የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ቡድን-በ20ኛው የዓለም ዋንጫ ...

ስፖርት - Sport related topics

Postby ተድላ ሀይሉ » Mon May 28, 2012 4:40 am

ሰላም የእግር ኳስ ስፖርት አፍቃሪዎች :-

ሴቶች እህቶቻችን የታንዛኒያ አቻዎቻቸውን 2 ለ 1 በማሸነፍ ቤታቸውን ሣያስደፍሩ : አንገታቸውን ቀና አድርጎ የሚያስኬድ ውጤት አስመዝግበዋል :: ተከታዩን ጨዋታ ሰኔ 11 (June 18 ) በዳሬሠላም ያደርጋሉ :: በዚያ ውድድር ካሸነፉ ወይም እኩል ከወጡ ወይም ተሸንፈውም ከ1 ጎል በላይ ካስቆጠሩና የተቆጠረባቸው ጎል ልዩነት ከ1 ካልበለጠ ለአፍሪቃ ዋንጫ የማለፍ ዕድል አላቸው :: ለኢትዮጵያ ቡድን ጎሎቹን ያስቆጠሩት ሔለን እና ቹቹ ናቸው ::

ምንጭ:- Mamo Gebrehiwot, EthioSport, Sunday May 27, 2012. Lucy defeats Twiga Stars 2-1.

The Ethiopian national women soccer team, popularly known as “Dinkinesh” or Lucy, defeated its Tanzanian counterpart, the Twiga Stars 2-1 here today in the first leg of the second round of the Africa Women Championship (AWC) Qualifiers.

Helen and Chuchu scored the goals for Lucy.

The two teams will play the return leg match in Dar es Salaam at the National Stadium on June 18, with the winner qualifying for the finals, which will be hosted by Equatorial Guinea in November of this year.

The Ethiopian team eliminated Egypt 6-4 on aggregate score in the first round. After losing 4-2 in Cairo, Lucy reversed the situation with a 4-0 thrashing victory in Addis Ababa.
ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Sat Jun 16, 2012 7:00 pm

ሰላም የእግር ኳስ ጨዋታ አፍቃሪዎች :-

ሴቶች የኢትዮጵያ አናብስት የታንዛኒያ አቻዎቻቸውን በዳሬሰላም ስቴድዬም 1 ለ 0 አሸንፈው ኢኳቶሪያል ጊኒ በምታዘጋጀው የሴቶች የአፍሪቃ ዋንጫ ለመወዳደር ትኬታቸውን ቆርጠዋል :: በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ የሴቶች ቡድን ያስመዘገበው አሥደናቂ ድል ነው :: በማጣሪያው የግብፅን ብሔራዊ ቡድን በደርሶ መልስ 6 ለ 4 : ታንዛኒያን ሁለቴ በማሸነፍ (አዲስ አበባ ላይ 2 ለ 1 እንዲሁም ዛሬ ዳሬሰላም ላይ 1 ለ 0) .... በርቱ እህቶቻችን : ከዋንጫውም የሚያግዳችሁ ኃይል አይኖርም ::

ምንጭ:- ኢትዮ-ስፖርት : ቅዳሜ ሰኔ 9 ቀን 2004 ዓ.ም.::

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ብርቱካን ገ/ክርስቶስ በ65ደቂቃ ባስቆጠረችው ግብ የታንዛኒያ አቻውን 1-0 በማሸነፍ ኢኳቶሪያል ጊኒ ለምታዘጋጀው ስምንተኛ የአፍሪካ ማለፉን አረጋገጠ፡፡

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን 60ሺ ተመልካች በሚይዘው በስታዲየም ፍፁም የጨዋታ የበላይነት ነው ሉሲዎች ጨዋታውን በድል የማጠናቀቅ የቻሉት፡፡ቡድኑ በታንዛኒያ ባስመዘገበው ድል ኢትዮጵያ ቡድን ለሁለተኛ ጊዜ ለአፍሪካ ዋጫቻ እንዲያልፍ አድርገዋል፡፡

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby መጽናናት » Sat Jun 16, 2012 8:28 pm

እልልልልልልልልልልልልልል ደስ የሚል ነው ስጠብቅ የነበርውን ዜና ነው ያሰማከኝ እልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልል
መጽናናት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1133
Joined: Fri Aug 20, 2004 10:24 pm
Location: united states

Postby ተድላ ሀይሉ » Thu Jul 05, 2012 8:44 pm

ሰላም የእግር ኳስ ስፖርት አፍቃሪዎች :-

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለእግር ኳስ ስፖርት ትልቅ ፍቅር እንዳለው የሚያጠራጥር አይደለም :: ነገር ግን ይህንን የሕዝቡን የእግር ኳስ ጨዋታ ፍቅሩን የሚያረኩ ተጨዋቾችን የሚያፈራ የስፖርት አደረጃጀት በኢትዮጵያ ውስጥ አልተዘረጋም :: ይባስ ብሎ ደግሞ ያለችውን ትንሽ ጭል ጭል የምትል ተስፋ የሚገድል የተጨዋቾች ኩብለላ በተደጋጋሚ ይታያል :: በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያ በአፍሪቃ ዋንጫ ከተሣተፈች ያለፈው ጥር ወር 30ኛ ዓመቷን ደፍናለች :: እንግዲህ በዚህ ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታዎች መካከል ድንገት ብቅ ያሉ ተጨዋቾች ኢትዮጵያን ለአፍሪቃና የዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታዎች ለማሣለፍ ደፋ-ቀና እያሉ ነው :: ተሣክቶላቸው ቢያንስ በእኒህ ታላላቅ ውድድሮች የአገራችንን ሠንደቅ ዓላማ እንዲውለበለብ ካደረጉ በታሪክ ሲታወስ የሚኖር ተግባር ሆኖ ይቆጠርላቸዋል ::

በዚህ ረገድ ለአፍሪቃ ዋንጫ የፍፃሜ ውድድሮች ለመድረስ ኢትዮጵያ አንድ ቀሪ የዙር ውድድር ይቀራታል :: ዛሬ በወጣው ዕጣ መሠረት ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር የደርሶ መልስ ግጥሚያዎችን ትጋጠማለች :: ግጥሚያዎቹ የሚደረጉት በሚመጣው ጳጉሜን 2 -4 : 2004 ዓ.ም. እና ጥቅምት 2 - 4 : 2005 ይሆናል ::

ይህንን የመጨረሻ ዙር የሚያደርጉት የ30ዎቹ የአፍሪቃ አገሮች ቡድኖች ድልድል የሚከተለውን ይመስላል ::
  1 ..... ማሊ ከቦትስዋና
  2 ..... ዚምባብዌ ከአንጎላ
  3 ..... ጋና ከማላዊ
  4 ..... ናይጄሪያ ከላይቤሪያ
  5 ..... ዛምቢያ ከኡጋንዳ
  6 ..... ኬፕ-ቨርዴ ከካሜሩን
  7 ..... ሞዛምቢክ ከሞሮኮ
  8 ..... ሴራሊዮን ከቱኒዚያ
  9 ..... ጊኒ ከኒጀር
  10 ..... ሱዳን ከኢትዮጵያ
  11 ..... ሊቢያ ከአልጄሪያ
  12 ..... ኮት-ዴ-ቯር ከሴኔጋል l
  13 ..... ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ ከኢኳቶሪያል ጊኒ
  14 ..... ጋቦን ከቶጎ
  15 ..... ቡርኪና ፋሶ ከማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፑብሊክ
ደቡብ አፍሪቃ አዘጋጅ አገር በመሆኗ በቀጥታ የውድድሩ ተሣታፊ አገር ትሆናለች ::

ምንጭ:- CAF, Thursday July 5, 2012. Orange AFCON South Africa 2013 Preliminary Draw off to a good start in Johannesburg.

መልካም ዕድል ለኢትዮጵያ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Sat Sep 29, 2012 11:01 pm

ሰላም የእግር ኳስ ስፖርት አፍቃሪዎች :-

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ዛሬ ቅዳሜ መስከረም 19 ቀን 2005 ዓ.ም. ከኬንያ አቻዎቻቸው ጋር የወዳጅነት ግጥሚያ አድርገው ነበር:: ያስመዘገቡት ውጤት ከዚህ በፊት በወንዶቹም የብሔራዊ ቡድን ተመዝግቦ የማያውቅ ነው :- የኬንያን ቡድን 5 ለ 0 አሸንፈዋል:: በታሪክ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ቡድን በአዋቂዎች ምድብ በዚህን ያህል ሠፊ ልዩነት ያሸነፉበትን ግጥሚያ አላስታውስም ::

ምንጭ:- DireTube, Sat 29 Sep 2012. Ethiopia's Lucy 5 - 0 Kenya Womens Football Team.

ሴት አናብሥቱ : በርቱልን : ወንዶቹ ለአፍሪቃ ዋንጫ ውድድር ለመግባት ከ30 ዓመታት በላይ ሲወስድባቸው እናንተ በጥቂት ዓመታት ተሣትፎ ለዋንጫው ቀርባችኋል :: እግዚአብሔር ይርዳችሁ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Wed Oct 24, 2012 7:46 pm

ሰላም የእግር ኳስ አፍቃሪዎች :-

የኢትዮጵያ ሴት የእግር ኳስ ቡድን በመጪው እሑድ ጥቅምት 18 ቀን 2005 ዓ.ም. በኢኳቶሪያል ጊኒ በሚካሄደው የ8ኛው የሴቶች የአፍሪቃ ዋንጫ ውድድር ለመሣተፍ ዛሬ ረቡዕ ጥቅምት 14 ቀን 2005 ዓ.ም. ወደዚያው አቅንተዋል :: ቡድናችን በምድብ ሁለት ከናይጄሪያ : ከካሜሩን እና ከኮት-ዴ-ቯር ጋር ተመድቧል :: መልካም ዕድል ለሴት አናብስቶቻችን ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Fri Nov 02, 2012 2:14 am

ሰላም የእግር ኳስ ስፖርት አፍቃሪዎች :-

የሴቶች ቡድናችን ከ8ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ በጊዜ ተሠናብቷል :: ሰኞ ዕለት በኮት-ዴ-ቯር 5 ለ 0 ሲሸነፉ አንዳንድ ምክንያት ቀርቦ ነበር :: ዛሬ በአፍሪቃ የሴቶች እግር ኳስ ንግሥቶች (ናይጄሪያ) 3 ለ 0 ሲሸነፉ ደረጃችን የት ድረስ እንደሆነ ግልፅ ሆናል :: ነገር ግን በእኔ አተያይ ከኢትዮጵያ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን ይልቅ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ሺህ-ዕጥፍ ይልቃሉ :: በቂ ሥልጠና ሣይሠጣቸው : መደበኛ ውድድር ሣያደርጉ : የረባ እንክብካቤ ሣያገኙ : ይህንን ሁሉ መሠናክል አልፈው ባለፉት 10 ዓመታት ለ3ኛ ጊዜ (በ1995 : በ1997 እና ዘንድሮ በ2005 ዓ.ም.) በአፍሪቃ ዋንጫ የፍፃሜ ግጥሚያዎች ለመወዳደር በቅተዋል :: ስለዚህ ልናበረታታቸውና ልንኮራባቸው ይገባል እላለሁ ::

በርቱ እህቶቻችን ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby geremew » Sun Nov 04, 2012 12:37 am

ሰላም ተድላ:
የሴት ቡድናችን ጥሩ የኳስ ክህሎት እና ፍላጎት ባላቸው ተጫዋቾች የተዋቀረ ሲሆን ከዘንድሮ አመት ጀምሮ ደሞ ሁሉም የፕሪሚየር ሊግ ቡድኖች የሴት ቡድኖች እንዲኖራቸው ፌዴሬሽኑ ወስንዋል:: ይህ ቡድን ከኬንያ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ያደረገ ሲሆን 5-0 ማሸነፋችን ይታወሳል:: ለዚህ ውድድር ግብጽን እና ታንዛንያን አሸንፈው ማለፋቸው ጥሩ መሆናቸውን ያሳያል:: ለለንደን ኦሊምፒክ ለመቅረብ አንድ ጨዋታ ሲቀራቸው በደቡብ አፍሪካ መሸነፋቸው ይታወሳል:: አሰልጣኛችውም ብራዚል ድረስ ሄዶ የተማረ እንዲሁም የወንድ ቡድኖችን ያሰለጠነ ነው:: የናይጄርያ የሴት ቡድን ግን በጣም የፈረጠሙ እና ችሎታ ያላቸው ናቸው:: ቡድናችን ጥሩ መስመር ላይ እንዳለ ያስታውቃል:: እኔም እንዳንተ ልንኮራባቸው ይገባል እላለሁ::

ተድላ ሀይሉ wrote:ሰላም የእግር ኳስ ስፖርት አፍቃሪዎች :-

የሴቶች ቡድናችን ከ8ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ በጊዜ ተሠናብቷል :: ሰኞ ዕለት በኮት-ዴ-ቯር 5 ለ 0 ሲሸነፉ አንዳንድ ምክንያት ቀርቦ ነበር :: ዛሬ በአፍሪቃ የሴቶች እግር ኳስ ንግሥቶች (ናይጄሪያ) 3 ለ 0 ሲሸነፉ ደረጃችን የት ድረስ እንደሆነ ግልፅ ሆናል :: ነገር ግን በእኔ አተያይ ከኢትዮጵያ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን ይልቅ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ሺህ-ዕጥፍ ይልቃሉ :: በቂ ሥልጠና ሣይሠጣቸው : መደበኛ ውድድር ሣያደርጉ : የረባ እንክብካቤ ሣያገኙ : ይህንን ሁሉ መሠናክል አልፈው ባለፉት 10 ዓመታት ለ3ኛ ጊዜ (በ1995 : በ1997 እና ዘንድሮ በ2005 ዓ.ም.) በአፍሪቃ ዋንጫ የፍፃሜ ግጥሚያዎች ለመወዳደር በቅተዋል :: ስለዚህ ልናበረታታቸውና ልንኮራባቸው ይገባል እላለሁ ::

በርቱ እህቶቻችን ::

ተድላ
geremew
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 285
Joined: Tue Dec 28, 2004 8:43 pm
Location: united states

Postby ወርቅነች » Sat Nov 10, 2012 9:01 am

መልካም ዕድል ለሴት አናብስቶቻችን ::


ሰላም ዘነገደ - ዘረኛ ፈዛዛው ዘገምተኛው ተድላ

መልካም እደል እንዲሁም ለወያኔ አናብስቶቻችንን የመለመለው..... ለሁሉም ነገር ያዘጋጃቸው ምሰጋና ይድረሳቸው ትላለች ጀሚላ ከቸርችል ጎዳና :lol:


ተድላ ሀይሉ wrote:ሰላም የእግር ኳስ አፍቃሪዎች :-

የኢትዮጵያ ሴት የእግር ኳስ ቡድን በመጪው እሑድ ጥቅምት 18 ቀን 2005 ዓ.ም. በኢኳቶሪያል ጊኒ በሚካሄደው የ8ኛው የሴቶች የአፍሪቃ ዋንጫ ውድድር ለመሣተፍ ዛሬ ረቡዕ ጥቅምት 14 ቀን 2005 ዓ.ም. ወደዚያው አቅንተዋል :: ቡድናችን በምድብ ሁለት ከናይጄሪያ : ከካሜሩን እና ከኮት-ዴ-ቯር ጋር ተመድቧል :: መልካም ዕድል ለሴት አናብስቶቻችን ::

ተድላ
ወርቅነች
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 967
Joined: Sun Oct 03, 2010 10:05 am

Postby ተድላ ሀይሉ » Tue Jan 22, 2013 5:19 am

ሰላም ለእግር ኳስ ስፖርት አፍቃሪዎች:-

ከ31 ዓመታት በኋላ ለአፍሪቃ ዋንጫ የፍፃሜ ውድድሮች ማለፍ የቻለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን ይህን አንድ ትውልድ ዕድሜ በኋላ የተገኘ ዕድል እንዴት ይጠቀምበት ይሆን? ዛሬ በመክፈቻው ዕለት አንድ ሬጎሪ ስተው : ከአንድ በላይ ጥሩ የጎል ሙከራ አድርገው : በረኛቸው በጥፋት በቀይ ካርድ ወጥቶባቸው : ቀድሞ ጎል ተቆጥሮባቸው : ካለፈው የአፍሪቃ ዋንጫ አሸናፊ ከዛምቢያ ጋር እኩል 1 ወጥተዋል:: ይህ ጥሩ አጀማመር ይዘልቅ ይሆን?

የዛሬው ጨዋታ በከፊል የሚከተለውን ይመስል ነበር::

ምንጭ:- EthioTube, - January 21, 2013. The 2013 Africa Cup of Nations - Ethiopia vs Zambia: Full Match Highlights.

መልካም ዕድል ለብሔራዊ ቡድናችን!

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Sat Jan 26, 2013 12:52 am

ሰላም የእግር ኳስ ስፖርት አፍቃሪዎች:-

በዛሬው ጨዋታ ቡድናችን ሙሉ ለሙሉ ተበልጧል:: ቡርኪናቤዎች መሐል ሜዳውን ያለምንም ችግር መቆጣጠር ስለቻሉ የእኛ ቡድን አጥቂዎች በረዥም ከሚጣልላቸው ኳስ በስተቀር በደንብ በተጠና አጠቃቅ ወደ ጎል መቅረብ አልቻሉም:: እንግዲህ አሠልጣኙ በዚህ አጨዋወት ቡርኪናቤዎችን ለማሸነፍ ይቻላል ብሎ አስቦ ከሆነ ውጤቱ ይበልጥ ይናገራል::

የእኛ ቡድን ናይጄሪያን ማሸነፍ ይችላሉ:: ስለዚህ ለሩብ ፍፃሜ የማለፍ ዕድላቸው ሙሉ ለሙሉ አልተዘጋም::

መልካም ዕድል ለብሔራዊ ቡድናችን::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Wed Jan 30, 2013 1:51 am

ሰላም ለእግር ኳስ አፍቃሪዎች:-

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ዕድገት ሁለት እምርጃ ወደፊት : አንድ እርምጃ ወደኋላ ነው::

በዛሬው ጨዋታ ከቡርኪናፋሶ በጨዋታም : በችሎታም ባነሠው በዝርክርኩ የናይጀሪያ ቡድን የተሸነፈው የኢትዮጵያ ቡድን ብዙ የሚያስቆጩ የግብ ሙከራዎችን አድርጎ ነበር ማለት ይከብዳል:: ናይጄሪያ ደካማ ቡድን ብቻ ሣይሆን ጥንት በ10ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ የነበረውን ቡድናቸው ዓይነት አሠልፈው የእኛን ቡድን ማሸነፍ ችለዋል:: በዚያ ላይ የሞሮኮው ዳኛ የመጀመሪያውን ሪጎሪ በሥጦታ መልክ አበርክቶላቸዋል::

የእኛ ቡድን አሁንም የሚጎድሉት ብዙ ነገሮች ቢኖሩም መሠረታዊ የሚባሉት:-
  1 ..... መሐል ሜዳውን መቆጣጠር የሚችሉ ጥሩ ቴክኒሽያን ተጨዋቾች:
  2 ..... የማይገባ ጥፋት እየፈፀሙ በቀይ ካርድ የማይወጡ በረኞች::
እኒህ ሁለቱ በጣም ጉልህ የኢትዮጵያ ቡድን ችግሮች ናቸው:: እስካሁን እኔ በማውቀው በአፍሪቃ ዋንጫ በሦሥት የምድብ ጨዋታዎች በሁለቱ ቀይ ካርድ የወጡ ሁለት በረኞች ያሉት ቡድን የኢትዮጵያ ቡድን ብቻ ነው::

እንግዲህ ይኸው ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ድክመቶቹን አርሞ አንድ ተጨማሪ ታሪክ እንደሚሠራ ተስፋ አለኝ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby TAዛBI » Wed Jan 30, 2013 6:28 am

እንግዲህ ይኸው ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ድክመቶቹን አርሞ አንድ ተጨማሪ ታሪክ እንደሚሠራ ተስፋ አለኝ::


ሰላም ጋሽ ተድላ

የአለም ዋንጫ ማጣርያ የሚባል ነገር የቀረ መሰለኝ በዚህ የአፍሪካ ዋንጫ ከ1-4 የሚወጡት በቀጥታ ለአለም ዋንጫ የሚያልፉ ይመስለኛል ካልተሳሳትኩ
TAዛBI
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 152
Joined: Mon Dec 22, 2008 8:42 am

Postby ተድላ ሀይሉ » Wed Jan 30, 2013 5:26 pm

TAዛBI wrote:
እንግዲህ ይኸው ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ድክመቶቹን አርሞ አንድ ተጨማሪ ታሪክ እንደሚሠራ ተስፋ አለኝ::


ሰላም ጋሽ ተድላ

የአለም ዋንጫ ማጣርያ የሚባል ነገር የቀረ መሰለኝ በዚህ የአፍሪካ ዋንጫ ከ1-4 የሚወጡት በቀጥታ ለአለም ዋንጫ የሚያልፉ ይመስለኛል ካልተሳሳትኩ

ሰላም "TAዛ BI" :-

እንደዚያ የነበረው ባለፈው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ነበር:: ያኔ ብዙ የአውሮፓ ክለቦች "ከአፍሪቃ የምናመጣቸው ፕሮፌሽናል ተጨዋቾች በብዙ የብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች ስለሚሣተፉ ቡድኖቻችን በውጤት ተጎዱብን" ብለው ለፊፋ አቤቱታ በማቅረባቸውና ፊፋ እና ካፍ በመስማማት እንደዚያ ያለ ጊዜያዊ የማጣሪያ ዘዴ ፈጥረው ነበር:: በ2006 ዓ.ም. (ብራዚል-2014) ለሚካሄደው ውድድር ግን ያ የማጣሪያ አሠራር ቀርቷል::

በብራዚል-2014 የአፍሪቃ ዞን ማጣሪያ ኢትዮጵያ በምድብ ሀ ከመካከለኛው አፍሪቃ : ከደቡብ አፍሪቃ እና ቦትስዋና ጋር ተደልድላለች:: በእስካሁኑ የማጣሪያ ውድድሮች መካከለኛው አፍሪቃን አዲስ አበባ ላይ አሸንፈን : ከደቡብ አፍሪቃ ጋር ደቡብ አፍሪቃ ላይ እኩል ወጥተን በ4 ነጥብ በአንደኝነት እንገኛለን:: በምድብ ውድድሩ በ1ኛነት ካጠናቀቅን በመጨረሻውና ሦሥተኛው ዙር ማጣሪያ በሌላ ምድብ 1ኛ ከሆነ ቡድን ጋር የደርሶ መልስ ውድድር እናደርጋለን (ከርሞ በጥቅምት-ኅዳር 2006 ዓ.ም.):: ዝርዝሩ በሚከተለው ድረ-ገፅ አለ::

ምንጭ:- የፊፋ የዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ውድድሮች:- የአፍሪቃ ዞን የምድብ ድልድና ሠንጠረዥ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Thu Jan 31, 2013 4:53 am

ሰላም የእግር ኳስ ስፖርት አፍቃሪዎች:-

ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ሣይሰለች ያለውን አቋም በማንፀባረቅ የሚታወቅ የስፖርት ጋዜጠኛ ነው:: እንደ እርሱ አመለካከት "ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ጨዋታ ያለመሻሻል ችግሩ አሠለጣጠኑ ነው:- ምክንያቱም ተጨዋቾቻችንን መሠረት ያደረገ ሥልጠና አይሠጥም" ብሎ ያምናል:: በመካሄድ ላይ ባለው በ29ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ የእኛ ቡድን ድክመቶች ምን : ምን እንደነበሩ ከራሱ ዕይታ አንፃር አብራርቷልና ተከታተሉት::

ምንጭ:- ገነነ መኩሪያ : ሊብሮ : እሑድ ጥር 19 ቀን 2005 ዓ.ም.:: በረኛ በመቀየር ስህተት ማረም አይቻልም - ያልሰሩትን አጭር ኳስ መተግበር አይቻልም::

ገዛኽኝ የባንክ በረኛ ነው፡፡ በ1995 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን ተመረጠ፡፡ ወደ ቡድኑ ለመቀላቀል ፍቃደኛ አይደለም፡፡ ከዚያ በፊት ለወጣት ቡድን ተመርጦ ለሱዳን ጉዞ ፍቃደኛ ሳይሆን ብዙ ጭቅጭቅ ተነስቶ ነበር፡፡ ለኦሎምፒኩ ግን በግድ ትመጣለህ ሲባል አልፈልግም አለ፡፡ ካልመጣህ ትቀጣለህ ሲባል ራሴን አጠፋለሁ አለ፡፡ ይህን ቃል ለሱዳኑም ጨዋታ ተናግሮት ነበር፡፡ ከተቀጣ ከክለቡም ይባረራል ሳይወድ በግድ ከቡድኑ ጋር ወደ አንጎላ ተጓዘ፡፡ አዲስ አበባ ላይ በተደረገው ጨዋታ ሳዳት ነበር የተሰለፈው፡፡ ለመልሱ ጨዋታ ሳዳት እጁ ላይ ጀሶ አስገብቶ መጣ፡፡ ሳዳት አልተጎዳም እቤቱ የራሱ ጀሶ ስላለው መሰለፍ በማይፈልግበት ጊዜ ይጠቀምበታል (ማን ሞኝ አለ ፣ማን ይሞታል- ዘሪሁን ተታለለ) ምስኪኑ ገዛኽኝ አንጎላ ሄደ እሱም ሳይፈልግ ነው የሄደው፡፡ አንደኛ በረኛ ሆኖ ገባ፡፡ የተነገረው ያገኘኽውን ለጋ ነው፡፡ ሲለጋ ቶሎ ቶሎ ይመጣበታል፡፡ አሰልጣኙ አውጣ ይላሉ፡፡ ቤንች ላይ ያሉት ተጫዋቾች ጫናውን ፈርተው አውጣን ይላሉ(አምላካቸውን)፡፡ 2ለ0 እየተመራን ገዛኽኝ የለጋው ኳስ እኛ ላይ እየመጣ ጥቃት ስለሚፈፀም ከኋላ ለመጀመር በሚል በቀኝ ላለው ተከላካይ በእጁ ወረወረለት፡፡ ልጁ እሚቀበለው ስላጣ (ልክ ትላንትና ቡርኪናፋሶ ጋር ተከላካዩ የሚቀበለው አጥቶ እንደተነጠቀው) ሰው ስላጣ ለገዛኽኝ ሲመልስለት አጥቂው ሮጦ ስለመጣ ግራ ገብቶት ከፔኔልቲ ውጪ በእጁ ያዘ፡፡ ቅጣት ምት ተሰጠ ገባ፡፡ 3ለ0 ረፍት ሆኑ፡፡ በእረፍት መልበሻ ክፍል በአንተ የተነሳ ነው ጎል የገባብን በሚል ገዛኽኝ እንዲወጣ ተደረገ፡፡ በአንተ ቦታ ሌላ ሰው ይገባል አይደለም የተባለው፡፡ ከቡድኑ እንደተባረረ ነው የተነገረው፡፡ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ በእረፍት የተባረረ የመጀመሪያው ሰው ነው፡፡ ተጫዋች ተቀይሮ ይወጣ እንጂ ከብሔራዊ ቡድን ተባረሀል አይባልም፡፡ ገዛኽኝ ይውጣ እንጂ ጫናውና ጎሉ አልቀነሰም፡፡ ወደ አዲስ አበባ ሲመሉ በውጤቱን የሰማችው የበረራ አስተናጋጅ ገዛኽኝን አይዟቹ ስትለው እሱ እኔ እኮ የነሱ አይደለሁም አላት ፡፡ ምክንያቱም እሱ ተቀንሷል እንዲሁም ሁለተኛ ብሔራዊ ቡድን መሳተፍ አይፈልግም፡፡ ከሀገር ውጪ ክለቦችና ብሔራዊ ቡድን በብዙ ጎል ተሸንፈው ሲመጡ በረኞች ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡ ይህ ጣጣ ደግሞ ተሰላፊዎችን አይለቃቸውም፡፡ ገዛኽኝም የሚጠላው ይህንን ነው፡፡ በ1989 ስንታየሁ ስራህ ቡዙ የተባለው ግብ ጠባቂ ካይሮ ለመሄድ አልፈለገም፡፡ አዎክበው ወሰዱት ፍቃደኛ ሆኖ ተሰለፈ፡፡ 8ለ1 ተሸነፍን አሰልጣኙ አቶ ሰውነት ቢሻው ናቸው፡፡ በነገራችን ላይ በማጣሪያ ብዙ ጎል የገባው ይህ ነው፡፡ ይህም ሪከርድ ነው፡፡ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በምስራቅ አፍሪካ ቡድን 5 ጎል ሲያገባብን የሱዳኑ የመጀመሪያ ቡድን ነው ይህም የሰውነት ቡድን ነው፡፡ ስንታየሁ ከካይሮ 8 ጎል ገብቶበት ሲመለስ ክለቡ አባረረው፡፡ በየቦታው ክለቦች ጎል ጠሪ ነው አንቀበልም አሉት፡፡ ከዚያ በኋላ ስንታየው ክለብ አነበረውም፡፡ ጨዋታውን ብታዩት የስንታየው ምን ስህተት የለውም፡፡ የጎሉ ቁጥር ነው ስንታየውን ከሀገር ያጠፋው፡፡ አሁን ሰሞኑን በሬዲዮ ስሰማ ችግሩ የበረኛ ነው በሚል ዛሪሁንን እየበለቱት ነው፡፡ የአሁኖቹን እያጣጣሉ የትላንት በረኞቻችንን ሲክቡ አደመጥኩ፡፡ በ1981 ከግብፅ ጋር ተካበ 6 ጎል ተቆጠረበት፣ በ1987 በለጠ 5 ጎል ተቆጠረበት፣ 1968 የመቻል በረኛ ካንጋሮ 6 ጎል ተቆጠረበት፡፡ በካይሮ ግጥሚያ የኢትዮጵ በረኞች ከ5 -9 ጎል ተቆጥሮባቸዋል፡፡ ካይሮ የስፖር ካዚኖ ማሽን አለ፡፡ ተወራራጁ ሳንቲም ይከትና ማሽኑን ይጫነዋል፡፡ የተለያየ ሀገር በረኞች በአፋቸው ኳስ እየተፉ ነው የሚመጡት፡፡ ተወራራጁ ማሽኑን ሲነካው እንዲመጣ የሚፈልገው የኢትየዮጵያ በረኛ ምስል ነው፡፡ብዙ ኳስ የሚተፋው፡፡ ይህ ማለት ብዙ ጎል የሚቆጠረው በኢትዮጵያ በረኛ ነው ለማት ነው፡፡ በግብፅ ሀገር በክለቦች ውድድር አንድ በረኛ በአንድ ጨዋታ ብዙ ጎል ከተቆጠረበት ይህ የኢትዮጵያ በረኛ ነው ይላሉ፡፡ እኛ የበረኛ ችግር ነው ያለብን ወይስ በረኘ ደረስ የሚመጣውን ኳስ ነው ለማገድ ያልቻልነው?

ጋርዚያቶ በ1893 ዋጣት ቡድን ይዞ አዲስ አበባ ላይ በአፍሪካ ወጣቶች ዋንጫ በግብፅ በመድብ ጨዋታ 2 ጎል ሲቆጠርብን ችግር የበረኛ ነው በሚል አስልጣኙ አዳሙን አስወጣና ሳዳትን አስገባ፡፡ ሳዳት በአንሎላ 5 ጎል ሲቆጠርበት እሱን አይችልም አለና መልሶ አዳሙን ለሚቀጥለው ጨዋት አስገባው፡፡ የመጀመሪያው ስህተት የበረኛው ከሆን በረኛው ተቀይሯል፡፡ ስህተቱ ይህ ከሆነ ታርሟል፡፡ የሚቀጥለው ጫዋታ ለይ እንዴት በረኛ ይቀየራል? ፡፡ በሶስተኛው ጨዋታ ለደረጃ ግጥሚያ 2ለ0 ስንሸነፍ ጋርዚያቶ አዳሙና ሳዳትን አባረረና ደያስን ወደ አርጀንቲና ይዞት ሄደ፡፡ በ3 ጨዋታ ደያስ ላይ 8 ጎል ተቆጠረ፡፡ አንድም ጨዋታ ማሸነፍ አልቻልንም፡፡ ከምድባችንም ውራ ወጣን፡፡ጋርዚያቶ ሲመለስ ብዙ ጎል በቡድኑ ላይ በመቆጠሩ ‹‹ ኢትዮጵያ ውስጥ የጎል ኪፐር ችግር አለ የበረኛ ኮሌጅ ሊቋቋም ይገባል›› አለ ቡድኑ ላይ ያለውን እንቅስቃሴ ሳይመረምር ችግሩ በረኛ ነው ብሎ ደመደመ፡፡ ሁሉም ሰው አምኖ ተቀበለ፡፡ ምክንያቱም በረኞቻችን ላይ ብዙ ጎል ሲቆጠር አይተናል፡፡ ጋርዚያቶም በረኛ ነው ችግሩ ብሎ አዳሙ በሳዳት ተካው፡፡ ሳዳትን በደያስ ፡፡ ችግሩ በረኛ ነው ብሎ በረኛ እየቀያየረ ጎሉን መቀነስ አልቻለም፡፡ ጋርዚያቶም የቡድንን እቅስቃሴ ሲመሰርት እኛ ሳንሆን ባለጋራ ብልጫ በሚይዝበት መንገድ ው ያዘጋጀነው፡፡ የሱ አውቀት ይህ ነው፡፡ ተጋጣሚያችን እኛ ስለሚበልጠን እየነዳን እኛ ጎል ድረስ ይመጣል፡፡ ጎል ሲቆጠር በረኛ ተጠያቄ ይሆናል፡ ግን መፍትሄ ሊሆን አልቻም፡፡ ጋርዚያቶ የበረኛ ችግር ነው ያለው፣ የበረኛ ት/ቤት ክፈቱ ሲል መፍትሄ የሰጠን መሰለንና ዮሓንስ ሳህሌ ከአሜሪካ የበረኛ አሰልጣኝ ይዞ መጥቶ ለበረኛ አሰልጣኖች ኮርስ ሰጠ፡፡ ሁሉም ክለብ የበረኛ አሰልጣኝ መቅጠር አለበት ተባለ ተቀጠረ ፡፡ እንዳውም ጊዮርጊስ የበረኛአሰልጣኝ ከውጪ አመጣ፡፡ ዘሪሁን የሚሰለጥነው በሀገር ውስጥ ሳይሆን በውጪ ሀገር የበረኛ አሰልጣኞ ነው ፡፡ ትላንትና ዘሪሁን ላይ 4 ጎል ሲገባ ዘሪሁን ተወቀሰ፡፡ ባለፈው ሲሳይ ለይ 5 ጎል ሲገባ በአንቅስቃሴው ላይ አልተነጋገርንም፡፡ አሁንም ዘሪሁን ላይ 4 ጎል ሲቆጠር የቡድኑ እጂ የዘሪሁን አይደለም፡፡ ለጎሉ መቆጠር አሰልጣኙ እንጂ ዘሪሁን ተጠያቂ መሆን የለበትም፡፡ ምክንያቱም ቡድኑ በእንቅስቃሴ መቆጣጠር ስላልቻ ዘሪሁን ድረስ የሚመጣውን ኳስ ማቆም ባለመቻሉ ነው፡፡ ባለፈው ጀማልና የዛሚቢያው አጠቂ ፊት ለፊት ተገናኙ ልጁን ማንም ሊያቆመው አለቻለም፡፡ ጀማል በቀይ ወጣ ምንም ማድረግ አልቻለም፡፡ ምክንያቱም ጀማል ድረስ ኳሱ አፍጥጦ ከመጣ ምን ማድረግ ይቻላል፡፡ አሁን ደግሞ የሚነገረው የውጪ በረኞች ኢትዮጵያ ውሰጥ ስለሚጫወቱ የሀገር ውስጥ በረኞች ቤንች ስለሚሆኑ ለብሔራዊ አይመጥኑም እየተባለ ነው፡፡ ዘሪሁን የኦዶንካራ ቤንች ነው፡፡ ጀማል ደግሞ ባለፈው አመት የደቡብ አፍሪካው በረኛ ቤንች ነው፡፡ ይህ ሲታይ ትክክለ ይመስላል፡፡ ከ10 ዓመት በፊት በነ ደሳለኝ፣ ተካበ፣በለጠ በኢንተርናሽናል ብዙ ጎል ሲቆጠር የውጪ በረኞች ሀገር ውስጥ አነበሩም ዋናው ችግር በሜዳ ላይ የሚታየው ቡድን በእንቅስቃሴው ብልጫ ሲወሰድበት እና በረኛ ድረስ ችግሩ ሰተት ብሎ ሰለሚመጣ በረኛ ተጠያቂ እናደረጋለን፡፡ እሺ ችግሩ በረኛ ነው ካልን ይህን ያህል ዓመት በረኛ ቀይረን ለምን ስህትቱ አልታረመም፡፡ በረኛው ተቄይሮ ሲህተቱ ካልታረመ እንቅስቃሴውን ማይት ነው፡፡ እኛ የጉልበት ጨዋታ መርጠን በተፈጥሮ በጉልበት ስለሚበልጡን ደረማምሰውን ጎላችን ድረስ ይመጣሉ፡፡ አሰልጣኝ ሰውነት የቡድኑ እቅስቃሴ መመርመር አልቻለመ፡፡ ከጫወታው በፊት በራዲዮ በሰጡት መግለጫ እነሱን በጎልበት ስለማንችላቸው ኳስ ይዘን አጭር ኳስ ተጫወተን በልጣን ለማሸነፍ ነው የምንገባው አሉ፡፡ እኔ አመቱን ሙሉ ቡርኪናፋሶና ናይጄሪያ በጎልበት ስለማንችላቸው ኳስ ሊጫወት የሚችል ቡድን ያስፈልጋል ብዬ አሳውቄ ነበር፡፡ አሰልጣኞች ይህንን አልፈለጉም፡፡ ቡድኑን በኃይልና ጉልበት ላይ ነው ያዘጋጁት፡፡ ናይጄሪያንና ቡርኪናፋሶን ጥሩ በሆኑበት በጉልበት አጨዋወት መቋቋም ያስቸግረናል፡፡ ሰውነት ግን ጉልበትና ፍጥነትን ይዞ ሄደ፡፡ ቡርኪና ከናይጄሪያ ጋር ሲጫወቱ በጉልበት ሀይለኞች እንደሆኑ ሲመለከት ‹ በጉልበት ስለማንችላቸው አጭር ኳስ ነው የምንጫወተው አለ፡፡ አጭር ኳስ ለመጫወት እውቀት ይጠይቃል፡፡ መጀመሪያ የቴክኒክ ችሎታ ያላቸው ምምረጥ፡፡ ለዚህ የሚሆን ስልጠና መስጠት፡፡ ስራውን ለማከናውን ዋነኛው ተግባር ተጫዋቹን በአአምሮ ማገናኘት ነው፡፡ ተጫዋቹቸን በአእምሮ ለማገናኛኘት ደግሞ ሐሳቡ ስለሌላቸው (በስልጠናው ላይ ) ቢያንስ 6 ወር ይፈጃል፡፡ ሰውነት ግን በአንድ ቀን ሊተገብር ነው የፈለገው፡፡ ሁለቱ ጎል የተቆጠረው ተጫዋቾቹ መቀባበል አቅቷቸው ተነጥቀው ነው፡፡ ተመልካቹ ተጫዋቹን ተጠያቂ ያደርጓል፡፡ ያልሰሩትን የማይችሉትን ነገር አጭር ኳስ ተጫዋቱለ ሲባል ከየት ያምጡት፡ በዚያ ላይ 5 ነጣቂ አሰልፎ እንዴት ነው ተጫወቱ የሚሉት፡፡ እነሱ መንጠቅ እንጂ መጫወት አይችሉም፡፡ ለዚህ ቡድን መዝረክረክ ዋናኛ ተጠያቂዎቹ አሰልጣኞቹ ናቸው፡፡ አሁንም እኛ የምዕራብ አፍሪካ ቡድን በጉልበትና በሃይል መቋቋም አንችልም፡፡ ያለን ችሎታ ቴክኒክ ነው፡፡ ቴክኒክ ደግሞ ከእውቀት ጋር የሚያያዘው ነው ፡፡ ለዚህ ስልጠና የሚሆን ተጫዋች መርጦ፣ ስልጠና መስጠት ከተቻለ እኛ በዚህ ብልጫ ስለምንወስድ በአፍሪካ ውስጥ ጠንካራ መሆን እንችላለን፡፡ ከለበለዚያ ላለፉት 50 ዓመታት የተከናነብነውን ውርደት ለመጪውም 50 አመታት ይቀጥላል፡፡ የአፍሪካ ዋንጫ ሲጀመረ በመጀመሪያ ውድድር 4ለ0 ተሸንፈን በሰፊ ጎል የመሸነፍ ሪከርድ ያዝን ይህን የሚያሻሽል ጠፋና በ5ተኛው አፍሪካ ዋንጫ በሴኔጋል 5 ጎል ተቆጠረብንና ሪከርድ አሻሻልን ፡፡ በ7ተኛው አፍሪካ ዋንጫ 6ለ1 ተሸነፍንና የራሳችንን ሪከርድ አሻሻልን፡፡ ላለፉት 45 ዓመት ይህ እኛ የያዘውነው ሪከርድ አልተሰበረም፡፡ ልምን እንዳልተሰበረ ታውቃላችሁ? እኛ ለ31 ዓመት ስላልተሳተፍን ነው፡፡ እኔን እመኑኝ ብንሳተፍ እንሰብረው ነበር፡ አሁንም በቡርኪና ጨዋታ እንሰብረው ነበር፡፡ ያ ሁሉ ሪከርድ ጎል ሲቆጥርብን በረኛ ነው ተጠያቄ የምናደርገው፡፡ ግን የትላንቱ ስህት የሆነው አጨዋወታችን ዛሬ ድረስ ያለማረማችን ነው፡፡ ቀላሉ ነገር ወደ ጠሩ ነገር ለመምጣት ኪዚህ አጨዋወት መውጣት አለብን፡፡ ይህ አጨዋወት ውርደታች ነው፡፡ በረኛ ተጠያቂ በማድረግ መፍትሄ አይመጣም ዋናው አጨዋወታችንን ቀይሮ ወደ በረና ኳስ እንዳይመጣ ማደረግ ነው፡፡ ቡና 1995 አመቱን ሙሉ ሲጫወት ወደ በረኛ ኳስ ብዙ አይመጣም ነበር፡፡ ባርሴሎና ኳስ ብዙ ወደ በረኛው አይመጣም ፡፡ በረኛው ላይ ጫና የለም መፍትሄ ያደረጉት በእንቅስቃሴ ባላጋራቸውን ሜዳው ላይ መያዝ(ማፈን) ነው፡፡ ቡድናችን ከበፊቱ የተለየና የተሟላ ነው፡፡ በፊት የስነ ምግብ ባለሙያ አነበረም፡፡ የስነ ልቦናም ባለሙያ ከቡድኑ ጋር አይሄድም፡፡ ውጤታችን ደካማ የነበረው እነዚህ ስላልነበሩ ነው ይባል ነበር፡፡ አሁን ስነ ምግብና ስነ ልቦና ለረጅም ጊዜ አብረው ሲዘጋጁ ነበር፡፡ ነገር ግን እንደሚታየው ውጤቱን አልቀየረውም በብዙ ጎልም ከመሸነፍ አላዳነውም፡፡ ስነ ምግብም ለራሱ በላ(ልጆቹ እንደነገሩኝ ከሆነ) ስነ ልቦናም እንኳን ሊያረጋጋቸው ለራሱም አልተረጋጋም፡፡ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ችግር ይጎላል የተባሉ ሁሉ ለዚህ ቡድን ተሟልቷል፡፡ በቂ የዝግጅት ጊዜ፣ የወዳጅነት ጨዋታ፣ ሽልማት፣ በቂ የህዝብ ድጋፍ፣ በቂ የሚዲያ ሽፋን፣የስነ ልቦናና የስነ ምግብ ባለሙያ ተሟልቷል፡፡ ግን ቡድኑን አንኮታኮተው፡፡ ችግሩ ፌዴሬሽኑ ጋር ነው ያለው ችግሩን በእውቀት መመርመር አልቻለም፡፡ እኔ የሚያሳዝነኝ የህዝቡ ሞራል ነው፡፡ ሚዲያው በተሳሳተ መንገድ ቡድኑን እላይ አውጥቶ ህዝቡን ቆስቁሶ አንገቱን አሰደፋ፡፡
ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

PreviousNext

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest