ስለ አሜሪካን ፉት ቦል እናውራ ! GO GREEN BAY !

ስፖርት - Sport related topics

Postby MR_PRESIDENT » Fri Jan 13, 2012 3:19 pm

ሰላም እዚህ ቤት - ጩጉዳው ማብራሪያህ ሁሉ በጣም አሪፍ ነው እውነትም ጥሩ ኢንስትራክተር ይወጣሀል : ስለ 2 ነጥቧ ጥሩ አስቀምጠሀል ግን ትንሽ ማረሚያ ቢጤ አለችኝ:: ኳርተር ባኩ ብቻ ሳይሆን ማንኛውም አጥቂ ተጫዋች ከ1 ያርድ ጀርባ ከታፈነ ወይም ጋማውን :lol: ከተባለ ሰፍቲ ይባላል:: በተረፈ ይመቻችሁ - ጌታው እኔም የኮልት ደጋፊ ነኝ ግን ዘንድሮ ማኒ ታሞ ባይጫወት እንዲህ እንዋረድ እንዴ ጃል ? :shock: ሱፐር ቦሉን ዘንድሮ የሚበላ ግን ኒው ኦርሌንስ ሳይንትስ ይመስለኛል በጣም ያሰጋሉ:: አትላንታ ፋልኮኖቹን እወዳቸው ነበር ባልተጠበቀ ሁኔታ በጃየንትስ ተባረሩ::
MR_PRESIDENT
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 36
Joined: Mon Mar 28, 2005 12:48 am
Location: National palace

Postby ማይኮል_ም » Fri Jan 13, 2012 6:16 pm

<ከእግዚአብሄር ጋር ሁሉም ይቻላል> የሚለውን የዮሐንስ 3:16 ጥቅስ ብላክ አይ ላይ አርጎ የሚጫወተው ቲም ቲቦ የአሜሪካንን ፉትቦል ወረት እያናወጠ ነው::

የአሜሪካን ፉት ቦል የማያርፍ ሀበሻ ሁሉ እዚህ መጥተው ከነ ጩጉዳ ጌታና ዮኒ እኔም የምችለውን ሁሉ አስረዳለሁ ጉጉልም አርጋችሁ እባካችሁ ይህን ቀልብ የሚስብ ልዩ ጨዋታ ግን ለማያውቀው የሞኝ ግብግብ የሚመስል እንድትረዱ ጥሪ አረጋለሁ:: ሲረዱት በጣም ያረካል:: ጥሎማለፉንና ሱፐር ቦል ተመልከቱ በተለይ በጥሎ ማለፍ ጊዜ የሚታዩ ኮሜርሻሎቹ ውድና አዝናኝ ናቸው
ከትህትና ጋር
ማይኮል_ም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 302
Joined: Fri Dec 10, 2004 5:51 am
Location: 102 Gerjji ave Addis Ababa

Postby ሰምጥጤ » Sun Jan 15, 2012 3:25 am

49ርስስስስስስስስስ ቤይቢ!!!

የዛሬውን ከሴይንቶች ጋ እንዴት አያቹት?

እስኪ እኔ አዲስ የፉትቦል ክትብ ስለሆንኩ ጥልቅ ማብራርያቹን ጀባ በሉን
ሰምጥጤ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 14
Joined: Sat Dec 03, 2011 1:10 am

Postby ጩጉዳ » Sun Jan 15, 2012 7:27 am

የሚገርም ጨዋታ ነበር ሰምጥጤ ዋው! ብለው ዝም ነው:: ቁጭ ብድግ ያስደርጋል:: 49ርሶች ዲፌንስ ብቻ ሳይሆን ኦፌንስ ኳሊቲ እንዳላቸው አስመስከሩ:: ጥሩ ጨዋታ ነበር:: እስካሁን ካየኋቸው ጥሎ ማለፍ ሁሉ ይሄኛው ከዘንድሮ ይሻላል:: ይመጣጠናሉም:: የኒው ኢንግላንድና የቲቦ ቡድን ጨዋታ የማይመጣጠኑ ካሌጅ ቡድን ጌም ይመስል ነበር:: ሼም ኦን ብሮንኮ ሼም ኦን ቲም ቲቦ:: ታም ብረዲ ባንድ ጨዋታ 2 ሪኮርድ ሰብሯል:: 6 ተች ዳውን ፓስ በመወርወሩና ከእረፍት በፊት 5 ፓስ ለታች ዳውን በመወርወሩ .... ቡፍፍፍፍ
መታገስንና መቻልን የመሰለ ብቀላ የለም ::
ጩጉዳ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1267
Joined: Mon Jan 31, 2005 6:40 am
Location: Studio City, Wilson Republic

Postby yoni_love » Mon Jan 16, 2012 12:06 am

ሰላም ፈላስ! በዛሬው ጧት ጌም ባልቲሞር ሪቨንስ ሂውስተን ተክሳኖችን 20 ለ 13 አሸንፈው ከፕለይ ኦፍ አሰናብተዋቸዋል::
በ2ኛው ጨዋታ አሁኑ እየተደረገ ባለው የኔዎቹን ግሪን ቤዮችን ትንሽ እያሰጋቸው ነው:: ጃየንቶች በጨዋታ በልጠዋል ኦልሬዲ በመጀመሪያ ሀፍ ብቻ 3 ተርን ኦቨር ፈጥረዋል ስኮራቸው 10 : 10 ቢሆኑም ሌላ ጃየንቶች ኳሱን በመያዝ ያጠቁበት ሰዐትና ኦፌንሲቭ ፓስ ኦልሞስት ከእኛ ደብል በልጠዋል:: ለማንኛውም ራጀርስና የግሪን ቤይ አጥቂዎች ተአምር አሁንም እንጠብቃለንና መልካም እሑድ ምሽት ጌም! ኮምኩሙ!
Small world
yoni_love
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 130
Joined: Sun Jan 02, 2005 9:37 pm
Location: Baltimore

Postby ጎተራ » Mon Jan 16, 2012 2:08 am

ሰላም ሰላም አይገባም አይገባም ቁጭ በሉ:: የሰጣችሁኝን ተምሮ በሚገባ ተጠቅሜ ቢራዬን እየለጋው ጌሙን እየኮመኮምኩኝ ነው:: ፉት ቦል እንደዚህ ኢንትረስቲንግ አይመስለኝም ነበር:: እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቅ ለመሆኑ ፕሌይ ኦፍ ላይ ሲሆኑ ስንት ጨዋታ ነው የምያደርጉት አንድ ጌም ነው ወይስ እንደ ባስኬት ሰባት ግዜ ይሄዳሉ? ለማንኛውም መልካም ጌም ዮኒ ኮንግራ ክለብህ አሸንፏልሀል:: ጎተራ ባጫ ከድድ ማስጫ::
Some people are alive only, because it's illegal to kill them.
ጎተራ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 102
Joined: Mon Nov 28, 2011 2:58 am

Postby ሰምጥጤ » Mon Jan 16, 2012 5:01 am

ጎቴው እኔም እንዳንቺው ተከትቤልች የመጬ እየከለምኩ ነበር... ፕሌዮፍ እንደሚመስለን 1 ጨዋታ ብቻ ነው:: ሜዳው የሚወሰነው በ ረጉላር ሲዝን ደረጃው ከተጋታሚው የበለጠ ከነበረ ያ ባለጥሩ ደረጃው ቡድን ፕሌዮፉን በሜዳው ይጫወታል:: ከተሳሳትኩ አርሙኝ::
እኔ የምልሽ ጎቴው አንቺ በ ሱዳን ጣብያ ነው እንዴ የምትከልሚው? :lol: ...የዮኒ ቲም ግሪንቤይ ፓከርስ ዛሬ ባስደንጋጩ እኮ ነው የተሸነፈው:: አምና ሱፐርቦውል የበሉ ሀይለኛ ቲም ነው:: በነበር ቀረ እንጂ:: ኮሜንታተሮቹ ሲናገሩ እንደተረዳሁት ኮርተርባካቸው ሮጀርስ የሚሉት ችሎታው ላቅ ያለ ሳይሆን አይቀርም ዛሬ ግን ብዙ አልሆነለትም::

ጃንቶች ጥሩ ዲፈንስ አላቸው ደጋግመው ተርኖቨር ሲያደርጉ :lol: ምናምን ነበር ስልሽ!! ሰሞኑን የተማርኳቸው ሊንጎ ናቸው...ተርኖቨር, ሳክ ማድረግ, ፈምብል ምናምን ...ቅቅቅቅቅ

ዮኒ አይዞን እንግዲ


እኔ 49ረስ ነኝ:: አትሊስት በሜዳችን ነው ጃንቶችን የምንገጥማቸው::

እስኪ እነ ጨጉዳ ሚስተር ፕሬዝደንት እና ዮኒ የምጠይቃቹ ሆም ጌም ምን ያህል አድቫንቴጅ አለው? ለምሳሌ ሳከር ላይ ሆም ጌም በጣም ትልቅ አድቫንቴጅ አለው::
49ርሶች ከ ጃይንትስ ጋ ቻንሳቸው እንዴት ነው?
ሰምጥጤ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 14
Joined: Sat Dec 03, 2011 1:10 am

Postby ጎተራ » Mon Jan 16, 2012 6:02 am

ሰምጤ አማን ነው:: :lol: :lol: የኔ ነገር አንዱን ነጫጭባ ጎረቤቴን ጠርቼው ጃይንት ጃይንት እያለ ሲጫህብኝ ዮኒን የነሱ ደጋፊ አድርጌዋለው:: ስለ መልሱ አመሰግናለው አበሻቹ ፉት ቦል ብዙ ስለማይደላቸው አብሮህ የሚከልም አታገኝም:: ለማንኛውም ይመጭ ነብሴ:: ጎተራ ባጫ ከድድ ማስጫ::
Some people are alive only, because it's illegal to kill them.
ጎተራ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 102
Joined: Mon Nov 28, 2011 2:58 am

Postby ጩጉዳ » Mon Jan 16, 2012 3:43 pm

ሰላም ቤቶች > ባጫውና ሰምጥጥ መቼስ በፉት ቦሊኛ ልጥራችሁና ሩኪዎች ልበላችሁ <ሩኪ> ማለት ጀማሪ ወይም የመጀመሪያ አመት ተጫዋች ማለት ነው:: ጎተራው መልስህ ትክክል ነው:: በፉት ቦል ጥሎ ማለፍ አንዴ ብቻ ነው::

ግሪን ቤይ ኮላፕስ በማድረጉ ሻክ ያልሆነ ሰው የለም:: ዮኒ ሶሪ እንግዲህ ራሊያችሁ ባጭሩ ተቀጨ:: አጥቂዎቹ ሁሉ ፈዘዋል 7 ኳስ መያዝ የሚገባቸውን ጥለዋል:: ብዙ ተርን ኦቨር አርገዋል:: እኔ እንደሚመስለኝ የግሪን ቤይ ኦፌንሲቭ ኮርድነትሩ የ21 ዐመት ልጅ በድንገት በመሞቱ ሰውዬው ልጁን በቀበረ ማግሥት ነው ወደ ጌሙ የመጣው እሱም ዲስትራክት አርጎአል የሚል ጥርጣሬ ቢኖርም ግሪን ቤይ የጨዋታ ስታይሉ ፓሲንግ ወይም ሮጀርስ በጣም ጎበዝ ስለሆነ ከርቀት እየወረረ በሚያቀብለው ነው እስካሁንም ሳክሰስ ያደረጉት ጃየንቶች በደንብ ተዘጋጅተውበታል:: ይህን ጨዋታ የሚዘጋጁት ቪዲዮ እያዩ በቴክኖሎጂ ስለሆነ ተሳክቶላቸዋል : ሮጀርስ ማለት ግን ጉደኛ ልጅ ነው:: እንዳዛ ስቲፍ በሆነ ዲፌንስም 66 ያርድ ራሽ አርጎአል:: እነ ሰምጥጤ እንዲህ እንዲ ማለት ለሌሎቹ ኳስዋን መስጠት ሲገባው ራሱ ይዞ በመፈርጠጥ 5 ጊዜ 1ስት ዳውን አግኝቷል::

በተረፈ ባጫው ሆም ፊልድ አድቫንቴጅ ላልከኝ ምንም ጥርጥር የለውም በሬጉላር ሲዝን ጊዜ በየዲቪዥናቸው ባስመዘበቡት ውጤት መሰረትና ኦቨር ኦል ውጤት ይሆናል:: በመጨረሻ በጥሎማለፉ እስከ 6 ሲድ ይደለዳሉ:: ለምሳሌ 1ስት ሲድ የሚባለው ዘንድሮ ግሪን ቤይ ነው በሬጉላር ሲዝን አንዴ ብቻ የተሸነፈ ቡድ ስለሆነ ሪኮርድ ከሁሉም ላቅ ስለሚል - - ከየዲቪዚኖች ውስጥ አንዳንድ ትርፍ ስላት ስለሚኖር ደከም ብሎ ግን እንደ ምንም ተፍጨርጭሮ ጥሩ ውጥጠ ለሚያመጣ ቲም ደግሞ ዋይልድ ካርድ ዊነር ተብሎ ጥሎ ማለፍ ይሰጠዋል:: ግን በዋናው ጥሎ ማለፍ ጊዜ ለዋይልድ ካርድ ቡድኖች አንዳንድ ተጨማሪ ግጥሚያ ይሰጣቸዋል ::

በአሜሪካን ፉትቦል ዲቪዢኖቹ 2 ናቸው አሜሪካን ፉት ቦል ቻምፕዩን ሺፕ ወይም AFC እና ናሺናል ፉት ቦል ቻምዩን ሺፕ NFC ናቸው:: በዲቪዚዮኖቹ ውስጥ ኮንፈራንስ የሚባሉ አሉ:: ዌስት ኢስት ሳውዝና ኖርዝ ኮንፈራንስ በሚል ይታውቃሉ:: ባጠቃላይ 32 ቲሞች አሉ::

እናማ ወደ ጎተራው ጥያቄ ልምጣና ሆም ፊልድ አድቫንቴጅ በኃይለኛው ነው ያለው:: ተመልካቹ ስታዲየም ውስጥ ቢራና አልኮል ስለሚፈቀድለት ፖርክ ቻፕ ባርብኪዩ ደራርቦ በእሱ ላይ ይሄን ምለር ላይት ሲጎዘጉዝ የሚጮሄው ጩሄት ይታይህ :: የተመልካቹን ጩሄት ጥቅም ሚስጢር ልንገርህ: ተቃራኒው ቡድን ኦፌንስ በተለይ 3rd ላይ ከሆኑ ኳርተር ባኩ ከራሱ ሪሰቨሮች ጋር ሲመካከር ወይም ሀሳብ እንዳይለዋወጥ ጩሄቱ እንዳይሰማ የደርግና ቻንሱን አሳልፈው ይሰጡታል:: አስተዋላችሁ ከሆነ ተጭዋቾቹ እጃቸውን ከፍ ዝቅ እያረጉ ተለምካቹ እንዲጮህ ሲግናል ሲሰጡ ይታያሉ::

በነገራችን ላይ ኳርተር ባኩ በፉት ቦል ጨዋታ ከራሱ አሰልጣኛና ኦፌንሲቭ ኮርድነር ጋር መገናኛ ሬድዮ አለው:: በሄልሜቱ ውስጥ ጆሮው ላይ ማደመጫ ኢር ፎን ያለው ሲሆን በቀኝ እጁ ላይ ደግሞ እንደ ሰዐት ያለ ነገር የሚነካካበት ነገር መገናኛውን ተርን ኦን ኦፍ ማድረጊያ አለው:: ለዛሬ በዚሁ ላብቃ ጥያቄዎችን ለመቀበል ዝግጁ ነኝ::
መታገስንና መቻልን የመሰለ ብቀላ የለም ::
ጩጉዳ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1267
Joined: Mon Jan 31, 2005 6:40 am
Location: Studio City, Wilson Republic

Postby ዘለቃሽ » Thu Jan 19, 2012 8:32 am

ወቼው ጉድ አሉ ጎረቤታችን ከዚህ የአሜሪካኖች ፉት የትም ማምለጥ አይቻልም:: ዕድሜ አይለይም ጾታ አይለይም አንካሳውን አይለይም ሁሉም ያብዳል:: እኔን የሚገርመኝ ብዞዎቹ ለስቴቶቻቸው ወይም ለሚኖሩበት ከተማ ቡድን ሳይሆን የሚደግፉት ምንም ለማይገናኝ ሩቅ ላለው ቡድን እየደገፉ ይሞታሉ:: ሥራ ቦታ አለቆቼ ከተራ ሰራተኞች ጋር ክርክራቸው እስከ መኮራረፍ ይደርሳሉ:: በተለይ በተለይ ጎረቤቶቻችንን እያሳበደ ነው ከግራ በኩል ያለ ሰውዬ የፒትስበርግ (ባልሳሳት ስሙይ ስቲለርስ መሰለኝ) ቢጫ ባንዲራ ድራይቭ ዌይ ላይ አርጎ ማዶ ያለው ሰወዬ ደግሞ የሬደርስ ባንዲራ በመኪናው ላይ አርጎ ሲያልፉ ይገለማመጣሉ:: :shock: እኔ የምላችሁ ለመሆኑ በዚህ አሜሪካኖች ፉትቦል ስንት አሰልጣኞችና ዳኞች አሉ ? ዥንጉርጉር የለበሱ ዳኞች ሜዳ ውስጥ ይርመሰመሳሉ ከውጭ ደግሞ ኤር ፎንንና መነጋገሪያ የደቀኑ ሁሉም ስሪየስ ሆነው ትዕዛዝ የሚሰጡ የሚመስሉ ለመሆኑ አሰልጣኞች መሆናቸው ነው? እስቲ ጩጉዳዬ ወይም ጌታ .... ዮኒ .... ወይም የገባቹ ሌሎቻችሁ እርዱኝ ልጄ ተንኪዩ ....
ዘለቃሽ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 52
Joined: Sat Feb 12, 2005 1:31 am
Location: ከአዲሲቷ ኢየሩሳሌም

Postby yoni_love » Fri Jan 20, 2012 3:27 pm

ሰላም እዚ ቤት! እነ ኮርማው ጌታ ጩጉዳ ባጫውና ሌሎቻችሁም : - ዘለቃሽ ስለተሳትፎሽ ላመሰግንሽ እወዳለሁ:: የሥራ ቦታሽና የጎረቤቶችሽ ነገር አስቆኛል:: አሜሪካኖች ለጨዋታውም ብቻ ፓሺኔኽት ሆነው ግን አይምስለሽ ከዚያ ጀርባ ያለው ምን እንደሆነ ታውቂያለሽ ? መኒ ነው አዎን ገንዘባቸውን እያዋጡ ይቆምራሉ:: ፋንታሲ ፉትቦል ይባላል:: ወደፊት ደግሞ ስለዚህ እንማራለን:: ለጥያቄሽ ደግሞ : ዘለቃሽ ለሁሉም የፉት ቦል ክፍል ማለትም ለአጥቂዎች : ለተከላካዮች : ኮርዲነተሮች አሏቸው:: ለኳርተር ባኩ ግን ፐርሰናል ኮች አለው:: ዳኞች ደግሞ ባልሳሳት 3 ናቸው ሁለት ሳይድ ዳኞች ሲሆኑ አንዱ ዋናውና መሀል ሆኖ በጨዋታ መሀል የሚሮጥ ነው:: ከዚያ በተረፈ የሰዐት ዳኛ ታዛቢና ያርድ አጀስተሮች የሚባሉ አሉ::
Small world
yoni_love
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 130
Joined: Sun Jan 02, 2005 9:37 pm
Location: Baltimore

Postby ገንዳው » Sat Jan 21, 2012 4:15 am

ዌል ዌል ..... ግሪቤይም ከለመ ኒው ኦርሌንም ባፍ ጢሙ አሁን ካሉት ቲሞች ማን የሚበላ ይመስላችኋል ጃየንትና ኒው ኢንግላንድ ለሱፐር ቦል ይቀርባሉ ፔትሪየትስ ይበላል ቤቢ !!
ገንዳው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 334
Joined: Thu Dec 23, 2004 3:46 am
Location: united states

Postby ጌታ » Tue Jan 24, 2012 3:27 pm

ገንዳው wrote:ዌል ዌል ..... ግሪቤይም ከለመ ኒው ኦርሌንም ባፍ ጢሙ አሁን ካሉት ቲሞች ማን የሚበላ ይመስላችኋል ጃየንትና ኒው ኢንግላንድ ለሱፐር ቦል ይቀርባሉ ፔትሪየትስ ይበላል ቤቢ !!


ገንዳው ግምትህ እስካሁን ጥሩ ይዞልሃል:: ስለ እሁዱ ጨዋታ ከነዮኒ ጩጉዳ እና ባጠቃላይ ከቤቱ ጥሩ ዘገባ ጠብቄ ነበር:: አሁን የሬቨንስ አሸናነፍ አያሳዝንም? ተሸነፍ ያለው ቡድን ያለቀለት ተችዳውን ተፍተው ይባስ ብለው ደግሞ በረኛ የሌለውን ባዶ ፊልድ ጎል ስተው ደጋፊዎቻቸውን አሳዘኑ::

ጃይንቶች ደግሞ በሬድስኪንስ ሁለቴ እንዳልተገረፉ አሁን ጠንካራ ቡድኖችን መገነዳደስ ስራዬ ብለው ይዘውታል:: ፔትሪየትስ የተሻሉ እንደሆኑ ባምንም ጃይንቶች ባለፉት ሦስት ጨዋታዎች ያደረጉትን ከደገሙ ዋንጫው የነሱ ነው:: Go Giants!!!
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ጩጉዳ » Thu Jan 26, 2012 7:24 pm

ሰላም እዚህ ቤቶች !
ጌታው እንዳለው እስካሁን ገንዳው ግምቱ ግቡን እየመታ ነው:: ትላልቅ ቡድኖች መገንደስ ብቻ ሳይሆን ባፍ ጢማቸው አሉ እንጂ እኔን እስካሁን የሚገርመኝ የግሪን ቤይና የ ኒው ኦርሌይን መንጠባጠብ ነው::

49ርሶችን የምር ሆነው አግኝቻእዋለሁ:: አስደናቂ ጨዋታ በጣም አርኪ ጨዋታ አሳይተዋል:: የዕድል ጉሳይ ሆኖ ወጡ እንጂ ይህ አመት የእነሱ መሆን ነበረበት::

ዌል .... ጌታው ሪቨንስ በመጀመሪያ ደረጃ እዚያ በመድረሳቸው ዕድለኞች ናቸው:: አይታችሁ ከሆነ ጨዋታቸው በ40- ዐመቱ ሬይ ሉዊስ - አይረን መን (በበነገራችን ላይ ይህ ዕድሜ በፉት ቦል ዐለም በጣም ሼባ ይባላል) የሚመራ ስለሆነ ባመዛኙ ዲፌንሲቭ ናቸው እንጂ ኳርተር ባካቸው ፍላኮ በጣም ሎው ሬት ያለው ነው:: ይሁን እንጂ ከፒትርየስ ጋር ያደረጉት ትንቅንቅ አስገራሚ ነበር::

በሌላ በኩል ሱፐር ቦሉን ማን ይበላል ለሚለው - ፐትርትየስ ኳርተር ባካቸው ታም ብሬዲ እንደ ድሮ ተረጋግተው እንዲወረዉር የሚያደርገው ተከላካይ በዙሪያው የሉትም:: በመሆኑም በዚህ ዐመት ብቻ 32 ጊዜ ሳክ ተደርጓል 6 ጊዜ ፋምበል አርጓል ይህ የሚያሳየው ታም ብሬዲ እንደፈለገው ኳሷን ለማቀበል በዚህ ዐመት የተሳነው መሆኑን ያሳያል:: ስለሆነም በጣም በፈጣኖቹ ጃየንት አጥቂዎች እንደሚታፈን ይጠበቃል:: ባንጻሩ ጃየንትስ የተሟላና የተረጋጋ ቲም ይመስለኛል:: ግን ብዙ ጊዜ ሱፐር ቦል የተለየ ዝግጅትና ጥንቃቄ የሚጠይቅ ስለሆነ ካለፈ ታሪክ ጋር ማመሳሰል አስቸጋሪ ነው:: ሁሉም በጨዋታው ጊዜ የሚያደርጉት የአሰልጣኞቻቸው ፈጣን ውሳኔና ስትራቴጂ ነው:: ለማንኛውም እነኚ ሁለቱ ቲሞች ከጢቂት አመታት በፊት ወሳኝ ጥሎ ማለፍ ላይ ገጥመው ዐመቱን ሙሉ ሳይሸነፍ የቆየውን ኒው ኢንግላንድን ጃየንቶች ከሱፐር ቦል ፈንግለዋቸዋል:: በመሆኑም ኒው-ኢንግላንድ በብቀላ መንፈስ ስለሚጫወት የሚበላ ይመስለኛል:: በተረፈ ጨዋታውን በHD ዘና ብላችሁ ተከታተሉ - ቢራ የምትከልሙ ከሆነ ሚለር ላይት ምረጡ - ፒሳ የምትወዱ ከሆነ ላርጅ ፒሳ ከ ዶሚኖስ ፒሳ አዛችሁ በቀዝቃዛ ሚለር ላይት አወራርዱ ካልሆነም አሪፍ ቡና በጀበና አስፈልታችሁ ቤቱ ጨስጨስ እያለ በክርስቶል ክሊር ሳራውንዲንግ ሲስተም እየጎመመ በሚወጣው ድምጽ በኮሜርሻሎች ተዝናኑ ! ግን ጨዋታው ይበልጥ እንዲጥማችሁ ሚስቶቻችሁ / ገርሎቻችሁ ጨዋታውን እንዲያርፉ አስተምሩ -- ጓደኞቻችሁን ጋብዙ --- ይመቻችሁ :lol:
መታገስንና መቻልን የመሰለ ብቀላ የለም ::
ጩጉዳ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1267
Joined: Mon Jan 31, 2005 6:40 am
Location: Studio City, Wilson Republic

Postby ጌታ » Thu Jan 26, 2012 7:43 pm

ጩጉዳ wrote:በተረፈ ጨዋታውን በHD ዘና ብላችሁ ተከታተሉ - ቢራ የምትከልሙ ከሆነ ሚለር ላይት ምረጡ - ፒሳ የምትወዱ ከሆነ ላርጅ ፒሳ ከ ዶሚኖስ ፒሳ አዛችሁ በቀዝቃዛ ሚለር ላይት አወራርዱ ካልሆነም አሪፍ ቡና በጀበና አስፈልታችሁ ቤቱ ጨስጨስ እያለ በክርስቶል ክሊር ሳራውንዲንግ ሲስተም እየጎመመ በሚወጣው ድምጽ በኮሜርሻሎች ተዝናኑ ! ግን ጨዋታው ይበልጥ እንዲጥማችሁ ሚስቶቻችሁ / ገርሎቻችሁ ጨዋታውን እንዲያርፉ አስተምሩ -- ጓደኞቻችሁን ጋብዙ --- ይመቻችሁ :lol:


ጩጌ

ሚለር ላይት ቀምሼምማ'ቅ አይመስለኝም:: ላንተ ብዬ ልገዛው ነበር የፒዛ ምርጫህ እንድጠራጠርህ አደረገኝ:: ዳሚኖስ ፒዛ ለልጆቼ የመጨረሻ ምርጫ ነው:: እስቲ ለዘንድሮው ሱፐር ቦል Papa John'sን ሞክር
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

PreviousNext

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest