የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ቡድን-በ20ኛው የዓለም ዋንጫ ...

ስፖርት - Sport related topics

Postby ተድላ ሀይሉ » Tue Apr 19, 2011 7:11 pm

ሞፊቲ wrote:ሰላም ሰላም

በጣም ይገርማል;;
ድንቅ ሁጤት! እስከዚህ መጓዝ በራሱ ትልቅ ድል ነው::
በሰው ሀገር የጎል በርን በጥቂት ቁጥር አስጠብቆ የወጣ ኢትዮጵያን የሚወክል የነገ ተስፋ ብሄራዊ ቡድናችን
ሴቶቻችን ናቸው!!!

ቸር እንሰንብት!!


ሰላም ሞፊቲ :-

ለሴቶቻችን ተገቢውን ትኩረት አንሠጥም እንጂ በሥፖርቱ ብቻ ሣይሆን በሁሉም መስክ ከእኛ ከወንዶች የተሻሉ መሆናቸው የታወቀ ነው :: እስኪ ኢትዮጵያ ውስጥ እናት ብትሞት ቤተሰብ ሲፈርስ እንጂ አባት ሰብስቦ ሲያሣድግ ምን ያህል አይተን እናውቃለን ? ለማንኛውም ለእናቶቻችን እና እህቶቻችን ትልቅ ክብር ይገባቸዋል :: አንተ እንኳን በዚህ የምትታማ አትመስለኝም እንዲያው ነገሩ ካነሣኸው ላይቀር የሚሠማኝን ላካፍል ብዬ ነው ::

የኢትዮጵያ "ድንቅነሽ" የሴቶች እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ተከታዩ ተጋጣሚ የደቡብ አፍሪቃ ብሔራዊ ቡድን ነው :: የደቡብ አፍሪቃ ሴቶች ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን "ባናያ-ባናያ" ኃላፊዎች ገና ከአሁኑ የፈሩ ይመስላል :: ስለዚህ ሥነ-ልቦና ወሣኝ ነውና ያንን ተጠቅመን ለሎንዶን ኦሎምፒክ ትኬታችንን መቁረጥ እንችላለን :: አሁን ለቡድናችን አባሎች የሚያስፈልገው አስተማማኝ የሥራና የገቢ ምንጭ የሚያገኙበትን መንገድ ማመቻቸት : ተከታታይ የቡድን ሥራ ያለበት ሥልጠና መሥጠት እና ጥሩ ሞራል ናቸው ::

ተድላ
Last edited by ተድላ ሀይሉ on Fri Apr 29, 2011 4:18 am, edited 1 time in total.
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ወርቅነች » Thu Apr 28, 2011 6:14 am

አይ ጉድ ምነው እስፖርተኛ አልነበርክም እንዴ ደግሞ በናት ና ባባት መሀል ገባህ እንዴ...ባል ና ሚሰቱን ልታፋጅ ነው እንዴ ብዱን ብዱን የምትለው...እኛ ማንን ሰንበዳ አየተሀል..ከባሎቻችን ጋር ልታጣለን ነው እንዴ..ምን አይነት አቃጣሪ ነህ...በስፖርት አመካኝተህ በጎን አድርገህ የምታወራው....የዘፈን ዳር ዳሩ እስክሰታ ነው...ፈልገሀት እንደሆን እዚያው ብዳት...ብዱን ብዱን እያልክ ትናገራለህ...ትልቁ ሰይጣን ይብዳህ...ምን አይነት አቃጣሪ ነው..ቆሻሻ ባለጌ...እናትህ ብታውቅ ኖሮ አንተና ዘመድኩንን ለሊት ተነስታ ታርዳችሁ ነበር ቄራ ሳትደርሱ...መሞትህን ሰታውቀው ዋይ ዋይ ትላላች..እናትህ እስፖርተኛና ዘመድኩን እያለች ህዝቡን ታላቅሳለች :lol:

ጀሚላ ከቸርችል ጎዳና
ወርቅነች
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 967
Joined: Sun Oct 03, 2010 10:05 am

ወርቅነች

Postby ወዲአክሱም » Fri May 13, 2011 10:29 pm

ኣረ ባክህን ተው ጎበዝ? ሌላው ተዎው ና ስለ እግር ኳሱን ኣንድ ልብልህ ኣለም ላይ ያልታየ ጎል መጣረቀምያ ሆነው ይመለስሉሁል! በርቱ ነው የሚባለው ጀለሴ!
ወዲአክሱም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 117
Joined: Wed Nov 12, 2003 2:33 am

Postby ተድላ ሀይሉ » Sat Jul 23, 2011 5:23 am

ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ:-

ይህንን አጋጣሚ ለኢትዮጵያ የሴቶች የእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን የመልካም ዕድል ምልክት አድርገን እንውሰደው ?

ምንጭ:- Super sport, Friday July 22, 2011. Ethopia reject Banyana's request

Ethopia reject Banyana's request

The South African Football Association’s request for a postponement of Banyana Banyana’s second leg 2012 London Olympic qualifying match against Ethiopia in Addis Ababa on September 11 has been rejected by their opponents who are insisting that the game should go ahead as fixture by the Confederation of African Football.

When CAF and Fifa drew the fixture list of the 2012 London Olympic Games, Banyana Banyana were paired with Ethiopia in the final first leg qualifier in South Africa on August 28 and the second leg match penciled in for Addis Ababa on the weekend of September 11.

The other semifinal sees Nigeria playing against Cameroon on the same weekends and the winners in the two-legged qualifiers qualify for the London Olympics. However, that was before Banyana also qualified for the All Africa Games that get underway in Maputo on September 3-18.

The All Africa Games sees Banyana opening their programme against Zimbabwe on September 5. They then play Tanzania on September 8 and round off their group phase of the tournament against Ghana on September 11, the same day that they are also supposed to face Ethiopia in the second leg Olympic Games qualifier in Addis Ababa!

“We wrote a letter to CAF notifying them of the clash in fixtures as our second leg Olympic fixture clashed with our final All Africa Games group match against Ghana,” said Nomsa Mahlangu, the chairperson of women football and Safa National Executive member.

“However, we have just received a response from CAF informing us that they notified the Ethiopian federation about our predicament, but that our request has been turned down and the Ethiopians are insisting that the games should go ahead as scheduled.

“We have not yet given up hope and will engage both Ethiopia and CAF once more. But in the event of them turning us down again, we will have to consider negotiating with organizers of the Maputo All Africa Games.”

This might involve Banyana Banyana requesting permission to play their opening game against Zimbabwe possibly on September 3 instead of 5 and failing which, play Tanzania on September 8 and then complete the group matches against Ghana the next day.

Then catch a flight to Johannesburg and connect to Addis Ababa on September 10 and play the Ethiopians on September 11 and then fly back to Johannesburg and depending on if they have qualified for the semi-finals, rush back to Maputo to continue their participation in the event.

“It is certainly not an ideal situation,” admitted Mahlangu. “But what can we do? We articulated our predicament to CAF to relay to the Ethiopians and we thought they would be sympathetic to our problem. But clearly they are not impressed or interested and so, we have to re-arrange our plans.”

This now means Banyana will play Ethiopia who eliminated the Ghanaian Black Queens in the previous round of the 2012 London Olympic Games at the Sinaba Stadium on August 28 and then fly to Maputo for the All Africa Games opening ceremony.


መልካም ዕድል ለኢትዮጵያውያት ሴት አናብሥት !!!

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Sun Jul 24, 2011 7:14 pm

ሰላም ውድ ወገኖቼ :-

በኢትዮጵያ ስፖርት ታሪክ ወያኔነት ሥር የሠደደው በእግር ኳስ ፌዴሬሽን ውስጥ ነው : ዛሬ በወያኔ ጊዜ ብቻ ሣይሆን ከጥንት ከምስረታው ከአፄ ኃይለሥላሤ ጊዜ ጀምሮ :: እስኪ ይታያችሁ በራሱ አገር ሜዳ በጊኒ 4-1 የተሸነፈ የወንዶች ቡድን አለ :: ያ ቡድን ከዚያ በኋላ አንድ ጊዜ ብቻ ከኢትዮጵያ የተሻለ የእግር ኳስ ታሪክ የሌላትን የማዳጋስጋርን ቡድን 1-0 አሸንፏል :: በናይጀሪያ አቡጃ ላይ 4-0 ሲሸነፍ አዲስ አበባ ላይ 2-2 ተለያይቷል :: ስለዚህ እንዲህ ዓይነቱ ቡድን የውጪ ጨዋታ አደረገ አላደረገ ምን ፋይዳ አለው ? እንዲህ ያለውን ቡድን ይዞ በየውድድሩ መሄድ ኪሣራ እንጂ ትርፍ የለውም - የውርደት ክምር ከመሸከም በስተቀር :: በተቃራኒው የሴቶች ቡድንስ ? እስኪ ከታች ያስቀመጥኩትን የሊብሮውን አዘጋጅ የገነነ መኩሪያን አስተያዬት አንብቡት ::

ምንጭ:- ገነነ መኩሪያ : ሊብሮ : ቅዳሜ ሐምሌ 16 ቀን 2003 ዓ.ም. :: ኤግልስ ወደ መከላከያ ::
የኢትዮጵያ ሴቶች በአፍሪካ እግር ኳስ ጥሩ ስም አላቸው፡፡ አሁን ደግሞ ለኦሎምፒክ ለማለፍ ደጃፍ ላይ ናቸው ነገር ግን በአገር ውስጥ ያለው እግር ኳስ ትኩረት ያላገኘ፣ ድጋፍ ያጣ፣ አስታዋሽም ያላገኘ ነው፡፡ የሴቶች እግር ኳስ እስካሁንም የቆየው በራሳቸው በሴቶቹ ጥረት ነው፡፡ በተለይ ስፖርት ኮሚሽንና ፌዴሬሽኑ ለማጠናከር ምንም ጥረት አያደርጉም ፡፡ ይህ ለወደፊቱ በሴቶች እግር ኳስ ላይ ችግር ይፈጥራል፡፡ ከ3 ዓመት በፊት 15 ክለቦች ነበሩ፡፡ አሁን ግን ወደ 6 ወርደዋል፡፡ ቀስ እያሉ ደግሞ እየከሰሙ ይሄደሉ፡፡ አንዳንዶቹም ይፈርሱና ከብዙ ልመናና ጥረት በኋላ ስማቸውን ቀይረው ይይዟቸዋል፡፡ የሆነ ክፍለ ከተማ ሴቶች ሲወዳደሩ ቆዩና ሊፈርስ ሆነ፡፡ ኩዊንስ ኮሌጅ ያዛቸው፡፡ ኩዊንስ አልችልም ብሎ ሲፈርስ ቡና ያዘው፡፡ ቡና አልችልም ሲል ደግሞ ሴንትራል ያዘ ፡፡ ላለፉት 5 ዓመታት አግልስ በሚል ሲወዳደሩ የቆዩት ቡድን ሊቀጥል አልቻለም፡፡ ቡድኑ ሊፈርስ ስለሆነ የመከላከያ እግር ኳስ ከልብ ተጫዋቾችን አንድ ላይ በማቆት ለአገር የሚሰጡን ጥቅም ግምት ውስጥ በማስገባት ቡድን እንዳይበተን ይዟቸዋል፡፡ መከላከያ ስፖርት ክለብ ጥሩ ስራ ነው የሰራው፡፡ በተለይ አሁን ለኦሎምፒክ ለማለፍ በር ላይ ደርሰን ክለቦች አየፈረሱ ነው ሲባል የተጫዋቾችም ሞራል ሊነካ ይችላል፡፡ በነገራችል ላይ ከኤግልስ ክለብ ለብሔራዊ ቡድን ተሰላፊ የሆነቸው ቡርትካን ገ/ክርስቶስ ወደደቢት እንደገባች ይነገራል፡፡


እስኪ ተመልከቱ :roll: :roll: :roll: ውጤት የሌለውን የወንዶቹን ቡድን ያን ያህል ገንዘብ እያባከኑ የሚንከባከቡ ሰዎች ውጤት ያላቸውን የሴቶቹን ቡድን ግን እንዲፈርስ ይጥራሉ :: ታዲያ ችግር ፈጣሪዎቹ ወያኔያዊ እርኩስ መንፈስ የላቸውም ትላላችሁ 8) 8) 8) 8) 8) 8)

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ኮሎኔል » Wed Jul 27, 2011 7:27 pm

እስኪ ተመልከቱ ውጤት የሌለውን የወንዶቹን ቡድን ያን ያህል ገንዘብ እያባከኑ የሚንከባከቡ ሰዎች ውጤት ያላቸውን የሴቶቹን ቡድን ግን እንዲፈርስ ይጥራሉ :: ታዲያ ችግር ፈጣሪዎቹ ወያኔያዊ እርኩስ መንፈስ የላቸውም ትላላችሁ

በጣም እንጂ ልጅ ተድላ
የኢትዮጵያን ፉትቦል ቀደምት ታሪክ በደምብ አውቀዋለሁ
ያውም በማይረባ ወጪ የነበረውን ውጤት ሁላችሁም ታስታውሳላችሁ :: አሁን ግን ገንዘብም እያላቸው ቀዳሚው ወደኪስ ማስገባትና የአገሪቱን ኃይል ማዳከምና ማዋረድ ነው ሁላችን እናውቃለን ::
Ethiopia
ኮሎኔል
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 229
Joined: Fri Apr 07, 2006 7:19 pm
Location: zimbabwe

Postby ተድላ ሀይሉ » Sat Jul 30, 2011 5:13 am

ኮሎኔል wrote:
እስኪ ተመልከቱ ውጤት የሌለውን የወንዶቹን ቡድን ያን ያህል ገንዘብ እያባከኑ የሚንከባከቡ ሰዎች ውጤት ያላቸውን የሴቶቹን ቡድን ግን እንዲፈርስ ይጥራሉ :: ታዲያ ችግር ፈጣሪዎቹ ወያኔያዊ እርኩስ መንፈስ የላቸውም ትላላችሁ

በጣም እንጂ ልጅ ተድላ
የኢትዮጵያን ፉትቦል ቀደምት ታሪክ በደምብ አውቀዋለሁ
ያውም በማይረባ ወጪ የነበረውን ውጤት ሁላችሁም ታስታውሳላችሁ :: አሁን ግን ገንዘብም እያላቸው ቀዳሚው ወደኪስ ማስገባትና የአገሪቱን ኃይል ማዳከምና ማዋረድ ነው ሁላችን እናውቃለን ::


ሰላም ውድ ኮሎኔል :-

እንደምን ሠነበቱ ? ከዚህ መድረክ ሲጠፉ 'ደህና አይደሉም ወይ ?' ብለው የሚያስቡ ወገኖችዎ አሉና እንዲህ አንዳንዴ ድምፅዎን ያሠሙን ::

የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን አባሎች ለሎንዶኑ ኦሎምፒክ ለማለፍ ቁርጠኛ እንደሆኑ ባለፈው ሣምንት በአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ የእሑድ መጽሔት መርሃ ግብር ሲጠየቁ ከሠጧቸው መልሶች ለመገንዘብ ችያለሁ :: ወንዶቹ ተጨዋቾችም ሆኑ አሠልጣኞቻቸው ስለተከታይ ውድድሮች ሲጠየቁ (በተለይ ከአገር ውጪ ከሆነ) የሚሠጡት የተለመደ መልስ :- "ጥሩ ተከላክለን ውጤት አጥብበን እንመጣለን ::' የሚል ነው :: ገና ውድድሩን ሣያደርጉ በሥነ-ልቦና ተሸንፈው ስለሚሄዱ እስከዛሬ ከአገር ውጪ ያሸነፏቸው ውድድሮች በጣት የሚቆጠሩ ናቸው :: ሴቶቹ ግን አንበሶች መሆናቸውን ያወቅሁት ተከታዩን ከደቡብ አፍሪቃ ጋር የሚያደርጉትን ውድድር አሸንፈው ለሎንዶን ኦሎምፒክ እንደሚያልፉ በልበ-ሙሉነት ሲመልሱ ነው ::

በርቱልን እህቶቻችን : የኳስ ዕድል ከእናንተ ጋር ትሁን ::

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Sat Aug 27, 2011 8:20 pm

ሰላም ውድ ወገኖቼ:-

ዛሬ ሴት እህቶቻችን በሩጫውም : በእግር ኳሱም ጨዋታ አልቀናቸውም :: 'BBC Sport' እንደዘገበው ንኮ ማቶሉ የተባለቸዋ የደቡብ አፍሪቃ ተጫዋች ባስቆጠረቻቸው ሦሥት ጎሎች የደቡብ አፍሪቃ ቡድን የኢትዮጵያ አቻዎቻቸውን 3-0 አሸንፈዋል ::

ምንጭ:- BBC Sport, Saturday, 27 August 2011 18:13 UK. South Africa and Nigeria's women win Olympic first legs.

እህቶቻችን በመልሱ ግጥሚያ የደቡብ አፍሪቃን ቡድን ከሦሥት በበለጠ ጎል አሸንፈው እንደሚያልፉ አልጠራጠርም ::

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Thu Sep 08, 2011 9:06 pm

ሰላም ውድ ወገኖቼ:-

ሠሞኑን የእግር ኳሱ በሽታ ወደ አትሌቲክሱም ተጋብቶ ትልቅ ትርምስ ተፈጥሯል :: የሴቶች እግር ኳስ ግን ባልተጠበቀ ሁኔታ : ካልተጠበቀ አካል አጋር ያገኘ ይመስላል :: የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እያንዳንዱ በ'ፕሪሚዬር ሊግ' የሚወዳደር የእግር ኳስ ክለብ በሥሩ የአዋቂ ወንዶችን ቡድን ብቻ ሣይሆን የሴቶችን : የወጣቶችንና የአዳጊ ሕፃናትን ቡድኖች እንዲያቅፍ ደንብ በማውጣቱ ምክንያት የሴቶች እግር ኳስ አሁን የተሻለ አጋጣሚ አግኝቷል :: የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ይህንን ሞራል ይዘው የሚመጣው እሑድ የደቡብ አፍሪቃን ቡድን በማሸነፍ ለሎንዶን ኦሎምፒክ እንዲበቁ ትልቅ ምኞት አለኝ : ይቅናቸው ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Tue Sep 13, 2011 11:10 pm

ሰላም ውድ ወገኖቼ:-

ስለኢትዮጵያ ስፖርት በተለይም ስለ እግር ኳስ እንቅስቃሴ ጥሩ ትንታኔ ያቀርቡ ከነበሩት የቀድሞ ጋዜጠኞች ሟቹ ሰሎሞን ተሰማ ቀዳሚ ነበር :: ከእርሱ ሌላ ከእርሱም ቀደም ብሎ ሆነ ከዚያም በኋላ የስፖርት ዜናና ትንታኔ በማቅረብ ረገድ
በሬድዮ :- ፍቅሩ ኪዳኔ : ነጋ ወልደሥላሤ : ግርማ ነጋሽ : ይንበርበሩ ምትኬ : ጎርፍነህ ይመር እና ደምሴ ዳምጤ :
በቴሌቪዥን :- ፀጋ ቁምላቸው : ሰለሞን ገብረእግዚአብሔርና ዓለሙ መኮንን
የሚታወሱ ናቸው ::

የግል የስፖርት ጋዜጦች እንደ አሸን በፈሉበት ያለፈው 18 ዓመታት ውስጥ ከአቋሙ ሣይዋዥቅ : ያለውን ዕምነትና የስፖርት ፍልስፍና (በተለይ የእግር ኳስ) ለኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ያለመታከት በጋዜጣ ሲፅፍ ያስተዋልኩት ሰው ገነነ መኩሪያ ነው :: ገነነ በሙያው የስፖርት ጋዜጠኛ አይደለም :- ነገር ግን የቆዩ ታሪካዊ ሁኔታዎችን አስታውሶና አያይዞ ከመተንተን ጀምሮ የአሁኑንም የኢትዮጵያ የስፖርት እንቅስቃሴ ሁኔታ የሚዘግብበት ዘይቤ ይማርከኛል :: በእርግጥ እርሱ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ዕድገት አማራጭ የሥልጠና ሥልት ብሎ በሚያራምደው 'የተጠጋግቶ በዝግታ መጫዎት' ዘይቤ ብዙም ደጋፊ አይደለሁም : ምክንያቱም ዓለም 'በፍጥነት አስቦና ተንቀሳቅሶ በመጫዎት' ዘይቤ ወደፊት ሲራመድ የእኛ እግር ኳስ በዝግታ እና ጭራሽ በቀርፋፋ እንቅስቃሴ የተሻለ ውጤት እናመጣለን ብሎ ማሰቡ የዋህነት ስለሆነ :: ለማንኛውም ገነነ መኩሪያ ስለ እግር ኳሱ ዕድገት ሣይሆን ስለ አሠልጣኞችና ተጫዋቾች ደመወዝ ጣሪያ መንካት የጻፈውን መጣጥፍ አንብቡለት ::

ምንጭ:- ገነነ መኩሪያ : ሊብሮ ጋዜጣ : ማክሰኞ መስከረም 2 ቀን 2004 ዓ.ም. :: በ20 ዓመት በጀትና ደመወዝ የት ደርሷል ?

በ20 ዓመት በጀትና ደሞዝ የት ደርሷል?

ማክሰኞ መስከረም 2 ቀን 2004 ዓ.ም

በ1974 የጥቁር አንበሳ ቡድን አሰልጣኝ አቶ አባይነህ ደስታ 150 ብር ነበር የሚከፈላቸው ሞስኮብ 7 ዓመት ተምረው ነበር የመጡት፡፡ ከፍተኛ ባለሙያ ናችው፡፡ ጥቁር አንበሳ የሚጫወተው በትልቁ ዲቪዚዮን ውስጥ ነው፡፡ በዛን ዓመት አቶ አባይነህ የአዲስ አበባ ምርጥም አሰልጣኝ ነበሩ፡፡ በወቅቱ የአሰልጣኞች ደሞዝ ከዚህ የዘለለ አልነበረም፡፡ ይህ ጊዜ ማለት የኢትዮጵያ ቡድን ለሊቢያ የአፍሪካ ዋንጫ ያለፈበት ጊዜ ነበር፡፡ ቡድኑን ለአፍሪካ ዋንጫ ያሳለፈው መሐመድ ኡስማን(ሚግ) ሲሆን ደሞዙም 90 ብር ነበር፡፡ የማሸነፊያውን ጎል በማግባቱ የሚሰራበት ድሬዳዋ ጨርቃጨርቅ 4 ሜትር ጨርቅ በሽልማት ሰጥቶታል፡፡ ከ20 ዓመት በኋላ 2004 ላይ ሆነን ሁሉም ነገር ተቀይሯል፡፡ የተጨዋች ከፍተኛ ደሞዝ 3ሺ ብር ያህል ደርሷል፡፡ ኢንሴቲቭ፣ የፊርማና ሽልማት የመሳሰሉት ሲጨመር አንድ ተጨዋች በዓመት ከ 200 እስከ 300ሺ ብር ያገኛል፡፡ የዛሬ 20 ዓመት ፊርማ፣ ሽልማት፣ቦነስ፣ልዩ ልዩ ጥቅማጥቅም ስለሌለ ደሞዝ ብቻ በመሆኑ ተጨዋቹ በዓመት የሚያገኘው ጥቅም ከ1200 ብር አይበልጥም፡፡ በ1972 የኢትዮጵያ ሻምፒዮን የነበረው ትግል ፍሬ የዓመት በጀቱ 50ሺ ብር አይደርስም፡፡ ቡድኑ ሻምፒዮና ሲሆን ለተጨዋቾቹ የሰጠው ሽልማት 50 ብር ብቻ ነበር ያውም ብዙ ቀን አስጠብቋቸው፡፡ የሽልማቱ ገንዘብ ኮሚቴው ለመወሰን ስብሰባ ላይ ቁጭ ብሎ በጣም ሲከራከሩ ተጨዋቹ ውሳኔውን ለመስማት እዚያ ቁጭ ብለው ሰዓት እላፊ ስለደረሰ ሳይሰሙ ወደ ቤታቸው ሄዱ (ይህን የነገረኝ የቡድኑ አጥቂ የነበረው ንጉሴ አስፋው ነው)፡፡ ዛሬ ጊዜው ሁሉ ተቀይሯል፡፡ የዛሬ 20 ዓመት 150 ብር የነበረው የአሰልጣኝ ደሞዝ ዛሬ 20ሺ ደርሷል፡፡ በእግር ኳሱ በ20 ዓመት የታየው ለውጥ ምንድነው? የሚለውን ገምግሙት፡፡
ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Sun Oct 09, 2011 3:52 am

ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

በኢትዮጵያ ስፖርት ታሪክ ከአቶ ይድነቃቸው ተሰማ ቀጥሎ ቀዳሚ ታሪክ ካላቸው አንዱ አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ ናቸው :: ዛሬ ቅዳሜ መስከረም 27 ቀ 2004 ዓ.ም. በአውራ አምባ ታይምስ ቃለ-መጠይቅ ሠጥተዋል : ተከታተሉት ::

ምንጭ:- አቤል ዓለማየሁ : አውራ አምባ ታይምስ : ቅዳሜ መስከረም 27 ቀን 2004 ዓ.ም. :: "ይድነቃቸው ተሰማን የመሰለ 'መሪ' ያፈራች አገር ስፖርት ምን እንደሆነ በማያውቁ ሰዎች እጅ ወድቃ ትባዝናለች ::"

እኛ መልካም የመወያያ ወቅትን ስንፈልግ ቆየን እንጂ ለቃለ-ምልልስ ፈቃደኛነትዎን ከገለፁልን አምስት ወር ያልፋል:: ለዚህም በጣም እናመሰግናለን:: በአሁን ሰዓት የት እንደሚገኙ እና ምን እየሰሩ እንደሆነ ነግረውን ቆይታችንን እንጀምር ::

ለዚህ ቃለ-ምልልስ የአውራምባ ታይምስ መልዕክት የደረሰኝ ከዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከዴጉ- ደቡብ ኮሪያ ተነስቼ በፈረንሳይ- ፓሪስ በኢትዮጵያ- አዲስ አበባ በኩል አድርጌ ማፑቶ-ሞዛምቢክ ለመላው አፍሪቃ ጨዋታዎች ከርሜ ከጎጃም ተጉዞ ሱዳንን አቋርጦ የመጣው የአባይ ውሃ የሚፈስበት ምድረ ግብፅ ላይ ካይሮ ከተማ ሆኜ ነው::

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ስብሰባዎችን ስለምካፈል በተቻለኝ መጠን መልስ ለመስጠት ሞክራለሁ ብዬህ ነበር ሳይሳካልኝ ስለቀረ ፓሪስ ቤቴ ተመልሼ ነው ግዴታዬን ለመወጣት የቻልኩት :: አሁንም ወደ አዲስ አበባ የአፍሪካ ሕብረት ድርጅት ባዘጋጀው የአፍሪካ ስፖርት ሚኒስትሮች ጉባዔ ላይ የአፍሪካ ፉትቦል ኮንፌደሬሽን ተጠሪ ሆኜ ለመካፈል :: ከዚያም የመጪው አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ዝግጅትና ዕጣ አወጣጥ ሥነ-ስርዓት ለመከታተል ወደ ጋቦንና ኤኳቶሪያል ጊኒ ለመሄድ ሻንጣ እያዘጋጀሁ ነው :: ከዚህ ጉዞ ስመለስ የደቡብ ሱዳንን ሁኔታ ለማጣራት ወደ ጁባ አመራለሁ ::

ሥራዬ በአጠቃላይ የትልልቅ ዓለም አቀፍ ስፖርት ድርጅቶች መሪዎችን ማማከር : ጥናት ማካሄድ :: ሪፖርት መፃፍን የመሰለ ነው። ከብዙ ዓመታት በፊት በ65 ዓመቴ ጡረታ ወጥቼ አፍሪካን አገለግላለሁ የሚል ሃሳብ ነበረኝ ሙከራው በከፊል ቢሳካም በደንብ ለመሻሻል አልተቻለም :: አሁን ወደ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽኑ ተመልሻለሁ : ሁኔታውን እያጣራሁ ነው ::

"አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ ማናቸው?" ብሎ የሚጠይቅ በተለይ የስፖርት ቤተሰብ ይኖራል ማለት ቢከብድም ምናልባት ይህን ጥያቄ የሚያነሱ ካሉና ለማያውቆት በስፖርቱ ዓለም ያለዎትን አጀማመር፣ የዳበረ ልምድ ቢነግሩን::

ፍቅሩ ኪዳኔ አንድ ተራ ኢትዮጵያዊ በግዴታ ካልሆነ ስለራሱ ማውራት የማይወድ ነው። ዘሩን ሊጠይቁት ጉለሌ : ፒያሳ : አዲስ አበባ : ሸዋ : ኢትዮጵያ : አፍሪካ : ዓለም ብሎ የሚመልስ ነው ::

ስለ ስፖርት በአጠቃላይ የተማርኩት አገሬ ውስጥ ነው :: አቶ ይድነቃቸው ተሰማን የመሰለ ምርጥና ድንቅ መምህር ነበረኝ :: ከዛሬ 57 ዓመት በፊት በስፖርት አስተማሪነት ሥራ ጀመርኩ። ከሶስት ዓመት በኋላ ወደ ጋዜጠኝነት ሞያ ዞርኩ :: ጥንት የነበርነው ጋዜጠኞች ራሳችንን በራሳችን ያስተማርን:: የመጻፍና የመናገር ችሎታ ያለን : ሞያውን የምንወድ ብቻ ነበርን:: በኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የንጉሰ-ነገስቱ መንግስት ማስታወቂያ መሥሪያ ቤት የቀጠረው የስፖርት ጋዜጠኛ እኔ ነኝ::

የምሰራው በአማርኛና በፈረንሳይኛ ለሚታተመው የዛሬይቱ ኢትዮጵያ (ኤትዮፒ ኮዦርድዊ) እና ለኢትዮጵያ ሬዲዮ ጣቢያ ነበር:: ከዚህም በቀር ለመጀመሪያ ጊዜ በአገራችን ታሪክ ውስጥ ከአዲስ አበባ ስታዲዮም በቀጥታ በኢትዮጵያ ራዲዮ ጣቢያ ከ50 ዓመት በፊት ኢንተርናሽናል የእግር ኳስ ጨዋታ ያስተላለፍኩት እኔ ነኝ:: ከ51 ዓመት በፊትም የኦሊምፒክ ጨዋታ የሚል መጽሐፍ ጽፌ አሳትሜ ለሕዝብ አቅርቤያለሁ:: የሽማግሌ ታሪክ ረዥም ስለሆነ እዚሁ ላይ እንግታው ::

የትምህርት ሁኔታስ… በርካታ ቋንቋ ተናጋሪ ነዎት። ይህን የተማሩትስ እንዴት ነው?

የእኔ የትምህርት ደረጃ ቢያንስ የ75 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያንን የሚመስል ነው። ‹‹አልሞት ባይ ተጋዳይ›› ነኝ፤ አሁንም እየተማርኩ ነው። ኮምፕዩተር፣ የኪስ ስልክ ለመጠቀም ብቻ የቴክኒክ አዋቂ መሆን ያስፈልጋል። ፈረንሳይኛና እንግሊዘኛ ሊሴ ገብረ ማርያም ት/ቤት፣ ጣሊያንኛ ማታ ማታ ጣሊያን ት/ቤት፣ ስፓኒሽ ማታ ማታ በስፔን ኤምባሲ፣ አማካይነት አዲስ አበባ ውስጥ ተምሬያለሁ።

በዓለም ውስጥ ተበታትኖ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ሁሉ የማይናገረው ቋንቋ የለም። በአውሮፓና አሜሪካ ብዙ ኮርስ በመከታተል እውቀቴን አሻሽያለሁ። እኔም በተራዬ አስተምራለሁ። አንድ ሰው እድሜ ልኩን የሚኖረው ሐብት የቀሰመው ትምህርት ብቻ ነው። ድህነትም ራሱ ተማሪ ቤት ነው። በሁለት እግር ለመቆምና ራስን ለመቻል ልዩ ልዩ ዘዴና መፍትሄ የሚጠነስስበት ነው። በወገብዋ እንጨት ተሸክማ ከእንጦጦ የምትወርደው፣ ከሰል አዘጋጅታ የምትሸጠው፣ ጉሊት የምትውለው አልደላትም እንጂ ሕይወት ት/ቤት ተምራለች።

190 የሚጠጉ አገራትን እንደጎበኙ አውቃለሁ። ከእዚህ ሰፊ ጉዞዎ ከስፖርቱ ዘርፍ ምንን ተማሩ? የመጀመሪያ ጉዞ ያደረጉስት ወዴት ነበር? ጥንት ከተማ መዞር ያስነቅፍ ነበር፤ ዘዋሪ ነው ይባላል። አሁን ዓለምን የሚዞር ይደነቃል። ለማንኛውም ዘዋሪ ሆኜ ቀርቻለሁ። እስከ አሁን የጎበኘኋቸው አገሮች 188 ነበሩ። ደቡብ ሱዳን ነፃ በመውጣትዋ የተነሳ 189 ደርሻለሁ። ሕይወት ራሱ ቋሚ ተማሪ ቤት ስለሆነ በሄድኩበት አገር የሚቀሰም አይጠፋም፤ ቢያንስ በባህል ዘርፍ

ጥያቄው ስፖርት ነክ ስለሆነ ስዊድንን ልጥቀስ። በአንዳንድ የስዊድን መጠነኛ ከተሞች ውስጥ ያሉት ትምህርት ቤቶች መጻሕፍት ቤትና ስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች አሏቸው። እስከ ቀትር ድረስ ተማሪዎቹ ይጠቀሙበታል። ከቀትር በኋላ ደግሞ ያከትማል፤ ነዋሪዎች ይገለገሉበታል። ይህ ሐብታም አገርና ማዘጋጃ ቤቶቹ በዚህ ዘዴ የሚጠቀሙት ወጪ ለመቀነስ ነው። አፍሪካዊያኖች በእንደዚህ ዓይነት ዘዴ አንጠቀምም። ሁሉም የራሱን ግንብ መገንባት ነው የሚሻው። አንዳንድ የአፍሪካ አገሮች ትምህርት ቤቶች የክፍል ማነስ ችግር ሲገጥማቸው ባዶ ስፍራ ፈልገው ኳስ ሜዳው ላይ
ይሰራሉ።

በመጀመሪያ ያደረግኩት ጉዞ በባቡር ከአዲስ አበባ አዳማ ድረስ ነው። የክረምት ዕረፍቴን የማሳልፈው አዳማአጎቴ አዳፍሬ ገብሬ እና አክስቴ አበበች ገብሬ ዘንድ ነበር። ከዚያም ቦይስካውት ሆኜ በሊቶሪና (ባቡር) ድሬድዋ ድረስ ሄጃለሁ፤ በአውቶብስ ከድሬዳዋ ሐረርም ተጉዣለሁ። በአውሮፕላን ከቢሾፍቱ አስመራ፣ ከኢትዮጵያ ውጪ ደግሞ የሄድኩት ኮንጎ ነው። በአሁኑ ወቅት ጉዞ ራሱ ትምህርት ነው። በእጅ የሚከፈትና የሚዘጋ ቧንቧ እየጠፋ ነው። ራሱ ውሃ ለክቶ በሚያፈላ እየተተካ ነው። ኢሚግሬሽን በአምስት ጣቶች ማስፈረም ፎቶግራፍ ማንሳት ጀምረዋል። የጉምሩክ የፍተሻ መሳሪያ ቢያንስ ዋሽንግተን ኤርፖርት ዕርቃነ ሥጋ የሚያሳይ ነው። ፓስፖርቱም ተቀይሯል። ይህ ሁሉ ጣጣ ሳይመጣ ነው ዓለምን የዞርኩት።

ጥቂት የአፍሪካ አገሮችን የጎበኘሁት ገና ነፃ ሳይወጡ ስማቸውን ሳይቀይሩ ነው። ኬኒያ፣ ዩጋንዳ፣ ታንጋኒካ (ታንዛኒያ)፣ ኒያሳላንድ (ዛምቢያ)፣ ሮጄሺያ (ዚምባብዌ)፣ አንጎላ፣ ሩዋንዳ፣ ቡሩንዲ። ምስራቅ አፍሪካ በመባል ይጠሩ በነበሩት ሶስት አገሮች (ኬኒያ፣ ዮጋንዳ፣ ታንጋኒካ)በእንግሊዝ ቁጥጥር ሥር በነበሩበት ጊዜ በከተሞቻቸው ሆቴሎች ውስጥ መግባት የሚችሉት ጥቁሮች፤ ከነፃ አገር የመጡት ኢትዮጵያዊያኖች ብቻ ነበሩ።

አገራችን የእርስዎን ልምድ መጠቀም እንዳልቻለች ይነገራል። እርስዎ ለመርዳት ዝግጁ ካለመሆንዎ የመነጨ ነው ወይስ በስፖርቱ ውስጥ ያሉ ሰዎች መልካም ፈቃደኝነት አለመኖር? ‹‹እዚህኛው ፌዴሬሽን ውስጥ ላግዛችሁ ብላቸው ፈቃደኛ አልሆኑም›› የሚሉት ካለም ቢነግሩን?

አገሬ ኢትዮጵያን ዕድሜ ልኬን በነፃ አገልግያታለሁ። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ የብስክሌት ፌዴሬሽን፣ የቴኒስ ፌዴሬሽን፣ የሸዋ እግር ኳስ መምሪያ ዋና ፀሐፊ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ፣ እ.አ.አ. በ1968 እና በ1976 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር አዘጋጅ ኮሚቴ ዋና ፀሐፊ፣ የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህብር መሥራችና ፕሬዚዳንት ነበርኩ። አሁንም ቢሆን ለመርዳት እሞክራለሁ። ዳሩ ግን ይሄን ይሄን ሰራሁ ብዬ የሚያስፎክረኝ ምክንያት የለም። የአገልግሎቱ ግብ የሞራል ግዴታን ለመወጣት፣ ህብረተሰቡን ለመርዳት እንጂ በአደባባይ ፎቶግራፍ ለመነሳት አይደለም።

የኢትዮጵያ ስፖርት አመራር በመንግስት ቁጥጥር ሥር ያለና እና ፖለቲካ የተከናነበ መሆኑ ግልፅ ነው። ሆኖም ከማውቃቸው ጥቂት መሪዎች ጋር ያለኝ ግንኙነት በጣም ጥሩ ነው። ሃሳብ ለሃሳብ ለመለዋወጥ የሚያዳግት ነገር የለም። ሁሉም ቅርንጫፎች የራሳቸው ባለሙያዎች ስላልዋቸው እርዳታ አያስፈልጋቸውም። ለማንኛውም ‹‹አግዘኝ›› ተብዬ ተጠይቄ እንቢ ያልኩበት ጊዜ የለም። ለምሳሌ የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ጊዜ አገልግሎቴን አበረክቻለሁ።

እርስዎን ጨምሮ በዓለም አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴ፣ በካፍና በፊፋ ውስጥ እድል ገጥሟችሁ የሰራችሁ ሰዎች ለራሳችሁ በገንዘብ ተጠቃሚ ከመሆን ባለፈ ተተኪ አመራሮችን በማፍራት፣ ለአገራችሁ መልካም የስፖርት የልማት ስራዎች እንዲሰሩ በማድረግ አስተዋጽኦ እንዳላበረከታችሁ የሚናገሩ አሉ። ይህንን ይቀበላሉ?

እነኚህ የምትላቸው ሰዎች ለምሳሌ ያህል ለአገራቸው ያበረከቱን አስተዋጽኦ ብትጠቁመኝ ጥሩ ነበር። ለማንኛውም አንዳንድ ሰዎች ስለሚሉት ግድ የለኝም። ደግሞስ የት ያውቁኛል? ከአገሬ ከወጣሁ 36 ዓመት ሆኖኛል። ጥንት ያሰለጠንኳቸው እንኳን ጡረታ ወጥተዋል። ይህን ትችት የሚሰነዝሩ በሎተሪ ገቢ የሚኖሩ መሆን አለባቸው። የዓለም አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴ፣ ካፍ ወይም ፊፋ መሃይም አይቀጥሩም። የሚቀጥሩት ሰው ድርጅቱን እንዲያገለግል ነው እንጂ የአገሩን ሰው ፈልጎ ሥራ እንዲያሲዝ አይደለም።

አንድ ኢትዮጵያዊ ተፍጨርጭሮ ራሱን አስከብሮ ከፍተኛ ኃላፊነት ተረክቦ መሥራትና ቤተሰቡን ማስተዳደር ኃጢአት ከሆነ የቅዱስ ጊዮርጊስን ጠበል እጠጣለሁ። እኔ የሰራሁትን አልዘረዝርም፤ ምክንያትም የለም። እነኚህ ቡና ቤት ቁጭ ብለው ከሚዶለቱት የተሻለ ተግባር መፈፀሜን የሚያውቅ ይመሰክራል። ይህን አሁን የማስተምረው በመስከረም ቤልዢክ አገር ዩኒቨርሲቲ ለገባው የ18 ዓመቱ የልጅ ልጄ ነው። ስለ አስተዋጽኦ ከተነሳ የአገራችንን የስፖርት ፌዴሬሽኖች በልዩ ልዩ ተግባር ለመርዳት የሚችሉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች አሉ። ጡረታ የወጡም ስለነበሩ ለማገልገል ይችሉ ነበር፤ ነገር ግን የፖለቲካ መልካቸው አይጥም ይሆናል።

ስለ ኢትዮጵያ እግር ኳስ እና አትሌቲክስ ወቅታዊ ሁኔታ ምን ይላሉ?

የኢትዮጵያ እግር ኳስ አልተሳካለትም። ጥንት በብዙዎቹ ክለቦች ውስጥ ይጫወቱ የነበሩት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ነበሩ። አንዳንዶቹ እንደ ነፀረ ወልደ ስላሴ ከዳግማዊ ምኒሊክ ት/ቤት፣ ሙሉጌታ ወልደ ጊዮርጊስ ከኮተቤ ተመርጠው እስከ ብሔራዊ ቡድን መጫወት ችለዋል። የትምህርት ቤቶች ስፖርት ውድድር ከተቋረጠ በኋላ እንደ ቅርጫት ኳስ፣ የአጭር ሜትር ሩጫ ያሉ ስፖርቶች ተዳክመዋል።

አዲስ አበባ ውስጥ ወጣቶች መጫወቻ ሜዳ አጥተው ባቡር መንገድ ላይ ነው የሚጫወቱት። አዳዲስ የሚሰሩት ሕንፃዎች እንኳን ለሕፃናት መዝናኛ ስፍራ ይቅርና መኪና ማቆሚያም የላቸውም። የአንድ አገር ስፖርት የሚገነባው አስፈላጊው ጉዳዮች ከተሟሉ በኋላ ነው። እግር ኳስን ለማዳበር ከልጅነታቸው ጀምረው ተማሪ ቤት ወይም በክለብ ደረጃ እንዲሰለጥኑ ማድረግ ነው። የተተኪ ተጨዋቾች ምንጭ ነውና በብሄራዊ ደረጃ ከ17፣ ከ20ና ከ23 ዓመት በታች የወጣቶች ሻምፒዮና ማዘጋጀት የግድ ያስፈልጋል። የሴቶችም ሻምፒዮና በብሄራዊ ደረጃ
እንዲዘጋጅ መጣር ይገባል።

የእግር ኳሱን ወቅታዊ ደረጃ ያገናዘበ አሰልጣኝ፣ የዘመናዊ አሰራርና የዘመናዊ ስታዲየም አለመኖርስ…

የአሰልጣኞች ችግር እንዳለ ግልፅ ነው። በአሁኑ ወቅት ጥሩ አሰልጣኝ ለመመልመል ሃብት ያስፈልጋል። ኳስ ተጨዋች የነበረ ሁሉ አሰልጣኝ ሊሆን ይችላል ማለት ስህተት ነው። ጥሩ አሰልጣኝ የተማረ፣ በየጊዜው መጽሐፍ በማንበብ የቴክኒክ ለውጦችን የሚከታተል፣ ስለ ሰውነት ማዳበሪያ ስራዎች እውቀት ያለው መሆን አለበት። ከአማርኛ ውጭ ሌላ ቋንቋ የማያውቅ ከሆነ ራሱን ሊያሻሽል አይችልም።

የእግር ኳስን ስፖርት በኢትዮጵያ ለማስፋፋት ብዙ ሜዳዎች፣ አሰልጣኞች የሰውነት ማዳበሪያ ትጥቆች ወዘተ ያስልጋል። ከአፍሪካ ውስጥ ጥሩ ዘመናዊ ስታዲዮም የሌላት ብቸኛ አገር፤ ኢትዮጵያ ነች። በስታዲዮም እጦት የተነሳም አህጉር አቀፍ ውድድሮች ማዘጋጀት አልተቻለም። ለማንኛውም አንድ ጥሩ ቡድን ለመገንባት ዓመታት ይፈጃል። ብንሸነፍም ቅሉ በሁሉም ዘርፍ መካፈል ይጠቅማል።

አንድ ቡድን ሲሸነፍ አርቢትሩን እንደሚወነጅል ሁሉ ብሔራዊ ቡድኑ ሲሸነፍ አሰልጣኙና የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት መተቸታቸው አይቀርምና መሪዎቹ የተቻላቸውን ያድርጉ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሲጫወት በመጨረሻ ያየሁት ቤንጋዚ ሊቢያ እ.አ.አ. በ1982 ስለሆነ አስተያየቴ የተወሰነ ነው። ለማንኛውም ሁኔታው ተስፋ የሚያስቆረጥ አይደለም።

ባለፈው የዓለም ዋንጫ ውድድር ጋና ያሰለፈችው ተጨዋቾች የዓለም የወጣቶች ሻምፒዮና ያሸነፉ ነው። እኛም ወጣቶቹ ላይ ማተኮር አለብን። አሁን ለትችት የበቃው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከሁሉም ፌዴሬሽኖች የተሻለ፣ መደነቅና መከበር የሚገባው ነው። በአፍሪካ ውስጥ የራሱን ሕንፃ በመገንባት ብቸኛ ነው። የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ብሥራት ጋሻው ጠና በጣም ታታሪ፣ አርቆ አስተዋይ የአትሌቲክስን ስፖርት በአገራችን ለማስፋፋት ከፍተኛ ጥረት ያደረጉ መመስገን የሚገባቸው መሪ ናቸው።

ባለፈው የዓለም ሻምፒዮና ጥሩ ውጤት ስላልተገኘ ብቻ ቤት ለማፍረስ ቂም ለመወጣት የሚሞክሩ ቀዝቀዝ ቢሉ ይሻላቸዋል። ሁልጊዜ ምንም ያልሰራው ነው የሚገነፍለው። ሯጮቻችን እየደከሙ እንደሆነ ግልፅ ነው። በተለይ የኬኒያ አትሌቶች ጥሩ ውጤት ሲያመጡ ኢትዮጵያውያኖች የት ሄዱ? የሚል ጥያቄ ያስከትላል። እኔም ዴጉ ደቡብ ኮሪያ ነበርኩ። ያገኘነው ውጤት ካለፈው ጊዜ ያነሰ ነው እንጂ አስከፊ አይደለም። ስለ ሜዳሊያ ጉዳይ ሲነሳ ሁሌ የማስታውሰው ሕንድን ነው። ይህች የአንድ ቢሊዮን ሁለት መቶ ሚሊዮን ሕዝብ አገር ባዶ እጅዋን ስትሄድ እኛ ሜዳሊያ አነሰንእንላለን።

ሞዛምቢክ ላይ በመላው አፍሪካ ጨዋታዎች የተወዳደሩት ሁሉ አዳዲስ አትሌቶች ናቸው። በአጫጭር ሩጫዎችም ተስፋ የሚሰጥ ውጤቶች ስለተገኙ ጥሩ ማበረታቻ ነው። ኢትዮጵያም ልክ እንደ ኬኒያ ወጣቶቹን ማዘጋጀት አለባት። የለንደን ኦሊምፒክ እየተቃረበ ስለሆነ ለልምምድ የሚያስፈልገውን ማሟላት ነው። ለዝግጅቱ ግን የፖለቲካ ትርጉም መስጠት አያስፈልግም። ስፖርት፤ ስፖርት ነው። የፖለቲካ መሳሪያ አይደለም።

ወ/ሮ ብሥራትና የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ አመራሮች ስህተቶችን ለማረም ተገቢ የሆኑ ውሳኔዎችን መውሰድ ይችሉ ዘንድ ማበረታታት ነው እንጂ መወንጀልና መንቀፍ ተገቢ አይደለም። ‹‹ትክክል ስሰራ የሚያስታውስ የለም። ስሳሳት ግን የሚረሳ የለም› የሚለውን የእንግሊዝኛ ጥቅስ የሚያስታውስ ሁኔታ ነው።

አትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ በበርካታ ችግሮች የተተበተበ መሆኑ ይነገራል። እርስዎ ታዲያ በጎ አስተያየት የሰጡት ከምን ተነስተው ነው?

እኔ የምደግፈው ፌዴሬሽኑን ነው። ውጤት ሲጠፋ ምንም እንዳልሰሩ እና እንደ ወንጀለኛ መቁጠር ስህተት ነው። ስፖርት ላይ የምትፅፉ ጋዜጠኞች ይህንን ማስተማር አለባችሁ። አንድ አትሌት ሲጎዳ እንደ መኪና ሄደህ መርካቶ መለዋወጫ ልትገዛለት አትችልም። ሰብዓዊ ፍጡር ነው ሊቆስል፣ ሊደክምና ሊታመም ይችላል። ይህ ከሆነ ደግሞ ውጤት ላይገኝ ይችላል።

ልልዎት የፈለግኩት… ፌዴሬሽኑ አዎ ህንፃ ገንብቶ በኪራይ ገቢ ያገኛል፤ መልካም ነገር ነው። ለህዝቡ ህንፃው ያን ያህል ምን ይፈይድለታል?

ሜዳሊያዎችን (አገራዊ ክብርን) ያስቀድማል። በጥቅሉ ፌዴሬሽኑ ውስጥ ዘረኝነት መንገሱ፣ በአትሌቶች እና በአሰልጣኞች ምርጫ ሁሌም ቅሬታ እንዳለበት ይነገራል። እርስዎ ደግሞ ይህን ቤት የሚመሩትን ፕሬዚዳንት (ወ/ሮ ብስራትን) እያደነቁ ነው። አድናቆትዎ ተገቢ ነው? እኔ የማየው ከውጪ ሆኜ ነው። ወ/ሮ ብስራትንም መርጦ የሾማት ፌዴሬሽኑ እንጂ እኔ አይደለሁም። የምሰጠውም የራሴን አስተያየት ነው። አፍሪካን ዞሬ አይቻለሁ። የሴት መሪ አልገጠመኝም። ለኢትዮጵያ ይቅርና ለአፍሪካ ምሳሌ የሆነች ሴት ነች። አንተ ያልካቸው በዘር ላይ መሰረት ያደረጉ አሰራር እንዳለ እናውቃለን። በመንግስት ደረጃ ያለን ነገር ምን ታደርገዋለህ?

አሰልጣኞች… የሚያሰለጥኑት የድሮ ሯጭ ስለሆኑ ነው እንጂ ተምረው መፅሐፍ ገልጠው ሲያነቡ አንድም ጊዜ አይቼ አላውቅም። አንብበህ ዓለም ላይ ያለውን የቴክኒክ ለውጥ መረዳት አለብህ። የጃፓንን ወይም የአሜካንን አሰለጣጠን ለማጣቀሻነት አንብበው ካልተረዱ … እንዲው ዝም ብሎ ብቻ ‹‹አራት ጊዜ ሜዳውን ዙር›› ማለት ብቻ ማሰልጠን አይደለም። የእኛ አትሌቶች በተፈጥሮ ባላቸው እውቀት የተለዩ ናቸው እንጂ ሰው አሰልጥኗቸው አይደለም። በርግጥ ሊያስተምሯቸው የሚችሉት ትንንሽ ነገሮች የሉም ማለቴ አይደለም። በዜግነት አሜሪካዊ የሆነ አሰልጣኝ ስላመጡ በአጭር ሜትሮች መሻሻሎች እየታዩ ነው፤ ጥሩ ውጤት ሊያመጡ ችለዋል።

ሙሉ ምላሽ አልሰጡኝም። ወ/ሮ ብስራት በዋናነት ሰርተውታል የሚሉት ነገር ምንድነው?

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስርዓት እሷ እየመራችው ውጤት ተመዝግቧል፤ የራሱ ሆቴል (ብሔራዊ ሆቴል) ኖሮታል፣ ህንፃ ገንብቷል። አሁን ከሁሉ በኩል አስተያየት ስለተቀጣጠለ በፊት የሰሩትን ሁሉ እናፍርስ ነው?

በመጨረሻም በቀድሞው አመራር ዘመን በእግር ኳሱ ሰፈር በተፈጠረ አለመግባባት ኢትዮጵያ በፊፋ እንድትቀጣያደረጉ የእግር ኳሱ አመራሮች አንድ ቀን በፍርድ ቤት መጠየቅ አለባቸው የሚል ፅኑ አቋም እንዳልዎት ይነገራልና ጉዳዩን ቢያብራሩልኝ? በዋነኝነት ለዚያ ችግር መከሰት ጣትዎን የሚጠቁሙት ወደ ማነው?

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና በክለቦች መካከል ተፈጥሮ በነበረው ግጭት የስፖርት ሚኒስቴሩ መዳኘት ባለመቻሉ ኢትዮጵያ ከፊፋ አባልነት ታግዳ ነበር። ከዚያም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አማካይነት ፊፋ ጠቅላላ ጉባዔ ጠርቶ ምርጫ በማካሄድ ዕገዳው እንዲነሳ ሆኗል ይህ ሁሉ ትርምስ ለአገራችን ያስከተለው ውርደት ነው።

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን መሥራች አባል የሆነች፣ ሶስት ጊዜ የአፍሪካን ዋንጫ ውድድር ያዘጋጀች ለሌሎች ምሳሌ የነበረችና ይድነቃቸው ተሰማን የመሰለ ታዋቂ መሪ ያፈራች አገራችን ስፖርት ወይም እግር ኳስ ምን እንደሆነ በማያውቁ ሰዎች እጅ ወድቃ ትባዝናለች የተቆጨ ቢኖር ኖሮ ‹‹በሕግ አምላክ!›› ማለቱ አይቀርም ነበር።

የግል ጥቅማቸውን ከአገራቸው ጥቅም በላይ አድርገው ፌዴሬሽኑን እንዲታገድ ያበቁ እነማን እንደሆኑ ሕዝቡ ያውቃል ጠቋሚ አያስፈልገውም ለጊዜው ሁሉም ተድበስብሶ ስለተቀበረ መቃብር መቆፈሩ ዋጋ የለውም ነገር ግን የእግር ኳስ ጉዳይ እንደመሆኑ መጠን ስለማይረሳ አንድ ቀን ወጣቱ ትውልድ አገራችንን ያዋረዱትን በህግ ‹‹እንፋረድ›› ማለቱ አይቀርም።
ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Tue Oct 11, 2011 5:32 am

የ28ኛው የአፍሪቃ እግር ኳስ ሻምፒዮና ውድድር ተሣታፊ አገሮች ዝርዝር ታወቀ ::

ከትላንት ወዲያ በተደረጉት የመጨረሻ ዙር የማጣሪያ ውድድሮች ለ28ኛው ዙር የአፍሪቃ ዋንጫ የመጨረሻ 16 ውስጥ የገቡት ቡድኖች ታውቀዋል :: እነርሱም :- ጋቦንና ኢኳቶሪያል ጊኒ (አዘጋጅ አገሮች) : ኒጀር : አንጎላ : ቦትስዋና : ኮት-ዴቯር : ጋና : ጊኒ : ማሊ : ሴኔጋል : ቱኒዚያ : ዛምቢያ : ቡርኪና ፋሶ : ሞሮኮ ሊቢያና ሱዳን ናቸው :: ዘንድሮ ብዙ በተደጋጋሚ ለዋንጫ ፉክክር ያልቀረቡ አገሮች የሚታዩበት ውድድር ይሆናል ማለት ነው ::
ምንጭ:- CAF, Monday October 10, 2011. Qualified teams for Orange CAN 2012.

Gabon, Equatorial Guinea (co-hosts), Niger, Angola, Botswana, Côte d’Ivoire, Ghana, Guinea, Mali, Senegal, Tunisia, Zambia, Burkina Faso,Morocco, Libya and Sudan.

Libya and Sudan secured the two places at the 2012 Africa Cup of Nations reserved for the best runners-up from qualifying groups containing three or four teams.

በሌላ ወገን ከ16ቱ ውጪ ከሆኑት አንጋፋ ቡድኖች መካከል የ7 ጊዜ አሸናፊዋ ግብፅ : የ4 ጊዜ አሸናፊዋ ካሜሩን : የ2 ጊዜ አሸናፊዋ ናይጄሪያ : ከአፓርታይድ አገዛዝ ነፃ ከወጣችበት ጊዜ ጀምሮ በተከታታይ የተሣተፈችዋ ደቡብ አፍሪቃ ይገኙበታል :: ደቡብ አፍሪቃ የፊፋ ሕግ ተጥሦ ከውድድር ውጪ ሆኛለሁ ብላ ክሥ እያሠማች ትገኛለች ::
ምንጭ:- Super Sport, Monday October 10, 2011. Safa officially files protest.

The South African Football Association (SAFA) has officially filed a protest letter to the Confederation of African Football (CAF) on Monday following the controversial 2012 Africa Cup of Nations (AFCON) qualifying ruling that eliminated Bafana Bafana, despite them finishing on top of Group G on goal difference based on article 37.5 interpretation of the regulations.

CAF invoked rule 14.1, which states that in case of equality of points between two or more teams, after all the group matches, a greater number of points obtained in the matches between the concerned teams will determine the group winner.

"We hereby declare a dispute with CAF, in terms of article 14.7 of CAF statues, regarding the provisions of the regulations due to their inconsistency with the Regulations of Fifa Competitions and their effect of promoting unfair competition, amongst other things.

"We are of the opinion that this particular rule should be thrown out because it defeats the traditional way of determining a log standing," said SAFA CEO, Robin Petersen.

There is a legal precedent in South Africa were an appeal body rescinded unfair competition rules after the fact.

SAFA admitted to knowing that they were well aware of rule 14.1 ahead of Saturday's clash with Sierra Leone, but their interpretation of the rule differed from that of CAF. They interpreted "between" to mean between South Africa and each of the teams tied on points with them.

Based on that, it was the technical team's thinking that Bafana Bafana only needed a draw to qualify; so they played for a draw in the closing stages of the match.

On a previous occasion when three teams were left on equal number of points, both interpretation yielded the same outcome and therefore there was no complaints.

This is the first time that three teams ended up with the same number of points and the two interpretations lead to a different ranking and it is the first time the rule is identified as unfair because in this instance, the team that performed the best got eliminated.
ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Sun Jan 15, 2012 9:55 pm

እሑድ ጥር 6 ቀን 2004 ዓ.ም.

ሰላም ወገኖቼ :-

በመሸነፍም ሴቶቹ የተሻለ ሪከርድ አስመዘገቡ :: የኢትዮጵያ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን በግብፅ የሴቶች የእግር ኳስ ቡድን 4-2 ተሸንፈዋል :: በግብፅ ምድር ወንዶች 2 ጎሎች ያስቆጠሩበትን ጊዜ አላስታውስም :: እንዲያውም ከ6 ጎሎች ባነሠ የተሸነፉበት ጊዜ በጣም ጥቂት ነው :: ይህንን የትላንትናውን የካይሮውን ውድድር የተከታተለው የካፍ ሪፖርተር እንደዘገበው የኢትዮጵያ ቡድን ተጫዋቾች ቢሸነፉም ጨዋታውን ተቆጣጥረው ጨርሠዋል ::

ምንጭ:- CAF Online, Saturday January 14, 2012. Egypt beat Ethiopia 4-2 in Cairo.

Egypt women’s football team will take a two goal cushion to Addis Ababa in the return leg of the 2012 African Women Championship preliminary round match in a fortnight’s time. Home side Egypt emerged victorious in a closely fought encounter with two goals from captain Engi Atia and one each from Salma Tarek and Haiam Abd El Hafiz. Ethiopia replied through Erehima Biza and Shetaye Abaa.

Egypt were quick to settle into the game and forced early corner kicks as forwards Nesma Fekry , Mahera Ali and Salma Tarek sought to stretch out the Ethiopian defence. The first corner kick for Egypt had Dagmawet Bekele in goal for Ethiopia parry the ball away from her goal-line with her defenders still finding their feet. The sight of it all was all Engi Atia needed when she lined up the second corner kick which she swung with her left boot and it eluded all in the box to nestle into the back of the net for the opening goal.

A stunned Ethiopia slowly got back into the game and impressed with some short neat passes initiated from the back. Soon Eden Negri was finding her range with passes and linking up with midfielder Birtukan Ware, Biza and Abaa but the final ball and short was largely lacking. Egyptian defence held tightly by Neven Gamal and Yasmin Samir was soon over-working as the Ethiopians dominated play. One well worked out move started by Berktawit Aboye put Abaa through on goal but she shot tamely straight into Fawkia Amry’s hands but the warning signs were flashing for the hosts. As the half time mark beckoned Ethiopia were virtually camped in the Egyptian half leaving the home side chasing the ball. The equaliser eventually came through Biza who headed clinically past Amry from a delightful cross by Abaa after some neat exchanges. The teams went into the break at 1-1 with Egypt relieved for a change to regroup.

At the start of the second half both coaches introduced substitutes and the new players had immediate impact. Haiam Abd El Hafiz brought some pace and trickery upfront for Egypt. She almost put Egypt in front when she intercepted an attempted pass across the backline by the Ethiopians but her shot sailed over the cross bar. The Ethiopian defence didn’t seem to heed the danger of playing the square passes across the backline and they were to pay for it later. Abdel Hafiz got onto a through ball but seemed to have had a heavy touch as she raced towards goal. Bekele came off her goal-line and from the ensuing contact with Abd El Hafiz the Egyptians were awarded a penalty. Up stepped Atia to skillfully convert for hers and Egypt’s second goal. The goal brought back the momentum in Egypt’s favour and they went in search for more goals with Sara Abdallah and Salma Tarek making dangerous runs behind the opposition’s defence.

Egypt carved up a move involving a number of players and it was skillfully finished off by Tarek running onto a ball into space behind the defence and she picked her spot, knocking it past Bekele as she came off her line. Ethiopian was stunned again and it got worse shortly afterwards when Ethiopian captain Bezuhan Alemar who up until then had had a good game was caught in two minds with the ball at her feet. She was robbed of the ball by an alert Abd El Hafiz who ran on goal placed her shot beyond diving Bekele. Egypt sought to play out the game and the visitors encouraged by coach Abraham Teklehymanot went for a late rally to try and reduced the deficit. As urgency crept into the Ethiopian game, Ware’s delicate touch returned and she was again finding the forwards with some fine passes. Abaa made the most of a long ball that was not dealt with by Egyptian defence and she raced towards goal before shooting across Amry for Ethiopia’s second. There final whistle came not too long after that goal and the two teams will battle it out all over again in two weeks in Ethiopia.
ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Sun Jan 29, 2012 7:51 pm

በእግር ኳስ ጨዋታ ከኢትዮጵያ ወንዶች ይልቅ የኢትዮጵያ ሴቶች ይበልጣሉ ::

ዛሬ እሑድ ጥር 20 ቀን 2004 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሴቶች የእግር ኳስ ቡድን ታላቅ ታሪክ አስመዝግበዋል :- ከግብፅ የሴቶች የእግር ኳስ ቡድን ጋር በአዲስ አበባ ስታዲዬም ባደረጉት ግጥሚያ 4 ለ 0 አሸንፈዋል :: በዚህ መሠረት ለሴቶች የአፍሪቃ ዋንጫ ውድድር ተከታይ ግጥሚያ ለማለፍ ችለዋል :: ወንዶች ከሴቶች ተምረው መቼ ይሆን በግብፅ ቡድን ላይ 4 ጎል የሚያስቆጥሩት? ዘዝር ዜናው እነሆ ::

ምንጭ:- ኢትዮ-ስፖርት : እሑድ ጥር 20 ቀን 2004 ዓ.ም. :: ሉሲዎች የግብፅ አቻቸውን 4-0 አሸነፉ::

ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም የመልስ ጨዋታውን ያደረገው የኢትዩጵያ የሴቶች ብሄራዊ ቡድን የግብፅ አቻቸውን 4-0 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፈን አረጋገጠ፡፡

ብሄራዊ ቡደኑ በሰፊ የግብ ልዩነት ማሸነፍ የቻለው በ37 አና 53 ደቂቃ ራሂማ ዘርጋው ፤70ኛው ሄለን ሰይፉ ፤ 83ኛው ብርቱካን ገ/ክርስቶስ ባስቆጠሯቸው ጎሎች ነው፡፡

በተመልካቹ ከፍተኛ የሞራል ድጋፍ እየታገዙ የተጫወቱት ሉሲዎች በጨዋታ የበላይነት አንፀባራቂ ድል ለማስመዝገብ ችለዋል፡፡ የቡድኑ ስብስብ አንድም የወዳጅነት ጨዋታ ሳያደርግና የረጀም ጊዜ ዝግጅት ሳይኖረው፤ በዱባይና በባህሬን የወዳጅነት ጨዋታዎች በማድረግ ከሶስት ወር በላይ የተዘጋጀውን የግብፅ ቡድን በጨዋታ ብልጫ ማሸነፉ አስፈላጊው ድጋፍ ቢደረግለት የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚችል አሳይቷል፡፡ ፌዴሬሽኑ ቡድኑ ከፊቱ ለሚጠብቁት ጨዋታዎች የአቋም መለኪያ ጨዋታዎች አንዲያደረግ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ይጠበቅበታል፡፡
ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Tue Jan 31, 2012 9:47 pm

ሰላም የእግር ኳስ አፍቃሪዎች :-

በአትሌቲክስ እንጂ በእግር ኳስ ጨዋታ የምሥራቅ አፍሪቃ ቡድኖች የሚያስመዘግቡት ውጤት የሚያመረቃ አይደለም :: በአሁኑ የአፍሪቃ ዋንጫ የምሥራቅ አፍሪቃ ተወካይ የሱዳን ቡድን ብቻ ነው :: ሱዳን ለዚህ የዋንጫ ሽሚያ ውድድር የደረሰው ኢትዮጵያ ባዘጋጀቸው የ10ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ ውድድር በ1968 ዓ.ም. ከተሣተፈበት ጊዜ ወዲህ ከ38 ዓመታት በኋላ መሆኑ ነው :: ይህ ሬኮርድ ግን የወንዶቹ እንጂ የሴቶች እግር ኳስ ቡድኖች ውጤት አይደለም ::

በሴቶች እግር ኳስ ምሥራቅ አፍሪቃ ከሴሜን አፍሪቃ የተሻለ ውጤት አላቸው :: የኢትዮጵያ ሴቶች እግር ኳስ ቡድን በ1990 ዓ.ም. በተጀመረው የአፍሪቃ ዋንጫ የሴቶች ውድድር ውድድሮች ውስጥ በአንዱ በ1994 ዓ.ም. ለመሣተፍ ችሏል :: ዘንድሮም ወደ ዋንጫው ፉክክር ለመግባት የመጨረሻውን ውድድር ከታንዛኒያ የሴቶች ቡድን ጋር ያደርጋሉ :: ያለፈውን የአፍሪቃ ዋንጫ እንዳናልፍ ያደረጉን የታንዛኒያ ቡድን ናቸው : ዘንድሮም የደረሰን ከእነርሱ ጋር ነው :: እስካሁን የምዕራብ አፍሪቃ የሴቶች ቡድኖች የበላይነቱን እንደያዙ ናቸው :-

ናይጄሪያ በ2002 ዓ.ም. : በ1998 ዓ.ም. : በ1996 ዓ.ም. : እና በ1994 ዓ.ም. 4 ጊዜ ዋንጫውን አንስተዋል ::

ኢኳቶሪያል ጊኒ በ2000 ዓ.ም. የዋንጫ ባለቤት ::

ጋና : የመጀመሪያውን የዋንጫ ውድድር በ1992 ዓ.ም. አሸንፈዋል ::

እንግዲህ የኢትዮጵያ ሴቶች እግር ኳስ ቡድን የታንዛኒያ አቻዎቻቸውን ካሸነፉ በአፍሪቃ ዋንጫ የፍጻሜ ውድድሮች ይሣተፋሉ :: የኢትዮጵያ እና ታንዛኒያ ቡድኖች ውድድር የሚካሄደው በግንቦት እና ሰኔ ወሮች ይሆናል ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

PreviousNext

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest