ካሳሁን ተካ የት ነው ያለው??

ስፖርት - Sport related topics

Postby ገደል » Fri Jun 17, 2011 2:52 am

ተቀዳ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋች ነበር ለብሄራዊ ቡድን መሰለፉን አላውቅም:: ሰሎሞን ተርፋ, ተቀዳ. ፍስህ ወ/አማኑኤል: ሸዋንግዛው አጎናፍፍር በአንድ ሰሞን ነው ከጊዮርጊስ ለቀው ወደ አሜሪካ የሄዱት::

ክቡራን......የጀመርከውን ታሪክ ጨርስ: ግን እዚች ላይ ምን ለማለት እንደፈለክ ግልጽ አይደለም::
........ከእለታት አንድ ቀን ሉዑሉ በክብርነቱ ሆኖ ወደ ስታዲዮም ይሄዳል :: ልዑሉ ወደ ስታዲዮም የሄደው ዝም ብሎ ሳይሆን የሚኖርበት ቤት ለስታዲዮም ቅርብ በመሆኑና እሱ የሚደግፈውን ቡድን ሲጫወት ልመልከት ብሎ እንጂ ዝም ብሎ አልነበረም :: ይሁን እንጂ ሉዑል ዳዊት ስታዲዮም ሰደርስ ጨዋታው ያበቃል :: ጨዋታው ቢያበቃም ወደ መልበሻ ክፍል ሲሄድ ከካሳሁን ጋ ይገናኛሉ :: ካሳሁን የጥጥ ተጫዋች መሆኑን የሚያውቀው ሉዑል ዳዊት ገርሞት እዚህ ምን እንደሚሰራ ይጠይቀዋል ( ይቀጥላል ) ::
ገደል
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 489
Joined: Sat Jan 02, 2010 12:03 am

Postby ክቡራን » Sat Jun 18, 2011 1:17 am

ሰላም ገደል አጻጻፌ ንጉሳዊያን ቤተሰቦች ስለ አንድ ነግር ሲገልጹ ወይም ታሪክ ጸሀፊዎች ስለነሱ ሲጽፉ ወይም ሲናገሩ የሚጠቀሙበትን ስነ-ሀርግ ተጠቅሜ ለመጻፍ እንጂ የተለየ ትርጉም የለውም እዚህ ዋርካ ውስጥ ክብርነታችን ሾተል እንደዚህ አይነት አጻጻፍ ይጽፋል እኔም እጽፋለሁ:: የአጻጻፍ ዘዬ ብቻ ነው:: ይሄን ካልኩ በኈላ ሳይረሳ ስለ እርሻው ተጫዋች ሰለሞን አየለ ጎራዴው ወዳነሳው ነጥብ እንሄድና ከዛ ደሞ እነ ካሳሁን እንዴት ወደ ጊዮርጊስ ተዛወሩ ..? በዝውውራቸው ውስጥስ የሉዑል ዳዊት ሚና ምን ነበር ? የሚለውን እናያለን ማለት ነው::
" ሰለሞን አየለ የወጣት ቡድን ተጫዋች ሆኖ አውቀዋለሁ ይላል ካሳሁን ..አሰልጣኙ ነበርኩ:: ቡዙ ኢንተረናሺናል ጭዋታዎችን የማድረግ እድል አላጋጠመውም:: ይዠው ዩጋንዳ ግብጽና ዙምባቤ ሄጃለሁ:: አንድ ጨዋታ ላይ ታሞ ስለነበር አልተጫወተም:: ሰለሞን ቡዙ በኴሱ አለም አይግፋ እንጂ ጥሩ ታለንት ያለው ልጅ ነበር:: ግሩም የሆኑ አብዱ የመስራት ችሎታ አለው:: በዚህ ላይ የአካዳሚ ሰው ነበር:: አሁን ትምህርቱን ጨርሶ አትላንታ ይኖራል የሚል ወሬ ሰምቻለሁ:: ሰለሞን የወንጂ ልጅ ነው...የኢትዮጵያና የግብጽ ጨዋታ ጊዜ 15 ተጫዋቾች ሲጠፉ ሰለሞን አልጠፋም ከተመለሱት ሰባቱ አንዱ እርሱ እንደነበር አስታውሳለሁ:: በኈላ ግን አላባማ ዩኒቨርስቲ በግር ኴስ ጨዋታ ስኮላር አግኝቶ አሜሪካ ገብቶ አሁን ያለበት ደረጃ ላይ ደርሷል:: ይሄንን ነው ስለ ሰለሞን አየለ የማውቀው ..ጠያቂህ ሌላ ጥያቄ ካላቸው የማውቀውን ለመመለስ እሞክራለሁ..." ይላል ካሳሁን: ተካ::
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7963
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ማይኮል_ም » Wed Jun 22, 2011 6:05 am

ክቡራን wrote:ሰላም ገደል አጻጻፌ ንጉሳዊያን ቤተሰቦች ስለ አንድ ነግር ሲገልጹ ወይም ታሪክ ጸሀፊዎች ስለነሱ ሲጽፉ ወይም ሲናገሩ የሚጠቀሙበትን ስነ-ሀርግ ተጠቅሜ ለመጻፍ እንጂ የተለየ ትርጉም የለውም እዚህ ዋርካ ውስጥ ክብርነታችን ሾተል እንደዚህ አይነት አጻጻፍ ይጽፋል እኔም እጽፋለሁ:: የአጻጻፍ ዘዬ ብቻ ነው:: ይሄን ካልኩ በኈላ ሳይረሳ ስለ እርሻው ተጫዋች ሰለሞን አየለ ጎራዴው ወዳነሳው ነጥብ እንሄድና ከዛ ደሞ እነ ካሳሁን እንዴት ወደ ጊዮርጊስ ተዛወሩ ..? በዝውውራቸው ውስጥስ የሉዑል ዳዊት ሚና ምን ነበር ? የሚለውን እናያለን ማለት ነው::
" ሰለሞን አየለ የወጣት ቡድን ተጫዋች ሆኖ አውቀዋለሁ ይላል ካሳሁን ..አሰልጣኙ ነበርኩ:: ቡዙ ኢንተረናሺናል ጭዋታዎችን የማድረግ እድል አላጋጠመውም:: ይዠው ዩጋንዳ ግብጽና ዙምባቤ ሄጃለሁ:: አንድ ጨዋታ ላይ ታሞ ስለነበር አልተጫወተም:: ሰለሞን ቡዙ በኴሱ አለም አይግፋ እንጂ ጥሩ ታለንት ያለው ልጅ ነበር:: ግሩም የሆኑ አብዱ የመስራት ችሎታ አለው:: በዚህ ላይ የአካዳሚ ሰው ነበር:: አሁን ትምህርቱን ጨርሶ አትላንታ ይኖራል የሚል ወሬ ሰምቻለሁ:: ሰለሞን የወንጂ ልጅ ነው...የኢትዮጵያና የግብጽ ጨዋታ ጊዜ 15 ተጫዋቾች ሲጠፉ ሰለሞን አልጠፋም ከተመለሱት ሰባቱ አንዱ እርሱ እንደነበር አስታውሳለሁ:: በኈላ ግን አላባማ ዩኒቨርስቲ በግር ኴስ ጨዋታ ስኮላር አግኝቶ አሜሪካ ገብቶ አሁን ያለበት ደረጃ ላይ ደርሷል:: ይሄንን ነው ስለ ሰለሞን አየለ የማውቀው ..ጠያቂህ ሌላ ጥያቄ ካላቸው የማውቀውን ለመመለስ እሞክራለሁ..." ይላል ካሳሁን: ተካ::


ሰላም ያገር ልጅ ክቡራን:- በቅድሚያ አስተማሪና አዳዲስስ ነገሮችን እያመጣህ ስለምታስነብበን ያለኝን አድናቆቴን ልገልጽልህ እወዳለሁ::

ክሣሁን ተካ በርግጥ ሲጫወት በእድሜዬ ደርሼ ለማየት ባልታደልም አሁን አብሮኝ የሚኖር አጎቴ በጣም በቅርብ እንደሚያውቀው እየነገረኝ ነው:: እንደ አጎቴ አባባል ካሳሁን በጣም እልከኛ ጠንካራና በግራ እግሩ አክርሮ የሚመታ ተጫዋች ከመሆኑም በላይ መልኩም ጠቆር ስለሚልና ሰውነቱም ፈርጣማ ስለሆነ የሌሎች አፍሪካ አገር ተጫዋች ይመስል ነበር:: አጎቴ ከሚያውቃቸው የኢትዮጵያ ተጫዋቾች ካሳሁን ተካ : አስራት መክብብ ይርዳውና ንጉሴ ገብሬን በሰውነት ጥንካሬ እስካሁንም የሚተክላከላቸው የለም ይላል:: ይሁንና አጎቴ ለካሳሁን እቺን ወቀሳ ጣል አርጎልኛልና መልዕክቱን እስቲ ባንተ በኩል ትድረሰው:: ካሳሁን በአሰልጣኝነት ጊዜው ተጫዋቾቹን ከሚገባ በላይ ከማቅረቡ የተነሳ እነሱ ድራፍት ሲጠጡ አብረዋቸው ተቀምጦ ይታይ ነበር በተለይ የወጣቱን ቡድን ሲያሰለጥን የአንዱን ተጫዋች ገርል ፍሬንድ ቀምቷል ይባላል:: አደራህን ክቡራን ያለፈ ነገር አንስቼበት እንዳይበሽቅ:: (ወሬው ተራና አሉባልታ ሊሆንም ስለሚችል ማለቴ ነው)

ሌላው አዎን ! ሰሎሞን አየለ ለእርሻ ሲጫወት በጣም አድርጌ አስታውስዋለሁ:: ጥይት የሆነ ልጅ ነው አዎን የመተሐራ ልጅ ነው:: አብዶ ሲሰራ ልዩ ችሎታ የነበረው ልጅ ነው:: ዋው! ተንክዩ ጎራዴው ስላስታወስከው:: የአዲስ አበባ ልጅ ያልሆኑ በቀጥታ ለብሄራዊ ቡድን ለመሰለፍ ተጽዕኖ ስለነበረባቸው ይመስለኛል ሰሎሞን አየለ ለወጣት ቡድን እንኳ ለመሰለፍ ብዙ ጊዜ የፈጀበት ይመስለኛል:: ለማንኛውም ሰሎሞን አሜሪካን አገርመጥቶ ተምሮ ሰክሰስፉል ስለሆነ ባለበት መልካሙን ሁሉ እመኝለታለታለሁ::

አገሬን ወክለውና ማሊያዋን ለብሰው ባንዲራችንን እንዲውለበለብ ያስደረጉ ብሄራዊ መዝሙሯን የዘመሩ ሁሉ ሰላምና ጤና እንዲሁም ረጂሙን ዕድሜ ሁሉ እመኝላችኋለሁ:: ባላችሁበት ሁሉ የኢትዮጵያ አምላክ ይጠብቃችሁ:: ወታደሩ ደሙን አፈሰሰ እናንተ ደግሞ ለተጠራችሁበት ግዴታ ላባችሁን አፍስሳችኋልና!!
ከትህትና ጋር
ማይኮል_ም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 302
Joined: Fri Dec 10, 2004 5:51 am
Location: 102 Gerjji ave Addis Ababa

Postby ክቡራን » Thu Jun 23, 2011 6:50 pm

ማይክል _ም እንደጻፈው
ካሳሁን በአሰልጣኝነት ጊዜው ተጫዋቾቹን ከሚገባ በላይ ከማቅረቡ የተነሳ እነሱ ድራፍት ሲጠጡ አብረዋቸው ተቀምጦ ይታይ ነበር በተለይ የወጣቱን ቡድን ሲያሰለጥን የአንዱን ተጫዋች ገርል ፍሬንድ ቀምቷል ይባላል :: አደራህን ክቡራን ያለፈ ነገር አንስቼበት እንዳይበሽቅ :: (ወሬው ተራና አሉባልታ ሊሆንም ስለሚችል ማለቴ ነው )


ሰላም ወንድሜ ማይክል ስለ መልካም አስተያየትህ ምስጋናዬ ይደርስህ:: ጊዜ አልበቃ ብሎ እንጂ እነ ካሳሁንና ጔደኞቹ ቡዙ ትዝታዎችና ወጎች አሉአቸው:: የማገኘውን በተቻለኝ ለማካፈል እሞክራለሁ:: ከሰለሞን ሉቾ ጋርም እየተነጋገርን ነው:: ለሁለታችንም አመቺ ሲሆን ቃለ ምልልስ እንደምናደርግ ነግሮኛል:: እግረ መንገዳችሁን ስለ ሰለሞን ሉቾ ( ስለሞን መኮንን) ጎራዴው አጠር ያለ የአርብ መልክ ያለው ይመስላል ብሎታል .. :D ማወቅ የምትፈለጉትን ብታስቀምጡልኝ በውይይት መልክ ልናነሳው እንችላለን:: ሌላው ማይክል ያልከው ስለ ካሳሁን ከተጫዋቾች ጋር አብሮ ድራፍት ያነሳል እንደውም ካንዱ ልጅ ጔደኛ ጋር ግኑኝነት መስርቶ ነበር ያልከኘን ነገር እኔ አልጠይቅም:: :D ጌታዬ.. ሰውየው አሁንም ፈረጣማ ነው ደሞ ኴስ መስዬው በግራ እግሩ ይለጋኝ እንዴ...? እኔ እነደሆነ እዚህ ተመልሸ መምጣት እፈልጋለሁ...ባይሆን ሌሎች ጥያቄዎች ካሉህ ይልቅ ወዲህ በላቸው:: 8)
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7963
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ክቡራን » Sun Jul 03, 2011 11:40 pm

ሰላም የዚች ቤት ወዳጆች:: እስካሁን ያልተወያየንባቸው ነገሮች ከምላቸው ውስጥ የካሳሁን ከጥጥ ወጥቶ ወደ ሳንጆርጅ መግባትን የተመለከተ ነበር:: ጉዳዩ እንዲህ ነው:: ሉኡል ዳዊት የጊዮርጊስ ቡድን ጨዋታውን ጨርሶ ወደ መልበሻ ክፍል ሲገባ ይደርሳል:: ልኡሉ የቡድኑ የበላይ ጠባቂ ስለነበር ወደ መልበሻ ክፍላቸው ሲገባ ካሳሁንን በር ላይ ያገኘዋል:: የጥጥ ተጫዋች የነበረው ካሳሁን ምን ሊያደርግ እዚህ መጣ ብሎ በመገረም ልኡሉ ካሳሁንን በጥያቄ ያፋጥጠዋል:: ካሳሁንም ከጥጥ ክለብ ወደ ጊዮርጊስ ክለብ መምጣት እንደሚፈልግ ግን ክለቡ ( የጥጥ ክለብ ) መልቀቂያ ሊሰጠው እንዳልፈለገ ይነግረዋል;: ለካሳሁን የእግር ኴስ ጨዋታ አድናቆት ያለው ልዑል ዳዊት በማግስቱ ከንጉሴ ሮባ ጋር በመሆን ወደ ድሬዳዋ በመሄድ የካሳሁንን መልቀቂያ ያስጨርሳሉ:: በተደረገውም ስምምነት አስራትም ጥጥን ለቆ ወደ ጊዮርጊስ የመምጣት እቅድ ስለነበረው ሁለቱንም ባንዴ ማጣት ለቡድኑ እንደ ሎስ ስለሚሆን አስራት አንድ አመት ቆይቶ እንዲመጣ ስምምነት ተደረጎ ካሳሁን ግን በዛው አመት ወደ ጊዮርጊስ ቡድን እንዲዛወር ተደርጎአል:: ለካሳሁን ወደ ጥጥ መዛወር የልዑል ዳዊት ቀጥተኛ እጅና እርዳታ እንደነበረበት ካሳሁን ያስረዳል::
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7963
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Previous

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests