ኢትዮጵያ 0 - አይቮሪኮስት 1

ስፖርት - Sport related topics

ኢትዮጵያ 0 - አይቮሪኮስት 1

Postby admasradio » Tue Nov 10, 2009 4:46 pm

ሰላም በያላ ች ሁበት

ታዋቂው የስፖርት ጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ በስኩዋር ህመም የተነሳ የሁለት አይኑን ብርሀን ለማጣት በቅቷል:: ሀኪሞቹ ውጭ አገር ሄዶ ካልታከመ በፍጹም አይደንም ብለዋል::

ባሁኑ ሰአት እቤት ውስጥ ነው - መውጣት አይችልም:; ቅዳሜ የአድማስ ሬዲዮ እንግዳ ሆኖ ይቀርባል::

ተከታተሉት - የምንችለውን እናደርግለን ዘንድ እንተባበር::

አድማስ ሬዲዮ
Last edited by admasradio on Fri Dec 10, 2010 4:53 pm, edited 1 time in total.
The #1 Ethiopian infotainment radio in USA

Every Saturday from 2-6 pm (Eastern time) @1100AM(Atlanta) .... or LIVE at www.admasradio.info or LIVE from your cell phone (951) 262 4343 code 193902#
admasradio
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 169
Joined: Tue Mar 18, 2008 11:39 pm

Postby ሞፊቲ » Wed Nov 11, 2009 4:02 am

ምንድነው የማነበው?በናታችሁ ውሸት ነው በሉኝ?ሁለት አይኑን አጣ?......................ኦ አምላኬ!
ሞፊቲ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 837
Joined: Thu Dec 15, 2005 9:18 pm

Postby አሹ78 » Wed Nov 11, 2009 5:33 am

:( :( :( :( በጣም ያሳዝናል :( :( :( :( :( :(
Never trade what you want at the moment for what you want the most
አሹ78
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 75
Joined: Tue Feb 01, 2005 5:22 am
Location: united states

Postby እዮባ » Fri Nov 13, 2009 9:08 pm

ወይኔ ደምሴ
በኢትዮጵያ እግር ኳስ እንደተቃጠለ ኖሮ...
A+T ርኛ

MY THINKING IS CLEAR, MY SPEECH IS CRYPTIC.
እዮባ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 906
Joined: Sat Jun 20, 2009 3:30 am
Location: In the state of peace

Postby እንደጉድ! » Tue Nov 24, 2009 9:22 pm

ደምሴ ስለ ህመሙ ሲናገር እና እርዳታ ሲጠይቅ እዚህ ተመልከቱ: http://www.ethiotube.net/video/6749/ETV-Sport-News-112309--Radio-icon-Demissie-Damte-needs-help

:(
«አትናገር ብዬ ብነግረው፣ አትናገር ብሎ ነገረው።»
እንደጉድ!
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 380
Joined: Fri Sep 19, 2008 4:16 pm

Postby ተድላ ሀይሉ » Thu Feb 18, 2010 1:20 am

---
Last edited by ተድላ ሀይሉ on Thu Feb 18, 2010 3:32 am, edited 1 time in total.
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Thu Feb 18, 2010 1:25 am

ሰላም ውድ ወገኖቼ ኢትዮጵያውያን :-

ኡፎይይይይይይ ....

ደምሴ ዳምጤ የጤንነቱ ሁኔታ በከፊልም ቢሆን ተሻሽሎ ወደሚወዳት አገሩ ተመልሷል :: ዓይኑ በከፊል ያያል : ያልታሰበ የኩላሊት ሕመም ችግር አጋጥሞት ነበር ያም ተሽሎታል :: ብቻ ደስ የሚል የምሥራች ነው ::

ሙሉ ዘገባውን በረቡዕ የካቲት 10 ቀን 2002 ዓ.ም. የወጣው ሪፖርተር ጋዜጣ የስፖርት ዓምድ ቃለ-መጠይቁን ይዞ ቀርቧል ::

"በወጣቶች ጭንቅላት ዘር የሚዘራ ሙያተኛ የለም" ጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ

Wednesday, 17 February 2010 15:12
ለሙያው አቅሙ የፈቀደውን ሁሉ አድርጓል፤ እያደረገም ነበር፡፡ ከወራት በፊት የዓይን ብርሃኑ ድንገት የእለት ተግባሩን ያቆማል፡፡ የሙያ አጋሮቹ፣ አድናቂዎቹና የስፖርቱ ቤተሰብ አዘኑ፡፡

ጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ፤ የዓይን ብርሃኑን ወደ ቀድሞ ተግባሩ ለመመለስ በሀገር ውስጥ ሕክምና እንደማይቻል ሲነገረው የተሰማውን ሲያስታውስ እምባ ይተናነቀዋል፡፡ ዛሬ "በአምላክ ቸርነትና በወገኔ ፀሎት ከጨለማ ወደ ብርሃን ተመልሻለሁ" ይላል፡፡ በስፖርት ጋዜጠኝነት ከ40 ዓመት በላይ ያገለገለው ደምሴ ዳምጤ ለዓይኑ ሕክምና ከሄደበት ባንኮክ ባሳለፍነው ሣምንት መጨረሻ ወደ አገሩ ተመልሷል፡፡ ደረጀ ጠገናው አነጋግሮታል፡፡

ሪፖርተር፡- ጤንነትህ የተመለሰ ይመስላል?

ጋዜጠኛ ደምሴ፡- በወገኔ ጸሎት እዚህ ደርሻለሁ፡፡

ሪፖርተር፡- ሕክምናው እንዴት ነበር?

ጋዜጠኛ ደምሴ፡- በአገር ውስጥ ተከታትዬ እንደማይቻል ከተነገረኝ በኋላ በሕዝብ ድጋፍና ከባለሀብቶች በተደረገልኝ ድጋፍ ወደ ባንኮክ ተጉዤ ሕክምና አድርጌ ከጨለማ ወደ ብርሃን ተስፋ መጥቻለሁ፡፡

ሪፖርተር፡- ባንኮክ እንደደረስክ የሕክምናው ጉዳይ አስተማማኝ እንዳልነበር ተነግሯል፡-

ጋዜጠኛ ደምሴ፡- እንደደረስኩ መጀመሪያ የመረመሩኝ ሐኪሞች ተጓዳኝ በሽታም ስለነበረብኝ የዓይኔ ሕክምና ተስፋ እንደሌለው ነገሩኝ፡፡ ተስፋ ቆርጬ ወደ አገሬ መመለስ እንዳለብኝ ወስኜ እያለሁ እኔ ታምሜ ወደ ባንኮክ መምጣቴን የሰሙ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ተስፋ መቁረጥ እንደሌለብኝ በነገሩኝ መሠረት፣ በዚያው ከዓይን ሕመም ጋር በተያዘ የስኳር በሽተኞችን የሚያክሙ ሌላ ዶክተር አግኝቼ ሳነጋግር ተስፋ እንዳለኝ ተነገረኝ፡፡ ወደ ቦታው ሔጄ ሕክምናውን እንድጀምር ተደረገ፣ የአምላክ ቸርነት ሆኖ ጨልሞ የነበረው ብርሃኔ ተስፋ ሰጠኝ፡፡ በወቅቱ ብርሃኔ ሲመለስ ማመን አልቻልኩም ነበር፡፡ ምክንያቱም ምግብ መመገብ የምችለው በባለቤቴ እጅ ነበር፡፡ በእጄም ለመመገብ በቃሁ፡፡

ሪፖርተር፡- ሕክምናውን አጠናቀህ ነው የተመለስከው?

ጋዜጠኛ ደምሴ፡- ከሦስት ወር በኋላ እንደገና ለመመርመር እሄዳለሁ፡፡ መጀመሪያ ምርመራውን ያደረጉልኝ ዶክተር ግራ ዓይኔ ሙሉ ለሙሉ እንደማይሰራ፣ ቀኜ ግን 20 ከመቶው ጭላንጭል እንደነበረው ያንን ወደ 50 በመቶ ከፍ ለማድረግ እሞክራለሁ በሚል ነበር ተስፋ የሰጡኝ፡፡ የሚገርመው መታመሜ ብቻ ሳይሆን ከሐኪም ሐኪም የሚለያይ መሆኑን መረዳቴ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- አሁን በራስህ መሄድ ትችላለህ?

ጋዜጠኛ ደምሴ፡- መሔድ ብቻ ሳይሆን ጎላ ጎላ ብሎ የተጻፈ ጽሑፍ ማንበብ ሁሉ እችላለሁ፡፡ ሐኪሟ እንዳሉት የዓይኔ ብርሃን ወደ 50 በመቶ ከፍ ካለ በተሻለ ሁኔታ እንደምገኝ ተስፋ አለኝ፡፡ የወገኔ ጸሎትም ይረዳኛል፡፡

ሪፖርተር፡- ተጓዳኝ ሕመም እንዳለብህ ገልጸሀል፡፡ የሕመሙን ዓይነት ልትገልጽ ትችላለህ?

ጋዜጠኛ ደምሴ፡- በከፍተኛ ሁኔታ ተጎድቶ የተገኘው "ኩላሊቴ" ነው፡፡ ከዚያን በፊት ምንም ዓይነት የህመም ስሜት አልነበረኝም፡፡ እንዴት ሆኖ እዚያ ደረጃ እንደደረሰ አስገርሞኛል፡፡ ራሴን የመከታተል ድክመት እንደነበረብኝም የተረዳሁት አሁን ነው፡፡ ሁለተኛው "ስኳር" አለብኝ፣ ግፊትም እንደዚያው፡፡ የሚገርመው ግን እነዚህ በሽታዎች ከዓይን ሕመም ጋር ተያያዥነት አላቸው፡፡ ወገኖቼ ችላ ብለው እንዲህ ዓይነት ችግር ውስጥ እንዳይገቡ ተሞክሮዬን ሳልገልጽ አላልፍም፡፡ አሁን ግን ሁሉም በሕክምናው መፍትሔ አግኝተዋል፡፡ እዚህ ላይ ሳልገልጽ የማላልፈው ለአገራችን የሕክምና ሙያተኞች አክብሮት መስጠት እንዳለብን ነው፡፡ ምክንያቱም መጀመሪያ እንደታመምኩ እዚህ ሚኒሊክ ሆስፒታል ስታከም ዶክተር ትልቅሰው ተሾመ የነገሩኝን ባንኮክ የሚገኙት የሕክምና ሙያተኞች በተመሳሳይ ነግረውኛል፡፡

ሪፖርተር፡- ዶክተር ትልቅሰው ምን ነበር ያሉህ?

ጋዜጠኛ ደምሴ፡- "ዓይንህ እየደከመ ነው፡፡ ወደ ውጭ ሄደህ መታከም ካልቻልክ መጥፎ ነው፡፡ አገር ውስጥ መድኃኒቱ የለም፡፡ ካልሆነ ደግሞ መድኃኒቱን ማስመጣት ከቻልክ" ብለው ሊያክሙኝ እንደሚችሉ ነበር የነገሩኝ፡፡ በተለይ ግራ ዓይኔን እንድጠነቀቅ ነበር ያስረዱኝ፡፡ ባንኮክ ሄጄ የተወጋሁት መርፌ እሳቸው ከመሄዴ አንድ ዓመት በፊት ያዘዙልኝ ነው፡፡ በዚህም ለአገሬ ሙያተኞች ክብር አለኝ፡፡

ሪፖርተር፡- ለሕመምህ "ጥሬ ስጋ" መውደድህ ምክንያት ነው የሚሉ ወገኖች አሉ፡-

ጋዜጠኛ ደምሴ፡- ሳቅ . . . መነሻው ጥሬ ስጋ ሊሆንም፤ ላይሆንም ይችላል፣ የሆነ ሆኖ ግን ስጋ እወድ ነበር፡፡ በተለይ ጮማ፡፡ ይኽ ደግሞ ለስኳር አደገኛ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- አሁንስ?

ጋዜጠኛ ደምሴ፡- ከዓመት በፊት ነው የተለያየነው፡፡ በመንገድ ላይ ሳልፍ ስመለከት ነሸነጥ ቢያደርገኝም፣ እያዘንኩ ከማለፍ በስተቀር አማራጭ የለኝም፡፡ ስናደድ ገላምጬው አልፋለሁ፡፡

ሪፖርተር፡- እስከ ቀጠሮህ ሕመምህን የምትቆጣጠርበት ሁኔታ አለ?

ጋዜጠኛ ደምሴ፡- መድኃኒትም ሆነ ለክትትል የሚያመቸኝን መሣሪያ ሳይቀር ይዤ ነው የመጣሁት፡፡ እግረ መንገዴን ሙያተኛ እንዳልሆን . . . ሳቅ፡፡

ሪፖርተር፡- ከሙያህ ጋር በተያያዘ ያለህ አስተያየት ምንድነው?

ጋዜጠኛ ደምሴ፡- ፍቅሩ አለኝ፣ ግን . . . እንጃ፣ ምክንያቱም 27ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ግብጽና አልጄሪያ ያደረጉትን ጨዋታ መመልከት ፈልጌ ባለመቻሌ አዝኛለሁ፡፡ በባለቤቴ አስተርጓሚነት ሞክሬ አልጥምህ አለኝ ያን ቀን በጣም ከፋኝ . . .፡፡

ሪፖርተር፡- በሙያው እያለህ ከሁለቱ አገሮች ጋር በተያያዘ ገጠመኝ አለህ?

ጋዜጠኛ ደምሴ፡- ከ20 ዓመት በፊት ለያዘኝ ስኳር ምክንያቱ የግብጽ ብሔራዊ ቡድን የኢትዮጵያ አቻውን 6 ለ 1 ያሸነፈበት ነው፡፡ ምክንያቱም በወቅቱ ያንን ጨዋታ የተከታተልኩት እኔ ነበርኩ፡፡ ለተወሰነ ጊዜ ታምሜ ሐኪም ቤት ገብቻለሁ፡፡ ሽንፈቱ እስከአሁን በውስጤ አለ፡፡

ሪፖርተር፡- የምትወደው ሙያ መሆኑን ገልጸሀል፣ በተቃራኒው ደግሞ ስፖርቱ በተለይ እግር ኳስ አሳዛኝ ውጤት ላይ ደርሷል፡፡ ምን ይሰማሃል?

ጋዜጠኛ ደምሴ፡- ውስጤን ጎድቶታል፣ ይህንን በቅርብ የማያውቁት ደግሞ ቤተሰቦቼ ናቸው፡፡ በዚህም በተለይ እግር ኳሱ እኔን እዚህ እንድደርስ የጎላ ድርሻ አለው፡፡ እኔን ብቻም አይደለም ብዙ የተጎዱ ወገኖች አሉ፡፡ ምክንያቱም እግር ኳስን መውደድ ብቻ ሳይሆን መጫወት የሚችሉ ወጣቶች አሉን፡፡ ችግሩ መሠረት አጣጣላችን ይመስለኛል፡፡ የማያሳፍሩ ተተኪዎችን ለማፍራት የሚያስችል ፕሮጀክት ቀርፆ፣ በወጣቶች አለማመን፣ የስፖርት ትምህርት ቤቶችና ለዚያ ብቃት ያላቸው ሙያተኞች አለመኖር ችግር ይመስለኛል፡፡ ሌሎች አገሮች ያደጉበትን መንገድ ስናይ እኛ በሌለን ነገር ታምር እንጠብቃለን፡፡ መሰራት ያለበትን ነገር አልሰራንም፡፡ የምናጭደው የዘራነውን ነው፡፡ ያልዘራነውን መጠበቅ ደግሞ ከየዋህነት ያለፈ ትርፍ ያለው አይመስለኝም፡፡ በርካታ እግር ኳስን የሚወዱ ወጣቶች አሉን፡፡ በእነዚህ ወጣቶች ጭንቅላት ዘር የሚዘራ ሙያተኛ የለንም፡፡ በዘርፉ የተማረ የሰው ኃይል የለንም፡፡ በአሁኑ ሰዓት እጅግ የሚያበረታታ በኦሮሚያ ክልል የተጀመረ ነገር አለ፡፡ እንደዚህ ዓይነቱን ጅምር ማበረታታት፣ መደገፍና ማስፋፋት ያስፈልጋል፡፡ ከሰራን እናድጋለን፡፡ አደጉ የምንላቸው ማናቸውም ሰርተው እንጂ በምኞት አይደለም፡፡

ሪፖርተር፡- አለን የምንለው አትሌቲክስም ስጋት እንዳንዣበበበት ነው፡-

ጋዜጠኛ ደምሴ፡- በወጣቶች ላይ ማመን አትሌቲክሱንም ይመለከታል፡፡ ጥቂት ውጤታማ አትሌቶችን ይዘን የመሄድ አዝማማያ አለ፡፡ አያዋጣም፣ ታዋቂዎቹን ተኩም፤ አልተኩም ማሳተፍ ያስፈልጋል፡፡ ታዋቂዎቹም ቢሆኑ ሊተጉና የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የሚጥሩት ከስር የሚወጡ ተተኪዎች ሲኖሩ ነው፡፡ የመገናኛ ብዙኃን እንደዚህ ነው ሲሉ ኩርፊያና የመሳሰሉት ገጥሞኛል፡፡ ክህሎት ያላቸው ክልሎች ለምን አይዳሰሱም? የሚለው ለስፖርቱ ኃላፊዎች የሚጥም ጥያቄ አይደለም፡፡ ሚዲያ ለስፖርቱ ትልቅ ኃይል ነው፡፡ ሚዲያና ስፖርት ተያያዥ ናቸው፡፡ በዚህ የተነሳ ስሜቴን የነካ ነገር ገጥሞኛል፡፡ እኔ የ13 ዓመት ልጅ እያለሁ ነው ጋዜጠኝነትን የጀመርኩት፡፡ 40 ዓመት ሰርቻለሁ፡፡

ሪፖርተር፡- በሰራህባቸው ዓመታት ረክቻለሁ የምትለው፣ አልያም ይቆጨኛል የምትለው ነገር አለ?

ጋዜጠኛ ደምሴ፡- በስፖርቱ በተለይ እግር ኳስ ላይ ያዘንኩበት ካልሆነ የረካሁበት ጊዜ አልገጠመኝም፡፡ ምክንያቱም ቀደም ሲል እንደገለጽኩት ለስፖርቱ ተገቢው ትኩረት ባለመሠጠቱ ይመስለኛል፣ ስፖርቱ ዛሬ እዚህ ደረጃ ላይ ሊገኝ ችሏል፡፡ የአፍሪካ እግር ኳስ መስራች ነን፡፡ በአትሌቲክሱ በእነ አበበ ቢቂላ የጥቁር ሕዝብ ፋና ወጊ ነን፡፡ እነዚህ ሲታዩ የበለጠ ብንሰራ ኖሮ የሚለው ሁሌም የውስጥ ቁስል ይሆንብኛል፡፡ ስፖርት የሚፈጥረውን ገጽታ ማንም አይፈጥረውም፡፡ የኢትዮጵያን የውጭ ገጽታ የሚያበላሹ ብዙ ነገሮች እንሰማለን፡፡ በአትሌቶቻችን ድል ነው የአገራችን መልካም ገፅታ እየተገነባ ያለው፡፡ ስለዚህ ይህንንም እንዳናጣ እሰጋለሁ፡፡ በተለይ በእግር ኳሱ፡፡

ሪፖርተር፡- ወደ ተለያዩ አገሮች ተጉዘሃል፣ እንደገጠመኝ የምታስታውሰው አለ?

ጋዜጠኛ ደምሴ፡- ስፖርት የሚፈጥረውን ስሜት በምንም አታገኘውም፡፡ በተጓዝኩባቸው አገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ የኢትዮጵያ ስፖርተኞች በሚያገኙት ድል አንገታቸውን ቀና አድርገው ሲሄዱ፣ ሲሸነፉ ደግሞ የሚሰማቸውን ሁሉ ተመልክቼያለሁ፡፡ በዚያን ሰዓት የሚሰማኝ ለእኔ የተለየ ቦታ አለው፡፡ ሌላው በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሌላው ዘርፍ እንደሚያደርጉት የወገን አለኝታነት የአገራቸውን ስፖርት ለመታደግ በፋይናንስ ሲደጉሙ አይታዩም፡፡ ይህም ይቆጨኛል፡፡ በድላቸው እንደሚደሰቱ ሁሉ በችግሩም ተካፋይ መሆን ከቻሉ ለውጥ ይመጣል፡፡ ውጭ ያለው ኢትዮጵያዊያን ውጤት ሲጠፋ ሲያለቅሱ አይቻለሁ፡፡ ውጤት ሲገኝ ደግሞ ሲደሰቱ አይቻለሁ፡፡ ለአንድ አገር ጤናማ ዜጋ ለመፍጠር መሠረቱ ስፖርት ነው፡፡ በስፖርት የዳበረን አካል በሽታ አይበግረውም፡፡ ዛሬ ስንቱ ወጣት ነው ይህን የሚያውቀው? ወደ ስፖርት ሜዳ ከመሄድ ይልቅ ወደ ክሊኒክ የሚሄደው ወጣት ቁጥር እየበረከተ ነው፡፡


ሪፖርተር ጋዜጣ : ረቡዕ የካቲት 10 ቀን 2002 ዓ .ም . ::"በወጣቶች ጭንቅላት ዘር የሚዘራ ሙያተኛ የለም" ጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ ::

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby እንደጉድ! » Sat Feb 20, 2010 3:40 am

«አትናገር ብዬ ብነግረው፣ አትናገር ብሎ ነገረው።»
እንደጉድ!
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 380
Joined: Fri Sep 19, 2008 4:16 pm

Postby admasradio » Fri Dec 10, 2010 4:41 pm

በሴካፋ ውድድር ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ከአይቮሪኮስት ጋር ተጋጠመ - ቢያሸንፍ ለዋንጫ ያልፍ ነበር ... ግን 1 - 0 ተሸንፎዋል .... ዝርዝሩን ቅዳሜ አድማስ ሬዲዮ ላይ ይጠብቁ ...
The #1 Ethiopian infotainment radio in USA

Every Saturday from 2-6 pm (Eastern time) @1100AM(Atlanta) .... or LIVE at www.admasradio.info or LIVE from your cell phone (951) 262 4343 code 193902#
admasradio
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 169
Joined: Tue Mar 18, 2008 11:39 pm


Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests