ የሚከተለው መልክ አላቸው::

36ኛው የሣን ጂኦርጂዎ ሱ ሌኛኖ (ጣሊያን) አገር አቋራጭ የሩጫ ውድድር
ሙክታር እድሪስ የ9 ኪ.ሜ. የአገር አቋራጭ ውድድሩን በ26 ደቂቃ 43 ሴኮንድ አጠናቅቆ አንደኛ ሆኗል::

ምንጭ: Diego Sampaolo (for the IAAF), Jan 13, 2013. Birthday win for Edris at Cross della Vallagarina.

70ኛው የሁዋን ሙጉዬርዛ የአገር አቋራጭ የሩጫ ውድድር ውድድር
1 ..... ገለቴ ቡርቃ _____ 22:53
4 ..... ቡዙዬ ድሪባ _____ 23:10

ምንጭ:- Emeterio Valiente (for the IAAF), Mon Jan 14, 2013. Report Elgoibar, Spain: Kipruto and Burka the commanding victors at Elgoibar

የሒውስተን ግማሽ እና ሙሉ የማራቶን ውድድሮች

የወንዶች ምድብ ማራቶን

1 ..... በዙ ወርቁ _______ 2:10:17
2 ..... ተፈሪ ባልቻ ______ 2:12:50
3 ..... ሰለሞን ሞላ ______ 2:14:37
4 ..... ብርሃኑ ገደፋ ______ 2:15:21
5 ..... ደረጀ አበራ _______ 2:17:09

የወንዶች ምድብ ግማሽ ማራቶን
1 ..... ፈይሣ ሌሊሣ _______ 61:54
2 ..... ድሪባ መርጋ ________ 62:00

የሴቶች ምድብ ማራቶን
1 ..... መሪማ መሐመድ _____ 2:23:37
2 ..... ብዙነሽ ዳባ _________ 2:24:26
3 ..... መስከረም አሰፋ ______ 2:25:17
4 ..... መሠረት ለገሠ _______ 2:30:31

የሴቶች ምድብ ግማሽ ማራቶን
1 ..... ማሚቱ ደስቃ ________ 69:53
5 ..... ዘምዘም አህመድ _____ 73:25

Organizers for IAAF, Jan 13, 2013. Report Houston, USA: Youth trumps weather in Houston as Ethiopians take clean sweep of titles.

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ኮሎኔል » Tue Jan 15, 2013 8:35 pm

የድል ብስራት እንደመስማት ምን ደስ የሚል አለ::
ልጅ ተድላ ምን እንደምልህ አላቅም የዛሬው ዜና የሚጠብቀንን ኦሎምፒክ በጥሩ ሁናቴ የሚያሳይ ነው::
ኦሎምፒክን በተስፋ እንድንጠብቅ የሚያረግ ነው::
ቡዙ ሚሰማ ጆሯችን ይህንንም እንዲሰማ እግዜር ስለፈቀደ ነውና ክብሩ ይስፋ::
አሁን ደሞ በደቡባዊት አፍሪካ እግርኮአስ ቅዳሜ ጀምሮ እናያለን :
ኢትዮጵያ ከመጀመሪያው ዙር አልፋ ማየትን እመኛለሁ ::
ሆኖም በጣም ጠንካራ ምድብ ውስጥ ስላለች ብትመለስም ጥሩ ጨዋታና ጸባይ እንድናይ ጸልያለሁ::
ኢትዮጵያ ፉትቦል የጸባይ ችግር አሁን በጣም ጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳለም እያየን ነው::
እሱ ይርዳን::
Ethiopia
ኮሎኔል
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 229
Joined: Fri Apr 07, 2006 7:19 pm
Location: zimbabwe

Postby ተድላ ሀይሉ » Wed Jan 16, 2013 12:40 am

ኮሎኔል wrote:የድል ብስራት እንደመስማት ምን ደስ የሚል አለ::
ልጅ ተድላ ምን እንደምልህ አላቅም የዛሬው ዜና የሚጠብቀንን ኦሎምፒክ በጥሩ ሁናቴ የሚያሳይ ነው::
ኦሎምፒክን በተስፋ እንድንጠብቅ የሚያረግ ነው::
ቡዙ ሚሰማ ጆሯችን ይህንንም እንዲሰማ እግዜር ስለፈቀደ ነውና ክብሩ ይስፋ::
አሁን ደሞ በደቡባዊት አፍሪካ እግርኮአስ ቅዳሜ ጀምሮ እናያለን :
ኢትዮጵያ ከመጀመሪያው ዙር አልፋ ማየትን እመኛለሁ ::
ሆኖም በጣም ጠንካራ ምድብ ውስጥ ስላለች ብትመለስም ጥሩ ጨዋታና ጸባይ እንድናይ ጸልያለሁ::
ኢትዮጵያ ፉትቦል የጸባይ ችግር አሁን በጣም ጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳለም እያየን ነው::
እሱ ይርዳን::

ሰላም ውድ ኮሎኔል :-

እንዴት ሠነበቱ? ደህና ነዎት ወይ? እንኳን ለብርኃነ ልደቱ አደረሠዎት:: መጪዎቹ የጥምቀትና የቃና ዘገሊላ በዓሎች የደስታ እንዲሆኑልዎት እመኛለሁ::

በአትሌቲክሱ ረገድ አሁንም ተስፋ ያላቸው ሯጮች አሉን:: በእግር ኳሱም ዘንድሮ ከ31 ዓመታት በኋላ ወደ ጥንት ሥፍራችን ለመመለስ ችለናል:: ለዚህ ድል ያበቁን ሁለት መሠረታዊ ምክንያቶች ናቸው ብዬ አምናለሁ:-
    1 ..... በኢትዮጵያ ላይ ለ21 ዓመታት እንደ መዥገር ተጣብቆ የኖረው በላዔሰብ በእግዚአብሔር ትዕዛዝ በመወገዱ እና

    2 ..... ለዘለዓለም በኢትዮጵያ ላይ ሤራ ከመጎንጎን የማይተኙልን አረብ ግብፆች ከአፍሪቃ ዋንጫ መድረክ ገለል በማለታቸው ነው::
የዘንድሮው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ቡድን ከቀድሞዎቹ ቡድኖች የሚለይበት አንድ መሠረታዊ ልዩነት አለ:- ያም በአጥቂ መሥመር የሚሠለፉት ግብ አዳኝ ተጨዋቾች ብዛት ነው:: እስከ ቅርብ ዓመታት ድረስ የብሔራዊ ቡድን አሠልጣኞች የሚቸገሩት ከብዙ ጥሩ አማካይ ተጨዋቾች መካከል የትኞቹን ቋሚ ተሠላፊ አድርጎ በመምረጥ ላይ ነበር:: ዘንድሮ እንደሚታየው ግን አሠልጣኙ የትኞቹን አጥቂዎች ማሠለፍ እንዳለበት መቸገሩን እናያለን:: ከአጥቂዎቹ መካከል:- ሣላዲን ሰዒድ : ጌታነህ ከበደ እና አዳነ ግርማ ቋሚ ተሠላፊዎች ናቸው:: ሆኖም ተጠባባቂዎቹ ዑመድ ኡክሪ እና ፉአድ ኢብራሒም ጥሩ የጎል አዳኞች ናቸው:: በዚህ ላይ ፕሮፌሽናል ተጨዋቹ ፍቅሩ ተፈራ እና የቡናው የጎል አዳኝ ታፈሰ ተስፋዬ በዚህ ቡድን ውስጥ አልተካተቱም:: እናም ድሮ እንደነበረው በአንድ አጥቂ የሚመካ ቡድን የለንም:: ይህም ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ቡድን ትልቅ መሻሻል ነው ብዬ አምናለሁ:: በተቀረ ቡድኑ አሁንም በታክቲክ ያልበሠሉ የተጨዋቾች ስብስብ መሆኑን መዘንጋት የለብንም::

መልካም ዕድል ለኢትዮጵያውያን ስፖርተኞች!

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Thu Jan 17, 2013 4:39 am

ሰላም ለአትሌቲክስ ስፖርት ቤተሰቦች:-

በዛሬው ዕለት አንድ አሣዛኝ ዜና በኢንተርኔት ተበትኗል:: ይኸውም የማራቶን ሯጭ የነበረው ወጣቱ አትሌት አለማየሁ ሹምዬ ባለፈው አርብ በመኪና አደጋ ሕይወቱ የማለፉ መጥፎ አጋጣሚ ነው:: አለማየሁ ሹምዬ በተወለደ በ24 ዓመቱ ከዚህ ዓመት በሞት ከመለየቱ በፊት በማራቶን ውድድሮች በተለያዩ አገሮች አሸናፊ በመሆን ለወደፊቱ ብሩህ ተስፋ ያሣየ ሯጭ ነበር:: እግዚአብሔር ነፍሱን ይማር: ለቤተሰቦቹና ለወዳጆቹም መጽናናቱን ይስጣቸው::

ምንጮች:-

1 ..... Sodere, posted on January 16, 2013 at 12:25pm. Ethiopian Athelete Alemayehu Shumye has died in car Accident.

2 ..... IAAF, Jan 14, 2013. Marathon Runner Shumye dies in Car Crash


ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Fri Jan 25, 2013 5:05 pm

ማራቶን : ማራቶን : ማራቶን :!: :!: :!: :!: :!: :!: :!: :!:

በዛሬው ቀን በዱባይ ኢትዮጵያውያኑ ሯጮች በየዓመቱ ያስለመዱትን የማራቶን የድል ትርኢት አሣይተዋል:: በወንዶች ምድብ ጣልቃ ሣያስገቡ ከ1ኛ እስከ 4ኛ : በሴቶችም እንዲያውም ከ1ኛ እስከ 6ኛ ያለውን ደረጃ ተቆጣጥረዋል:: በወንዶቹ ምድብ በታሪክ 5 ሯጮች ከ2:05 በታች በሆነ ሰዓት የገቡበት ፉክክር ነበር:: ዝርዝር የውጤት ሠንጠረዡ የሚከተለውን ይመስላል::

የሴቶች ምድብ
1ኛ ..... ትርፊ ፀጋዬ _______ 2:23.23
2ኛ ..... እህተ ኪሮስ _______ 2.23.39
3ኛ ..... አማኒ ጎበና ________ 2.23.50
4ኛ ..... አሃዛ ኪሮስ _______ 2.24.30
5ኛ ..... በላይነሽ ኦልጂራ ____2.25.01
6.ኛ .... ሽታዬ በዳሣ _______ 2.25.47
8ኛ ..... አበበች አፈወርቅ ___ 2.27.08

የወንዶች ምድብ
1ኛ ..... ሌሊሣ ደሲሣ _______ 2.04.45
2ኛ ..... ብርሃኑ ሽፈራው _____ 2.04.48
3ኛ ..... ታደሰ ቶላ _________ 2.04.49
4ኛ ..... እንደሻው ነገሠ _____ 2.04.52
7ኛ ..... ዳዲ ያሚ __________ 2.07.55
9ኛ ..... ሐብታሙ አሰፋ ______ 2.08.28
10ኛ ... ገመቹ ብሩ _________ 2.08.53

ምንጭ:- Pat Butcher (Organisers for the IAAF), Fri Jan 25, 2013. Debutant Desisa wins Dubai Marathon in 2:04:45, five men under 2:05.

እንደድሮው መፈክር የማራቶኑ ድል በእግር ኳሱም ይደገማል! በማለት ዘገባችንን እናጠናቅቃለን::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Sun Jan 27, 2013 11:27 pm

እሑድ ጥር 19 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዛሬ በዴይኪርሽ (ሉክዘምበርግ) በተደረገ የአገር አቋራጭ የሩጫ ውድድር በሴቶች ምድብ እሌኒ ገብረሕይወት አሸናፊ ስትሆን በወንዶች ምድብ መላኩ በላቸው 3ኛ ሆኗል:: ዝርዝር ውጤቱ ይህንን ይመስላል::

የሴቶች ምድብ:- 5.35 ኪ.ሜ. ርቀት
1ኛ ..... እሌኒ ገብረሕይወት ____ 19:17
2ኛ ..... መስታወት ታደሰ ______ 19:59

የወንዶች ምድብ:- 10.2 ኪ.ሜ. ርቀት
3ኛ ..... መላኩ በላቸው _______ 31:57

ምንጭ:- Jörg Wenig (for the IAAF), Sun Jan 27, 2013. Kenya’s Rop and Ethiopia’s Gebrehiwot take Eurocross titles in Diekirch.

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Mon Apr 22, 2013 3:48 am

ሰላም የአትሌቲክስ ስፖርት አፍቃሪዎች:-

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከሎንዶን እስከ ቻይና የውድድር ፈርጦች ሆነዋል::

ምንጭ:- Mirko Jalava (for the IAAF), Sunday 21 April 2015. Ethiopian double in Yangzhou.
በያንግዙ (ቻይና) በተደረገው የማራቶን ውድድር በሴቶች ወርቅነሽ ደገፋ : በወንዶች ያዕቆብ ጃርሶ አሸናፊዎች ሆነዋል::

ምንጭ:- Matthew Brown (for the IAAF), Sunday 21 April 2013. Kebede and Jeptoo shine in the London sun.
ፀጋዬ ከበደ የዘንድሮው የሎንዶን ማራቶን አሸናፊ ሆኗል.

አትሌቶቻችን በርቱ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Previous

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: Bing [Bot] and 2 guests