ከእግር ኳስ ዓለም-ስፖርት ለፓስፖርት ኤርትራ ስታይል

ስፖርት - Sport related topics

ከእግር ኳስ ዓለም-ስፖርት ለፓስፖርት ኤርትራ ስታይል

Postby ተድላ ሀይሉ » Wed Jun 06, 2012 7:21 am

ሰላም የእግር ኳስ ስፖርት አፍቃሪዎች :-


***********************************************

ይህ ዓምድ ስለ እግር ኳስ ስፖርት የሚዘገብበት ነው::

************************************************በሚመጣው አርብ ሰኔ 1 ቀን 14ኛው የአውሮፓ የእግር ኳስ ሻምፒዮና በፖላንድና ኡክራይን የጋራ አዘጋጅነት በይፋ ይከፈታል :: በዚህ ውድድር አንድ አዲስ ክስተት እናያለን :- ከኢትዮጵያዊ አባት እና የቼክ ዜጋ ከሆነች እናት የተወለደው ቴዎድሮስ (ቲዮዶር) ገብረሥላሤ የተባለው የ24 ዓመት ወጣት የትውልድ አገሩን ቼክ ሪፑብሊክን ወክሎ በተከላካይ መሥመር ይሠለፋል :: ይህ ወጣት በአገሩ በቼክ ሪፑብሊክ ዘንድሮ ሻምፒዮን የሆነው የስሎቫን ሊበርቤክ ቡድን ፕሮፌሽናል ተጫዋች ሲሆን ተከላካይ ቢሆንም አልፎ አልፎ ለክለቡ ወሣኝ ጎሎችን ያስቆጥራል :: ለምሣሌ በሚከተለው ፊልም እንደሚታየው ዘንድሮ በቼክ ሻምፒዮና መጋቢት ወር ውስጥ ቡድኑ በምላዳ ምሎስላቭ እስከ 91ኛው ደቂቃ 1 ለ 0 እየተመራ እያለ በ92ኛው ደቂቃ ለቡድኑ ማንሠራራትና በደቂቃ ልዩነት ውጤቱ 2 ለ 1 እንዲጠናቀቅ ምክንያት የሆነችዋን የመጀመሪያዋን ጎል ሲያስቆጥር ታያላችሁ ::

ምንጭ:- Published on Mar 11, 2012 by fcviktoriaTV. Slovan Liberec 2 - 1 FK Mladá Boleslav 90+2. 90+3. football turnover.

ስለቴዎድሮስ በአብዛኛው የተጻፈው በቼክ ቋንቋ ስለሆነ ትርጉሙን ማቅረብ ባልችልም በአመዛኙ አድናቆት የተሞላው እንደሆነ ከምሥሎቹ መገንዘብ አያዳግትም ::
**********************************
ጋሼ ፓኑ :-

እግር ኳስ ብትወደም ባትወድም እባክህን አንዳንድ ዜናዎችን እየተረጎምክ ፍንጭ ስጠን ::
*****************************************************

ለመሆኑ ኢትዮጵያውያን የእግር ኳስ ተጨዋቾች ከዚህ ወጣት ምን ይማራሉ? ዋርከኞች እስኪ ኃሣባችሁን አካፍሉን::

ተድላ
Last edited by ተድላ ሀይሉ on Mon Dec 03, 2012 6:42 pm, edited 8 times in total.
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Fri Jun 08, 2012 9:42 pm

ሰላም የእግር ኳስ አፍቃሪዎች :-

ቴዎድሮስ ገብረሥላሤ ዛሬ ለአውሮፓ ዋንጫ ሻምፒዮና ለቼክ ሪፑብሊክ በ2 ቁጥር ቦታ ተሠልፎ ሲጫወት አየነው :: በአጠቃላይ የኳስ አያያዙ በራስ መተማመን ያለው ተጫዋች እንደሆነ ያስታውቃል :: በእርግጥ የአገሩ የቼክ ቡድን በሩሲያ 4 ለ 1 ቢሸነፍም እርሱ በግሉ ሦሥቴ ለጎል ሞክሯል :: የአጨዋወት ባህርይው እንደ ተከላካይ ሣይሆን እንደ ተደራቢ አጥቂ ነው :: ማክሠኞ ከግሪክ ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ በድጋሚ እናየዋለን ብዬ እገምታለሁ ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Sun Jun 10, 2012 8:51 pm

ሰላም የእግር ኳስ አፍቃሪዎች :-

አርብ ዕለት በአውሮፓ ዋንጫ የመክፈቻ ውድድር የቼክ ሪፑብሊክ ቡድን ከሩሲያ ቡድን ጋር ሲጫወቱ አንዳንድ ዘረኛ የሩሲያ ደጋፊዎች ቴዎድሮስን 'በዝንጀሮ የዑዑታ ድምፅ' ሲዘልፉ እንደነበረ ይታወሣል :: በዚያ እና የሩሲያ ደጋፊዎች በስቴድየሙ ባሣዩት ያልተገባ ድርጊቶች (አስተናጋጆችን ሲደበድቡ በካሜራ ተቀርፀዋል) የአውሮፓ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር በሩሲያ ላይ ከእግር ኳስ ተመልካቾች በሚጠበቅ ሥነ-ምግባር ረገድ ምርመራ ጀምሯል :: እንግዲህ ውሣኔው ምን እንደሚሆን አብረን እናያለን ::

ምንጭ:- David Hills, FootyTube, Sun Jun 19, 2012. Euro 2012: Uefa hits Russia with disciplinary probe over fans' attack.

Uefa opened disciplinary proceedings against Russia on Saturday night over the behaviour of fans during their match against the Czech Republic.

The decision followed reports that the Czech's only black player, Theo Gebre Selassie, was the target of monkey chants during the game in Wroclaw, with fans also seen displaying far-right "Russian Empire" flags. In a separate incident, four stewards needed hospital treatment after being attacked by a group of Russian fans inside the stadium.

Uefa – under pressure over their slow response to the racist abuse aimed at Holland's players during a training session in Krakow on Wednesday – said they would hold an immediate investigation.

"Having looked at the security reports and available images, disciplinary proceedings have been opened against the Football Union of Russia," said a Uefa statement. "This relates to the improper conduct of its supporters, the setting-off and throwing of fireworks and the display of illicit banners. The control and disciplinary body will review the case on Wednesday June 13.

"In addition, regarding reports of alleged abuse directed at Czech Republic players from Russia fans, Uefa is investigating this further and is working with Football Against Racism in Europe to collect more evidence."

The chief executive of FARE, Piara Power, had earlier confirmed that one of the group's match observers had reported "fleeting" racist abuse aimed at Selassie from a "small section of the crowd", though added: "It may not be easy to pull together evidence for a case to be brought."

The violence, footage of which appeared online, included one steward being punched to the ground and then kicked before the fans walked away. Police said the fans appeared to have become aggressive when stewards tried to detain a man who had thrown firecrackers towards the pitch. No arrests were made, but footage of the incident is being reviewed.

A Russia team spokesman, Nikolai Komarov, said the federation declined to comment on the details of the reported incidents, but added: "The federation has many fans. You don't have control over them all."

ይህ ምን ያሣየናል? ኮሚኒስቶች ወደ ናዚነት ለመቀየር የተመቻቸ የኅሊና ዝግጅት ያላቸው መሆኑን ነው ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ኢትዮማን » Tue Jun 12, 2012 5:18 pm

Czech 2 - Greece 0.... So far.... Theo just made a great assist for the second goal for czech, he looks a great prospect. He may get a chance to play for big teams.
ኢትዮማን
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 247
Joined: Wed Sep 06, 2006 6:00 pm

Postby ተድላ ሀይሉ » Tue Jun 12, 2012 7:05 pm

ኢትዮማን wrote:Czech 2 - Greece 0.... So far.... Theo just made a great assist for the second goal for czech, he looks a great prospect. He may get a chance to play for big teams.

የቢቢሲ የስፖርት ጋዜጠኞች ሊያጣጥሏቸው እንደሞከሩት ሣይሆን የቼክ ሪፑብሊክ ተጨዋቾች ባለፈው ከሩሲያ ጋር ካደረጉት ጨዋታቸው በተሻለ ተንቀሣቅሠዋል :: እንዲያውም ዛሬ የገጠማቸው የግሪክ ቡድን የድሮውን የምዕራብ ጀርመን ቡድንን አጨዋወት የሚከተሉ ጠንካራ ቡድን ናቸው :: ሆኖም የቼኩ በረኛ ፒተር ቼክ ባልጠበቀው መንገድ ኳሷን ለመያዝ ሲል በተፈጠረ ሁኔታ ግሪኮች በሥህተት ጎል ማስቆጠራቸው እንጂ ውጤቱ 2 ለ 0 ሊያልቅ ይችል ነበር ::

ዛሬም ቴዎድሮስ ጥሩ ተንቀሣቅሧል - 14 ቁጥሩ ፒላዥ በ6ኛው ደቂቃ ላስቆጠራት ለሁለተኛዋ ጎል አቀባይ እርሱ ነበር :: ምናልባትም በምዕራብ አውሮፓ ክለቦች አሠልጣኖች ዐይን ውስጥ ሊገባ የሚችል ችሎታ ያለው ልጅ ስለሆነ እንዳልከውም በትልልቅ ክለቦች ውስጥ ገብቶ ሊጫወት የሚችል ነው: ይቅናው ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ፓን ሪዚኮ » Wed Jun 13, 2012 5:47 am

ሰላም ቤቶች ...ትናንት ማታ የቼክ ሪፐብሊክን እና የግሪክን ሸዋታ ያየሁት ቢራ ቤት ሆኜ ነበር ....ቴዎዶር ገብረ ስላሴ"Valecnik" ጦረኛውተብሏል::እንግዲህ እኔ ጀብደኛእሱ ደግሞ ጦረኛትብለን በታላቁ ቢራ ቤት መሰየማችንን ስገልጽ ታላቅ ኩራትና ክብር ይሰማኛል ::
ፓኑ አባ ፈርዳ ከፕራግ ቢራ ቤት
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ተድላ ሀይሉ » Wed Jun 13, 2012 6:00 am

ሰላም የእግር ኳስ ስፖርት አፍቃሪዎች :-

ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 5/ 2004 ዓ.ም. ቼክ ሪፑብሊክ ከግሪክ ባደረጉት ጨዋታ ቴዎድሮስ ገብረሥላሤ ለሁለተኛው የቼክ ጎል እንዴት እንዳቀበለ ከሚከተለው አጭር ፊልም ተመልከቱ :-
ምንጭ:- Euro UEFA, Published on Jun 12, 2012. Greece vs. Czech Republic (1-2) Euro 2012 Highlights!


ዋና ዋና የጨዋታውን ሂደት ለመከታተል ደግሞ :-
ምንጭ:- Posted by shmooot, Tue Jun 12,2012. Greece v Czech Republic.

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Sun Jun 17, 2012 1:18 am

ፓን ሪዚኮ wrote:ሰላም ቤቶች ...ትናንት ማታ የቼክ ሪፐብሊክን እና የግሪክን ሸዋታ ያየሁት ቢራ ቤት ሆኜ ነበር ....ቴዎዶር ገብረ ስላሴ"Valecnik" ጦረኛውተብሏል::እንግዲህ እኔ ጀብደኛእሱ ደግሞ ጦረኛትብለን በታላቁ ቢራ ቤት መሰየማችንን ስገልጽ ታላቅ ኩራትና ክብር ይሰማኛል ::
ፓኑ አባ ፈርዳ ከፕራግ ቢራ ቤት

ፓኑ :-

እንኳን ደስ ያለህ : :D :D :D እንኳን ደስ ያለን :!: :!: :!: የዛሬ ቀን ለኢትዮጵያውያን የድርብ ድል ቀን ነው :: ወደ ዶክተር ጁሊዬስ ኔሬሬ አገር ያቀኑት አናብሥት እህቶቻችን እዚያም 1 ለ 0 አሸንፈው ለአፍሪቃ ዋንጫ አልፈዋል :: ያ ያልታወቀ ገጣሚ ምን ነበር ያለው ????

"መቅደላ አፋፉ ላይ ጩኸት በረከተ :
የሴቱን አላውቅም : ወንድ አንድ ሰው ሞተ"

እኛ ደግሞ ይህንን ሥንኝ እንገለብጥና :-

'የኢትዮጵያ ወንዶች ሱሪ ካወለቁ :
ሠላሣ ዓመት ደፍነው : በፍርሃት ሲደቁ :
ባልታሠበ ዘመን : ባልተጠበቅነው ሥፍራ
በሴት አናብሥቱ ሥማችን ተጠራ ::"

ምንጭ:- ethiofootball.com : ቅዳሜ ሰኔ 9 ቀን 2004 ዓ.ም.:: የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፉን አረጋገጠ::

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ብርቱካን ገ/ክርስቶስ በ65ደቂቃ ባስቆጠረችው ግብ የታንዛኒያ አቻውን 1-0 በማሸነፍ ኢኳቶሪያል ጊኒ ለምታዘጋጀው ስምንተኛ የአፍሪካ ማለፉን አረጋገጠ፡፡

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን 60ሺ ተመልካች በሚይዘው በስታዲየም ፍፁም የጨዋታ የበላይነት ነው ሉሲዎች ጨዋታውን በድል የማጠናቀቅ የቻሉት፡፡ ቡድኑ በታንዛኒያ ባስመዘገበው ድል ኢትዮጵያ ቡድን ለሁለተኛ ጊዜ ለአፍሪካ ዋጫቻ እንዲያልፍ አድርገዋል፡፡
ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ፓን ሪዚኮ » Sun Jun 17, 2012 7:25 am

ወዳጄ ወንድሜ እንኳን አብሮ ደስ ያለን :: በነገራችን ላይ የቼክ ሪፐብሊክ ማለፍ እና የቴዎ ግ/ስላሴ በዚህ ቡድን ውስጥ መሰለፍ የኢትዮጲያን ብሄራዊ ቡድን ብቻ ሳይሆን ዛሬ የፕርሜር ሊግ ደጋፊ የሆነውን ትውልድ ከተመልካችነት ወደ ተጫዋችነት መስመር ያስገባዋል የሚል የጸና እምነት አለኝ ::
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby የተሞናሞነው » Sun Jun 17, 2012 6:25 pm

ሰላም እነ ተድላና ፓኑ አባ ፈርዳ ቀምቃሚው :)

የዘሬን ብተው ያንዘርዝረኝ ነውና እኔም ለቴዎድሮስና ለቼካዊያን ለፓኑም መልካም ምኞቴን ስገልጽ በደስታ ነው:: እኔ ደግሞ ኮመንታተሩ 'ገብረ ስላሴ' እያለ ሲናገር 'ቴዎዶር'ን ርሰቼ ሀይሌን እየመሰለኝ :lol: ይህ '_ስላሴ 'የሚባል ስም መታወቂያችን ሆነ እኮ....ሀይለ ስላሴ...ሀይለ ገብረ ስላሴ አሁን ደግሞ ቴዎዶር ገብረ ስላሴ....በአለም ዘንድ መታወቂያችን ሆኗል....መለስ በሚል ስም እንደተዋረድን ሁሉ :lol:
የተሞናሞነው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1129
Joined: Wed May 11, 2011 5:39 pm

Postby እምቢ ለሀገር » Mon Jun 18, 2012 2:18 pm

ፓኑ አባ ፈርዳ ጀብደኛው ሀበሻ.. ቸኮች ቴዎድሮስ ገ/ስላሴን ጦረኛው ብለውታል አለን:: ፓኑ ወንዳጃችን ያንተ ውለታ አለበን::አንተ ባትኖር የሀበሻ ጀብዱን ማን ጀባ ይለን ነበር :?: ፓኑአችን ክፉ አይንካህ :!:
እኔ ደግሞ ቴዎድሮስ ገ/ስላሴን መይሳው ብየዋለሁ :!: ድል ለቼክ ብሄራዊ ቡድን :!:

ትንሽ ስጋ እንደ መርፌ ትወጋ :D :D

FREE ESKENDIR NEGA,ANDUALEM ARAGE AND ALL POLITICAL PRISONERS!!!


እምቢተኛው :!:
የፓኑ ወንድም :!:
ETHIOPIA ETHIOPIA ETHIOPIA
እምቢ ለሀገር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 262
Joined: Mon Feb 13, 2012 5:08 pm

Postby ተድላ ሀይሉ » Thu Jun 21, 2012 2:02 am

ሰላም የእግር ኳስ ስፖርት አፍቃሪዎች :-

የፓኑ አባ-ፈርዳ አገር ልጅ ከቼክ ተጨዋቾች መካከል በዚህ ሣምንት ዋና የመነጋገሪያ አጀንዳ ለመሆን በቅቷል: ምክንያቶችም ሁለት ናቸው
የቼክ ቡድን ነገ ተሣክቶለት ፖርቱጋልን ከውድድር ውጪ ካደረገ የቴዲም ኮከብ አብራ ትነሣለች ::

መልካም ዕድል ለቼክ ብሔራዊ ቡድን ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ገልብጤ » Thu Jun 21, 2012 8:36 pm

አምባቢወቻጭ እንደምን ዋላቹ ከዜና ፋይል ጋር

ገልብጤ ሞረቴው ነኝ

አርእስተ ዜና ...
የቼኩ እንተርናሽናል ቴወዶር ገብረስላሴ በአርሴናል እየተፈለገ ነው

http://www.caughtoffside.com/2012/06/21 ... -selassie/
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1676
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ተድላ ሀይሉ » Fri Jun 22, 2012 2:23 am

ሰላም የእግር ኳስ ስፖርት አፍቃሪዎች :-

ዛሬ ለቴዲ የተሠጠው ኃላፊነት እጅግ ከባድ ነበር :- በዓለማችን ላይ በአሁኑ ወቅት ምርጥ የክንፍ አጥቂ ከሚባሉት ቀዳሚውን ኮከብ ክሪስቲያኖ ሮናልዶን እንዲቆጣጠር መደረጉ :: ሮናልዶ አሣቻ ጊዜ ጠብቆ ወሣኟን ጎል በ78ኛው ደቂቃ ኳሷን በጭንቅላቱ ገጭቶ አስቆጥሯል :: ቴዲም ሮናልዶ ከአቅሙ በላይ ስለሆነበት ማቆም አልቻለም :: ቢሆንም ቴዎድሮስን በሚቀጥሉት የውድድር ዘመኖች በታላላቅ የአውሮፓ አገሮች የክለቦች ሻምፒዮና ላይ ማዬታችንን እንቀጥላለን የሚል ዕምነት አለኝ ::

የዚህ ወጣት ጥረትና ሥኬት ለኢትዮጵያውያን ከፊል-አማተር : ከፊል-ፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ተጨዋቾች ትልቅ ትምህርት ይሠጣል ብዬ አምናለሁ :: ራሣቸውን ለሙያ ሥነ-ምግባር ታማኝ ካደረጉና ለአሠልጣኝ ምክር ታዛዥ ከሆኑ በእግር ኳስ ስፖርት ከቴዲ በኋላ ብዙ ኢትዮጵያውያንን በዓለም በታላላቅ የስፖርት ክለቦች ፕሮፌሽናል ተጨዋቾች ሆነው ማዬት ብርቅ አይሆንም ::

ስለዚህ ለኢትዮጵያውያን የእግር ኳስ ተጨዋቾች :-ታዋቂ ፕሮፈሽናል ስፖርተኛ መሆን ይቻላል !!!

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Fri Jun 22, 2012 10:22 pm

ሰላም የእግር ኳስ ስፖርት አፍቃሪዎች :-

ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት ቴዎድሮስ ገብረሥላሤን በቬርደር ብሬመን ማልያ እናየዋለን ::

ምንጭ:- FIFA(Source: AFP), Friday 22 June 2012. Werder sign Gebre Selassie.

Czech Republic defender Theodor Gebre Selassie has left Slovan Liberec for Bundesliga side Werder Bremen, signing a four-year deal with the Bundesliga side.

The transfer of the 25-year-old Gebre Selassie, who made history as the first black player in the Czech national team last year, will be sealed after a medical at Werder.

Gebre Selassie, who has been capped 14 times, has been one of the most impressive performers at UEFA EURO 2012 for the Czechs, who bowed out in Thursday's quarter-final, losing 1-0 to Portugal.

"We are pleased that we were able to convince Theodor to come here despite a multitude of offers," Werder's general manager Klaus Allofs told the club's official website.

"He is a very talented right-back who has made a good impression at the European Championship."

Gebre Selassie said: "The decision to join Werder Bremen is definitely the right one.

"Werder are a club with a lot of stability and tradition, they always set their goals very high. I want to follow up a successful season with Liberec by playing well for Bremen."


ቴዲ በቬርደር ብሬመን በሚኖረው ቆይታ መልካሙን ሁሉ እመኝለታለሁ ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Next

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests