by ተድላ ሀይሉ » Tue Jan 22, 2013 3:55 am
ሰላም ለእግር ኳስ ስፖርት አፍቃሪዎች:-
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾች 'ከ31 ዓመታት በኋላ' ለአፍሪቃ ዋንጫ የፍፃሜ ውድድር የመጡ አይመስሉም:: ከመሐል ሜዳ ጀምሮ ወደ ተቃራኒ ጎል በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ጥሩ ይንቀሣቀሣሉ:: ይህ ትልቅ መሻሻል ነው:: ስለተሣተው ሬጎሪ ወይም ስለባከኑ የጎል ዕድሎች ብዙ ማክበድ አያስፈልግም:: ምክንያቱም ተቀባብለው ለጎል የሚሞክሩ አጥቂዎች ከሌሉ መጀመሪያውኑም የሚሣት ጎል የለምና::
ተከታዩ ተጋጣሚያችን ቡርኪና ፋሶ ነው:: ከዚህ ምድብ እንደ ቡርኪና ፋሶ የሚከብደን ቡድን አይኖርም:: ምክንያት:- ከዚህ በፊት የአፍሪቃን ዋንጫ አሸንፎ የማያውቅ : ቢሸነፍም ምንም የማያጣ : ነገር ግን እያሸነፈ ሄዶ ለዋንጫ ከቀረበ ታሪክ የሚሠራ ቡድን ነውና ተጨዋቾቹ ምንም ዓይነት ጭንቀት አይኖርባቸውም:: ስለዚህ በመጪው አርብ የእኛ ቡድን ከቡርኪና ፋሶ ጋር ቢያንስ አቻ እንኳን ከወጣ ናይጄሪያን በአንድ ወይም በሁለት ጎል ልዩነት አሸንፎ ለሩብ ፍፃሜ እንደሚያልፍ አልጠራጠርም::
ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::