ይድነቃቸውን የምታስታውሱ

ስፖርት - Sport related topics

ይድነቃቸውን የምታስታውሱ

Postby እንሰት » Tue Dec 21, 2010 5:47 pm

ሰሞኑን በእግር ኩዋስ ታሪካችን ወርቃማ ታሪክ የነበረው መንግስቱ ወርቁ አረፈ:: መንግስቱ አንዳንድ ድክመቶች ቢኖሩትም ሚዛን የሚደፉ አይደሉም:: ታሪክም ይህንን ግንዛቤ ውስጥ ያስገባና መንግስቱ ሲነሳ ድንቅ ስራው ተጋድሎው ነው::

ይድነቃቸውም እንዲሁ ናቸው:: እኛ ምንም ሳንል ሳናደርግ አፍሪካዊዋ አረባዊዋ ሞሮኮ ስታዲየሙዋን በስሙ የሰየመችለት ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን አፍሪካዊም አለማዊም ጀግና ነው:: አንዱና ተጠቃሹ ውለታው ቢያንስ በአፍሪካ ስታዲየሞችና የስፖርት ማስታወቂያዎች አልኮል ምናልባትም ትምባሆ እንዳይተዋወቅ ማድረጉ ነው::

ዘመነኛችን ሀይሌም ከእነኚህ ታላላቆች የሚመደብ ነው:: 2003 ከገባ ጀምሮ ግን ሀይሌ አነጋጋሪ እየሆነ መጥቶዋል::
መቸም እሱ የሚያውቀው እኛ የማናውቀው ችግር ምስጢር ሊኖረው ይችላል ግን የሰሞኑ የመጠጥ የውስኪ ማስታወቂያ
አንዱዋን ፊደል ብንቀይራት ማስታወኪያ በጣም አሳዛኝ ድርጊቱ ነው:: ስፖርት እና መጠጥ በምንም ሚዛን አብረው አይሄዱም:: የፔፕሲው ሲገርመኝ አሁን ደግሞ ውስኪ ይሄ ይለይላችሁ ይመስላል:: ምናለ እንደ ድሮው ልቡናው ትንሽ መለስ ብሎ ቢሰራ:: እውነቴን ነው የምላችሁ ማፈሬን አይደለም የምነግራችሁ መደንገጤን ነው!

ሰው የሚወደደውም የሚጠላውም በስራው ነው ረባም አልረባም የስፖርት ታሪካችን ላይ እኮ የውስኪው ማስታወቂያ ይነሳል:: ብሩ አሳስቶት ነው እንዳይባል ደግሞ በሀይሌ ደረጃ እዚህ ግባ በማይባል ብር 1.4 ሚሊየን (75 ሺ ዶላር) ነው እኮ ሰራሁ ያለው:: ምናልባት እኮ ያንድ ወር የሰራተኞቹን ደሞዝ ቢሸፍንለት ነው::

ግን ምን ነካው?“ 100 ሚልዮን ዶላር ቢከፍሉኝ እንኳ የመጠጥ ማስታወቂያ አልሠራም፡፡” አቶ ውብሸት ወርቃለማሁ የኀይሌን የውስኪ ማስታወቂያ መሥራት በመቃወም የተናገሩት

“እግዚአብሔር ያክብርህ ብለው ቢመርቁት ይሻል ነበር፡፡” ሠራዊት ፍቅሬ ለኀይሌ የተከፈለው የ 100ሺሕ ዶላር ክፍያ ትንሽ መኾኑን ለመግለጽ የተናገረው

ምንጭ አዲስ ነገር

ኀይሌ እና ዉስኪ

ኀይሌ በመቶ ሺሕ ዶላር ክፍያ የጆኒ ዎከር ዉስኪ ማስታወቂያ መሥራቱ እያነጋገረ ነው፡፡ ኀይሌ የስፖርት ሰው ኾኖ እንዴት ይህን ይሠራል በሚል የተተቸ ሲኾን እርሱ ግን ‹‹ጠጡ ግን ሐላፊነት ውሰዱ›› የሚል መልእክትን አስተላልፏል፡፡ ኢትዮጵያውያን ውስኪን ዘመድ ወዳጅ ሲጠይቁ ይዘዉት እንደሚሄዱ እና ማስታወቂያውን መሥራቱ ችግር እንደሌለው ይከራከራል፡፡ ከተከፈለው መቶ ሺህ ዶላር ውስጥ ከዚህ ውስጥ 22 በመቶ ለእንግሊዝ መንግሥት በታክስ መክፈሉን፣ 15 በመቶ ለማኔጀሩ እንደሚደርስ እና በእጁ የሚደርሰው ክፍያ 73ሺህ ዶላር ብቻ እንደኾነ ለአድማስ ጋዜጣ ተናግሯል፡፡

ምንጭ ጋንች <http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=43459>
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Re: ይድነቃቸውን የምታስታውሱ

Postby ዲጎኔ » Sun Dec 26, 2010 4:24 am

ሰላም ለሁላችን ይሁን
ውድ እንስት ለዚህ ወቅታዊ ልዩ ዘገባ ብዙ እጥፍ ምስጋና
ይድነቃቸው ተሰማ ባለልዩ ታሪክ የኢትዮጲያ ብርቅዬ ልጅ ነው::ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ይድኔም 'ፉትበል'ሆነ ያሉት ውስጠወይራ ግን ሀቅነት ነበረው::ስፖርተኛና መጠጥ ባይዋደዱ ይመረጣል ባለመታደል ግን እውቅ ተጫዋቾችና መሪዎች በአልኮል ጠንቅ ሲወድቁ አይቻለሁ::በጣም ጥቂቶች የኤሌትሪክ ቢረጋና መሀመድ ሮሜዎ ከአልኮል ጠንቅ የራቁ ናቸው::እንደኢትዮጲያ ባለ ሀገር የአልኮል ህግ ፈጽሞ የሌለ እንደውም ለመንዳት መቅመስ ተገቢ እነደሆነ በለየለት ስህተት በትራፊክ አደጋ ከአፍሪካ መሪነቱን ይዘናል::አብዛኛው የትራፊክ አደጋም ከስካር ጋር የተያያዘ ነው::በስካር ተመርዞ መንዳት DWI penalty is unfamiar to Ethiopia-UNDCP report,Vienna,Austria-1996-1998
ባላፈው አመት ባለሁበት ከተማ የቢራ ማስታወቂያ መነገሩ አወዛጋቢ ሆኖ ነበር::ነገር ግን ለሪሰርች የሚያደርጉት ድጋፍ ግምት ውስጥ ገብቶ አብዛኛው አሜሪካዊ ልኩን አውቆ የሚጠጣ በመሆኑ ተቃውሞው ሚዛን ሳይደፋ ቀረ የቢራው ፋብሪካም ቀጥሏል::
ይህ ሀይሌ የሚባል ሰው ግን እንደተረቱ ወጣወጣና ተንከባለለ እንደሙቀጫ ሆነበት::ፍቅረነዋይና ዝና አይኑን ስላሳወሩት ምንም ማድረግ አይቻልም::በበለጸጉት ሀገሮች ቢሆን የሀይሌ አንዳንድ ማእረጎች ላይ እቀባ በተለይ ስካርን በሚቃወሙት ዘንድ ይተገበርበት ነበር::
ዲጎኔ ሞረቴው ጌታቸው ዱላና ሰለሞን ሉቼ ጎረቤት ላጋርእንሰት wrote:ሰሞኑን በእግር ኩዋስ ታሪካችን ወርቃማ ታሪክ የነበረው መንግስቱ ወርቁ አረፈ:: መንግስቱ አንዳንድ ድክመቶች ቢኖሩትም ሚዛን የሚደፉ አይደሉም:: ታሪክም ይህንን ግንዛቤ ውስጥ ያስገባና መንግስቱ ሲነሳ ድንቅ ስራው ተጋድሎው ነው::

ይድነቃቸውም እንዲሁ ናቸው:: እኛ ምንም ሳንል ሳናደርግ አፍሪካዊዋ አረባዊዋ ሞሮኮ ስታዲየሙዋን በስሙ የሰየመችለት ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን አፍሪካዊም አለማዊም ጀግና ነው:: አንዱና ተጠቃሹ ውለታው ቢያንስ በአፍሪካ ስታዲየሞችና የስፖርት ማስታወቂያዎች አልኮል ምናልባትም ትምባሆ እንዳይተዋወቅ ማድረጉ ነው::

ዘመነኛችን ሀይሌም ከእነኚህ ታላላቆች የሚመደብ ነው:: 2003 ከገባ ጀምሮ ግን ሀይሌ አነጋጋሪ እየሆነ መጥቶዋል::
መቸም እሱ የሚያውቀው እኛ የማናውቀው ችግር ምስጢር ሊኖረው ይችላል ግን የሰሞኑ የመጠጥ የውስኪ ማስታወቂያ
አንዱዋን ፊደል ብንቀይራት ማስታወኪያ በጣም አሳዛኝ ድርጊቱ ነው:: ስፖርት እና መጠጥ በምንም ሚዛን አብረው አይሄዱም:: የፔፕሲው ሲገርመኝ አሁን ደግሞ ውስኪ ይሄ ይለይላችሁ ይመስላል:: ምናለ እንደ ድሮው ልቡናው ትንሽ መለስ ብሎ ቢሰራ:: እውነቴን ነው የምላችሁ ማፈሬን አይደለም የምነግራችሁ መደንገጤን ነው!

ሰው የሚወደደውም የሚጠላውም በስራው ነው ረባም አልረባም የስፖርት ታሪካችን ላይ እኮ የውስኪው ማስታወቂያ ይነሳል:: ብሩ አሳስቶት ነው እንዳይባል ደግሞ በሀይሌ ደረጃ እዚህ ግባ በማይባል ብር 1.4 ሚሊየን (75 ሺ ዶላር) ነው እኮ ሰራሁ ያለው:: ምናልባት እኮ ያንድ ወር የሰራተኞቹን ደሞዝ ቢሸፍንለት ነው::

ግን ምን ነካው?“ 100 ሚልዮን ዶላር ቢከፍሉኝ እንኳ የመጠጥ ማስታወቂያ አልሠራም፡፡” አቶ ውብሸት ወርቃለማሁ የኀይሌን የውስኪ ማስታወቂያ መሥራት በመቃወም የተናገሩት

“እግዚአብሔር ያክብርህ ብለው ቢመርቁት ይሻል ነበር፡፡” ሠራዊት ፍቅሬ ለኀይሌ የተከፈለው የ 100ሺሕ ዶላር ክፍያ ትንሽ መኾኑን ለመግለጽ የተናገረው

ምንጭ አዲስ ነገር

ኀይሌ እና ዉስኪ

ኀይሌ በመቶ ሺሕ ዶላር ክፍያ የጆኒ ዎከር ዉስኪ ማስታወቂያ መሥራቱ እያነጋገረ ነው፡፡ ኀይሌ የስፖርት ሰው ኾኖ እንዴት ይህን ይሠራል በሚል የተተቸ ሲኾን እርሱ ግን ‹‹ጠጡ ግን ሐላፊነት ውሰዱ›› የሚል መልእክትን አስተላልፏል፡፡ ኢትዮጵያውያን ውስኪን ዘመድ ወዳጅ ሲጠይቁ ይዘዉት እንደሚሄዱ እና ማስታወቂያውን መሥራቱ ችግር እንደሌለው ይከራከራል፡፡ ከተከፈለው መቶ ሺህ ዶላር ውስጥ ከዚህ ውስጥ 22 በመቶ ለእንግሊዝ መንግሥት በታክስ መክፈሉን፣ 15 በመቶ ለማኔጀሩ እንደሚደርስ እና በእጁ የሚደርሰው ክፍያ 73ሺህ ዶላር ብቻ እንደኾነ ለአድማስ ጋዜጣ ተናግሯል፡፡

ምንጭ ጋንች <http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=43459>
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests