Euro2012 ፖላንድ/ዩክሬን

ስፖርት - Sport related topics

Euro2012 ፖላንድ/ዩክሬን

Postby ቲኪ_ታካ » Thu Jun 07, 2012 5:52 pm

እንደምናቹ የእግርኳስ አፍቃርያን ስሜ ቲኪ-ታካ እባላለሁ:: የማቀርበውም ጽሁፍ እንደሚከተለው ይሆናል

ከአመታዊው የአውሮፓ ክለቦች ቻምፒየንስ ሊግ በመቀጠል ምርጥ ውድድር እንደሆነ ብዙዎች የሚስማሙበት የአውሮፓ ሀገሮች ዋንጫ ውድድር እነሆ አራት አመቱን ጠብቆ ሊጀመር አንድ ቀን ቀርቶታል:: ፖላንድና ኡክራይንም መሰናዶዋቸውን አጠናቀው የሚቀጥሉት ሶስት ሳምንታት እንግዶቻቸውን በሚገባ አስተናግደው ካለምንም እንከን ለመፈጸምና ከምንግዜውም በላይ ደማቅ ውድድር ሆኖ እንዲያልፍ ያቅማቸውን ጥረት እንደሚያረጉ አሳውቀዋል:: ሁለቱ የምስራቅ አውሮፓ ሀገራት በተለይ በዩክሬን ውስጥ ስር የሰደደ ዘረኝነት እንዳለ የተዘገበ ሲሆን የእንግሊዝ እግርኳስ ማህበርም ደጋፊዎቹን በግልጽ ከማስጠንቀቁም በላይ የአርሰናሎቹ ቲዎ ዋልኮት እና ኦክስዴል ቻምበርሌይን ቤተሰቦች ዘረኝነት ስድቦችና ትንኮሳን በመሸሽ ወደውድድሩ ስፍራ እንደማይጓዙ አሳውቀዋል:: ይህ የዘረኝነት ጉዳይ እንኳን ዘንቦበት ድሮም ጤዛ የሆነው ነውጠኛው ማሪዮ ባላቶሊንም አንድ ሰው በጥቁርነቴ ቢዘልፈኝ እገለዋለው ከማለቱም በላይ ጨዋታ አቋርጦ እንደሚወጣም አስረግጦ ተናግሯል:: ይህ ሁሉ ጉዳይ በስተመጨረሻ የውድድሩ ባለቤት የሆነው ዩዌፋን በፕሬዝደንቱ ሚሸል ፕላቲኒ አማካይነት የማስተባበያና የማስጠንቀቅያ ጋዜጣሚ መግለጫ ሰቷል:: የቀድሞው የፈረንሳይ ኮከብ አማካይ ተጭዋች ሲናገር የዘረኝነት ችግር የፖላንድ ወይንም የ ዩክሬይን ብቻ ሳይሆን የአለማቀፍ ችግር እንደሆነ እንዲሁም የእግርኳስ ብቻ ችግር ሳይሆን የማህበረሰቡ አጠቃላይ ችግር እንደሆነና ከዛ ለይተን ማየት የለብንም ነገር ግን በጨዋታ መሀል ይህ ጉዳይ ከተከሰተ ጨዋታዎች እንደሚቋረጡ ነገር ግን ተጭዋቾች ተሰደብን ብለው በራሳቸው ፍቃድ ሜዳ ለቀው ቢወጡ የቢጫ ማስጠንቀቅያ ካርድ እንደሚሰጣቸው አስረድቷል::

የዘረኝነት ጣጣ እንግሊዝንም እየናጣት እንዳለ መገናኛ ብዙሀን ሰሞኑን እያራገቡት ያለ ሌላው ዜና ነው:: አዲሱ አሰልጣኝ ሮይ ሆጅሰን ጆን ቴሪን መርጠው ሪዮ ፈርዲናንድን ግን ከቡድኑ ውጭ ሲያረጉት እንዳሉት ለ ከእግርኳሱ ጋ በተያያዘ ምክንያት ሳይሆን የሁለቱ ተከላካዮች ባንድ ቡድን ውስጥ መካተት ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ እንደሚያመዝን በማመናቸው ይመስላል:: እንደሚታወቀው ጆን ቴሪ ባለቀው የፕሪምየርሊግ ሲዝን ቡድኑ ቼልሲ ከ ዌስትብሮሚች አልቢዮን ካ በሚጋጠምበት ወቅት የ ሪዮ ፈርዲናንድ ውነድም የሆነውን አንቷን ፈርዲናንድን ጥቁርነቱን የሚያንቋሽሽ ስድብ ሲሰድበው በቲቪ ካሜራ ተይዞ መላው አለም የተመለከተው ከመሆኑም በላይ ከዚ ጋር የተያያዘው ክስ በይደር ቆይቶ ለጁላይ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ተይዞለታል:: እናም የሁለቱ አንድ ላይ እቡድን ካምፕ ውስት መኖር አሉታዊ ውጥረት እንደሚያስከትል በማመናቸው ይመስላል ሮይ ሆጅሰን አንዱን መርጠው አንዱን የተዉት:: በሚገርም ሁኔታ ግን ጋሪ ካሂል ቅዳሜ እለት በወዳጅነት ጨዋታ አገጩን ሁእልት ቦታ ተሰንጥቆ ከውድድሩ ውጭ ሲሆን የመሀል ተከላካይ እንደመሆኑ መጠን በተተኪነት አሰልጣኙ ልምድ ያለውን ሪዮን ይጠሩታል ሲባል አንድ ፍሬ የሆነውን የቀኝ ተከላካይ የሊቨርፑሉን ኬሊን ጠርተው ብዙዎችን አስገርመዋል:: እንግሊዞች ሚድያውና ህዝቡም ጭምር በሚገርም ሁኔታ እግርኳሳቸው/ውድድር ላይ ከማተኮር ይልቅ ከሜዳ ውጭ የሚከሰቱ እነ እገሌ የሚባሉ ተጭዋቾች ሚስቶቻቸውን ይዘው ሳውዛፍሪካ መጡ የመሳሰሉ ፍሬ አልባ ወሬዎች ላይ ኢነርጅያቸውን በማጥፋት ምንግዜም ባጭሩ ሲሰናከሉ ይታያል:: ገና ኳስ ሀ ብለው ከመታታቸው አስቀድሞ ከውድድር የወጡበትን ምክንያት ምን ይሁን በሚለው ላይ ቀድመው ሲጨናነቁ እና የቡድኑን ትክክለኛ ድክመት ሸፋፍነው በራሳቸው ተኮፍሰው ያልፉታል:: ይህ ጉዳይ በ1998 የደቪድ ቤካም ከ አርጀንቲና ጋር በቀይ የወጣበትን ኢንሲደንት ልክ ዋንጫውን እሱ እንዳስጣላቸው አላከውበት ልጁን 1 አመት ሙሉ በየስቴድየሙ ቁምስቅሉን ያሳዩበትን አጋጣሚ ዚነዲን ዚዳን ማታራዚን በአለም ዋንጫ ፍጻሜ 10 ደቂቃ ሲቀር በቴስታ ተማቶ የወጣበትን እና የፈረንሳይ ህዝብ ሪአክሽን ለንጽጽር ብናቀርብ የኢንግሊዝ ሚድያና ፉትቦል ደጋፊ ምን ያህል ብዥታ ውስጥ እንዳሉ መገንዘብ ይቻላል::

ግሩፖቹን እና የጨዋታ ፕሮግራሞችን ለመመልከት የ ዩዌፋን ዌብ ሳይት ሊንኩን

በነገው እለት ደግሞ ከትኩስ ዘናዎች በተጨማሪ ዋንጫውን ይበላሉ ስለሚባሉት ስፔን ጀርመን እና ኔዘርላንድ የምለው ይኖራል::

መልካም የመዝናኛ ውድድር ይሁንላቹ::
ቲኪ_ታካ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 17
Joined: Tue Jun 05, 2012 4:58 pm

Postby ገልብጤ » Thu Jun 07, 2012 6:43 pm

አሪፍ አገላለጽ እናም ወንድም ቀጥል ጥሩ ትታዘባለህ
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1680
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ባርናባስ_23 » Fri Jun 08, 2012 7:30 pm

ሰላም ታኮ1
በነገራችን ላይ ታኮ ምወደው ምግብ ነው :: የግሪክን ቡድን እንዴት አየህው?
ፖላንድን ሜዳው ላይ አሽው ነው ሚባለው
It always seems impossible until its done
ባርናባስ_23
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 305
Joined: Sun May 31, 2009 2:00 pm

Postby ባርናባስ_23 » Fri Jun 08, 2012 7:51 pm

ጉድ አይታችሁዋል ገብርስላሴ ሚባል ኢትዮፒያዊ ለቼክ ሚጫወት ሲጀመር የራሽያ ደገፊ ነበርኩ ልጁ አባቱ ኢትዮፒያዊ መሆኑን ኮሜንታተሩ ሲናገር ወዲያው ተገልብጨ ቅልጥ ያልኩ የቼክ ደጋፊ ሆኝ አረፍኩት አይ ደም ምትሀት አለው
It always seems impossible until its done
ባርናባስ_23
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 305
Joined: Sun May 31, 2009 2:00 pm

Postby ቲኪ_ታካ » Sat Jun 09, 2012 3:02 am

ቴንኪው ውድ ገልብጤ:: አንተም በውድድሩ ወቅት የታዘብከውን ማናቸውንም ነገሮች ብታካፍለን መልካም ነው::
ባርናባስ_23 በቅድምያ ስሜ የምትወደው ምግብ ታኮን የሚመለከት ሳይሆን በስፔን ባህላዊ አጨዋወት የሆነውና ባለፉት 4 አመታት በብሄራዊ ቡድኑና በ ባርሴሎና ክለብ አማካይነት አለም አቀፍ አድናቆትና እውቅና ያገኘ ጠባብ ቦታ ላይ በሚደረግ ፈጣንና አጫጭር ቅብብሎሽን መሰረት ያደረገ አጨዋወት ነው::

ወደ ዛሬው ጨዋታ ስመለስ ሁለቱም ጨዋታዎች ማራኪና ሁሉም ቡድኖች ማጥቃትን መርጠው የተጫወቱበት ሁኔታን እናገኛለን:: በተለይ ግሪክ በ ጀርመናዊው የቀድሞ አሰልጣኛቸው ኦቶ ሬሀግል ስር ለረጅም አመታት ይታወቁበት የነበረውና በ 2004 የአውሮፓ ዋንጫን ያሸነፉበትን አሰልቺ በጥብቅ መከላከል ላይ ያተኮረን ጨዋታቸውን እርግፍ አድርገው ትተው አዲሱ ፖርቹጊዝ አሰልጣኝ ፈርናንዶ ሳንቶስ ሪስክ የሚወስድ ጀብደኛ ቲምን ይዘው መቅረባቸው በተለይ ዛሬ ገና በመጀመርያው ግማሽ ተጨዋች አላግባብ ከሜዳ ተወግዶባቸውና በአዘጋጅ ቡድኑ እየተመሩ ባሉበት ሁኔታ ከረፍት መልስ ድፍረት በተሞላበት ውሳኔ ኦፌሲቭ ተጫዋች የሆነውን ሳልፒንዲዝን ቀይሮ በማስገባት የጨዋታውን ሂደት 180 ዲግሪ እንዲቀየር አድርገው ለኛም ለተመልካቾች ለመተንበይ አስቸጋሪ የሆነን ማራኪ ጭዋታ አስኮምኩመውናል::

ፖላንድ ከረፍት በፊት በተለይ አጥቂው ሮበርት ሎዋንዶውስኪ እና የቀኝ ተመላላሹ ፒዝቼክ ጎልተው ቢታዩም ከረፍት መልስ ግን ቡድኑ በጠቅላላ ፓራላይዝድ ሆነው ነበር የጨረሱት:: ለዚህ የግሪኮች ታክቲካዊ ለውጥ እና እንዳዘጋጅነት ካለባቸው ጫናም ሊሆን ይችላል:: በቀይ የወጣው ግብ ጠባቂው የአርሰናሉ ቼዝኒ 1 ጨዋታ ቅጣት በሆአላ በመጨረሻው የግሩፕ ጨዋታ ከራሽያ ጋ ይሰለፋል:: ከላይ የተጠቀሱት ሎዋንዶውስኪ ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ ፒዝቼክ ደሞ ወደሪያል ማድሪድ ሊዘዋወሩ እንደሆነ በሰፊው እየተዘገበ ይገኛል::

የጨዋታው ኮከብ :- የግሪኩ 14 ቁጥር ሳልፒንዲዚስ


ወደ ሁለተኛው የራሽያና ቼክ ሪፐብሊክ ጨዋታ ስናልፍ ከምንም ቀድሞ ለኛ ዜና ሊሆነን የሚገባው ኢትዮጵያዊ ደም ያለው ቴዎዶር ገበርሰላሴ የ የ ቼክ ብሄራዊ ቡድንን የወከለም ከመሆኑ በላይ በእነደዚ ታላቅ ውድድር ላይ- የአፍሪካ ዋንጫን ሳንጨምር - ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ምስራቅ አፍሪካን የወከለ የመጀመርያው ተጭዋች እንደሆነ ነው:: በትልቅ ውድድር ሀገሪቷን ወክሎ ባይካፈለም ጣልያናዊው ፋቢዮ ሌቨራኒ( እናቱ ሶማልያ) እስከ ብሄራዊ ቡድን የደረሰ የመጀመርያው ፈር ቀዳጅ ምስራቅ አፍሪካዊ ሲሆን በከለብ ደረጃ ግን ኢትዮፕያዊው ዩሱፍ ሂርሲ ለ አያክስ እና ሆላንድ ወጣት ቡድን,በቅርብ ደሞ ኬንያዊያኖቹ ማክዶናልድ ማሪጋ (ኢንተርሚላ / ፓርማ) እና ዘንድሮ ከአንደኛ ዲቭዝዮን ለወረዱት የፈረንሳዩ ኦግዜር የሚጫወተው ደኒስ ኦሊቼ በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ::
ከላይ እንደጠቀስኩት የ ቴዎዶርኝ ልዩ የሚያረገው ከአለምዋንጫ የበለጠ ከባድ ውድድር በተባለው የአውሮፓ ሀገሮች ዋንጫ ውድድር ላይ አሉ ከሚባሉት ትልቅ የ እግር ኳስ ሀገራት አንዷ ቼክ ሪፐብሊክ በቋሚ ተሰላፊነት መጫወቱ ነው:: ልጁ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ተጨዋች ኳስ ላይ ኮሞፍርተብል ሲሆን አጨዋወቱ ወደ ታዋቂው ብራዚላዊ ዳኒ አልቬዝ ወሰድ ያረገዋል:: በተለይ በሁለተኛው አጋማች አየር ላየር የሞከራት ቮሊ ነገሮችን ለመሞከር ያለው ፍቃደኝነትን እና ቴክኒካል ኳሊቲውን አሳይታናለች:: በተጨማሪም ሌላው ጠንካራ ጎኑ አደገና የትቃት ሂደቶችን የሚያቋርትበት ፍጥነቱ ነው:: የራሽያው ኮከብ አንድሬ ኣርሻቪን እግር ስር ደጋግሞ ኳሶችን ሲያስጥል ተመልክተነዋል:: ይህ ፍጥነቱና አነስ ያለው ተክለሰውነቱ ደሞ የማንቸስተር ሲቲውን ጌይል ክሊሼን ይመስላል:: እንግዲህ በተለይ ክሮስ የማድረግና ከ አጥቂ ጋ አንድ ለ አንድ ሲሆን ኳሶችን ማስጣል ላይ ጠንክሮ ከሰራ ልጁ ትልቅ ደረጃ እንደሚደርስ ምልክቶች ይታያሉ::

ወደጨዋታው ስንመለስ ራሽያ በጣም ጥሩ ቡድን ነው:: እንደተጋጣሚው ቡድን ያጨዋወት ሂደት እየቀያየሩ በሚጠቁበት ሰአት ለምሳሌ ኳስን ሲያገኙ መብረቃዊ በሆነ መልሶ ማጥቃት አልያም ደሞ ተጋጣሚ አፈግፍጎ ሲከላከል በርግጠኝነት ኳሷን ባጭር ቅብብልና በጠባብ ቦታ በማንሸራሸሸር ተጋጣሚን ያስከፍታሉ:: ለአጨዋወታቸው የሚመቹ ኳስ ጠንቅቀው የሚጫወቱ ልጆችንም ያቀፈ ቡድን ነው:: በበኩሌ የራሽያን ቡድን የዛሬ አራት አመት ካየሁት ቡድናቸው የበለጠ የተሟላ ሆኖ አግኝቼዋለው::አርሻቪን አንድን ቡድን እንዲመራና የፈለገቦት ቦታ እየሄደ እንዲጫወት ሙሉ ነጻነት ከተሰጠው ምን አይነት አደገኛ ተጭዋች መሆኑን ዛሬም አስመስክሯል:: ከሱ በላይ ግን ወጣቱ የራሽያ ፉትቦል ወርቃማ ልጅ 17 ቁጥሩ ዛጎዬቭ የእለቱ ኮከብ ነበር:: ሁለት ምርት ግቦችን በተንካራ ምቱ ከማስቆጠሩም በላይ በቡድን አጨዋወቱና ወደመሀል እየሄደ አማካዩን የሚረዳው ነገሩ ከእድሜው በላይ በሳል ተጭዋች እንደሆነ ነው ያሳየው:: የራሽያ ቡድን በውሰት ከአርሰናል ሰንት ፒትስበርግ የመጣውን አርሻቪንን ጨምሮ በጠቅላላው ከ ሀገር ውስጥ ክለቦች ነው የተመረጡት::ዛሬ ከተሰለፉት ውስጥ ሰባቱ የሴንት ፒስበርግ ተጭዋቾች ናቸው:: ይህ አመራረጥ ብዙዎች ክሪቲሳይዝ እንዲያረጉ በሩን ቢከፍትም ግን ከዚህ ቀደም ስፔንከባርሳ ሆላንዶች ከ አያክስ በርካታ ተጭዋቾችን በአሰላለፍ ውስጥ በማካተት ወጥ አቸዋወትን እና አመርቂ ውጤትን አግኝተውበታል:: እንግዲህ የራሽያም በቀጣዩ ሳምንታት ውስት የሚታይ ይሆናል:: በቼክ ሪፐብሊክ በኩል ማስተዛዘኛዋን ጎል ያገባው 14 ቁጥሩ ፒላር ረዳት ካገኘ ጥሩ ተጫዋች ይመስላል:: ከመለስተኛ ጉዳት የተመለሰው የአርሰናሉ ሮዚስኪ ብዙ ቢሞክርም እንደፈለገው ወሳኝ የሆኑ ኳሶችን ለአጥቂዎች ማቅረብ አልቻለም:: ባጠቃላይ ቼኮች በራሽያኖች ፈጣን ማፈናፈኛ የሚያሳጣ አጨዋወት ኦቨርዌልም ቢሆኑም ጥሩ ቡድን ነው ያላቸው:: ምናልባት በቀጣዩ 2 ጨዋታዎች በተለይ የተከላካይ ድክመታቸው አርመው ከቀረቡ ወደቀጥዩ ዙር የማያልፉበት ምንም ምክንያት የለም::
ቲኪ_ታካ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 17
Joined: Tue Jun 05, 2012 4:58 pm

Postby ተድላ ሀይሉ » Sat Jun 09, 2012 3:49 am

ቲኪ_ታካ wrote: ከላይ እንደጠቀስኩት የ ቴዎዶርኝ ልዩ የሚያረገው ከአለምዋንጫ የበለጠ ከባድ ውድድር በተባለው የአውሮፓ ሀገሮች ዋንጫ ውድድር ላይ አሉ ከሚባሉት ትልቅ የ እግር ኳስ ሀገራት አንዷ ቼክ ሪፐብሊክ በቋሚ ተሰላፊነት መጫወቱ ነው:: ልጁ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ተጨዋች ኳስ ላይ ኮሞፍርተብል ሲሆን አጨዋወቱ ወደ ታዋቂው ብራዚላዊ ዳኒ አልቬዝ ወሰድ ያረገዋል:: በተለይ በሁለተኛው አጋማች አየር ላየር የሞከራት ቮሊ ነገሮችን ለመሞከር ያለው ፍቃደኝነትን እና ቴክኒካል ኳሊቲውን አሳይታናለች:: በተጨማሪም ሌላው ጠንካራ ጎኑ አደገና የትቃት ሂደቶችን የሚያቋርትበት ፍጥነቱ ነው:: የራሽያው ኮከብ አንድሬ ኣርሻቪን እግር ስር ደጋግሞ ኳሶችን ሲያስጥል ተመልክተነዋል:: ይህ ፍጥነቱና አነስ ያለው ተክለሰውነቱ ደሞ የማንቸስተር ሲቲውን ጌይል ክሊሼን ይመስላል:: እንግዲህ በተለይ ክሮስ የማድረግና ከ አጥቂ ጋ አንድ ለ አንድ ሲሆን ኳሶችን ማስጣል ላይ ጠንክሮ ከሰራ ልጁ ትልቅ ደረጃ እንደሚደርስ ምልክቶች ይታያሉ::

ሰላም ቲኪ_ታካ :-

ስለ ዛሬው የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታዎች ትንታኔ የምንስማማበትም : የምንለያይባቸውም አስተየዬቶች ይኖራሉ :: ያ እንግዲህ እንደ ተመልካቹ ስለሆነ ችግር የለውም :: የእኔ ጥያቄ ቴዎድሮስን "አነስ ያለው ተክለ ሰውነቱ" ብለህ ስትገልፀው ትንሽ ግር ብሎኝ ነው :: የአንድ የእግር ኳስ ተጨዋጭ ቁመቱ ስንት ቢሆን ነው "አነስ ያለ ተክለ ሰውነት" አለው የሚባለው? የቴዎድሮስ ባዮ-መረጃ የሚከተለውን ይመስላል :-
    ቁመት: 1 ሜትር ከ81 ሤንቲ ሜትር (6 ጫማ)

    ክብደት: 70 ኪሎ ግራም (154.3 ፓውንድ)

ምንጭ:- Transfermarkt, (Last updated Fri June 8, 2012). Theodor Gebre Selassie.

በነገራችን ላይ ስለ ልጁ አጨዋወት በሠጠኸው አስተያዬት ሙሉ በሙሉ እስማማለሁ :: እንዲያውም አሠልጣኞች ለምን በተደራቢ አጥቂነት አማካይ ተጨዋች አድርገው እንደማያጫውቱት አልገባኝም :: የልጁ ዝንባሌና ችሎታ የሚመጥነው ከኋላ የመሥመር ተከላካይ ሆኖ ከመጫወት ይልቅ አማካይ ተጨዋጭ ቢሆን ነው :: ዛሬም የቼክ ሪፑብሊክ ቡድን በሩሲያ ቡድን ሙሉ በሙሉ ብልጫ የተወሠደበት በተለይ በአማካይ ሥፍራ በነበሩት ተጨዋቾች ላይ ነበር :: ስለዚህ ቴዎድሮስ ከተከላካይነት ይልቅ በአማካይ ሥፍራ ቢጫወት ኖሮ ቡድናቸው በዚያን ያህል የሠፋ የጎል ልዩነት ከመሸነፍ ሊድን ይችል ነበር ብዬ እገምታለሁ ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ቲኪ_ታካ » Sat Jun 09, 2012 7:32 pm

ጤና ይስጥልኝ ተድላ::
የቴዎዶር ተክለሰውነት አነስተኛ ስል ከሌሎች ጋ አነጻጽሬ እንጂ ደቃቃ ነው ብዬ ለማሳነስ አልነበረም:: እርግጥ ከሱ ጋር ይወራረድኩት የቀድሞው የአርሰናል ተከላካይ ጌይል ክሊሼ በ 2 ኪሎ ቴዎዶርን ይበልጠዋል:: እኛ ምስራቅ አፍሪካውያን ምንም ኪሎዋችን ሚዛን ቢደፋም muscle mass ለምሳሌ እንደሌሎቹ አይደለንም:: በአጠቃላይ ፈረንጆቹ slightly built የሚሉት አይነት ቁመና ነው ልጁ ያለው:: እና ያንን ለማለት ነው ቃሉን የተጠቀምኩት::
በዚ አጋጣሚ ዛሬ የወጡት ዜናዎች እንደሚያመለክቱት ቴዎዶር የጦጣ ጩእት በሚያሰሙ የራሽያ ደጋፊዎች ዘረኝነት ጥቃት ሰለባ እንደነበር ታውቆዋል:: እነኚህ የምስራቅ አውሮፓ ሀገራት ግን በጣም ስር የሰደደ የዘረኝነት በሽታ አለባቸው:: ባገኙት አጋታሚም ይህንን ሲያንጸባርቁ ነው የሚታየው::

ሆላንድ ባስደንጋጩ በ ዴንማርክ 1-0 ተሸንፋለች:: አጥቂዎቻቸው ብዙ እድሎችን ሲያመክኑ አምሽተዋል:: ይህ የሞት ምድብ ነው የሚሉት:: ጀርመን ከ ፖርቹጋል አሁን ሊጀርም ነው::
ቲኪ_ታካ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 17
Joined: Tue Jun 05, 2012 4:58 pm

Postby ገልብጤ » Sat Jun 09, 2012 10:00 pm

በዚ አጋጣሚ ዛሬ የወጡት ዜናዎች እንደሚያመለክቱት ቴዎዶር የጦጣ ጩእት በሚያሰሙ የራሽያ ደጋፊዎች ዘረኝነት ጥቃት ሰለባ እንደነበር


http://www.thesun.co.uk/sol/homepage/ne ... brawl.html
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1680
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ባርናባስ_23 » Sun Jun 10, 2012 12:05 pm

ሰላም ቲኪ_ታካ!
ስምህን በማሳሳቴ ይቅርታ ቸኩዬ እኮ ነው ለወሬ :D
የእግር ኳስ ጋዜጤኛ ሳትሆን እንደማትቀር ዝምብዬ ጠርጥሪያለሁ 8)
ድንቅ ለሆነው ሞያዊ ትንታኔ ባርኔጣዬን አንስቼ አመሰግናለሁ እስከፍጻሜው
እንደማታቁዋርጥ ተስፋ አደርጋለሁ :: ዛሬ ጣሊያኖች የአለም ምርጦቹን ይቛቛማሉ ትላለህ? የባላቶሊን አቛም እንዴት አየህው? መልካም እደል ለጣሊያን ቡድን እያልኩ እሰናበታለሁ :: ዛሬ ካስበሉኝ አንድ ሰላቶ መፈንከቴ ማይቀር ነው :lol: :lol:
It always seems impossible until its done
ባርናባስ_23
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 305
Joined: Sun May 31, 2009 2:00 pm

Postby ቲኪ_ታካ » Mon Jun 11, 2012 1:48 am

በርናባስ_23 ሰላም እኔ በጣም ደህና ነኝ:: ጋዜጠኛ እንኳን አይደለሁም በኳች ጨዋታ ፍቅር የተቃጠልኩ ምስኪን ኢትዮፕያዊ ነኝ:: የሶላቶው ነገር አስቆኛል:: ጣልያኖች ከ ስፔን አቻ መለያየታቸው ያንተን ብር ከመበላት አንዱን ፒዛ ነጋዴ ደሙ ደመ ከልብ ከመሆን አትርፎታልና እሰየው ነው::

ወደጨዋታው ስንመለስ ጥሩ ፉክክርና ለየት ያለ የታክቲክ አቀራረብ የታየበት ነበር:: ስፔኖች ከፊት ያሉት 6 ተጭዋቾችን ካለፊት አጥቂ በአማካይ ተጭዋች ብቻ ገብተዋል:: ፋብሪጋስን እንደ አስመሳ አጥቂ ወይንም እነሱ እንደሚሉት -ፎልስ ናይን- /ሻዶው ስትራይከር ሆኖ እንዲጫወት ያረጉት ነገርን ነው ያየነው:: ይህ አሰላለፍ ስፔኖች ያላቸውን ጠንካራ ጎን ማለትም ኳስ የሚያንሸራሽሩ በርካታ አዋቂ ተጭዋቾቻቸውን አድቫንተጅ ለመጠቀምና በይበልጥ ደግሞ ጣልያኖች አሰልጣኙ ቼዛሬ ፕራንዴሊ ሚድፊልዱን የሚያጨናንቅና ለስፔኖች መፈናፈኛ የማይሰጥ 3-5-2 አሰላለፍን እንደሚጠቀም በግልጽ በመናገሩ ያንን ለማክሸፍ የመረጡትም ዘዴ ነበር:: በኔ በኩል በጣልያኖች ኢምፕረስድ ሆኛለሁ:: ስፔኖችን በደንብ መቋቋም ብቻ ሳይሆን የራሳቸውን ኳስ ቁጥጥር ላይ ያተኮረ የማጣቃት ስልትን ነው የተከተሉት:: የሮማው ዳነኤል ደሮሲ የጨዋታው ኮከብ ነበር:: በተለይ ከረፍት በፊት በርካታ የስፔኖችን ረቂቅ ቅብብል እያነፈነፈ ሲያቋርጥና የተመጠኑ ታክሎችን ሲገባ ተስተውሏል:: ከረፍት መለስ ጥቂት የውሳኔ ስህተቶችንና ቶሬስን በቀላሉ እንዲያልፈው ያደረገውን ነገሮች በቀር በተከላካይ ቦታ ለብሄራዊ ቡድኑ ለመጀመረያ ግዜ እንደመሰለፉ እጅግ ድንቅ ፐርፎርማንስን ነው ያሳየው:: የባላቶሊ ነገር ሁሌም ካሁን ካሁን ምን ሊያረግ ነው ወይ በቀይ ሊወጣ ነው እያሉ በመሳቀቅ የሚገል ልጅ ሆኖ ነው ያገኘሁት:: አሁን ባለበት የጸባይ ጣጣ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ስለሚያመዝን እንደኔ ቢሆን ኖሮ ቤንች ላይ ነበር የማስቀምጠው:: በዛ ላይ ጎልዋን ያስቆጠረው የዩደኔዜው አጥቂ ዲናታሌ አቋሙ ብዙም የማይዋዥቅ ድንቅና አስተማማኝ አጥቂ ነው:: ለዚህም ምስክሩ ዛሬ ያስቆጠራት አሪፍ ጎል ናት:: ምናልባት እሱና አንቶኒዮ ካሳኖ አብረው ከተሰለፉ ጣልያን ፊት መስመር ላይ የበለተ አስተማማኝ ትሆናል ብዬ እገምታለሁ:: ፒርሎም እንደተለመደው ድንቅ ችሎታውን አሳይቶናል:: የሚጥላቸው ምጥን ኳሶች ሁሌም ይገርሙኛል::
ስፔን አንዱ ጋዜጠኛ እንዳለው ወጥቤት ሲበዛ ወጥ ያራል አይነት ችግር እንዳይታይባቸው እፈራለው:: ከመጠን በላይ በችሎታ የተሞላ ቲም ነው ያላቸው:; ለዚህ ቤንቹን ብቻ ማየት ይበቃል:: ቶሬስ, ሁዋን ማታ, ፈርናንዶ ሎርዬንቴ, ዣቪ ማርቲኔዝ, የሱስ ናቫስ, ሳንቲ ካርዞላ, ክላውድዮ ሬይና, ፔድሮ የመሳሰሉት ሌላ ማናቸው ብሄራዊ ቡድን ውስጥ ቋሚ ተሰላፊ የሚሆኑ ልጆች ናቸው:: የተጎዱት ዳቪድ ቪያ እና ፑዮልም አይረሱም:: በዛ ላይ ለኦሎምፒክ ቡድኑ ሲባል ያልተካተቱት ኢከር ሙናይን የማንችስተሩ በረኛ ደሄየ እና የባርሳው ቲያጎ አልካንታራ የመሳሰሉት ካሰብን ደሞ ስፔን ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ መልኩ በታላላቅ ታለንቶች እንደተሞላች ይገባናል:: የባርሳው ፔድሮ ሲናገር ለብሄራዊ ቡድን አልመረጥም ብዬ ፈርቼ ነበር ሲል ይህ ልጅ የ 2012 አለም ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ላይ በቋሚነት የተሰለፈ ሳይሆን ገና ከ ቢ ያደገ ተጭዋች ነው የሚመስለን::
እናም ዘንድሮ ስፔንን አስጥሎ ዋንጫ የሚበላ ቡድን (እሱም ምናልባት ከሆነ ነው) በውነቱ እጅግ እጅግ ጥሩ ቡድን መሆን አለበት:: ወደ ስፔን ጉዳይ ስመለስ ምናልባት አሰልጣኝ ዴልቦስኬ ዛሬ የሞከሩት ታክቲክ በባርሳ ቡድን ጋርዲዮላ ደጋግሞ ተተቅሞበት ውጤታማ ሆኖበታል በሚልና የዛ ቡድን አባላት የብሄራዊ ቡድኑንም የጀርባ አጥንት ከመሆናቸው ጋ አያይዞት ሊሆን ይችላል:: ግን የረሱት አንድ ነገር አለ:: እሱም ሊዮኔል ሜሲ ይባላል:: በባርሳ ቅድም ከላይ የተጠቀሰውን የአስመሳይ ስትራይከር ወይም false 9 ቦታ በሚገባ የሚሸፍንላቸውና 73 ጎሎችን በዛ መልኩ ያስቆጠረው ጂንየሱ ሜሲ ነው:: ባጭሩ ፋብሪጋስ በፍጹም ሜሲን ሊሆን አይችልም:: እርግጥ በሲዝኑ መጀመርያ ሰሞን ለባርሳ ፋብሪጋስ ነበር በዛ ስፍራ ተሰልፎ ጎሎችን ያገባ የነበረው ግን ሲዝኑ እየገፋ ሲመጣ ልጁ ችሎታው ከ ዛ ስፍራ ይልቅ ለአማካይነት የተፈጠረ በመሆኑ ቀስበቀስ ሊደበቅና ሊወርድ ችሎዋል:: እንግዲህ እንደ ሎርዬቴና ኔግሬዶ አይነት ጎል ማግባት እንጀራቸው የሆነ ናቹራል ስትራይከር ያላት ሀገር ለምን ልትጠቀምባቸው እንዳላሰበች ሁሉንም ግር አሰንኝቷል:: ምናልባት ከቀጣዩ ጨዋታ ጀምሮ እውነተኛ አጥቂን ሊያሰልፉም ይችሉ ይሆናል:: ይህ በ ፎልስ 9 መጫወት ነገር ትናትናም ሆላንዶች በስሱ የሞከሩት ነበር:: እንደሚታወቀው ቫን ፐርሲ አንድ ቦታ የማይረጋ ወደውስጥ ገብቶ መጫወት የሚወድ አጥቂ ነው:: ከሮበን እና አፊላይ ጋር ቦታ እየተቀያየሩ ሲጫወቱም አይተናል:: ግን ጎል እምቢ ብሎዋቸዋል:: ለዚህም ደጋፊና ታላልቅ የደች ፉትቦል ኤክስፐርቶች ቫንፐርሲን ቤንች ላይ ትተው የሻልካውን ሁንቲላር ጨዋታውን እንዲጀምር አስተያየት እየሰቱ ይገናል:: ሁንቲላር ዘንድሮ ጀርመን ሊግ ግብ ባካፋ ሲዝቅ የነበር ልጅ ነው:: ከቫን ፐርሲ ያነሰ ቴክኒካል ችሎታ ቢኖረውም ጎል ጋ ኳስ ካገኘ ደሞ አይምርም:: አንዳንድ ኳሊቲው እንደ ቫንኒስትሎይ ነው:: በተጨማሪም አማካይ ክፍሉ ከደቾች ባህል ያፈነገጠ አላግባብ ጥንቃቄ ያበዛ ሁለት ዲፌንሲቭ አማካዮችን ማሰለፉም ዮሀን ክራይፍን ጨምሮ ብዙዎች ኡኡ እያስባለ ነው:: እንደነሱ አባባል ቫንቦሜል በቂ ነው ስለዚ የቶተናውሙ ቫንደርቫርት ሊሰለፍ ግድ ይላል:: ትናትናም ሲጨንቀው አሰልጣኙ ቫንደርቫርትንም ሁንቲላርንም አስገብቶዋቸዋል:: ግን የጭንቅ ውሳኔው ምንም አልፈየደም:: ቀጣይ ጨዋታቸው ከምንግዜም ባላንጣቸው ጀርመን ጋር ይሆናል:: now, that will be a great game !!

ረጅም ጽሁፌን በትእግስት ስላነበባቹልኝ ከልቤ አመሰግናለሁኝ::
ቲኪ_ታካ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 17
Joined: Tue Jun 05, 2012 4:58 pm

Postby ተድላ ሀይሉ » Fri Jun 15, 2012 2:01 am

ሰላም የእግር ኳስ ጨዋታ አፍቃሪዎች :-

ሰላም ቲኪ_ታካ :-

ለተመልካች የፀባይ ዋንጫ የሚሸለም ቢሆን ኖሮ ሻምፒዮን የሚሆኑት የአየርላንድ ደጋፊዎች ነበሩ :: እንዴት የሚያስደስቱ ናቸው እባካችሁ :D :D :D :D :D :D :D :D :D :D ቡድናቸው 4 ለ 0 የተሸነፈ ሣይሆን እንዲያውም በተቃራኒው 11 ለ 0 ያሸነፈ ቡድን ደጋፊዎች ይመስሉ ነበር :: ከአየርላንድና እስፓኝ ጨዋታ ባልተናነሠ በጣም ያረካኝ የደጋፊዎቹ አስደሣች ድጋፍ አሠጣጥ ነበር ::
############################

ቲኪ_ታካ:-
እንዴት ይመስልሃል ... ዘንድሮም እስፓኞች ዋንጫውን ይደግሙት ይሆን :roll: :roll: :roll: :roll: :roll: :roll: እንደ አያያዛቸው አሁን ያሏቸው ተጨዋቾች ታኬታ እስኪሠቅሉ ድረስ እንኳን በዚህ የአውሮፓ ዋንጫ ይቅርና በሚወዳደሩበት የእግር ኳስ ውድድር ሁሉ ሻምፒዮን ከመሆን የሚያግዳቸውና የሚያቆማቸው ቡድን የሚገኝ አይመስልም ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ቲኪ_ታካ » Fri Jun 15, 2012 6:28 am

ጤና ይስጥልኝ ተድላ:: በሆነ ምክንያት ያለፉት ሁለት ቀን ጨዋታዎችን ተረጋግቸ ማየትም አልቻልኩም :: የጀርመን ከ ሆላንድን ራሱ ስራ ቦታ አጮልቄ ኦንላይን ድምጽ አጥፍቼ ለማየት ሞካክርያለሁ:: እንዳልከው የስፔን ቡድን እንዳያያዛቸው የውድድሩ ክሊር ፌቨሬት ናቸው:: ሶስት ውድድሮችን በተርታ ድል በማድረግ ታሪክ ሊሰሩም መንገዱን እያመቻቹ ይገኛሉ:: ትልቁ ኳሊቲያቸው ሆኖ የታዘብኩት አሮጋንስ የሚባል ነገር የለባቸውም:: ሁሉንም ቡድን እና ውድድር በትንቃቄ አክብረው ነው የሚጫወቱት ከዚ ቀደም የነበሩ ታላልቅ ቡድኖች ወይ ተጋጣሚን በመናቅ ወይም በውስጥ ሽኩቻ ራሳቸውን ጠልፈው ሲጥሉ አይተናል:: ስፔኖች በተለይ የውስጥ ፖለቲካቸው ለዘመናት አንቆ ሲያስቀራቸው እንዳልነበር አሁን ግን ተምረው እንማይነቃነቅ ታላቅ ቡድንን ገንብተዋል:: በይበልጥ እኔ የምወድላቸው ለአጨዋወት ባህላቸው እጅግ ታማኝ ናቸው:: ሁሌም ኳስ ቁጥጥርን ያማከለ የማያቋርጥ ማጥቃት!! ዛሬ ራሱ 4 ጎል አግብተው ሌላ ሊደግሙ የመነበራቸው አፒታይት ስታይ ሊደነቁ ይገባል:: እነኝን እንቁ ልጆች ደግመው ዋንጫ ቢያገኙ ደስ ይለኛል::
በተረፈ ጀርመን ጠንካራ ቲም ነው:: ግን ተከላካዩ መስመር ላይ ጥርጣሬ አለኝ:: የ ቦሩስያ ዶርትሙንዱ ማት ሁምልስ አጨዋወቱ የድሮውን ማትያዝ ሳመርን ቢያስታውሰኝም የመጀመርያው ሜጀር ውድድር በመሆኑ አንዳንድ ስህተቶችን ሲሰራና ሲዘናጋ ይስተዋላል:: ግን በጣም ኳሊቲ ያለው ኳስ የሚያቅ ተከላካይ ነው:: ፈረንሳይም እስኪ ነገ እናየዋለን:: ስፔንን ጨምሮ ማናቸውንም የሚያንበረክክ ኢንዲቪጅዋል ኳሊቲ አላቸው:: ኳስንም ተቆጣጥረው በተጋታሚ ክልል ውስጥ ጫና ፈጥረው መጫወት ላይ ያዘነብላሉ:: አጥቂም ካሪም ቤንዜማ በጨዋታ ወደዋላ እየተመለሰ በአንድ ሁለት ቅብብል መግባት የሚፈልግ መሆኑ ለሚከተሉት አጨዋወት አመቺ ይመስላል::

ደጋፍያቸው ከሆንክ ይቅርታ እንደ እንግሊዝ ቡድን ማየት ያስጠላኝ ቡድን ደሞ የለም:: ጉራና ምክንያት ብቻ የሚያበዙ ግን ኳሊቲ የሌለው ቡድን ነው:: ፕሪምየር ሊግ እድሜ ለውጭ ዜጎች ይበሉ እንጂ እንደእንግሊዞች ችሎታ ቢሆን ገና ድሮ አክትሞለት ነበር :: ገና አንድ ተጫዋች ብቅ ሲል እላይ ይሰቅሉትና ማን ይሆን ብለክ ስታይ እዚ ግባ የማይባል ተራ ነው::

አየርላንድ በደጋፊም ብዛት አንደኛ ሳይሆኑ አይቀሩም:: ብዙ ደጋፊዎች ወደ ውድድሩ ሀገር እንደተመመ ነው የተሰማው:: ከረጅም ግዜ በዋላ ካልተሳሳትኩ ከ 1994 አሜሪካ አለም ዋንጫ በዋላ ቡድኑ በሜጀር ውድድር መሳተፉ ስለሆነም ናፍቆዋቸውም ሊሆን ይችላል:: በጸባይም 10/10 ይሰጣቸዋል::

ውድድሩ እስካሁን አርክቶኛል:: ጎል ያልገባበት ጨዋታ እስካሁን የለም:: በሁሉም ጨዋታዎች ላይ ጎል ተቆጥሮዋል:: ይህ ራሱ ማጥቃት አዲሱ ፋሽን እንደሆነ ነው:: እድሜ ለ ስፔን እና ባርሴሎና ክለብ!!

እስኪ አስተያየትክን ጣል ጣል አርግልን
ቲኪ_ታካ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 17
Joined: Tue Jun 05, 2012 4:58 pm

Postby የተሞናሞነው » Fri Jun 15, 2012 12:58 pm

እኔ ምላችሁ....አንዱን በነ ማንቼ አርሴ ያበደ ጄለሴን...'እኔ ግን ለምንድን ነው እንደናንተ የኳስ ወሬ ይህን ያህል የማይስበኝ የማይጥመኝ' ስለው 'ፋራ ጎጃሜ ስለሆንህ ነው አይለኝ መሰላችሁ :roll: ይሄ ቅል ራስ...አሁን ሳስበው ግን ፋራ ሲለኝ እዚያው ላይ እንደ ኳስ አንጥሬ ማንፈራፈር ነበረብኝ :evil:

እና 'ፋራ' መሆኔን ለማሳወቅ ያህል ነው ብቅ ያልኩት :roll: ግን ይህ ሁሉ ከላይ የጻፋችሁት ያላነበብሁት ስለ ኳስ ብቻ ነው ይሆን :? ሰው ብርቱ ነው :o

ፋራው ሞንሟናው ነኝ ከጎዣም :wink:
የተሞናሞነው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1129
Joined: Wed May 11, 2011 5:39 pm

Postby ተድላ ሀይሉ » Fri Jun 15, 2012 5:36 pm

ቲኪ_ታካ wrote:ጤና ይስጥልኝ ተድላ:: በሆነ ምክንያት ያለፉት ሁለት ቀን ጨዋታዎችን ተረጋግቸ ማየትም አልቻልኩም :: የጀርመን ከ ሆላንድን ራሱ ስራ ቦታ አጮልቄ ኦንላይን ድምጽ አጥፍቼ ለማየት ሞካክርያለሁ:: እንዳልከው የስፔን ቡድን እንዳያያዛቸው የውድድሩ ክሊር ፌቨሬት ናቸው:: ሶስት ውድድሮችን በተርታ ድል በማድረግ ታሪክ ሊሰሩም መንገዱን እያመቻቹ ይገኛሉ:: ትልቁ ኳሊቲያቸው ሆኖ የታዘብኩት አሮጋንስ የሚባል ነገር የለባቸውም:: ሁሉንም ቡድን እና ውድድር በትንቃቄ አክብረው ነው የሚጫወቱት ከዚ ቀደም የነበሩ ታላልቅ ቡድኖች ወይ ተጋጣሚን በመናቅ ወይም በውስጥ ሽኩቻ ራሳቸውን ጠልፈው ሲጥሉ አይተናል:: ስፔኖች በተለይ የውስጥ ፖለቲካቸው ለዘመናት አንቆ ሲያስቀራቸው እንዳልነበር አሁን ግን ተምረው እንማይነቃነቅ ታላቅ ቡድንን ገንብተዋል:: በይበልጥ እኔ የምወድላቸው ለአጨዋወት ባህላቸው እጅግ ታማኝ ናቸው:: ሁሌም ኳስ ቁጥጥርን ያማከለ የማያቋርጥ ማጥቃት!! ዛሬ ራሱ 4 ጎል አግብተው ሌላ ሊደግሙ የመነበራቸው አፒታይት ስታይ ሊደነቁ ይገባል:: እነኝን እንቁ ልጆች ደግመው ዋንጫ ቢያገኙ ደስ ይለኛል::

የእስፓኝ ቡድን ውጤት ያለው አዲስ የአጨዋወት ሥልት ለዓለም አስተዋውቀዋል :: በአሁኑ ሰዓት የእነርሱን የአጨዋወት ሥልት በአስተማማኝ ሁኔታ የሚልቅ የለም :: በግል ደግሞ ተጨዋቾች ያላቸው የቲም-ዲሲፕሊን በጣም የሚያስደስት ነው :: ለዚያ ነው እኒህ ተጨዋቾች ታኬታ እስኪሠቅሉ ድረስ በየትኛውም ውድድር የሚቀርበውን ዋንጫ ጠቅልሎ ከመውሠድ የሚያግዳቸው የለም ያልኩት ::

ቲኪ_ታካ wrote:በተረፈ ጀርመን ጠንካራ ቲም ነው:: ግን ተከላካዩ መስመር ላይ ጥርጣሬ አለኝ:: የ ቦሩስያ ዶርትሙንዱ ማት ሁምልስ አጨዋወቱ የድሮውን ማትያዝ ሳመርን ቢያስታውሰኝም የመጀመርያው ሜጀር ውድድር በመሆኑ አንዳንድ ስህተቶችን ሲሰራና ሲዘናጋ ይስተዋላል:: ግን በጣም ኳሊቲ ያለው ኳስ የሚያቅ ተከላካይ ነው::

ጀርመን ምንጊዜም ጀርመን ነው : የትኛውንም ውድድር ሣይንቁ ያሏቸውን ምርጥ ተጨዋቾች ከጠንካራ የቲም-ዲሲፕሊን ጋር ያቀርባሉ :: እነርሱ ዋዛ : ፈዛዛ አያውቁም :: ባለፈው የዓለም ዋንጫ ከነበራቸው አቋም የአሁኑ ከፍ ያለ ነው :- በተለይ ደግሞ የአማካዩ ክፍል ይበልጥ ልምድና ችሎታ ያላቸውን እነ መሱት ኦዚልን እና ሣሚ ከድርያን ያቀፈ ሥለሆነ እንደ ዱሮዋቸው ኳስ ሣይጠልዙ በተረጋጋ ሁኔታ ተቀባብለው ጎል የሚያገቡ ሆነዋል :: አንተም እንደጠቀስከው የጀርመን የኋላ መሥመር ከጄሮም ቦቴንግ ውጪ አስተማማኝ ችሎታ ያላቸው አይመስለኝም :: እንግዲህ ይህንን የምናረጋግጠው የጥሎ ማለፉ ዙር ውስጥ ሲገቡ ይሆናል ::

ቲኪ_ታካ wrote:ፈረንሳይም እስኪ ነገ እናየዋለን:: ስፔንን ጨምሮ ማናቸውንም የሚያንበረክክ ኢንዲቪጅዋል ኳሊቲ አላቸው:: ኳስንም ተቆጣጥረው በተጋታሚ ክልል ውስጥ ጫና ፈጥረው መጫወት ላይ ያዘነብላሉ:: አጥቂም ካሪም ቤንዜማ በጨዋታ ወደዋላ እየተመለሰ በአንድ ሁለት ቅብብል መግባት የሚፈልግ መሆኑ ለሚከተሉት አጨዋወት አመቺ ይመስላል::

በግል ጎበዝ : ጎበዝ የሆኑ ተጨዋቾች ቢኖሯቸውም ፈረንሣይ ገና ወጥ የሆነ ቡድን የላቸውም :: እንደ ዚዙ ዓይነት አማካይ-አጥቂ ተጨዋች ይቅርና የሰውነት ቁመናው አነስ ያለ የዣን ቲጋና ዓይነት የኳስ ቴክኒሽያን የላቸውም :: የዛሬውን ጨዋታቸውን ካሸነፉና የምድባቸው አንደኛ ከሆኑ በተከታዩ ዙር የሚጋጠሙት ከጣሊያን ወይም ከክሮሽያ ጋር ስለሚሆን ገና ብዙ ልናያቸውና ልንገመግማቸው ዕድል ይኖረናል ::

ቲኪ_ታካ wrote:ደጋፍያቸው ከሆንክ ይቅርታ እንደ እንግሊዝ ቡድን ማየት ያስጠላኝ ቡድን ደሞ የለም:: ጉራና ምክንያት ብቻ የሚያበዙ ግን ኳሊቲ የሌለው ቡድን ነው:: ፕሪምየር ሊግ እድሜ ለውጭ ዜጎች ይበሉ እንጂ እንደእንግሊዞች ችሎታ ቢሆን ገና ድሮ አክትሞለት ነበር :: ገና አንድ ተጫዋች ብቅ ሲል እላይ ይሰቅሉትና ማን ይሆን ብለክ ስታይ እዚ ግባ የማይባል ተራ ነው::

ምነው ምን አልኩህ ወዳጄ :( እንግሊዝ :o እንኳን በቁሜ በድኔም ከማይደግፋቸው ቡድኖች አንዱ የእንግሊዝ ቡድን ነው :: ዘንድሮ ያንን የተለመደ ዘረኝነታቸውን በድጋሚ አምጥተውታል : እንደተለመደው ውርደታቸውን ተከናንበው ይመለሣሉ :: ጀርመን እንኳን ሠልጥኖ አንድም ጀርመን ውስጥ ያልተወለዱ ወይም በዘር ሙሉ በሙሉ ጀርመናዊ የሆነ ተጨዋች የሌለው ብሔራዊ ቡድን ባዋቀሩበት ዘመን እንግሊዞች በተቃራኒው በፍፁም ዘረኝነት ተነሣሥተው ሪዮ ፈርዲናንድን ያህል 'World Class Defender' የማያሠለፉ ጉዶች ናቸው :: ድሮ ዓለም ገና ለእግር ኳስ ጨዋታ እንግዳ በነበረበት ዘመን በግርግር አምታትተው የበሏት የ1958 (እ.ኤ.አ. 1966) የዓለም ዋንጫ አለች : በዚያች ጉራቸውን ይቸርችሩ ::

አየርላንድ በደጋፊም ብዛት አንደኛ ሳይሆኑ አይቀሩም:: ብዙ ደጋፊዎች ወደ ውድድሩ ሀገር እንደተመመ ነው የተሰማው:: ከረጅም ግዜ በዋላ ካልተሳሳትኩ ከ 1994 አሜሪካ አለም ዋንጫ በዋላ ቡድኑ በሜጀር ውድድር መሳተፉ ስለሆነም ናፍቆዋቸውም ሊሆን ይችላል:: በጸባይም 10/10 ይሰጣቸዋል::

ውድድሩ እስካሁን አርክቶኛል:: ጎል ያልገባበት ጨዋታ እስካሁን የለም:: በሁሉም ጨዋታዎች ላይ ጎል ተቆጥሮዋል:: ይህ ራሱ ማጥቃት አዲሱ ፋሽን እንደሆነ ነው:: እድሜ ለ ስፔን እና ባርሴሎና ክለብ!!

እስኪ አስተያየትክን ጣል ጣል አርግልን

አዎ የዘንድሮውን የአውሮፓ ዋንጫ ካለፉት ሦሥትና አራት ውድድሮች ጋር ስናወዳድረው ይኼኛው የላቀ ጨዋታ እያየንበት ነው :: በእርግጥ ወደኋላ ሄደን የእነ ሩድ ጉሊትን ዘመን ካስታወስን ያ አጨዋወት ምንጊዜም ከትዝታ የሚጠፋ አይደለም :: የዛሬውን ጨዋታዎች እንመለከትና ያየነውን እንደ አተያያችን እናወራዋለን ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Fri Jun 15, 2012 5:46 pm

የተሞናሞነው wrote:እኔ ምላችሁ....አንዱን በነ ማንቼ አርሴ ያበደ ጄለሴን...'እኔ ግን ለምንድን ነው እንደናንተ የኳስ ወሬ ይህን ያህል የማይስበኝ የማይጥመኝ' ስለው 'ፋራ ጎጃሜ ስለሆንህ ነው አይለኝ መሰላችሁ :roll: ይሄ ቅል ራስ...አሁን ሳስበው ግን ፋራ ሲለኝ እዚያው ላይ እንደ ኳስ አንጥሬ ማንፈራፈር ነበረብኝ :evil:

እና 'ፋራ' መሆኔን ለማሳወቅ ያህል ነው ብቅ ያልኩት :roll: ግን ይህ ሁሉ ከላይ የጻፋችሁት ያላነበብሁት ስለ ኳስ ብቻ ነው ይሆን :? ሰው ብርቱ ነው :o

ፋራው ሞንሟናው ነኝ ከጎዣም :wink:

ሞንሟናው :-

ፋራነትን በሠነድ ለጎጃሜ ብቻ ያስረከበውም የለም ሁሉም አካባቢ 'ፋራ' አለው : መሐል አራዳ-ፒያሣ ተወልደው ካደጉት ጀምሮ :) :) :) የእግር ኳስ ጨዋታ ያለመውደድ ግን መብትህ ነው :: ደግሞም አልፈርድብህም ያደግህበት ዘመን እግር ኳስ ከመጫወት ይልቅ ከፌዴራል ፖሊስ ቆመጥና ከወያኔ ጥይት ለማምለጥ ሲባል ሩጫ የገነነበት ዘመን ስለሆነ :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Next

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests