ሰላም ውድ ወገኖቼ :-
ኢትዮጵያ የአፍሪቃ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን ከመሠረቱት 4 አገሮች አንዷ ነች :: ግብጽ እና ደቡብ አፍሪቃ በስፖርቱም ዕድገት ሆነ በዓለም አቀፍ ተሣትፏቸው ከፍተኛ መሻሽል ሲያሣዩ ሱዳን እና ኢትዮጵያ ቁልቁል ሲጓዙ ኖረዋል :: ሆኖም ሱዳን በትንሹም ቢሆን የተሻለ እንቅስቃሴ ታደርጋለች :: በኢትዮጵያ ግን በአንድ ክለብ ከማመን አባዜ ጋር በተያያዘ ለረዥም ዘመናት የእግር ኳሱ ስፖርት ዕድገት እንደ ካሮት ወደመሬት ሆኖ ዘልቋል :: ይኼ ሣያንስ ወያኔ ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረ ጀምሮ የጎሣው ፖለቲካ እግር ኳሱንም ሲያምስ እና ሲያተራምስ እናያለን :: ይባስ ብሎ በወያኔ የትውልድ መንደር ደደቢት ሥም የተቋቋመ ቡድን በግድ ዋንጫ ይብላ ተብሎ በጥሎ ማለፍ የፍጻሜ ውድድር ላይ ለ5 የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን ተጫዋቾች የቀይ ካርድ በማደል ዋንጫውን ለለገሠ (መለስ) ግልገል ቡችሎች አስረክበዋል :: ለምን ከመጀመሪያውኑ ይህ ዋንጫ የደደቢት ቡድን የግል ንብረት ነው ብለው አያሣውቁም ነበር ?
እስኪ ይህንን አሣፋሪ ትዕይንት ተመልከቱት ...
ምንጭ:- ETV Sport News - St George players beat up a referee and five of them get red card
ተድላ