የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ቡድን-በ20ኛው የዓለም ዋንጫ ...

ስፖርት - Sport related topics

Postby ባሻ ብሩ » Sat Jul 03, 2010 7:46 pm

ዝብልሉ
እኔ የደደቢት ጠበቃም ምንም አደለሁም... እንዳውም ዛሬን ካንተ አይነቱ መጋዣ ዳያስፖራ ተብዬ ጋር ሊቀላቅለኝ እንጀራ ከሀገሬ እኔን ከማስወጣቱ በፊት... የቡና ቀንደኛ ደጋፊዎች መሀል ቁጭ ብዬ ቡናን ስደግፍ ... ጠብ ተነስቶ በተባራሪ ድንጋይ የተፈነከትኩበትን ከጭንቅላቴ ጀርባ ያለ ጠባሳ ሳይ ያቃጥለኛል .... :evil:

ደሞ የኢትዮጵያ ኩዋስን እንደጨዋታ እያዩ መደገፍ :!: :roll: .... ስለደደቢቶች እየተናገርኩ ያለሁት በፕሮጀክት ህጻናቶችን እያበሰሉ ማዘጋጀት ለኢትዮጵያ እግር ኩዋስ እድገት ወሳኝ ነገር ነው የሚል እምነት ስላለኝና በዛሬው የኢትዮጵያ ተጨዋቾች ብቃት እየተቃጠልን ያለነው ሳያንስ እንደ ተድላ አይነቱ የሰው ታሪክ ሊያጎድፍ ሲወራጭ ታሪክ አልባ ጭንጋፍ ሆኖ የቀረ... ዘረኝነት እንደ ልጅነት ልምሻ ያላወሰውና... እግር ኩዋስን ከዚሁ በሽታው ጋር እያያዘ ለወደፊቱ እንኩዋን ተስፋ እንዳይኖረን ... የእግር ኩዋስ አፍቃሪውን ተስፋ በጥርስ አልባው ድዱ ሲገዘገዝ ሳይ አላስችል ብሎኝ ለሀቅ ተናገርኩ እንጂ እንኩዋን ለደደቢት ከልጅነቴ ስደግፈው ለኖርኩት ቡና እንኩዋን ምንም ስሜት የለኝም:: አትሊስት ባሁኑ ደረጃ....

ከላይ ለቀዘንከው ወሬ ደግሞ መረጃ አምጣ ... ካልሆነ ካንጋፋው ጅል ተድላ መረጃ ተቀባበልና.. ዱቅ አርጋት:: እሱ ጎበዝ ጎልጉዋይ ነው :lol: :lol:
ባሻ ብሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1834
Joined: Sat Feb 12, 2005 5:24 pm
Location: ዋርካ ቦተሊካ

Postby ሰመመን97 » Sun Jul 04, 2010 5:08 am

ውውውው........ይ! ስንት ዶማ ሞልቷል በእናታችሁ?
በተግባርም(ተጫዋቾች):በጽሁፍም(የዋርካዎች ፖለቲካም ስፖርትም ሳይገባቸው በስሜት ብቻ የሚነዱት) እንደህ አይነት ሰዎች ሆነን ነው ማደግን የምንናፍቀው?....በእውነት ራሴን ታዘብኩት! .....ለካ የሌሎችን ስናወራ ነው አዋቂ የምንመስለው!...እኔ የእውነት አፍሬያለሁ በተለጠፈው ቪዲዮም በጽሁፎችም:: ...ከጥቂት አስተያየት ሰጪዎች በስተቀር

መጀመሪያ ስሜታችንን ማሸነፍ አለብን:: ከዚያ ነው ነገሮች የሚጀምሩት! ሰው ራሱን ካሸነፈ ቀጣዩ ብዙ አይከብድም::ማንንም መንቀፍ ፈልጌ አይደለም አዝኜ ነው እንጅ!...ያለመታደል! :cry: ....በዚህ አይነት የስፖርት አመለካከታችን ነው ስፖርቱ የሚያድገው???....ይሁና! :?
በዚህ አመለካከታችን ነው ፖለቲካው የሚያድገው እና ፍትህ:እድገት :ብልጽግና:.....የሚመጡት?....ይሁና!! :?

በርግጥም እነዚሁ ሰዎች ከሆኑ ስልጣን ለመያዝ ደፋ ቀና የሚሉት:ለእኔ ይቅሩብኝ:: እዚያው ወያኔ እንደጀመረ ይጫወትባት ይህችን ምስኪን ሀገር :ወደ ልባችን ተመልሰን አምላክ በምህረት እስከሚጎበኘን ድረስ!

ሰላም!
"If it can happen,it will happen.The question is the matter of time!!!"
ሰመመን97
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 15
Joined: Thu Dec 03, 2009 12:00 am

Postby ተድላ ሀይሉ » Sun Jul 04, 2010 6:34 am

Monica**** wrote:ዋው ተድልሽ ቪዲዮውን አየሁት
ጊዮርጊስ ምነው ማልያችው እንደዚህ የሚያስጠላ ሆነ???
ለነገሩ ከድሮውም የኛን አገር ፉትቦል ተከታትዬውም አላውቅም ጊዮርጊስንም የምደግፈው አባቴ ስለሚወደው ነበር!!!

ሞኒክ :- ጊዮርጊስ አሁን የሼሁ የግል ንብረት እንጂ እንደ ቀድሞው የሕዝብ ቡድን አይደለም ::

ውይ ተጨዋቾቹ ግን ስውነታችው የተጎዳ ይመስላል ቅጭጭ ነገር ብለው....አይ ቤት ዩ ምንም አይነት ኖሪሽመንት የሚስጡዋችው አይመስለኝም ስሩ አውት ዘ ይር....ልክ ጨዋታ ሊኖራችው ሲል ምናልባት ይመግቧችው ይሆናል እንጂ!!!

የኢትዮጵያን እግር ኳስ ተጫዋቾች ከሌላው ዜጋ ለይተሽ አትመልከቻቸው :: አብዛኞቹ በኑሮ ከደቀቀው ማኅበረሰብ የተገኙ ናቸው :: በዚያ ላይ በክለብ ታቅፈው እግር ኳስ መጫወት የሚጀምሩት ቢያንስ 25 ዓመት ከሆናቸው በኋላ ስለሆነ ምንም ቢመገቡ ሰውነታቸው ሊፋፋ አይችልም :: የሚቀርብላቸው ምግብ በካፊቴሪያ የተዘጋጀ ሲሆን እኒህ ተጫዋቾች ያንን ምግብ እየተው ሌላም ዓይነት ሱስ ውስጥ ይገባሉ :- ሲጃራ : ጫት : መጠጥ :: ቀንደኛ ጠጪ ከሚባሉት ውስጥ ለምሣሌ ኤልያስ ጁሃር (ለብሔራዊ ቡድኑ 10 ቁጥር እና የመብራት ኃይል ቡድን ተጫዋች የነበረ) : ጌታቸው አበበ (ዱላ) (የጊዮርጊስ እና የብሔራዊ ቡድኑ በረኛ የነበረ) : ..... ዝርዝራቸው ረዥም ነው :: ስለዚህ የዚህን ዓምድ ርዕስ "በሌለ እግር ኳስ ..." ብዬ የሠየምኩት ለዚያ ነው ::
ደደቢት ግን በጣም አስቆኛል ከምር ስድብ ይመስላል!!!!
የወያኒ ቡድን መሆን አለበት ልክ እነደነሱ ደደቦቹ መርጠው ሊሆን ይችላል....ናችው አላልኩም ስላማላቃችው ግን ሊሆን ይችላል ነው :lol: :lol:

ደደቢት ወያኔዎች ተመሠረትንበት የሚሉትና ትግራይ ውስጥ ያለ የቦታ ሥም ነው ::

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Sun Jul 04, 2010 6:36 am

ባሻ ብሩ wrote:የዳኛውን ባጅ ሳታከብር እኔን ለምን ትጠይቀኛለህ? :lol:
አለም ዋንጫ ያላጫወትክ የምትለኝ አለም ዋንጫ ላይ እንዲህ ያለ ስርአት የለቀቀ ነገር አይተሀል እንዴ? የብራዚሉ ካካ እንኩዋን ተጨዋችና ዳኛ ሲደበድብ ታይቶ አደለም... የኮትዲቭዋሩን ተጨዋች ሆን ብሎ መንገድ ቢዘጋበትና ተጨዋቹ ወድቆ ቢንፈራፈር እኮ ነው በቀይ የተባረረው... :)

ሰላማዊ ስፖርት እና ሰላማዊ ያልሆነ ስፖርት ደሞ ምንድነው? :lol: ኦኬ.... ቦክስና MMA ን መሸሽህና ገበጣና ቼዝን መምረጥህ ነው? :lol:

ሹምባሽ ብሩ :-

ሌላስ የቀረ ሥድብ አለህ :?:

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ባሻ ብሩ » Sun Jul 04, 2010 6:06 pm

ተድላ ሀይሉ wrote:ሹምባሽ ብሩ :-

ሌላስ የቀረ ሥድብ አለህ :?:

ተድላ


ተድላ
ስድብ አይጎዳም , አይለጠፍምም:: ቢጎዳና ቢለጠፍ እስከዛሬ አንተ የሰደብከኝም ይለጠፍና ይጎዳኝ ነበር:: ጎጂው ተንኮል የገነባው ምግባር ነው:: ከሱ ተቆጠብ::
ባሻ ብሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1834
Joined: Sat Feb 12, 2005 5:24 pm
Location: ዋርካ ቦተሊካ

Postby ዞብል2 » Wed Jul 07, 2010 5:49 pm

ባሻ(ጋሽ ጅሩ) :P ስለ ደደቢቶች ፕሮፌሽናል ቡድን ለመሆን የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ቅርብህ ስለሆኑ ጠይቀህ መረዳት ትችላለህ :wink:

ሳን ጆርጅና ደደቢቶችን ያጫወተው ዳኛ የደደቢት ምሩቅ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም :P ምክንያቱም የኢትዮጵያ ፉትቦል ፌዴሬሽን ዳኛ ቢሆን ኖሮ የፊፋን ህግ ስለሚያውቅ በህጉ መሰረት ዳኛው እንደ ተመታ ቀይ ካርድ ሳይሆን ጫዋታውን አቋርጦ ተሸናፊነትን በተማቺው ቡድን ላይ ወስኖ ሪፖርቱን ያቀርብ ነበር::

"የደደቢት ቡድን በኢትዮጵያ ብቸኛው ፕሮፌሽናል ቡድን ለመሆን እንቅስቃሴ እያደረገ ነው :P :lol: :lol:


ዞብል ከአራዳ
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2026
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Postby geremew » Wed Jul 07, 2010 11:29 pm

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋቾችና በክለቡ ላይ እገዳና የቅጣት ውሳኔ ማስተላለፉን ከትናንት በስቲያ አስታወቀ፡፡ በክለቡ የቡድን መሪና ደጋፊዎች ላይ የሚያሳልፈውን ውሳኔ ለማሳወቅ ማስረጃ እየመረመረ እንደሚገኝም ገልጿል፡፡
ባለፈው ሳምንት በቅዱስ ጊዮርጊስና በደደቢት ክለቦች መካከል የክለቦች ጥሎ ማለፍ የፍጻሜ ጨዋታ በተደረገበት ወቅት፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋቾች ጨዋታውን በመሐል ዳኝነት ሲመሩ የነበሩትን ኢንተርናሽናል ዳኛ በአምላክ ተሰማን ደበደቡ መባሉ ይታወሳል፡፡

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዲስፕሊን ኮሚቴ ሰኔ 23 ቀን 2002 ዓ.ም. በሰበታ ስታዲዮም የጥሎ ማለፍ ጨዋታ በተካሔደበት ወቅት፣ ጥፋት ፈጽመው በተገኙ ተጫዋቾች የእገዳና የቅጣት ውሳኔ አሳልፏል፡፡

በዚህ መሠረት ለእለቱ ግጭት በመንስዔነት የተጠቀሰው ሚካኤል ደስታ የተባለው ተጫዋች፣ ባለፈው የውድድር ዓመት በፈጸመው ጥፋት ተወስኖበት የነበረው ቅጣት በገደብ ተይዞለት እያለ፣ በድጋሚ ይህንን ጥፋት በመፈጸሙ፣ የዲስፕሊን ኮሚቴው ሁለት ዓመት ከጨዋታ እንዲታገድና በእለቱ ላጠፋው ጥፋት ስድስት ጨዋታ እንዳይጫወት ተደርጐ፣ በተጨማሪም ሦስት ሺሕ ብር እንዲከፍል ወስኖበታል፡፡

አዳነ ግርማ የተባለው ተጫዋች ዳኛ ላይ መትፋቱ በማስረጃ ስለተረጋገጠበት፣ አንድ ዓመት ከጨዋታ እንዲታገድና አምስት ሺሕ ብር እንዲከፍል፣ ሳላዲን ሰይድ የተባለው ተጫዋች ደግሞ ዳኛ በመማታት ሁለት ዓመት ከጨዋታ እንዲታገድና አምስት ሺሕ ብር እንዲከፍል ተወስኗል፡፡

ኡጋንዳዊው በረኛ እንዲዚ ኤማናና ተጠባባቂው በረኛ ዘሪሁን ታደሰ የተባሉት ተጫዋቾች በፈጸሙት ጥፋት አንድ፣ አንድ ጨዋታ እንዲታገዱ ተደርጓል፡፡ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መተዳደሪያ ደንብ በአንድ ጨዋታ አምስት ተጫዋቾች ቢጫና ቀይ ካርድ ካዩ በሚለው ሕግ መሠረት፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ በክለብ አምስት ሺሕ ብር እንዲቀጣ ተወስኖበታል፡፡ በተጨማሪም በክለቡ የቡድን መሪ፣ ደጋፊዎችና ክለቡ ላይ ለሚተላለፈው ውሳኔ ማስረጃዎችን አጣርቶ ከመረመረ በኋላ ትናንትናው ዕለት ሰኔ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ቢያሳውቅም፣ ሕትመት እስከባንበት ሰዓት ድረስ ውሳኔውን ማወቅ አልተቻለም፡፡
geremew
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 285
Joined: Tue Dec 28, 2004 8:43 pm
Location: united states

Postby ተድላ ሀይሉ » Wed Jul 07, 2010 11:51 pm

'geremew' :-

እባክህ የመረጃውን ምንጭ ጥቀስልን ::

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby geremew » Thu Jul 08, 2010 2:40 am

ሰላም ተድላ ሀይሉ:
የዜናው ምንጭ ሪፖርተር ሲሆን ወሳኔው ያንስ እንድሆን እንጂ እንደማይበዛ ነው እኔን የተሰማኝ:: በቴሌቭዥን እንዳየነው ዳኛን በቴስታ መማታት ቢያንስ ሰባት አመት ሊያስቀጣ ይገባ ነበር:: ተስፋዬ ኡርጌቾ የተባለ ተጫዋች ተድላ የተባለ አርቢትርን በቦክስ መትቶ 7 አመት እንደተቀጣ አስታውሳለሁ:: ስህተቱን አምኖ ከዛ በፊት የነበረው የጨዋነት ሪኮርድ ታይቶ በዳኛው ምህረት ለብሄራዊ ቡድን መጫወቲ ሁሉ ተደማምሮ ቅጣቱ ተሰርዞለት ነበር:: ቅጣቱ ይገባቸዋል ባይ ነኝ::
geremew
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 285
Joined: Tue Dec 28, 2004 8:43 pm
Location: united states

Postby ተድላ ሀይሉ » Thu Jul 08, 2010 3:14 pm

geremew wrote:ሰላም ተድላ ሀይሉ:
የዜናው ምንጭ ሪፖርተር ሲሆን ወሳኔው ያንስ እንድሆን እንጂ እንደማይበዛ ነው እኔን የተሰማኝ:: በቴሌቭዥን እንዳየነው ዳኛን በቴስታ መማታት ቢያንስ ሰባት አመት ሊያስቀጣ ይገባ ነበር:: ተስፋዬ ኡርጌቾ የተባለ ተጫዋች ተድላ የተባለ አርቢትርን በቦክስ መትቶ 7 አመት እንደተቀጣ አስታውሳለሁ:: ስህተቱን አምኖ ከዛ በፊት የነበረው የጨዋነት ሪኮርድ ታይቶ በዳኛው ምህረት ለብሄራዊ ቡድን መጫወቲ ሁሉ ተደማምሮ ቅጣቱ ተሰርዞለት ነበር:: ቅጣቱ ይገባቸዋል ባይ ነኝ::


ምንጭ:- ሪፖርተር ጋዜጣ : ሰኔ 30 ቀን 2002 ዓ.ም. :: እግር ኳስ ፌዴሬሽን የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋቾችን ቀጣ

ስለተሠጠው ፍርድ እኔ የምለው ቢኖር በሌለ እግር ኳስ ይህን ያህል ማካበዱ ትርጉም የለውም ነው :: አዲሱ ጊዮርጊስ 'ደደቢት' ነው ከሆነ ደግሞ ውሃ መውቀጥ ማለት ነው ::

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby geremew » Sun Jul 11, 2010 7:01 pm

ሰላም ተድላ ሲጠበቅ የነበረው ውሳኔ ተግባራዊ ሆኖዋል:: የቀረው ከቡድኑ የሚሰጠው ውሳኔ ብቻ ይሆናል::

ሪፖርተር የሚቀጥለውን ዘግቧል::


የዳኞች ማኅበር ውሳኔው የፀና እንዲሆን ጠይቋል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዲሲፕሊን ኮሚቴ፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብን መቅጣቱን ሐምሌ 1 ቀን 2002 ዓ.ም. አስታወቀ፡፡ ውሳኔው በሌላ ውሳኔ እንዳይሻር የፀና ሆኖ እንዲቆይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ዳኞች ማኅበር ጠይቋል፡፡
ሰኔ 23 ቀን 2002 ዓ.ም. ከቀኑ 5፡00 ሰዓት በሰበታ ስታዲየም በቅዱስ ጊዮርጊስና በደደቢት እግር ኳስ ክለቦች መካከል በተደረገው የጥሎ ማለፍ የዋንጫ ጨዋታ፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨዋቾች አንዳንዶቹ የመሐል ዳኛን ደብድበዋል በሚል፣ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዲሲፕሊን ኮሚቴ ጥፋተኛ ሆነው የተገኙ ተጨዋቾች ላይ የእገዳ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ኮሚቴው ከተጨዋቾቹ ቅጣት በተጨማሪ ስፖርት ክለቡ 40 ሺሕ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲከፍልና ድብደባ የደረሰበት ኢንተርናሽናል ዳኛ በአምላክ ተሰማ ያወጣውን የሕክምና ወጭ ሙሉ ለሙሉ እንዲተካ ወስኗል፡፡

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዲሲፕሊን ኮሚቴ፣ በፌዴሬሽኑ የዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 6 አንቀፅ 34 ንዑስ አንቀፅ 3 በተጠቀሰው መሠረት ብር 40"000 (አርባ ሺሕ ብር) የገንዘብ ቅጣት ለፌዴሬሽኑ እንዲከፍል የተወሰነበት የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ፣ ገንዘቡን እስከ ሐምሌ 9 ቀን 2002 ዓ.ም. ባሉት ቀኖች ውስጥ ሙሉ በሙሉ ገቢ እንዲያደርግ ተጠይቋል፡፡

በተጨዋች አካላዊ ጉዳት የደረሰበት ኢንተርናሽናል ዳኛ በአምላክ ተሰማ ለሕክምና ያወጣው ሙሉ ወጪ በሚያቀርበው ሕጋዊ ማስረጃ መሠረት ክለቡ ተከታትሎ እንዲያስፈፅም የዲሲፕሊን ኮሚቴው በደብዳቤ ቁጥር 2/ኢ.እ.ፌ/ወ-4/43 ቀን 01/11/2002 ዓ.ም. ይፋ አድርጓል፡፡

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ዳኞች ማኅበር በበኩሉ፣ በቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨዋቾች ላይ የተወሰነው የቅጣት ውሳኔ ተመጣጣኝ መሆኑን ገልጾ፣ ለወደፊቱ የዲሲፕሊን መመሪያ ደንቡ በጠቅላላ ጉባኤ ትኩረት ተሰጥቶት እንዲሻሻል ጠይቋል፡፡ በማያያዝም የተወሰነው ውሳኔ ወደፊት በዳኞችና በተጨዋቾች መካከል የሚኖረውን ስፖርታዊ ግንኙነት የሚያሻክር እንዳይሆን፣ ውሳኔው ጽኑ፣ የማይሻርና የማይቀለበስ፣ ብሎም በይግባኝ የማይቀነስ እንዲሆን ሲል አስታውቋል፡፡

የተከሰተውን የዲሲፕሊን ጥሰት በማስመልከት አንዳንድ የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ደጋፊ የሆኑ፣ ነገር ግን ስማቸው እንዳይገለፅ የጠየቁ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚናገሩት፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ አመራር ድርጊቱን ከማውገዝ ባለፈ ጥፋት በፈጸሙ ተጨዋቾችና የቡድን አባላት ላይ የዲሲፕሊን ዕርምጃ መውሰድ እንዳለበትና ጥፋቱን በይፋ ይቅርታ መጠየቅ እንደሚገባው አስገንዝበዋል፡፡
geremew
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 285
Joined: Tue Dec 28, 2004 8:43 pm
Location: united states

Postby ተድላ ሀይሉ » Tue Jul 13, 2010 9:54 pm

geremew wrote:ሰላም ተድላ ሲጠበቅ የነበረው ውሳኔ ተግባራዊ ሆኖዋል:: የቀረው ከቡድኑ የሚሰጠው ውሳኔ ብቻ ይሆናል::

ሪፖርተር የሚቀጥለውን ዘግቧል::


የዳኞች ማኅበር ውሳኔው የፀና እንዲሆን ጠይቋል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዲሲፕሊን ኮሚቴ፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብን መቅጣቱን ሐምሌ 1 ቀን 2002 ዓ.ም. አስታወቀ፡፡ ውሳኔው በሌላ ውሳኔ እንዳይሻር የፀና ሆኖ እንዲቆይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ዳኞች ማኅበር ጠይቋል፡፡
ሰኔ 23 ቀን 2002 ዓ.ም. ከቀኑ 5፡00 ሰዓት በሰበታ ስታዲየም በቅዱስ ጊዮርጊስና በደደቢት እግር ኳስ ክለቦች መካከል በተደረገው የጥሎ ማለፍ የዋንጫ ጨዋታ፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨዋቾች አንዳንዶቹ የመሐል ዳኛን ደብድበዋል በሚል፣ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዲሲፕሊን ኮሚቴ ጥፋተኛ ሆነው የተገኙ ተጨዋቾች ላይ የእገዳ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ኮሚቴው ከተጨዋቾቹ ቅጣት በተጨማሪ ስፖርት ክለቡ 40 ሺሕ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲከፍልና ድብደባ የደረሰበት ኢንተርናሽናል ዳኛ በአምላክ ተሰማ ያወጣውን የሕክምና ወጭ ሙሉ ለሙሉ እንዲተካ ወስኗል፡፡

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዲሲፕሊን ኮሚቴ፣ በፌዴሬሽኑ የዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 6 አንቀፅ 34 ንዑስ አንቀፅ 3 በተጠቀሰው መሠረት ብር 40"000 (አርባ ሺሕ ብር) የገንዘብ ቅጣት ለፌዴሬሽኑ እንዲከፍል የተወሰነበት የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ፣ ገንዘቡን እስከ ሐምሌ 9 ቀን 2002 ዓ.ም. ባሉት ቀኖች ውስጥ ሙሉ በሙሉ ገቢ እንዲያደርግ ተጠይቋል፡፡

በተጨዋች አካላዊ ጉዳት የደረሰበት ኢንተርናሽናል ዳኛ በአምላክ ተሰማ ለሕክምና ያወጣው ሙሉ ወጪ በሚያቀርበው ሕጋዊ ማስረጃ መሠረት ክለቡ ተከታትሎ እንዲያስፈፅም የዲሲፕሊን ኮሚቴው በደብዳቤ ቁጥር 2/ኢ.እ.ፌ/ወ-4/43 ቀን 01/11/2002 ዓ.ም. ይፋ አድርጓል፡፡

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ዳኞች ማኅበር በበኩሉ፣ በቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨዋቾች ላይ የተወሰነው የቅጣት ውሳኔ ተመጣጣኝ መሆኑን ገልጾ፣ ለወደፊቱ የዲሲፕሊን መመሪያ ደንቡ በጠቅላላ ጉባኤ ትኩረት ተሰጥቶት እንዲሻሻል ጠይቋል፡፡ በማያያዝም የተወሰነው ውሳኔ ወደፊት በዳኞችና በተጨዋቾች መካከል የሚኖረውን ስፖርታዊ ግንኙነት የሚያሻክር እንዳይሆን፣ ውሳኔው ጽኑ፣ የማይሻርና የማይቀለበስ፣ ብሎም በይግባኝ የማይቀነስ እንዲሆን ሲል አስታውቋል፡፡

የተከሰተውን የዲሲፕሊን ጥሰት በማስመልከት አንዳንድ የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ደጋፊ የሆኑ፣ ነገር ግን ስማቸው እንዳይገለፅ የጠየቁ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚናገሩት፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ አመራር ድርጊቱን ከማውገዝ ባለፈ ጥፋት በፈጸሙ ተጨዋቾችና የቡድን አባላት ላይ የዲሲፕሊን ዕርምጃ መውሰድ እንዳለበትና ጥፋቱን በይፋ ይቅርታ መጠየቅ እንደሚገባው አስገንዝበዋል፡፡

አሁንም እደግመዋለሁ :- ኢትዮጵያ ውስጥ የእግር ኳስ ደጋፊ እንጂ ስፖርቱን በተቋም ደረጃ የሚያንቀሣቅስ ፌዴሬሽንም ሆነ ለስፖርቱ የሚመጥኑ ተጫዋቾችን ያቀፉ ክለቦች የሉም :: ስለዚህ ይህ 'በጊዮርጊስ ቡድን ተጫዋቾች ላይ ቅጣት ተወሰነ' ወይም ተመሣሣይ ወሬ በሌለ ነገር ላይ የሚደረግ የጨረባ ተዝካር ነው ::

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Re: በሌለ እግር ኳስ ጨዋታ የወያኔ ደደቢት ቡድን አሸናፊነት

Postby ቢተወደድ » Wed Jul 14, 2010 3:41 am

አይ ተላ

ነገሮችን በሚዛናዊነት ለመመልከት እንዲያበቃ በደርግ ጊዜም ምን ያህል እንዳሽቆለቆለ ብትጠቅስ አይጎዳም ነበር:: አንተ ግን እንደ ናዝሬት ጋሪ አይንህ ግራ ቀኙን እንዳያይ ተሸፍኖዋል::

ተድላ ሀይሉ wrote:ሰላም ውድ ወገኖቼ :-

ኢትዮጵያ የአፍሪቃ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን ከመሠረቱት 4 አገሮች አንዷ ነች :: ግብጽ እና ደቡብ አፍሪቃ በስፖርቱም ዕድገት ሆነ በዓለም አቀፍ ተሣትፏቸው ከፍተኛ መሻሽል ሲያሣዩ ሱዳን እና ኢትዮጵያ ቁልቁል ሲጓዙ ኖረዋል :: ሆኖም ሱዳን በትንሹም ቢሆን የተሻለ እንቅስቃሴ ታደርጋለች :: በኢትዮጵያ ግን በአንድ ክለብ ከማመን አባዜ ጋር በተያያዘ ለረዥም ዘመናት የእግር ኳሱ ስፖርት ዕድገት እንደ ካሮት ወደመሬት ሆኖ ዘልቋል :: ይኼ ሣያንስ ወያኔ ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረ ጀምሮ የጎሣው ፖለቲካ እግር ኳሱንም ሲያምስ እና ሲያተራምስ እናያለን :: ይባስ ብሎ በወያኔ የትውልድ መንደር ደደቢት ሥም የተቋቋመ ቡድን በግድ ዋንጫ ይብላ ተብሎ በጥሎ ማለፍ የፍጻሜ ውድድር ላይ ለ5 የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን ተጫዋቾች የቀይ ካርድ በማደል ዋንጫውን ለለገሠ (መለስ) ግልገል ቡችሎች አስረክበዋል :: ለምን ከመጀመሪያውኑ ይህ ዋንጫ የደደቢት ቡድን የግል ንብረት ነው ብለው አያሣውቁም ነበር ?

እስኪ ይህንን አሣፋሪ ትዕይንት ተመልከቱት ...

ምንጭ:- ETV Sport News - St George players beat up a referee and five of them get red card

ተድላ
When we do it right No-one remembers,
When we do it wrong No-one forgets.
ቢተወደድ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1965
Joined: Tue Jul 21, 2009 3:21 pm
Location: Dabra Za`Yet

Re: በሌለ እግር ኳስ ጨዋታ የወያኔ ደደቢት ቡድን አሸናፊነት

Postby ተድላ ሀይሉ » Fri Jul 16, 2010 4:41 pm

ቢተወደድ wrote:አይ ተላ

ነገሮችን በሚዛናዊነት ለመመልከት እንዲያበቃ በደርግ ጊዜም ምን ያህል እንዳሽቆለቆለ ብትጠቅስ አይጎዳም ነበር:: አንተ ግን እንደ ናዝሬት ጋሪ አይንህ ግራ ቀኙን እንዳያይ ተሸፍኖዋል::


ኢትዮጵያ በአፍሪቃም ሆነ በዓለም የእግር ኳስ እንቅስቃሴዋ ምን ይመስላል ?
1........... በአፍሪቃ ዋንጫ ተሣትፎ
ሀ.........በአጼ ኃይለሥላሤ የአገዛዝ ዘመን
* 1ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ :- በ1949 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ 1957) - ከሦሥት አገሮች (ሱዳን : ግብፅ እና ኢትዮጵያ) ሁለተኛ
* 2ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ :- በ1951 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. 1959) - ከሦስት አገሮች (ሱዳን : ግብፅ እና ኢትዮጵያ) ሦሥተኛ
* 3ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ :- 1954 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. 1962) ከዘጠኝ አገሮች የውድድሩ አዘጋጅ እና ሻምፒዮና
* 4ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ :- 1955 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. 1963) - አራተኛ
* 5ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ :- 1957 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ 1965) - መጀመሪያ ዙር
* 6ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ :- 1960 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. 1968) - የውድድሩ አዘጋጅ እና አራተኛ
* 7ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ :- 1962 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. 1970) - መጀመሪያ ዙር
* 8ኛው እና 9ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ :- በ1964 እና 1966 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. 1972 እና 1974) - ማጣሪያውን አላለፈችም
ለ .........በደርግ የአገዛዝ ዘመን
* 10ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ :- 1968 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. 1976) - አዘጋጅ አገር እና በመጀመሪያ ዙር ተሠናባች
* 11ኛው እና 12ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ :- 1970 እና 1972 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. 1978 እና 1980) - ማጣሪያውን አላለፈችም
* 13ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ :- 1974 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. 1982) - በመጀመሪያው ዙር ተሠናባች
* 14ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ :- 1976 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. 1984) - ማጣሪያውን አላለፈችም
* 15ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ :- 1978 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. 1986) - ከውድድሩ ራሷን አግልላለች
* 16ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ :- 1980 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. 1988) - በማጣሪያው ወቅት ከውድድሩ ራሷን አግልላለች
* 17ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ :- 1982 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. 1990) - ማጣሪያውን አላለፈችም
ሐ .........በወያኔ የአገዛዝ ዘመን
* 18ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ :- 1984 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. 1992) - በማጣሪያው ወቅት ራሷን ከውድድር አግልላለች
* 19ኛው : 20ኛው እና 21ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ :- 1986 : 1988 እና 1990 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. 1994 : 1996 እና 1998) - ማጣሪያውን አላለፈችም
* 22ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ :- 1992 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. 2000) - ከውድድሩ ራሷን አግልላለች
* 23ኛው : 24ኛው : 25ኛው እና 26ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ :- 1994 : 1996 : 1998 እና 2000 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. 2002 : 2004 : 2006 እና 2008) - ማጣሪያውን አላለፈችም
* 27ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ :- 2002 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. 2010) - ከውድድሩ ታግዳለች

ምንጭ:- ዊኪፔዲያ

በአጼ ኃይለሥላሤ የአገዛዝ ዘመን ከ9 የአፍሪቃ ዋንጫ ውድድሮች በ7ቱ መካፈል ችላ : ሁለት ውድድሮች አዘጋጅታ : አንድ ጊዜ የዋንጫ ባለቤት ሆናለች ::

በደርግ የአገዛዝ ዘመን ከ8 የዋንጫ ውድድሮች በሁለቱ ተሣትፋለች : አንድ ጊዜ ውድድሩን ለማስተናገድ ችላለች ::

በወያኔ የአገዛዝ ዘመን ከ10 የዋንጫ ውድድሮች በአንዱም ለመሣተፍ ያለመቻሏ ብቻ ሣይሆን በተደጋጋሚ ከውድድር መውጣት እና በቅርቡ በተደረገው ውድድርም በፊፋ እስከመታገድ ደርሣ ነበር ::

ይህ ሁሉ ምንን ያመለክታል ? ታሪኩ ይህንን ይመስላል :: እንግዲህ ከዚህ ዓለም ያወቀው : ፀሐይ የሞቀው ሃቅ ውስጥ የራስህን ተቃራኒ የምትለውን የአንተን የወያኔን አገዛዝ መልካም ሥራ አሣዬን ::

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ከንቲባ. » Fri Jul 16, 2010 8:40 pm

እንደዚህ ያለ ታሪክ አይቼም ሰምቼም አላውቅም እንዴት ሆኖ ፉትቦል ሊያድግ ይችላል ? አይደለም ማደግ ከኖረም ይገርመኛል : ወያኔ የትኛውን ይሆን ለቀቅ የሚያደርገው ?
ምን አይነት ጉዶች ናቸው ግን ያለህግ የሚኖሩ ነገሮች::
ደደቢቶቹስ ሳይጫወቱ ዋንጫ ምን የሚሉት ነው ?
መጥኔ ለነሱ

አቶ ቢ ተ ወ ደ ድ የተሳደብከው ራስህን ሆኖ ነው ያገኘሁት ::
ከአስተያየትህ በፊት ቅንነትን ብታስቀድም መልካም ነው ከተድላ ብዙ እንደተማርክ እኔም ተምሬያለሁ::
Ethiopia tikdem
ከንቲባ.
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 50
Joined: Fri Jan 08, 2010 10:12 pm
Location: Roma

PreviousNext

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest