ቡና ሻምፕዮን ሆነ!!!! ቡና ገበያ አደገኛ.....

ስፖርት - Sport related topics

ቡና ሻምፕዮን ሆነ!!!! ቡና ገበያ አደገኛ.....

Postby MEYESAW 01 » Mon Jun 27, 2011 4:39 pm

ከሰዕታት በፊት በተጠናቀቀው የ2003 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ለመጀመሪያ ጊዜ ሻምፕዮን ሆኖዋል;; ቡና ለዚህ ታሪካዊ ድል የበቃው በፍጻሜው ጨዋታ ሙገርን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ነው!! ብራቮ ቡና!!!
MEYESAW 01
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 128
Joined: Wed Jun 16, 2010 1:29 am

Re: ቡና ሻምፕዮን ሆነ!!!! ቡና ገበያ አደገኛ.....

Postby ተድላ ሀይሉ » Mon Jun 27, 2011 9:02 pm

MEYESAW 01 wrote:ከሰዕታት በፊት በተጠናቀቀው የ2003 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ለመጀመሪያ ጊዜ ሻምፕዮን ሆኖዋል;; ቡና ለዚህ ታሪካዊ ድል የበቃው በፍጻሜው ጨዋታ ሙገርን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ነው!! ብራቮ ቡና!!!

ሰላም MEYESAW:-

የኢትዮጵያ ቡና ክለብ አሠልጣኝ : በሙሉ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ተጨዋቾች (የተገዛ ተጫዋች ያልተቀላቀላቸው) ሥር የሠደደውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን አድሏዊ አሠራር : የዳኞችን ተንኮል እና በአገሪቱ የሠፈነውን የተዛባ ፖለቲካ አሸንፈው ዋንጫ በማንሣታቸው ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ጥሩ የተስፋ ብርሃን ፈንጥቀዋል :: እኔ በወንዶቹ እግር ኳስ ያን ያህል የሚያስጨፍር እና የሚያስደስት ታሪክ ባይኖረንም የቡና ተጨዋቾች ከረዥም ጊዜ ትግል በኋላ በዙሩ ውድድር ዋንጫ ማንሣታቸው ለኢትዮጵያ ሕዝብም የጥሩ ዕድል ምልክቶች ናቸው ብዬ አምናለሁ ::

ብራቮ ቡና

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ


Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests