ሀይሌ ገብረ ስላሴ ግን

ስፖርት - Sport related topics

ሀይሌ ገብረ ስላሴ ግን

Postby የተሞናሞነው » Fri Mar 02, 2012 12:07 pm

ቢበቃው ምናለ? አሁንስ አንድ ቀን ልቡ ፈንድቶ ጉድ ሆኖ እኛንም ጉድ እንዳያደርገን እየፈራሁ መጣሁ:: እንዴው የብዙ ሪከርዶች ባለቤት ቢሆንምና ለኛም ኩራት ለሱም ዝናና ሀብት ቢያመጣለትም ያሸነፈባቸውን ውድድሮች ስመለከት በሙሉ ተሰቃይቶ ነው የሚጨርሰውና ሰላሜን ነው የሚነሳው :lol: መሰረት ደፋርም እንደዚያው....ስቅይይይት.... እኔንም አብራ አሰቃይታ ነው የምትጨርሰው... :lol: ባሏ እንኳን ጭንቀቷን አላይም በማለት ይመስላል አንዴ ሲጠየቅ እሷ ትልቅ ውድድር ላይ ለማሸነፍ እንዲያ መከራ ስታይ ቤተ ክርስቲያን ጸሎት እያደረግሁ ነበር ሲል ሰምቸዋለሁ...አንዱ ለዳቦ ይጸልያል እሱ ደሞ እባክህ እንድታሸንፍ ርዳልኝ የጀመርኩትን ፎቅ መጨረሻ ሚሊዮን ብር አምጣልኝ እያለ... :lol: ከምር....ፊታቸው በጭንቀት ሳይሸማቀቅ እኛንም ሳያስጨንቁ ዘና ብለው እንዳማረባቸው ከሚያሸንፉት ቀነኒሳና ጥሩነሽ ናቸው:: አቤት ጥሩየንማ ስወዳ......ት የኔ ጠይም አይናማና ኮልታፋ :)

ሀይሌ ግን አሁንም ለንደን ላይ እሮጣለሁ አለ? ወይ ጉድ...ብቻ ልቡ እንዳታመልጠው ፈራሁለት :roll:
የተሞናሞነው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1129
Joined: Wed May 11, 2011 5:39 pm

Postby ጩጉዳ » Sun Mar 04, 2012 6:01 pm

ሀሀሀ :lol: :lol: :lol: ኃይሊቲ ለማሸነፍ አይደለም የምትሮጠው መች ሞኝ ሆነችና በስሎው ሞሺን ሳብ ሳብ እያረገች መሮጥ ከጀመረች ቆየች:: የፈረንጅ ትሪክ በሚገባ ገብቷታል:: የእሷ በሩጫ ላይ መገኘት ብቻ $$$ ነው አባ ! ብሪቱ - መኒ - ዶላሯ ትናገራለች::

ጋዜጣዊ መግለጫ በመስጠቱ የተለያዩ ምልክቶች እየተደገፈ ፎቶ በመነሳቱና ስፖርታዊ ተቋሞችን በመጎብኘቱና ንግግር በማድረጉ ብቻ በመቶ ሺ የሚቆጠር $$ ያሸክሙታል:: ኦፊሻሊ የሚያፍሰው ማስታወቂያ $$ ሳይቆጠር ማለቴ ነው:: እንዴት ሆነ የምትል ከሆነ ኃይሌ ማለት ከ25 በላይ የዐለም ሪኮርድ የሰበረ : በቅጽል ስሙ የጎዳናው ንጉሥ በሚል መታወቁ ብቻ በቂ ነው:: እንዲሁም በዐለም ላይ ካሉትም ካለፉትም ሁሉ ሲደመር ከ20 ድንቅ አትሌቶች አንዱ መባሉ ደግሞ የ$$ መሺን ያረገዋል:: ይህን ጩባ ዝና ካልተንቀሳቀሰበት ሚስተር $$$ እግር አውጥቶ ቤቱ አይመጣም:: እልሀለሁ ልቢትም በጣም ብልጥ በሆነ ሰው ውስጥ ተሸጉጣ ስለምትገኝ ይበልጥ ይመቻታል አትፈነዳም አይዞን ! :D
መታገስንና መቻልን የመሰለ ብቀላ የለም ::
ጩጉዳ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1267
Joined: Mon Jan 31, 2005 6:40 am
Location: Studio City, Wilson Republic


Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest