የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ቡድን-በ20ኛው የዓለም ዋንጫ ...

ስፖርት - Sport related topics

Postby ተድላ ሀይሉ » Fri Feb 22, 2013 4:22 pm

ሰላም የእግር ኳስ ስፖርት አፍቃሪዎች:-

ስለአፍሪቃ ዋንጫ ብዙ እንዳንወያይ ዋርካ በቫይረስ ተበከለችና ሣይሣካ ቀረ:: ለዛሬ ከኢትዮጵያ የእግር ኳስ ተጨዋቾች የቅርብ ጊዜ እንቅስቃሴ:- ከአራት ቀናት በፊት ፍቅሩ ተፈራ በካይዘር ቺፍስ ቡድን ላይ ያገባትን ድንቅ ጎል አገባብ እንድትኮመኩሙ እጋብዛችኋለሁ::

ምንጭ:- 2013championsleague. Goal of the year: Fikru Tefera AMAZING VOLLEY GOAL (Free State Stars) vs Kaizer Chiefs 18-02-2013.

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Sat Jun 08, 2013 4:05 pm

ሰላም የእግር ኳስ አፍቃሪዎች:-

የኢትዮጵያ ጥቁር አንበሶች የቦትስዋናን ቡድን 2 ለ 1 በማሸነፍ በሚመጣው ዓመት በብራዚል ለሚደረገው የዓለም ዋንጫ ለማለፍ የሚያስችላቸውን ዕድል አስፍተዋል:: ለኢትዮጵያ ቡድን ጎሎቹን ያስቆጥሩት: ጌታነህ ከበደ በ33ኛው ደቂቃ : ሣላዲን ሰዒድ በ45ኛው ደቂቃ ሲሆን ለቦትስዋና የማጽናኛዋን ጎል ቴቦጎ ሴምቦዋ በ76ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል:: በዚህ እርምጃቸው ከቀጠሉ ጥቁር አንበሶችን በብራዚሉ የዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ውድድሮች እናያቸው ይሆን?

መልካም ዕድል ለጥቁር አንበሶች !!!

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Mon Jun 17, 2013 12:16 am

ሰላም ለአግር ኳስ ስፖርት አፍቃሪዎች:-

ጥቁር አንበሶች አንድ ትልቅ እርምጃ ወደፊት ተራምደዋል:: በመጨረሻው ሦሥተኛ ዙር አሸናፊ ሆነው ለብራዚሉ የዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ውድድር እንዲበቁ እመኛለሁ::

ምንጭ:- የዛሬው ጨዋታ ጎሎች : lonelyninjas1, Ethiopia Vs South Africa 2-1 All Goals and Highlights 16/06/2013(june 16) ::

ሙሉ የመጀመሪያው ግማሽ ጨዋታ: soderemedia,[Full] Ethiopia vs South Africa First Half June 16, 2013.

ሙሉ የሁለተኛው ግማሽ ጨዋታ: ethiopiantv, Ethiopia vs South Africa : 2014 FIFA World Cup Qualifier - Second Half.

ለደቡብ አፍሪቃ:- ቤርናርድ ፓርከር (34ኛ ደቂቃ)
ለኢትዮጵያ:- ጌታነህ ከበደ (42ኛ ደቂቃ) ቤርናርድ ፓርከር (70ኛ ደቂቃ: በራሱ ጎል)

ተድላ

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

የኢ/ያ ቡድን እርሙን ያሳካ እየመሰለ ይ እድል ከብራዚል ሊቀር?

Postby ጥቁር » Mon Jun 17, 2013 5:31 am

ይህ ነገር ወዴት ይሆን ሚወስደን? መቼም ይቅር የማይባል ስህተት ፈዴረሽኑ የሠራ ይመስላል... እንዴት በቢጫ ምክንያት አንድ ዙር ሊያልፈው የሚገባን ተጫዋች አሰለፈ?
[/url]
ጥቁር
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 8
Joined: Fri Oct 03, 2003 10:45 pm

Postby ተድላ ሀይሉ » Sun Nov 17, 2013 6:06 pm

ሰላም የእግር ኳስ ስፖርት አፍቃሪዎች:-

የኢትዮጵያ ጥቁር አንበሶች በብራዚሉ የዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ውድድር የመሣተፍ ዕድል ትላንት በናይጄሪያ ቡድን ተጨናግፏል:: እስካሁን ያደረጉትን ጥረት አደንቃለሁ:: ለወደፊት ማሻሻል የሚገባቸውን ነገር ግን የስፖርት ጋዜጠኛው ገነነ መኩሪያ ከሚለው ውስጥ ሥልጠናን በሚመለከት ብቻ ባለው እስማማለሁ::

ምንጭ:- ገነነ መኩሪያ : እሑድ ኅዳር 8 ቀን 2006 ዓ.ም. : ቀዳማዊ ዋሊያ::
ቀዳማዊ ዋሊያ

በ1970ዎቹ መጀመሪያ ለኢትዮጵያ ሻምፒዮና ለማለፍ ቀይበህርና ዋሊያ ተጫወቱ፡፡ ቀይባህር 5ለ0 እየመረ በረብሻው ጨዋታው ተቋረጠ፡፡ የዋሊያ እድል በማሸነፍ ላይ ብቻ ነው የተመሰረተው ግን መቋቋም አቅቶት፣መጨረስ አቅቶት እጅ ሰጥቶ ጨረሰ፡፡ይህ ቡድን የመጀመሪያው ዋሊያ ነበር፡፡2ተኛው ዋሊያ ብሔራዊ ቡድናችንነው፡፡ ቀዳማዊ ዋሊያ ስያሜውን ያገኘው በ1960ዎቹ አጋማሽ ነው፡፡ ቡድኑ አንደኛ ክፍለጦርን የሚወክል ነው፡፡ እን መርሻ ሚደቅሳ፣አስፋው ባዩ ፣አላሚን፣ቡታ አስመሮም፣ሙሉአለም እጅጉ፣ ደረጄ ፣ አረፋይኔ ምትክን የፈራ ነው፡፡ አብዛኞቹ ተጫዋቾች የብሄራዊ ቡድን ተሰላፊዎች ነበሩ፡፡ ምናልባት ለረሳችሁ ወይም ለማታውቁ ቀዳማዊ ዋሊያ ይህ ነው፡፡

ለባቲ ተቃኝተን አምባሰል እየተጫወትን ነው፡፡

ለአለም ዋንጫ እጣ የወጣ ቀን ኢትዮጵያ ከናይጄሪያ መሆኗ ሲታወቅ የናይጄሪያው አሰልጣን ፈገግ አለ፡፡ ፈገግታው የብራዚሉን ትኬት በቀላሉ እንደቆረጠ ስላወቀ ነው፡፡ ቀላል የሆነለት ከደካማነታችን ባለመውጣታችን ነው፡፡ ትላንት እንደነበርን ነው ዛሬም ያገኘን፡፡ ቡድናችን በመልሱ ጨዋታ ለማለፍ 2ለ0 መሸነፍ ነበረበት ነገር ግን 2ለ0 ምንም የማያደርግልት ቡድን አሸንፎ ጨዋታውን ጨረሰ፡፡ ናይጄሪያ ያሸነፈው መሸነፍ ስለፈለገ ብቻ ነው፡፡ እኛ ግን ማሸነፍ ብንፍለግ ማድረግ አንችልም፡፡ መፈለግ በሁለታችን መሃል ልዩነት አለው፡፡ በአንድ አይነት አጨዋወት ውስጥ ነው ያለነው፡፡ ይህ ጨዋታ ደግሞ ፍጥነት፣ጉልበት ይፈልጋል፡፡ በዚህ ደግሞ ከኛ በተፈጥሮ የተሻሉ ናቸው፡፡ ይህ ማለት ከዚህ አጨዋወት ውስጥ ካለወጣን እነሱ እንደሚበልጡን የታወቃ ነው፡፡ አሰልጣኛችን በሚበልጡን ነገር እያወቀ ነው ይዞን የገባው፡፡ ናይጄሪያን በዚህ አጨዋወት አትችልም ተብሎ ተነግሮታል፡፡ ሲነገር ሀገር ሰምቷል፡፡ የተነገረው እንዲያርም ነው፡፡ እሱ አረመ ማለት ከዚያ አጨዋወት ይወጣል ማለት ነው ከዚያ ከወጣ ደግሞ እኛ በምንሻልበት ይገባል፡፡ በዚህ ስንጫወት ደግሞ እንበልጣቸዋልን፣ ስንበልጣቸው እናሸንፋቸዋልን፡፡ እነ ናይጄሪያን በለጥን ማለት ደግሞ በአፍሪካ ትልቅ ደረጃ ደረስን ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ለኢትዮጵያ ጥቅም ነው፡፡ ነገር ግን አሰልጣኙም ሀሳቡን መቀበል አልፈለገም፡፡ማቀበል ስላልፈለገ ጉዳቱ በሀገር ላይ መጥቷል፡፡ እስካሁን 6 ጊዜ ከናይጄሪያ ጋር ተጫውቶ አንዱንም ማሸነፍ ሳይችል በሁሉም ቦታ እንደተበለጠ ነው፡፡ 5 ጨዋታ በተመሳሳይ ነገር ተበልጦ 6ተኛው ለመጫወት ሲሄድ ከ5ቱ ስህተት ትምህርት አልተወሰደም፡፡ አሰልጣኙ የያዘው ቡድን የዛሬ 15 ዓመት በታዳጊ ቡድን ሌጎስ ላይ 2ለ0 ተሸነፈ፣ እንደገና በታዳጊ ቡድን በገለልተኛ ሜዳ 4ለ0 ተሸነፈ፣ ባለፈው ዓመት በአፍሪካ ዋንጫ በገለልተኛ ሜዳ 2ለ0 ተሸነፈ፣ ትላንት ደግሞ ካላባር ላይ 2ለ0 ተሸነፈ እነዚህ ከሜዳ ውጪ የተደረጉ ናቸው፡፡ 4ቱንም ተመሳሳይ የሚያደርጋቸው እየተከላከልን መጨረሳችን ነው፡፡

የምነከላከለው መከላከል ፈልገን አይደለም መውጫ ስላጣን ነው፡፡ መውጫ የሌለን በነሱ ቁጥጥር ስር ስለሆንን ነው፡፡ በነሱ ቁጥጥር ስር የሆነው በነሱ አጨዋወት ውስጥ ስለገባን ነው፡፡ በ15 አመት ውስጥ 6 ጊዜ ማሸነፍ ካልቻልን ከዚህ እስካልወጣ 50 ዓመትም ማሸነፍ አንችልም፡፡ አሁን ማሰብ ያለብን ስለመጪው ነው፡፡ለመጪውም በዚህ አጨዋወት ውስጥ ከሆንን የሚፈጠረውን ስለምናውቅ ለነናይጄሪያ እጅ እንሰጣለን፡፡ የነሱ መስታወትና ገባር ሆነን መቀጠል ነው፡፡ ይህ ቡድን ደቡብ አፍሪካ ላይ ናይጄሪያን ሲገጥም ለማለፍ ያለው እድል ማሸነፍ ነው ነገር ግን 90ውንም ደቂቃ ሲከላከል ነው የጨረሰው፡፡ ትላንትም 10 ያህል ተጫዋች እኛ ሜዳ ላይ ሲከላከል ነበር፡፡ ያገኙትን ኳስ እየጠለዙ ለሳላዲን ነበር የሚሰጡት፡፡ በግል ስንገናኝ እንደማንበልጣቸው እየታወቀ እሱን ለብቻው ማጋፈጡ ምንም ውጤታማ አላደረገንም እንደማያደርገንም ይታወቃል፡፡ ጌታነህ አጥቂ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ግን ሲጠልፍ ነው የሚታየው፡፡ የሚጠልፈው ስለፈለገ አይደለም ኳሱ ከተሰጠው በኋላ የሚረዳው የለም፡፡ ነጥቀውት ሲሮጡ እንደማይቀድማቸው ያውቃል ስለዚህ ይጠልፋል ፡፡ ጌታነህህ ጥፋት ውስጥ የከተተው የተመረጠው አጨዋወት እንጂ ልጁ ፈልጎ አይደለም፡፡ አብዛኛው ተጫዋች እኛ ሜዳ ላይ ስላለ እነ ጌታነህን ኳስ ሲያገኙ ምንም ረዳት የላቸውም፡፡ ባለፈው አዲስ አበባ ላይ ጨዋታ ሲደረግ የኢትዮጵያ ቡድን ኳስ ሲቀባበል እንደተጫወተ ነበር የተነገረወ፡፡ የተቀባበልነው እነሱ በሌሉበት በራሳችን ሜዳ ላይ ነው፡፡ የበለጥነው ናይጄሪያን አይደለም ምክንያቱም እነሱ እኛ ሜዳ ላይ አነበሩም፡፡ ስለዚህ በኳስ የበለጥነው ሜዳችንን ነው፡፡ ቡድናችን ኳስ የሚጫወት ቢሆን ኖሮ ትላንት ያሳየን ነበር፡፡መጫወት ያልቻለው ነፃ ቦታ ስላላገኘ ነው፡፡ ናይጄሪያ እዚያው ሜዳችን ላይ ያዘን ፡፡ ለዚህም ነው ልጆቻችን ያገኙትን ኳስ የሚጠልዙት፡፡ ኳስ የሚጫወት ቡድን ሜዳው ላይ ቢያዝም ተቀባብሎ ወጥቶ የናይጄሪያንም ቡድን ጠርጎ ያስወጣው ነበር፡፡ በኮንፌዴሬሽን ካፕ ስፔን ናይጄሪያን ከራሱ ሜዳ ጠርጎ አውጥቶ እዚያው ክልል ውስጥ ከቶ መውጫ አሳጥቶ ነው ያሸነፈው፡፡ ያንን ጨዋታ ስፔን ካራባል ላይ ቢጫወት ናይጄሪያን እንደዚያው ነው የሚያደርገው፡፡

እኛ ግን እግር ኳስን በእውቀት አይደለም የምንጫወተው፡፡ ጌዲያዎን ወደ ብሔራዊ ቡድን መጥቶ የትላንትነው ጨዋታ ላይ ቢሰለፍ ምን የሚያደርግ ይመስላችኋል? እየተጠለዘ ያንን ተጋፍቶ የሚጫወት ይመስላችኋል? ጌዲዮን ቢመጣ የተመረጠው ስልጠና እና አጨዋወት ሊተገብረው አይችልም፡፡ ከጌዲዮን ችሎታ ጋር የሚመጥን አጨዋወት ብንዘረጋ ናየጄሪያን መብለጥ እንችላለን ያንን ስልጠና ብነዘረጋ ደግሞ ጌዲዮንን አንፈልገውም፡፡ ከጌዲዮን የሚበልጡ በየሰፈሩ ተቀብረው የቀሩ ልጆች ነፃ ይወጣሉ፡፡ እነሱ ደግሞ ነፃ ሲወጡ አገራችን ነፃ ትወጣለች፡፡ እስከዚያ ግን ናይጄሪያ ሙቀጫ ውስጥ አስገብቶ ይወቅጠናል ይህ የተረጋገጠ ሀቅ ነው፡፡

የአሁኑ ቡድን 10 ውስጥ በመግባቱ በፊት ከነበሩት ቡድኖች የተሻለ እንደሆነ ነው የሚነገረው፡፡ የበፊቱ ቡድኖች ለምንድነው 10 ውስጥ ያልገቡት? ለምሳሌ በ2001 የነበረው ቡድን ሞሪታኒያን ከሜዳ ውጪ አሸነፈ ከ15 ቀን በኋላ በሞሮኮ 3ለ0 ተሸነፈ፡፡ ከሜዳው ሳይወጣ፡፡ በ2003 ኦኔራ የያዘው ቡድን ከሜዳው ውጪ ማዳጋስካርን 1ለ0 አሸነፈ ከ3 ሳምንት በኋላ በናይጄሪያ 4ለ0 ተሸነፈ፡፡ የአሁኑ ቡድን ደግሞ ቦትስዋናን ከሜዳው ውጪ አሸነፈ በናይጄሪያ 2ለ0 ተሸነፈ፡፡ ሶስቱም ጊዜ የነበሩት ቡድኖች ደካሞቹን ከሜዳ ውጪ ያሸንፋሉ ፡፡ ጠንካሮቹን ግን መቋቋም አልቻሉም፡፡ ቦትስዋና የዛሬ 2 ዓመት በ28ተኛው የአፍሪካ ዋንጫ አልፎ ከምድቡ አንድም ጨዋታ ሳያሸንፍ ይባስ ብሎ በጊኒ 6ለ1 የተሸነፈ ቡድን ነው፡፡ በአፍሪካ ዋንጫ በብዙ ግብ የተሸነፈው የኢትዮጵያ ቡድን ነው ፡፡ በ7ተኛው የአፍሪካ ዋንጫ በአይቮሪኮስት 6ለ1 የተሸነፍንበት፡፡ ላለፉት 42 ዓመታት እኛ ነበርን ሪከርዱን የያዝነው ያንን የተጋራን ቦትስዋና ነው፡፡

ሴንትራል አፍሪካ ደካማ ነው ከነ ኡጋንዳና ታንዛኒያ ያነሰ ነው፡፡ ደቡብ አፍሪካ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፍ አቅቶት አዘጋጅ እየሆነ ነው የሚሳተፈው፡፡ እነዚህ ቡድኖች ልክ እነደነ ማዳጋስካርና ሞሪታኒያ አይነቶች ናቸው፡፡ ልክ እንደሌላው ጊዜ ናይጄሪያ እኛ ምድብ ወስጥ ቢኖር ኖሮ ለአፍሪካ ዋንጫ የምናልፍ ይመስላችኋል? እኛ የተመደብነው ደካሞች የተደለደሉበት ነው፡፡ ቡድናችን ያለፈው በኛ ብቃት ሳይሆን በነሱ ደካማነት ነው፡፡ የነዚህ አይነት ምድብ ለ100 አመታትም የምናገኝ አይመስለኝም፡፡ እድል የሚባለውም ያገኘነው ምድብ ነው፡፡ እነ ኬኒያ፣ ኡጋንዳንም ስንወስድ በድልድሉ እድለኛ አነበሩም፡፡ ኬኒያ ከናይጄሪያ ጋር ተመደበ፣ ኡጋንዳም ከሴኔጋል ጋር ተመደበ፡፡ እነዚህ ቡድኖች ደግሞ በግድ ስለሚያሸንፉ እነ ኡጋንዳ እድለኞች አልሆኑም፡፡ቡድናችን ግን ደካሞች ጋር ስለተመደበ ከዚህ ለማለፍ አልተቸገረም፡፡ በዚህ አመጣጡ 10 ውስጥ ስለገባ ወርቃማ ልንለው እንችላለን? ወርቃማ ሊባል የሚችለው እነ ናይጄሪያን ጥሎ ሲያልፍ ነው፡፡ ይህን ወርቃማ ካልን ሆሌም ለናይጄሪያ እጅ እየሰጠን ልንኖር ነው፡፡

ለምሳሌ ይህ ቡድን እረጅም አመት አብሮ ቆይቷል፡፡ አሰልጣኙም እንደሚነግሩን በራሱ የሚተማመንና ማንንም የማይፈራ የማሸነፍ ብቃት እንዳለውና ከዚህ በፊት ከነበሩት ቡድኖች የተሻለ እንሆነ ነው፡፡ የበፊቶቹ ቡድኖች አዲስ አበባ ያሸንፉና ሌጎስ ላይ ተሸንፈው ከውድድር ይወጣሉ፡፡ ይህ ማለት የአሁኑ ቡድን ከቀድሞቹ የሚሻልበትን ሊያሳየን እንደተዘጋጀ ነው፡፡ ሰውም ተስፋ አድርጎ ነቅሎ ወጣ እነ እንትናም አዋራ የሚያጨስ ዋሊያ አሉ ፡፡ ይህ ቡድን በናይጄሪያ አዲስ አበባ እና ካራባር ላይ ተሸነፈ፡፡ ምኑ ነው ከሌላው ጊዜ የተሻለ፡፡ የሌላው ጊዜ ቡድን እኮ እዚህ አይሸነፍም ነበር፡፡

ይህ ቡድን ከሌሎቹ ቡድኖች የሚሻለው በመፋቀሩ እንደሆነ ነው የተነገረን፡፡ የበፊቶቹ አይፋቀሩም ማለት ነው፡፡ ናይጀሬያን እዚህ ያሸነፉት የማይፋቀሩት ናቸው፡፡ ቶም ሴኒቲፊት ለሳምንት አሰልጥኖ እዚህ ከናይጄሪያ ጋር አቻ ወጥቷል፡፡ ከቶም ቡድኑን የተረከበው አሰልጣኝ ሁለት አመት አብሮ ቆይቶ ፣ ልምድ አካብቶ በናይጄሪያ በሜዳው ነው የተሸነፈው፡፡

በቡድናችን ላይ ያለውንችግር ለመቅረፍ የስነ ልቦና፣ የስነምግብ ባለሙያ ተመድቦ አይተናል፡፡ እነ ቦትስዋናን ስናሸንፍ የስነ ምግብ ባለሙያዎች ይመጡና ይህንን አብልተን ነው ይሉናል፡፡ እነ ቦትስዋናን ሳንበላም እናሸንፋቸዋለን፡፡ የስነ ምግብ ባለሙያው ከናይጄሪያ ጨዋታ በፊት መጥቶ የሚቋቋሙበትን አብልቻቸዋለሁ በኔ ይሁንባችሁ አለን ሜዳ ላይ ግን ሲታይ እየፈነገሉን ነበር የሚሄዱት፡፡ ከ3 አመት በፊት ናይጄሪያን አዲስ አበባ ላይ ስንገጥም የስነ ምግብ ሙያተኛ አነበረም፡፡ ግን ማሸነፍ አልቻልንም፡፡ ኖሮም ሳይኖርም ናይጄሪያ በልጦናል፡፡ የስነ ምግብ ባሉሙያ የመጣው እኮ ችግራችንን ሊፈታ ነው ፡፡ ችግሩ ግን ይህ አይደለም፡፡ ዋናውን ችግር ትተን ሌላ ቦታ ነው የምንሄደው፡፡

የሰን ምግብ ባሉመያው እኮ ከተጫዋቾች አልፎ ለደጋፊም ምን በልቶ እንደሚደግፍ ሲያብራራ ነበር፡፡ ያም ቢሆን ችግራችንነ ሊፈታልን አልቻለም፡፡

ሌላው ችግራችን ተብሎ የቀረበው የስነ ልቦና ሙያተኛ ነው፡፡ ባለፈው ዓመት የሴቶች ቡድን ታንዛኒያን አሸንፎ ለአፍሪካ ዋንጫ ሲያልፍ ቡድኑ ያለፈው በስነ ልቦና እገዛ ስለተደረገለትና በአፍሪካ ዋንጫም በስነ ልቦና ታግዞ ትልልቆቹን እንደሚያሸንፍ ነገሩን ሰውም ተስፋ አደረገ፡፡ ቡድኑ ከሜዳው መውጣት አቅቶት በናይጄሪያና ባይቮሪኮስት በድምሩ 8ለ0 ተሸንፎ ከአጠቃላይ መጨረሻ ወጣ፡፡

የወንዶቹ ቡድን ሱዳንን ሲያሸንፍ በስነልቦና ብቁ ስለሆነ ነው ከዚህ በኋላ ማንም እንደማይፈራ ክስተትም እንደሚሆን ተነገረን፡፡ በናይጄሪያና በቡርኪናፋሶ በድምሩ 6ለ0 ተሸንፎ ከጠቅላላው ውራ ወጣ፡፡ በዚያኑ አመጥ ሴቶችም ወንዶችም በአፍሪካ ዋንጫ ውራ ነው የወጡት፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ በፊት በአፍሪካ ዋንጫ ውራ ነው የሚወጣው ይህንን ችግር ለመቅረፍ ነበር ስነ ምግብና ስነ ልቦና ባለሙያውች የመጡት፡፡ እነሱም እያሉ ሳይኖሩም ውራነታችንን አላጣንም፡፡ ስለዚህ ችግሩ ስነ ምግብና ስነ ልቦና አይደለም፡፡ ዋናው ችግሩ እኮ ስልጠናው ላይ ነው፡፡ ስልጠናውን ማሻሻል አልቻልንም፡፡ እሱን እስካልቀረፍን ድረስ ስን ምግብ፣ስነልቦና.....ስነ ምናምን እያልን ብንሄድ ናይጄሪያ ሲያገኘን ያሸናል፡፡

ችግሮቻችንን በሌለ ቦታ ነው የምንፈልገው፡፡ ባለፈው አዳነ ስለወጣ ነው የተሸነፍነው ተባለ አሁን አዳነ ሙሉ ጨዋታ ተጫወተ ግን ሽንፈቱ አልቀረም፡፡ ስለዚህ መጀመሪያም ችግሩ የአዳነ መውጣት አይደለም፡፡ የችግራችን መንስኤ ሄደን ያለመመርመራችን ነው፡፡ ትላንትና በረኛ ከጀመራል ይልቅ ሲሳይ ነው የገባው፡፡ ሲሳይ ከጀማል በተሻለ ሁኔታ ሪጎሬ ያድናል በቻን ወድድር ሩዋንዳ ላይ ወደ መለያ ምት ሊኬድ ሲል ጀማል ወጥቶ ነው ሲሳይ የገባው በሪጎሬ የተሻለ ተብሎ ስለሚታምን ነው፡፡ ይህ ማለት ትላንት ሪጎሬ እንደሚሰጥብን ቀድሞ ታውቋል ማለት ነው፡፡ ይህም ፔናልቲ ውስጥ እንደሚደርሱ እና እንደምንጠልፍ ታውቋል ማለት ነው (የተገኘው በዚያ ባይሆንም) ፡፡ የምንጠልፈው ደግሞ ስለሚያመልጡን ነው፡፡ የሚያመልጡን በሩጫ ስለማንቋቋማቸው ነው፡፡ በሩጫ የማንቋቋም ደግሞ ስላልሰራን ሳይሆን በተፈጥሮ ስለሚበልጡን ነው፡፡ መፍትሄው ከዚህ መውጣት ነው እንጂ መጥለፍ አይደለም፡፡

እነሱ ግብ ድረስ እየተግተለተሉ ሱመጡ እንደ ትላንትናው ለ10 በመከላከል አይደለም የምናቆመው ፡፡ እስካሁን ናይጄሪያን በዚህ አጨዋወት መቋቋም እንደማችል አይተነዋል፡፡ ከዚህ አጨዋወት ብንወጣና ወደራሳችን ብንገባ እንጠቀማለን እንጂ አንጎዳም፡፡ ነገ እኮ እነ ናይጄሪያ፣ጋና፣አይቮሪኮስት ከኛ ሲደለደሉ ትላንተም እንደማያሳልፉን ነገም አያሳልፉንም፡፡ 31 አመትም የቆየነው እነሱ ከነሱ ጋር እየተደለደልን ነው፡፡ እነሱን ለመብለጥ ከነሱ ነገር መውጣት አለብን፡፡ አንድ ቡድን የአጨዋወት ዘዴውን ለመዘርጋት ተጨዋቹን መነሻ ማድረግ አለበት፡፡ እስካሁን የሄድንበት ነገር ግን እነሱ ተጫዋቾቻቸውን አይተው የዘረጉትን እየተከተልን ለኛ ተጫዋቾች የማየሆነውን ፍጥነትና ጉልበትን እየሰራን ነው፡፡ ስለዚህ መቋቋም አልቻልንም፡፡ እነሱን ለመቋቋም አዲስ አጨዋወት መንደፍ አለብን፡፡ አጨዋወቱን ስነነድፍ ደግሞ ስልጠናው ከዛ አጨዋወት አንፃር መቋኘት አለበት አሁን ያን ችሎታ ሌላ የምንጫወተው ሌላ፡፡ ይህ ማለት ለባቲ ተቃኝተን አምባሰል ነው የምንጫወተው፡፡የሚያስፈልገን ለባቲ ተቃኝተን ባቲን መጫወት ነው፡፡

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Mon Nov 18, 2013 12:05 am

ሰላም የእግር ኳስ አፍቃሪዎች:-

ገነነ መኩሪያ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ የጠለቀ ዕውቀት ያለው እና በሚያቀርባቸው የመሞገቻ ኃሣቦቹም በቀላሉ የማይበገር ነው:: በዚህ ከዓመት በፊት ክ,ቀረበ ቃለ-መጠይቅ የምንማረው ብዙ ቁምነገር ይኖራል::

ምንጮች:-
1 .............. ethiopian interview Genene Mekurya libro part 1

2 .............. ethiopian interview Genene Mekurya libro part 2

3 .............. ethiopian sport interview Genene Mekurya libro part3

4 .................. ethiopian interview Genene Mekurya libro part4

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ወርቅነች » Mon Nov 18, 2013 9:41 am

ሥልጠናን በሚመለከት ብቻ ባለው እሥማማለሁ

ቅቅቅቅ...ፈዛዛው ከሥልጠና ሌላ ምን የተናገረው አለ ብለህ ነው እሥማማለሁ አልሥማማ እምትለው ትለሀለች ጀሚላ ከቸርችል ጎዳና :lol: :lol: :lol:

ተድላ ሀይሉ wrote:ሰላም የእግር ኳስ ስፖርት አፍቃሪዎች:-

የኢትዮጵያ ጥቁር አንበሶች በብራዚሉ የዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ውድድር የመሣተፍ ዕድል ትላንት በናይጄሪያ ቡድን ተጨናግፏል:: እስካሁን ያደረጉትን ጥረት አደንቃለሁ:: ለወደፊት ማሻሻል የሚገባቸውን ነገር ግን የስፖርት ጋዜጠኛው ገነነ መኩሪያ ከሚለው ውስጥ ሥልጠናን በሚመለከት ብቻ ባለው እስማማለሁ::

ምንጭ:- ገነነ መኩሪያ : እሑድ ኅዳር 8 ቀን 2006 ዓ.ም. : ቀዳማዊ ዋሊያ::
ቀዳማዊ ዋሊያ

በ1970ዎቹ መጀመሪያ ለኢትዮጵያ ሻምፒዮና ለማለፍ ቀይበህርና ዋሊያ ተጫወቱ፡፡ ቀይባህር 5ለ0 እየመረ በረብሻው ጨዋታው ተቋረጠ፡፡ የዋሊያ እድል በማሸነፍ ላይ ብቻ ነው የተመሰረተው ግን መቋቋም አቅቶት፣መጨረስ አቅቶት እጅ ሰጥቶ ጨረሰ፡፡ይህ ቡድን የመጀመሪያው ዋሊያ ነበር፡፡2ተኛው ዋሊያ ብሔራዊ ቡድናችንነው፡፡ ቀዳማዊ ዋሊያ ስያሜውን ያገኘው በ1960ዎቹ አጋማሽ ነው፡፡ ቡድኑ አንደኛ ክፍለጦርን የሚወክል ነው፡፡ እን መርሻ ሚደቅሳ፣አስፋው ባዩ ፣አላሚን፣ቡታ አስመሮም፣ሙሉአለም እጅጉ፣ ደረጄ ፣ አረፋይኔ ምትክን የፈራ ነው፡፡ አብዛኞቹ ተጫዋቾች የብሄራዊ ቡድን ተሰላፊዎች ነበሩ፡፡ ምናልባት ለረሳችሁ ወይም ለማታውቁ ቀዳማዊ ዋሊያ ይህ ነው፡፡

ለባቲ ተቃኝተን አምባሰል እየተጫወትን ነው፡፡

ለአለም ዋንጫ እጣ የወጣ ቀን ኢትዮጵያ ከናይጄሪያ መሆኗ ሲታወቅ የናይጄሪያው አሰልጣን ፈገግ አለ፡፡ ፈገግታው የብራዚሉን ትኬት በቀላሉ እንደቆረጠ ስላወቀ ነው፡፡ ቀላል የሆነለት ከደካማነታችን ባለመውጣታችን ነው፡፡ ትላንት እንደነበርን ነው ዛሬም ያገኘን፡፡ ቡድናችን በመልሱ ጨዋታ ለማለፍ 2ለ0 መሸነፍ ነበረበት ነገር ግን 2ለ0 ምንም የማያደርግልት ቡድን አሸንፎ ጨዋታውን ጨረሰ፡፡ ናይጄሪያ ያሸነፈው መሸነፍ ስለፈለገ ብቻ ነው፡፡ እኛ ግን ማሸነፍ ብንፍለግ ማድረግ አንችልም፡፡ መፈለግ በሁለታችን መሃል ልዩነት አለው፡፡ በአንድ አይነት አጨዋወት ውስጥ ነው ያለነው፡፡ ይህ ጨዋታ ደግሞ ፍጥነት፣ጉልበት ይፈልጋል፡፡ በዚህ ደግሞ ከኛ በተፈጥሮ የተሻሉ ናቸው፡፡ ይህ ማለት ከዚህ አጨዋወት ውስጥ ካለወጣን እነሱ እንደሚበልጡን የታወቃ ነው፡፡ አሰልጣኛችን በሚበልጡን ነገር እያወቀ ነው ይዞን የገባው፡፡ ናይጄሪያን በዚህ አጨዋወት አትችልም ተብሎ ተነግሮታል፡፡ ሲነገር ሀገር ሰምቷል፡፡ የተነገረው እንዲያርም ነው፡፡ እሱ አረመ ማለት ከዚያ አጨዋወት ይወጣል ማለት ነው ከዚያ ከወጣ ደግሞ እኛ በምንሻልበት ይገባል፡፡ በዚህ ስንጫወት ደግሞ እንበልጣቸዋልን፣ ስንበልጣቸው እናሸንፋቸዋልን፡፡ እነ ናይጄሪያን በለጥን ማለት ደግሞ በአፍሪካ ትልቅ ደረጃ ደረስን ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ለኢትዮጵያ ጥቅም ነው፡፡ ነገር ግን አሰልጣኙም ሀሳቡን መቀበል አልፈለገም፡፡ማቀበል ስላልፈለገ ጉዳቱ በሀገር ላይ መጥቷል፡፡ እስካሁን 6 ጊዜ ከናይጄሪያ ጋር ተጫውቶ አንዱንም ማሸነፍ ሳይችል በሁሉም ቦታ እንደተበለጠ ነው፡፡ 5 ጨዋታ በተመሳሳይ ነገር ተበልጦ 6ተኛው ለመጫወት ሲሄድ ከ5ቱ ስህተት ትምህርት አልተወሰደም፡፡ አሰልጣኙ የያዘው ቡድን የዛሬ 15 ዓመት በታዳጊ ቡድን ሌጎስ ላይ 2ለ0 ተሸነፈ፣ እንደገና በታዳጊ ቡድን በገለልተኛ ሜዳ 4ለ0 ተሸነፈ፣ ባለፈው ዓመት በአፍሪካ ዋንጫ በገለልተኛ ሜዳ 2ለ0 ተሸነፈ፣ ትላንት ደግሞ ካላባር ላይ 2ለ0 ተሸነፈ እነዚህ ከሜዳ ውጪ የተደረጉ ናቸው፡፡ 4ቱንም ተመሳሳይ የሚያደርጋቸው እየተከላከልን መጨረሳችን ነው፡፡

የምነከላከለው መከላከል ፈልገን አይደለም መውጫ ስላጣን ነው፡፡ መውጫ የሌለን በነሱ ቁጥጥር ስር ስለሆንን ነው፡፡ በነሱ ቁጥጥር ስር የሆነው በነሱ አጨዋወት ውስጥ ስለገባን ነው፡፡ በ15 አመት ውስጥ 6 ጊዜ ማሸነፍ ካልቻልን ከዚህ እስካልወጣ 50 ዓመትም ማሸነፍ አንችልም፡፡ አሁን ማሰብ ያለብን ስለመጪው ነው፡፡ለመጪውም በዚህ አጨዋወት ውስጥ ከሆንን የሚፈጠረውን ስለምናውቅ ለነናይጄሪያ እጅ እንሰጣለን፡፡ የነሱ መስታወትና ገባር ሆነን መቀጠል ነው፡፡ ይህ ቡድን ደቡብ አፍሪካ ላይ ናይጄሪያን ሲገጥም ለማለፍ ያለው እድል ማሸነፍ ነው ነገር ግን 90ውንም ደቂቃ ሲከላከል ነው የጨረሰው፡፡ ትላንትም 10 ያህል ተጫዋች እኛ ሜዳ ላይ ሲከላከል ነበር፡፡ ያገኙትን ኳስ እየጠለዙ ለሳላዲን ነበር የሚሰጡት፡፡ በግል ስንገናኝ እንደማንበልጣቸው እየታወቀ እሱን ለብቻው ማጋፈጡ ምንም ውጤታማ አላደረገንም እንደማያደርገንም ይታወቃል፡፡ ጌታነህ አጥቂ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ግን ሲጠልፍ ነው የሚታየው፡፡ የሚጠልፈው ስለፈለገ አይደለም ኳሱ ከተሰጠው በኋላ የሚረዳው የለም፡፡ ነጥቀውት ሲሮጡ እንደማይቀድማቸው ያውቃል ስለዚህ ይጠልፋል ፡፡ ጌታነህህ ጥፋት ውስጥ የከተተው የተመረጠው አጨዋወት እንጂ ልጁ ፈልጎ አይደለም፡፡ አብዛኛው ተጫዋች እኛ ሜዳ ላይ ስላለ እነ ጌታነህን ኳስ ሲያገኙ ምንም ረዳት የላቸውም፡፡ ባለፈው አዲስ አበባ ላይ ጨዋታ ሲደረግ የኢትዮጵያ ቡድን ኳስ ሲቀባበል እንደተጫወተ ነበር የተነገረወ፡፡ የተቀባበልነው እነሱ በሌሉበት በራሳችን ሜዳ ላይ ነው፡፡ የበለጥነው ናይጄሪያን አይደለም ምክንያቱም እነሱ እኛ ሜዳ ላይ አነበሩም፡፡ ስለዚህ በኳስ የበለጥነው ሜዳችንን ነው፡፡ ቡድናችን ኳስ የሚጫወት ቢሆን ኖሮ ትላንት ያሳየን ነበር፡፡መጫወት ያልቻለው ነፃ ቦታ ስላላገኘ ነው፡፡ ናይጄሪያ እዚያው ሜዳችን ላይ ያዘን ፡፡ ለዚህም ነው ልጆቻችን ያገኙትን ኳስ የሚጠልዙት፡፡ ኳስ የሚጫወት ቡድን ሜዳው ላይ ቢያዝም ተቀባብሎ ወጥቶ የናይጄሪያንም ቡድን ጠርጎ ያስወጣው ነበር፡፡ በኮንፌዴሬሽን ካፕ ስፔን ናይጄሪያን ከራሱ ሜዳ ጠርጎ አውጥቶ እዚያው ክልል ውስጥ ከቶ መውጫ አሳጥቶ ነው ያሸነፈው፡፡ ያንን ጨዋታ ስፔን ካራባል ላይ ቢጫወት ናይጄሪያን እንደዚያው ነው የሚያደርገው፡፡

እኛ ግን እግር ኳስን በእውቀት አይደለም የምንጫወተው፡፡ ጌዲያዎን ወደ ብሔራዊ ቡድን መጥቶ የትላንትነው ጨዋታ ላይ ቢሰለፍ ምን የሚያደርግ ይመስላችኋል? እየተጠለዘ ያንን ተጋፍቶ የሚጫወት ይመስላችኋል? ጌዲዮን ቢመጣ የተመረጠው ስልጠና እና አጨዋወት ሊተገብረው አይችልም፡፡ ከጌዲዮን ችሎታ ጋር የሚመጥን አጨዋወት ብንዘረጋ ናየጄሪያን መብለጥ እንችላለን ያንን ስልጠና ብነዘረጋ ደግሞ ጌዲዮንን አንፈልገውም፡፡ ከጌዲዮን የሚበልጡ በየሰፈሩ ተቀብረው የቀሩ ልጆች ነፃ ይወጣሉ፡፡ እነሱ ደግሞ ነፃ ሲወጡ አገራችን ነፃ ትወጣለች፡፡ እስከዚያ ግን ናይጄሪያ ሙቀጫ ውስጥ አስገብቶ ይወቅጠናል ይህ የተረጋገጠ ሀቅ ነው፡፡

የአሁኑ ቡድን 10 ውስጥ በመግባቱ በፊት ከነበሩት ቡድኖች የተሻለ እንደሆነ ነው የሚነገረው፡፡ የበፊቱ ቡድኖች ለምንድነው 10 ውስጥ ያልገቡት? ለምሳሌ በ2001 የነበረው ቡድን ሞሪታኒያን ከሜዳ ውጪ አሸነፈ ከ15 ቀን በኋላ በሞሮኮ 3ለ0 ተሸነፈ፡፡ ከሜዳው ሳይወጣ፡፡ በ2003 ኦኔራ የያዘው ቡድን ከሜዳው ውጪ ማዳጋስካርን 1ለ0 አሸነፈ ከ3 ሳምንት በኋላ በናይጄሪያ 4ለ0 ተሸነፈ፡፡ የአሁኑ ቡድን ደግሞ ቦትስዋናን ከሜዳው ውጪ አሸነፈ በናይጄሪያ 2ለ0 ተሸነፈ፡፡ ሶስቱም ጊዜ የነበሩት ቡድኖች ደካሞቹን ከሜዳ ውጪ ያሸንፋሉ ፡፡ ጠንካሮቹን ግን መቋቋም አልቻሉም፡፡ ቦትስዋና የዛሬ 2 ዓመት በ28ተኛው የአፍሪካ ዋንጫ አልፎ ከምድቡ አንድም ጨዋታ ሳያሸንፍ ይባስ ብሎ በጊኒ 6ለ1 የተሸነፈ ቡድን ነው፡፡ በአፍሪካ ዋንጫ በብዙ ግብ የተሸነፈው የኢትዮጵያ ቡድን ነው ፡፡ በ7ተኛው የአፍሪካ ዋንጫ በአይቮሪኮስት 6ለ1 የተሸነፍንበት፡፡ ላለፉት 42 ዓመታት እኛ ነበርን ሪከርዱን የያዝነው ያንን የተጋራን ቦትስዋና ነው፡፡

ሴንትራል አፍሪካ ደካማ ነው ከነ ኡጋንዳና ታንዛኒያ ያነሰ ነው፡፡ ደቡብ አፍሪካ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፍ አቅቶት አዘጋጅ እየሆነ ነው የሚሳተፈው፡፡ እነዚህ ቡድኖች ልክ እነደነ ማዳጋስካርና ሞሪታኒያ አይነቶች ናቸው፡፡ ልክ እንደሌላው ጊዜ ናይጄሪያ እኛ ምድብ ወስጥ ቢኖር ኖሮ ለአፍሪካ ዋንጫ የምናልፍ ይመስላችኋል? እኛ የተመደብነው ደካሞች የተደለደሉበት ነው፡፡ ቡድናችን ያለፈው በኛ ብቃት ሳይሆን በነሱ ደካማነት ነው፡፡ የነዚህ አይነት ምድብ ለ100 አመታትም የምናገኝ አይመስለኝም፡፡ እድል የሚባለውም ያገኘነው ምድብ ነው፡፡ እነ ኬኒያ፣ ኡጋንዳንም ስንወስድ በድልድሉ እድለኛ አነበሩም፡፡ ኬኒያ ከናይጄሪያ ጋር ተመደበ፣ ኡጋንዳም ከሴኔጋል ጋር ተመደበ፡፡ እነዚህ ቡድኖች ደግሞ በግድ ስለሚያሸንፉ እነ ኡጋንዳ እድለኞች አልሆኑም፡፡ቡድናችን ግን ደካሞች ጋር ስለተመደበ ከዚህ ለማለፍ አልተቸገረም፡፡ በዚህ አመጣጡ 10 ውስጥ ስለገባ ወርቃማ ልንለው እንችላለን? ወርቃማ ሊባል የሚችለው እነ ናይጄሪያን ጥሎ ሲያልፍ ነው፡፡ ይህን ወርቃማ ካልን ሆሌም ለናይጄሪያ እጅ እየሰጠን ልንኖር ነው፡፡

ለምሳሌ ይህ ቡድን እረጅም አመት አብሮ ቆይቷል፡፡ አሰልጣኙም እንደሚነግሩን በራሱ የሚተማመንና ማንንም የማይፈራ የማሸነፍ ብቃት እንዳለውና ከዚህ በፊት ከነበሩት ቡድኖች የተሻለ እንሆነ ነው፡፡ የበፊቶቹ ቡድኖች አዲስ አበባ ያሸንፉና ሌጎስ ላይ ተሸንፈው ከውድድር ይወጣሉ፡፡ ይህ ማለት የአሁኑ ቡድን ከቀድሞቹ የሚሻልበትን ሊያሳየን እንደተዘጋጀ ነው፡፡ ሰውም ተስፋ አድርጎ ነቅሎ ወጣ እነ እንትናም አዋራ የሚያጨስ ዋሊያ አሉ ፡፡ ይህ ቡድን በናይጄሪያ አዲስ አበባ እና ካራባር ላይ ተሸነፈ፡፡ ምኑ ነው ከሌላው ጊዜ የተሻለ፡፡ የሌላው ጊዜ ቡድን እኮ እዚህ አይሸነፍም ነበር፡፡

ይህ ቡድን ከሌሎቹ ቡድኖች የሚሻለው በመፋቀሩ እንደሆነ ነው የተነገረን፡፡ የበፊቶቹ አይፋቀሩም ማለት ነው፡፡ ናይጀሬያን እዚህ ያሸነፉት የማይፋቀሩት ናቸው፡፡ ቶም ሴኒቲፊት ለሳምንት አሰልጥኖ እዚህ ከናይጄሪያ ጋር አቻ ወጥቷል፡፡ ከቶም ቡድኑን የተረከበው አሰልጣኝ ሁለት አመት አብሮ ቆይቶ ፣ ልምድ አካብቶ በናይጄሪያ በሜዳው ነው የተሸነፈው፡፡

በቡድናችን ላይ ያለውንችግር ለመቅረፍ የስነ ልቦና፣ የስነምግብ ባለሙያ ተመድቦ አይተናል፡፡ እነ ቦትስዋናን ስናሸንፍ የስነ ምግብ ባለሙያዎች ይመጡና ይህንን አብልተን ነው ይሉናል፡፡ እነ ቦትስዋናን ሳንበላም እናሸንፋቸዋለን፡፡ የስነ ምግብ ባለሙያው ከናይጄሪያ ጨዋታ በፊት መጥቶ የሚቋቋሙበትን አብልቻቸዋለሁ በኔ ይሁንባችሁ አለን ሜዳ ላይ ግን ሲታይ እየፈነገሉን ነበር የሚሄዱት፡፡ ከ3 አመት በፊት ናይጄሪያን አዲስ አበባ ላይ ስንገጥም የስነ ምግብ ሙያተኛ አነበረም፡፡ ግን ማሸነፍ አልቻልንም፡፡ ኖሮም ሳይኖርም ናይጄሪያ በልጦናል፡፡ የስነ ምግብ ባሉሙያ የመጣው እኮ ችግራችንን ሊፈታ ነው ፡፡ ችግሩ ግን ይህ አይደለም፡፡ ዋናውን ችግር ትተን ሌላ ቦታ ነው የምንሄደው፡፡

የሰን ምግብ ባሉመያው እኮ ከተጫዋቾች አልፎ ለደጋፊም ምን በልቶ እንደሚደግፍ ሲያብራራ ነበር፡፡ ያም ቢሆን ችግራችንነ ሊፈታልን አልቻለም፡፡

ሌላው ችግራችን ተብሎ የቀረበው የስነ ልቦና ሙያተኛ ነው፡፡ ባለፈው ዓመት የሴቶች ቡድን ታንዛኒያን አሸንፎ ለአፍሪካ ዋንጫ ሲያልፍ ቡድኑ ያለፈው በስነ ልቦና እገዛ ስለተደረገለትና በአፍሪካ ዋንጫም በስነ ልቦና ታግዞ ትልልቆቹን እንደሚያሸንፍ ነገሩን ሰውም ተስፋ አደረገ፡፡ ቡድኑ ከሜዳው መውጣት አቅቶት በናይጄሪያና ባይቮሪኮስት በድምሩ 8ለ0 ተሸንፎ ከአጠቃላይ መጨረሻ ወጣ፡፡

የወንዶቹ ቡድን ሱዳንን ሲያሸንፍ በስነልቦና ብቁ ስለሆነ ነው ከዚህ በኋላ ማንም እንደማይፈራ ክስተትም እንደሚሆን ተነገረን፡፡ በናይጄሪያና በቡርኪናፋሶ በድምሩ 6ለ0 ተሸንፎ ከጠቅላላው ውራ ወጣ፡፡ በዚያኑ አመጥ ሴቶችም ወንዶችም በአፍሪካ ዋንጫ ውራ ነው የወጡት፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ በፊት በአፍሪካ ዋንጫ ውራ ነው የሚወጣው ይህንን ችግር ለመቅረፍ ነበር ስነ ምግብና ስነ ልቦና ባለሙያውች የመጡት፡፡ እነሱም እያሉ ሳይኖሩም ውራነታችንን አላጣንም፡፡ ስለዚህ ችግሩ ስነ ምግብና ስነ ልቦና አይደለም፡፡ ዋናው ችግሩ እኮ ስልጠናው ላይ ነው፡፡ ስልጠናውን ማሻሻል አልቻልንም፡፡ እሱን እስካልቀረፍን ድረስ ስን ምግብ፣ስነልቦና.....ስነ ምናምን እያልን ብንሄድ ናይጄሪያ ሲያገኘን ያሸናል፡፡

ችግሮቻችንን በሌለ ቦታ ነው የምንፈልገው፡፡ ባለፈው አዳነ ስለወጣ ነው የተሸነፍነው ተባለ አሁን አዳነ ሙሉ ጨዋታ ተጫወተ ግን ሽንፈቱ አልቀረም፡፡ ስለዚህ መጀመሪያም ችግሩ የአዳነ መውጣት አይደለም፡፡ የችግራችን መንስኤ ሄደን ያለመመርመራችን ነው፡፡ ትላንትና በረኛ ከጀመራል ይልቅ ሲሳይ ነው የገባው፡፡ ሲሳይ ከጀማል በተሻለ ሁኔታ ሪጎሬ ያድናል በቻን ወድድር ሩዋንዳ ላይ ወደ መለያ ምት ሊኬድ ሲል ጀማል ወጥቶ ነው ሲሳይ የገባው በሪጎሬ የተሻለ ተብሎ ስለሚታምን ነው፡፡ ይህ ማለት ትላንት ሪጎሬ እንደሚሰጥብን ቀድሞ ታውቋል ማለት ነው፡፡ ይህም ፔናልቲ ውስጥ እንደሚደርሱ እና እንደምንጠልፍ ታውቋል ማለት ነው (የተገኘው በዚያ ባይሆንም) ፡፡ የምንጠልፈው ደግሞ ስለሚያመልጡን ነው፡፡ የሚያመልጡን በሩጫ ስለማንቋቋማቸው ነው፡፡ በሩጫ የማንቋቋም ደግሞ ስላልሰራን ሳይሆን በተፈጥሮ ስለሚበልጡን ነው፡፡ መፍትሄው ከዚህ መውጣት ነው እንጂ መጥለፍ አይደለም፡፡

እነሱ ግብ ድረስ እየተግተለተሉ ሱመጡ እንደ ትላንትናው ለ10 በመከላከል አይደለም የምናቆመው ፡፡ እስካሁን ናይጄሪያን በዚህ አጨዋወት መቋቋም እንደማችል አይተነዋል፡፡ ከዚህ አጨዋወት ብንወጣና ወደራሳችን ብንገባ እንጠቀማለን እንጂ አንጎዳም፡፡ ነገ እኮ እነ ናይጄሪያ፣ጋና፣አይቮሪኮስት ከኛ ሲደለደሉ ትላንተም እንደማያሳልፉን ነገም አያሳልፉንም፡፡ 31 አመትም የቆየነው እነሱ ከነሱ ጋር እየተደለደልን ነው፡፡ እነሱን ለመብለጥ ከነሱ ነገር መውጣት አለብን፡፡ አንድ ቡድን የአጨዋወት ዘዴውን ለመዘርጋት ተጨዋቹን መነሻ ማድረግ አለበት፡፡ እስካሁን የሄድንበት ነገር ግን እነሱ ተጫዋቾቻቸውን አይተው የዘረጉትን እየተከተልን ለኛ ተጫዋቾች የማየሆነውን ፍጥነትና ጉልበትን እየሰራን ነው፡፡ ስለዚህ መቋቋም አልቻልንም፡፡ እነሱን ለመቋቋም አዲስ አጨዋወት መንደፍ አለብን፡፡ አጨዋወቱን ስነነድፍ ደግሞ ስልጠናው ከዛ አጨዋወት አንፃር መቋኘት አለበት አሁን ያን ችሎታ ሌላ የምንጫወተው ሌላ፡፡ ይህ ማለት ለባቲ ተቃኝተን አምባሰል ነው የምንጫወተው፡፡የሚያስፈልገን ለባቲ ተቃኝተን ባቲን መጫወት ነው፡፡

ተድላ
ወርቅነች
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 967
Joined: Sun Oct 03, 2010 10:05 am

Previous

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests

cron