የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ቡድን-በ20ኛው የዓለም ዋንጫ ...

ስፖርት - Sport related topics

የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ቡድን-በ20ኛው የዓለም ዋንጫ ...

Postby ተድላ ሀይሉ » Wed Jun 30, 2010 9:54 pm

ሰላም ውድ ወገኖቼ :-

ኢትዮጵያ የአፍሪቃ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን ከመሠረቱት 4 አገሮች አንዷ ነች :: ግብጽ እና ደቡብ አፍሪቃ በስፖርቱም ዕድገት ሆነ በዓለም አቀፍ ተሣትፏቸው ከፍተኛ መሻሽል ሲያሣዩ ሱዳን እና ኢትዮጵያ ቁልቁል ሲጓዙ ኖረዋል :: ሆኖም ሱዳን በትንሹም ቢሆን የተሻለ እንቅስቃሴ ታደርጋለች :: በኢትዮጵያ ግን በአንድ ክለብ ከማመን አባዜ ጋር በተያያዘ ለረዥም ዘመናት የእግር ኳሱ ስፖርት ዕድገት እንደ ካሮት ወደመሬት ሆኖ ዘልቋል :: ይኼ ሣያንስ ወያኔ ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረ ጀምሮ የጎሣው ፖለቲካ እግር ኳሱንም ሲያምስ እና ሲያተራምስ እናያለን :: ይባስ ብሎ በወያኔ የትውልድ መንደር ደደቢት ሥም የተቋቋመ ቡድን በግድ ዋንጫ ይብላ ተብሎ በጥሎ ማለፍ የፍጻሜ ውድድር ላይ ለ5 የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን ተጫዋቾች የቀይ ካርድ በማደል ዋንጫውን ለለገሠ (መለስ) ግልገል ቡችሎች አስረክበዋል :: ለምን ከመጀመሪያውኑ ይህ ዋንጫ የደደቢት ቡድን የግል ንብረት ነው ብለው አያሣውቁም ነበር ?

እስኪ ይህንን አሣፋሪ ትዕይንት ተመልከቱት ...

ምንጭ:- ETV Sport News - St George players beat up a referee and five of them get red card

ተድላ
Last edited by ተድላ ሀይሉ on Sun Jun 09, 2013 1:38 pm, edited 22 times in total.
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby geremew » Thu Jul 01, 2010 3:26 am

ሰላም ተድላ
ስፖርት ስለምወድ ብቻ post ያረከውን link ተመለከትኩ:: በጣም አፈርኩኝ:: በሳላዲን እና በአዳነ ግርማ:: ለትልቅ ስፍራ ሲጠበቁ ዳኛን መደብደብ ምን ዋጋ እንደሚያስከፍላቸው አለማወቃቸው አፈርኩላቸው:: ተድላ አንተም ብትሆን ዳኛን መደብደብ ማበረታታት ያለብህ አይመስለኝም:: ወያኔ ምርጫን በማጭበርበር: ሰዎችን በማሰር: ወዘተ ተቃወም እንጂ የጊዮርጊስ ልጆች ባጠፉት ስህተት ዳኛውን ጥርስ መስበራቸውን ዘንግተህ ወያኔ ብለህ መተቸትህ ያስተዛዝባል:: የጽሁፎችህንም ተአማኒነት ጥያቄ ምልክት ውስጥ ይከተዋል::
geremew
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 285
Joined: Tue Dec 28, 2004 8:43 pm
Location: united states

Postby ተድላ ሀይሉ » Thu Jul 01, 2010 4:27 am

geremew wrote: ... ተድላ አንተም ብትሆን ዳኛን መደብደብ ማበረታታት ያለብህ አይመስለኝም:: ወያኔ ምርጫን በማጭበርበር: ሰዎችን በማሰር: ወዘተ ተቃወም እንጂ የጊዮርጊስ ልጆች ባጠፉት ስህተት ዳኛውን ጥርስ መስበራቸውን ዘንግተህ ወያኔ ብለህ መተቸትህ ያስተዛዝባል:: የጽሁፎችህንም ተአማኒነት ጥያቄ ምልክት ውስጥ ይከተዋል::


ውድ ወንድሜ :-

"በሌለ እግር ኳስ ጨዋታ ..." ብዬ ርዕስ ያወጣሁት ለዚያ ነው ::

የኢትዮጵያን እግር ኳስ ቁልቁል እንደ ካሮት ዕድገት እንዲያሽቆለቁል ምክንያት የሆኑት ቀዳሚዎቹ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ናቸው ::

የደደቢት ቡድን ዋንጫ እንዲበላ ተብሎ 5 ተጨዋቾችን ከሜዳ እንዲያስወጣ ትዕዛዝ የተቀበለው ዳኛ ሥህተት ነው :: ነገሩ እንደተለመደው የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን አሸናፊ ቢሆን ኖሮ እንደተለመደው 'ሣንጆርጅ አንበሣው ዋንጫዎችን ሁሉ ጠቀለላቸው ::" ተብሎ ይፎከር እንደነበረ አምናለሁ ::

የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን ተጫዋቾች ዳኛውን መደብደባቸው ሙሉ በሙሉ ጥፋት ነው :: ዳኛውም ከበላይ የፖለቲካ አለቆቹ ትዕዛዝ ተቀብሎ ቀይ ካርድ ማደሉ እኩል ጥፋት ነው ::

የደደቢት ቡድን በቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን ላይ ያጠላ አዲሱ 'ጊዮርጊስ' ስለሆነ በዚያ የተለመደ አድሏዊነት ያለበት መንገድን ተከትሎ የሚሰበሰብ ዋንጫ ለእኔ ዓይነቱ ስፖርት አፍቃሪ ከስፖርት ውድድር መንፈስ ውጪ ስለሆነ አልቀበለውም ::

አሁንስ አቋሜ ግልፅ ሆነልህ ?

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Re: በሌለ እግር ኳስ ጨዋታ የወያኔ ደደቢት ቡድን አሸናፊነት

Postby ባሩክ ዮዳሄ » Thu Jul 01, 2010 9:38 am

ተድላ ሀይሉ wrote:ሰላም ውድ ወገኖቼ :-

ኢትዮጵያ የአፍሪቃ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን ከመሠረቱት 4 አገሮች አንዷ ነች :: ግብጽ እና ደቡብ አፍሪቃ በስፖርቱም ዕድገት ሆነ በዓለም አቀፍ ተሣትፏቸው ከፍተኛ መሻሽል ሲያሣዩ ሱዳን እና ኢትዮጵያ ቁልቁል ሲጓዙ ኖረዋል :: ሆኖም ሱዳን በትንሹም ቢሆን የተሻለ እንቅስቃሴ ታደርጋለች :: በኢትዮጵያ ግን በአንድ ክለብ ከማመን አባዜ ጋር በተያያዘ ለረዥም ዘመናት የእግር ኳሱ ስፖርት ዕድገት እንደ ካሮት ወደመሬት ሆኖ ዘልቋል :: ይኼ ሣያንስ ወያኔ ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረ ጀምሮ የጎሣው ፖለቲካ እግር ኳሱንም ሲያምስ እና ሲያተራምስ እናያለን :: ይባስ ብሎ በወያኔ የትውልድ መንደር ደደቢት ሥም የተቋቋመ ቡድን በግድ ዋንጫ ይብላ ተብሎ በጥሎ ማለፍ የፍጻሜ ውድድር ላይ ለ5 የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን ተጫዋቾች የቀይ ካርድ በማደል ዋንጫውን ለለገሠ (መለስ) ግልገል ቡችሎች አስረክበዋል :: ለምን ከመጀመሪያውኑ ይህ ዋንጫ የደደቢት ቡድን የግል ንብረት ነው ብለው አያሣውቁም ነበር ?
እስኪ ይህንን አሣፋሪ ትዕይንት ተመልከቱት ...

ምንጭ:- ETV Sport News - St George players beat up a referee and five of them get red card

ተድላመቸም እባቡ መለሰና የኢቭል ስራው በኢትዮፒያ ውስጥ እያለ
ኢትዮፒያ ውስጥ እንኮን የስፖርት ነጻነት ሊኖር ቀርቶ ህዝባችን
የዕለት ምግብ እንኮን የሚያገኘው ከውጭ ከዘመዶቻቸው ከሚላክለት
እርዳታ ነው:: ስለዚህ የኢትዮፒያ እግር ኮስ ቁልቁል ቢወርድ
ጨርሶ የሚያስደንቅ አይደለም::

ነገር ግን አንድ የገረመኝ ነገር ቢኖር እነዚህ ሰዎች
ደደቦችም ሆኑ ሰዎች የተጫወቱበት የከብት ማጎሪያ ነው
ወይንስ ትክክኛ የእግር ኮስ ሜዳ ነው? :shock: :shock: :shock: :shock: :shock:
ባሩክ ዮዳሄ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 801
Joined: Sun Mar 15, 2009 4:07 am

Postby እዮባ » Thu Jul 01, 2010 5:13 pm

አፈርኩባቹ...................ምድረ ሸፋፋ ደሞ ጊዮርጊሶች የት እግር ኳስ አውቀው ነው?.................እድሜ ለአላሙዲን በብር ሀይል በግድ የኢትዮጵያን ሊግ እያሸነፉ ውጪ ሲወጡ የሱዳንን ክለብ እንኳን ማሸነፍ አቅቷቸዋል...............አሁን ከነሱ የሚበልጥ ሲገኝ ምን ኮምፕሌክስ መሆኑ ነው? ሽንፈትን አምነው የማይቀበሉ..............የነሱ ጥጋብ የጀመረው እኮ ዛሬ አይደለም.............ያኔ ከፕሪምየር ሊግ አንሳተፍም ብለው ከወጡ ጊዜ ጀምሮ ነው......................የሚገርመኝ ደሞ የናንተ እዚህ ያላቹ ቦርጫሞች ቱልቱላ መንፋት ነው......................................በረኛው ሆን ብሎ ከመስመር ውጪ ኳስ በእጁ ሲይዝ በቀይ ለምን ተሰጠው? የዳኛውን ጥርስ በቴስታ መቶ ታድያ ምን ጎበዝ ሊባል ነበር? የኛ ኳስ አዋቂዎች..................ደሞ እነሱን ብሎ ኳስ ተጫዋቾች..........አውሮፓ አይደለም ዌስት አፍሪካ ቢሄዱ እኮ ሶስተኛ ዲቪዝዮን ክለብም አይመረጡም...................እኔን የሚያሳዝነኝ ያንን አስቀያሚ ማልያ ለብሰው በዚህ አስቀያሚ አቋማቸውና አስቀያሚ አጨዋወታቸው ኢትዮጵያን ሲያሰድቡ ማየቴ ነው.............
A+T ርኛ

MY THINKING IS CLEAR, MY SPEECH IS CRYPTIC.
እዮባ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 906
Joined: Sat Jun 20, 2009 3:30 am
Location: In the state of peace

Postby ባሻ ብሩ » Sat Jul 03, 2010 11:39 am

ተድላ ግዙፉ ጅል :)
አንዱ ፖለቲካ ክፍል የፈሳውን ተቀብለህ አብረህ ትፈሳለህ... :) ዳኛው በቴስታ እየተደበደበ ቀይ ካርድ መስጠቱ ከበላይ የመጣለት ትእዛዝ ነው ትላለህ? በረኛው ከፍጹም ቅጣት ምት ክልል ውጭ ሁለት ግዜ በእጁ በመያዙ ቀይ ካርድ አይገባውም ትለናለህ... ትእዛዝ ነው ልትለን ይዳዳሀል .... አረ እንዴት ያለህ ያዛውንት ቀላል ነህ በፈጣሪ....? ጎግል ላይ ዜና ጎልጉሎ ማውጣት ብቻ ታላቅ አዋቂ የሚያስብልህ ይመስልሀል .... አረ ትንሽ ከአሉባልታ የዘለለ እንኩዋን ለማወቅ ሞክር...

ደደቢት ቡድን ዛሬ የመጣ ሳይሆን በጣም የቆየ ነው:: በዋነኛነት የሚታወቀውም ተጨዋቾችን በፕሮጀክት ይዞ ከልጅነታቸው በመኮትኮት ለታላላቅ ቡድኖች በማቅረቡ ነው.... አንተ በዘረኝነትና እርጅና በላሸቀው አይምሮህ ትላልቅ እና ትናንሽ እያልክ የምትመድባቸው ቡድኖች ከደደቢት ፕሮጀክት ወጣቶች መሀል ተጨዋቾችን በብዛት ይወስዳሉ .... ደደቢት ዋንጫ ወሰደም አልወሰደም ኢትዮጵያ ውስጥ በመልካምና አርአያነት ያለው ተግባሩ በሁሉም የሚወደስና የሚታወቅ አንጋፋ ቡድን መሆኑን እኮ ሁሉም ያውቃል .... የአንተ አይነት የሰው ሀገር ዝፍዝፍ ዘረኛና አጉል ፖለቲከኛ ተብዬ የአሉባልታ ፈረስ እያወቀ ቢደባብስም...

የጨዋታ ስነምግባር የሌለው ቡድን በምንም መልኩ ሊደገፍ አይችልም .... ዳኛው መሀል የሆኑት እኮ ስርአት ሊያስይዙ እና ሊቀጡ ነው... :roll: ዳኛ እየደበደቡ እየታዩ እንዴት አርገህ ነው የሰዉን አይን አስረህ ባሉባልታ ልታሳምነው የምትሞክረው? ቪድዮ እኮ ነው ያቀረብከው.... እንደወትሮው የአሉባልታ ጽሁፍ አደለም:: :)

በመጨረሻ ምክር ለታላቁ ጅል ተድላ - ስፖርት አፍቃር ነኝ ስላልክ ነው :lol:
ስፖርትን ካፈቀርከው ስራው... ተዘፍዝፈህ ብቻ አታውራው :lol:
ባሻ ብሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1834
Joined: Sat Feb 12, 2005 5:24 pm
Location: ዋርካ ቦተሊካ

Postby ተድላ ሀይሉ » Sat Jul 03, 2010 1:22 pm

ባሻ ብሩ wrote:ተድላ ግዙፉ ጅል :)
አንዱ ፖለቲካ ክፍል የፈሳውን ተቀብለህ አብረህ ትፈሳለህ... :) ዳኛው በቴስታ እየተደበደበ ቀይ ካርድ መስጠቱ ከበላይ የመጣለት ትእዛዝ ነው ትላለህ? በረኛው ከፍጹም ቅጣት ምት ክልል ውጭ ሁለት ግዜ በእጁ በመያዙ ቀይ ካርድ አይገባውም ትለናለህ... ትእዛዝ ነው ልትለን ይዳዳሀል .... አረ እንዴት ያለህ ያዛውንት ቀላል ነህ በፈጣሪ....? ጎግል ላይ ዜና ጎልጉሎ ማውጣት ብቻ ታላቅ አዋቂ የሚያስብልህ ይመስልሀል .... አረ ትንሽ ከአሉባልታ የዘለለ እንኩዋን ለማወቅ ሞክር...

ኧረ ለካ የፊፋ ባጅ ያለህ አጫዋች ነህ :P :P :P :P :P :P
ደደቢት ቡድን ዛሬ የመጣ ሳይሆን በጣም የቆየ ነው:: በዋነኛነት የሚታወቀውም ተጨዋቾችን በፕሮጀክት ይዞ ከልጅነታቸው በመኮትኮት ለታላላቅ ቡድኖች በማቅረቡ ነው.... አንተ በዘረኝነትና እርጅና በላሸቀው አይምሮህ ትላልቅ እና ትናንሽ እያልክ የምትመድባቸው ቡድኖች ከደደቢት ፕሮጀክት ወጣቶች መሀል ተጨዋቾችን በብዛት ይወስዳሉ ....

ይህ ማለት ዳኛውን በቴስታ የተማታውን ተጫዋች ይጨምራል ማለት ነው :roll:
ደደቢት ዋንጫ ወሰደም አልወሰደም ኢትዮጵያ ውስጥ በመልካምና አርአያነት ያለው ተግባሩ በሁሉም የሚወደስና የሚታወቅ አንጋፋ ቡድን መሆኑን እኮ ሁሉም ያውቃል .... የአንተ አይነት የሰው ሀገር ዝፍዝፍ ዘረኛና አጉል ፖለቲከኛ ተብዬ የአሉባልታ ፈረስ እያወቀ ቢደባብስም...

ቂቂቂቂቂ :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:
የጨዋታ ስነምግባር የሌለው ቡድን በምንም መልኩ ሊደገፍ አይችልም .... ዳኛው መሀል የሆኑት እኮ ስርአት ሊያስይዙ እና ሊቀጡ ነው... :roll: ዳኛ እየደበደቡ እየታዩ እንዴት አርገህ ነው የሰዉን አይን አስረህ ባሉባልታ ልታሳምነው የምትሞክረው? ቪድዮ እኮ ነው ያቀረብከው.... እንደወትሮው የአሉባልታ ጽሁፍ አደለም:: :)

እንኳንም አንተ በዓለም ዋንጫ ያላጫወትክ :P :P :P :P :P :P

በመጨረሻ ምክር ለታላቁ ጅል ተድላ - ስፖርት አፍቃር ነኝ ስላልክ ነው :lol:
ስፖርትን ካፈቀርከው ስራው... ተዘፍዝፈህ ብቻ አታውራው :lol:

አንተ የመረጥከውን ሠላማዊ ስፖርት መወዳደር እንችላለን : ይህን የምልህ በሙሉ ልብ ነው 8)

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ባሻ ብሩ » Sat Jul 03, 2010 1:32 pm

የዳኛውን ባጅ ሳታከብር እኔን ለምን ትጠይቀኛለህ? :lol:
አለም ዋንጫ ያላጫወትክ የምትለኝ አለም ዋንጫ ላይ እንዲህ ያለ ስርአት የለቀቀ ነገር አይተሀል እንዴ? የብራዚሉ ካካ እንኩዋን ተጨዋችና ዳኛ ሲደበድብ ታይቶ አደለም... የኮትዲቭዋሩን ተጨዋች ሆን ብሎ መንገድ ቢዘጋበትና ተጨዋቹ ወድቆ ቢንፈራፈር እኮ ነው በቀይ የተባረረው... :)

ሰላማዊ ስፖርት እና ሰላማዊ ያልሆነ ስፖርት ደሞ ምንድነው? :lol: ኦኬ.... ቦክስና MMA ን መሸሽህና ገበጣና ቼዝን መምረጥህ ነው? :lol:
ባሻ ብሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1834
Joined: Sat Feb 12, 2005 5:24 pm
Location: ዋርካ ቦተሊካ

Postby Monica**** » Sat Jul 03, 2010 2:31 pm

ተድላነት ስላም ነህ?
ደደቢት የሚባል ቡድን አለ ኢትዮጵያ ውስጥ?????
Are you guys serious????
Out of all names under the sun they named the team Dedebit????? :lol: :lol:
ደሞ ጊዮርጊስን ለቀቀ አድርጉ!!!!
ባይቆጭ ያንገበግባል!!! :P
Yesterday is history, tomorrow is mystery, but today is a gift and that is why they call it the present!!!
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby ገንዳው » Sat Jul 03, 2010 2:33 pm

Monica**** wrote:ተድላነት ስላም ነህ?
ደደቢት የሚባል ቡድን አለ ኢትዮጵያ ውስጥ?????
Are you guys serious????
Out of all names under the sun they named the team Dedebit????? :lol: :lol:
ደሞ ጊዮርጊስን ለቀቀ አድርጉ!!!!
ባይቆጭ ያንገበግባል!!! :P


:lol: :lol: :lol: :lol: :lol: ደደቢት በቦንብ የሚጫወቱ የደደቦች ስብስስብ ኳስ ሊጫወቱ ?
ገንዳው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 334
Joined: Thu Dec 23, 2004 3:46 am
Location: united states

Postby Monica**** » Sat Jul 03, 2010 2:43 pm

ዋው ተድልሽ ቪዲዮውን አየሁት
ጊዮርጊስ ምነው ማልያችው እንደዚህ የሚያስጠላ ሆነ???
ለነገሩ ከድሮውም የኛን አገር ፉትቦል ተከታትዬውም አላውቅም ጊዮርጊስንም የምደግፈው አባቴ ስለሚወደው ነበር!!!
ውይ ተጨዋቾቹ ግን ስውነታችው የተጎዳ ይመስላል ቅጭጭ ነገር ብለው....አይ ቤት ዩ ምንም አይነት ኖሪሽመንት የሚስጡዋችው አይመስለኝም ስሩ አውት ዘ ይር....ልክ ጨዋታ ሊኖራችው ሲል ምናልባት ይመግቧችው ይሆናል እንጂ!!!
ደደቢት ግን በጣም አስቆኛል ከምር ስድብ ይመስላል!!!!
የወያኒ ቡድን መሆን አለበት ልክ እነደነሱ ደደቦቹ መርጠው ሊሆን ይችላል....ናችው አላልኩም ስላማላቃችው ግን ሊሆን ይችላል ነው :lol: :lol:
Yesterday is history, tomorrow is mystery, but today is a gift and that is why they call it the present!!!
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby Monica**** » Sat Jul 03, 2010 2:44 pm

እውነትህን ነው ገንዳው???
ደደቢት ቴረሪስቶች ናችው ማለት ነው???? :lol: :lol:
ጥሩ ጠርጥሬያለሁ ማለት ነው :lol: :lol:
ገንዳው wrote:
:lol: :lol: :lol: :lol: :lol: ደደቢት በቦንብ የሚጫወቱ የደደቦች ስብስስብ ኳስ ሊጫወቱ ?
Yesterday is history, tomorrow is mystery, but today is a gift and that is why they call it the present!!!
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby ባሻ ብሩ » Sat Jul 03, 2010 5:33 pm

ሁለት መስተካከል ያለባቸው መስለው የታዩኝ ጉዳዮች ስለሆኑ ነው:: ኖ ኦፌንስ ቆንጅዬ...

1ኛ - ወያኔ ---- አደለም.... ወያኔ ---- ከተባለ ወያኔን ማንበርከክ አቅትዋቸው ኢንተርኔት ላይ የሸፈቱና በስተርጅና እንደህጻን የሚያደርጋቸው የተድላ ቢጤ የአሉባልታ ብቻ ፖለቲከኛ ተብዬዎች የደደቦች ---- ይባላሉ ማለት ነው:: :lol:

2ኛ. ቅዱስ ጊዮርጊስን በፊት የሚደግፉት ሰዎች እውነት አላቸው... ጠንካራና አቻ የማይገኝለት ቡድን ነበር .... አሁን ግን ተቃራኒ ነው.... በከባዱ በፋይናንስ እየተረዱ ተጨዋች እየገዙ ..... ብቻ የተሻለ ነገር እየተደረገላቸው እንደግመል ሽንት ወደውሀላ ብቻ .... ተጨዋቾቹ ቀጫጮች ከሆኑ መቀጨጭ ሲያንሳቸው ነው ... አብዛኞቹ ቃሚዎች ጠጪዎች አልፎ አልፎም አጫሾች ናቸው:: ይህን ማንም ያውቃል ..... ይህ የቢራ ብቻ ሳይሆን ያብዛኞቹ ክለብ ተጨዋቾች ሀላፊነት የጎደለው ድድብናቸው ናቸው::

ተድላ
አንተስ ሰውነትህ እንዴት ነው? ይሄኔ ሆድህ እንደካቦርተኒ ኩዋስ ተነርቶ እንዲህ የምትቸከችክባቸው እጆችህ እንደ እስቴኪኒ ሾለዋል :lol:

አንተ ባክ አፕ ምናምን እያገኘኽ ነው ገደል የገባኸው! የኔን ምክር ብትሰማ ይሻልሀል? አሉባልታ ቀንስ? ታሪክ አጫውተን ስለምታውቀው ብቻ :!: የማታውቀውን አዋቂ ለመባል አትዋሽ.... የሰው አይን አስረህ አትንቦጣረቅ ..... ምክሬን ስማ... አትሊስ ሰው ሆነህ እንኩዋን ብታልፍ...
ባሻ ብሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1834
Joined: Sat Feb 12, 2005 5:24 pm
Location: ዋርካ ቦተሊካ

Postby ባሻ ብሩ » Sat Jul 03, 2010 6:20 pm

ለ ብሄራዊ ቡድኑ መሻሻል እንዲህም እየተደረገ ነው:: አሁን የመጣ ዜና ነው::

ኢፊ ኦኖውራ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሊሆን ነው

Iffy Onoura chosen to coach Ethiopia
Glasgow-born former Gillingham, Huddersfield and Swindon striker Iffy Onoura has been named head coach of the Ethiopia national team.

The 42-year-old, who is of Nigerian descent, began his coaching career in 2004 with Walsall.

He was sacked by manager Paul Merson, who said he needed more experience, but later had coaching positions with Swindon, Lincoln and Gillingham.

Onoura also had spells as caretaker manager of all three clubs.

He was first-team coach with Gillingham and assistant to Peter Jackson at Lincoln but left Sincil Bank in 2008.

Onoura started his senior career with Huddersfield and went on to play for Mansfield Town, Gillingham, Swindon, Sheffield United, Wycombe Wanderers, Grimsby Town, Tranmere Rovers and Walsall.

He takes over the Walya Antelopes as they emerge from a time of turmoil in Ethiopian football.

The national team, who lie 123rd in the world rankings, were readmitted to international competition last year after a suspension that led to them being disqualified from the latest World Cup and Africa Cup of Nations tournaments.

In their last outing in the Africa Cup of Nations qualifying, Ethiopia finished bottom of their group.

There followed an internal feud over an attempt to sack Dr Ashebir Woldegiorgis as head of the Ethiopian Football Federation and that ultimately led to the Fifa suspension in 2008.


http://news.bbc.co.uk/sport2/hi/scotland/8785727.stm
ባሻ ብሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1834
Joined: Sat Feb 12, 2005 5:24 pm
Location: ዋርካ ቦተሊካ

Postby ዞብል2 » Sat Jul 03, 2010 6:35 pm

የደደቢት እግር ኳስ ቡድን ለውያኔዎች የመቻል ቡድን እንደ ማለት ነው.......ከሁለት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ብቸኛ ፕሮፌሽናል ቡድን ለመሆን እንቅስቃሴ እያደረገ ለመሆኑ በመኮንኖች ክበብ ባደረገው መጠነ ሰፊ ቅስቀሳ አስታዉቆ ነበር :P

እስቲ እግዜር ያሳያችሁ አንድ ቡድን ብቻውን በስም ብቻ ፕሮፌሽናል ሲሆን :P ለነገሩ ፕሮፌሽናል የሚለውን ቃል ትርጉም አለማወቃቸው ነው እንጂ ስራቸው እግር ኳስ(ስፖርት) እስከሆነ ድረስ ምንም እንቅሳቃሴ አይስፈልጋቸውም ::


አይ ደደቢቶች :P ዋርካ ላይ እንደ ባሻ ዓይነት መጋዣ ጠበቃ አላችሁ :P ከሁሉ ግን ብቸኛው የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ቡድን ለመሆን የሚለው አባባል አይመስጥም :wink: :P :lol: :lol:


ዞብል ከአራዳ
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2436
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Next

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests