የ37 አመቱ ሀይሌ በእሁዱ የቶኪዮ ማራቶን አይወዳደርም::

ስፖርት - Sport related topics

የ37 አመቱ ሀይሌ በእሁዱ የቶኪዮ ማራቶን አይወዳደርም::

Postby ክቡራን » Sat Feb 26, 2011 2:07 pm

የአለም ሪኮርድ ባለቤት የሆነው እውቁ ኢትዮጵያዊ አትሌታችን ሀይሌ ገ/ስላሴ እሁድ ( ፌብራሪ 27, 2011 ) በሚደረገው የቶኪዮ የማራቶን ውድድር እንደማይሳተፍ አስታወቀ:: አትሌት ሀይሌ ለዚህ የሰጠው ምክንያት በልምምድ ሰአት ሁለቱ ጉልበቶቹ ላይ ጉዳት ስለደረሰበት መሆኑን ይገልጻል:: ባለፈውም አመት በኒውዮርክ በተደረገው ውድድር በጉልበቱ ምክንያት ሳይወድ በግዱ ከስፖርት አለም መሰናበቱን ለሚዲያ አሳውቆ የነበረ ቢሆንም ግን በሰአታት ልዩነት ውሳኔውን ያደረኩት ስሜታዊ ሆኜ ነው ብሎ እንደማይወጣ ማስተካከያ ሰጥቶ ነበር:: ዘንድሮም ይቺ ጉልበቱ ምቀኛ ሆና ቶኪዮን ከመሰለ ታላቅ ውድድር አስቀረቸው:: በዚህ ውድድር ላይ በሩጫው አለም የገዘፈ ስም ያላቸው የኬንያዎቹ ፊሊክስ ሊሞ, ፓውል ቢዎት, ሳሊም ኢስጋንግ የሚገኙ ሲሆን ከኢትዮጵያም ደግሞ ከሀይሌ ሌላ ሀይሉ መኮንንና የማነ ጸጋዬ ተሳታፊ እንደሚሆኒ ማወቅ ተችሏል:: ዝርዝሩን ለማግኘት እቺን ይጫኑ::
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7988
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests