Euro2012 ፖላንድ/ዩክሬን

ስፖርት - Sport related topics

Postby ተድላ ሀይሉ » Wed Jun 20, 2012 8:16 pm

ሰላም የእግር ኳስ ስፖርት አፍቃሪዎች :-

ሰላም ለቤቱ ባለቤት ቲኪ_ታካ :-

እንግዲህ የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ ጨዋታዎች ተጠናቅቀዋል :: እስካሁን ካያችኋቸው ጨዋታዎች
    የትኞቹ የሚስቡ ነበሩ?

    የትኞቹስ እንቅልፍ የሚያስመጡ?
እንዲሁም
    ባልተጠበቀ ሁኔታ ከውድድር የወጡት የትኞቹ ቡድኖች ናቸው?

    የትኞቹስ ሣይጠበቁ በለስ ቀንቷቸው ለሩብ ፍፃሜ ለማለፍ ቻሉ

መልሶቹን ጨዋታዎቹን በሙሉ ለተከታተሉት እተወዋለሁ ::

እንግዲህ ነገ ቼክ ሪፑብሊክ ከፖርቱጋል በሚያደርጉት ጨዋታ የሩብ ፍፃሜው ዙር ይጀመራል :: ስለሆነም ቴዶር ገብረሥላሤ ነገ ከሮናልዶ ወይም ከናኒ ጋር ሜዳ ላይ ሲፋለም ለማዬት ዕድል ይኖረናል :: ለቼክ ቡድን መልካሙን እመኛለሁ ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Thu Jun 28, 2012 4:32 am

ሰላም የእግር ኳስ ስፖርት አፍቃሪዎች :-

ሰላም ቲኪ_ታካ :-

የዛሬው የእስፓኝ እና ፖርቱጋል ጨዋታ እንዲሁም ባለፈው እሑድ ጣሊያን እና እንግሊዝ ያደረጉት የሩብ ፍፃሜው የመጨረሻ ጨዋታ ብዙም የሚያስደስት ፉክክር ሣይታይባቸው በአስቀያሚው የእግር ኳስ ጨዋታ ገፅታ (የመለያ ፍፁም ቅጣት ምቶች) አሸናፊዎቹ ተለይተዋል :: በተለይ የዛሬው የእስፓኝ እና የፖርቱጋል ጨዋታ ዘጊ ነበር :: እንግዲህ ነገ ጀርመን እና ጣሊያን የተሻለ ጨዋታ ካላሣዩን በስተቀረ የዚህ የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር እንደ ምድብ እና የሩብ ፍፃሜ ውድድሮች አጓጊ ሣይሆን ከግማሽ ፍፃሜ ጀምሮ ያሉት ምንም የሚያቁነጠንጥ የኳስ ጥበብ ሣናይባቸው ውድድሩ ሊጠናቀቅ ነው :( ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ማንደፍሮ ቀለሙ » Thu Jun 28, 2012 12:24 pm

እኔ ያልግባይኝ ንግር እንዴት የስፓኝ ችዋታ አያስደሰትም ዪባላል. ኳስ ማቆጣጥር እና ማክብር ብርቅ ንግር ንው
ማንደፍሮ ቀለሙ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 1
Joined: Thu Jun 28, 2012 12:14 pm

Postby ተድላ ሀይሉ » Sun Jul 01, 2012 9:45 pm

ሰላም የእግር ኳስ አፍቃሪዎች :-

እስፓኝ የዓለም የእግር ኳስ ነገሥታት : የአውሮፓን ዋንጫ ጣሊያንን 4 ለ ምንም በመርታት በተከታታይ ለሁለተኛ ጊዜ አነሡ :: የዛሬው የእስፓኞች ጨዋታ በእግር ኳስ ጨዋታ ታሪክ ተዓምር የታየበት ነበር :: በአውሮፓ ዋንጫ አንድ ቡድን በፍፃሜው 4 ለ 0 ሲያሸንፍ የእስፓኝ ቡድን የመጀመሪያው ነው :: ጣሊያኖች የሚችሉትን ያህል ቢፍጨረጨሩም የእስፓኝን ውበት ያለው የ'ቲኪ : ታካ' አጨዋወት ማቆም አልቻሉም :: የእስፓኝ አጨዋወት ከብራዚል አጨዋወት ቀጥሎ የተከሠተ አዲስ ውበት ያለው የእግር ኳስ አጨዋወት ሆኖ ነግሧል ::

ኦላ እስፓኝ :D :D :D :D :D :D :D :D :D :D :D :D

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby recho » Sun Jul 01, 2012 9:46 pm

ተድላ ሀይሉ wrote:ሰላም የእግር ኳስ አፍቃሪዎች :-

እስፓኝ የዓለም የእግር ኳስ ነገሥታት : የአውሮፓን ዋንጫ ጣሊያንን 4 ለ ምንም በመርታት በተከታታይ ለሁለተኛ ጊዜ አነሡ :: የዛሬው የእስፓኞች ጨዋታ በእግር ኳስ ጨዋታ ታሪክ ተዓምር የታየበት ነበር :: በአውሮፓ ዋንጫ አንድ ቡድን በፍፃሜው 4 ለ 0 ሲያሸንፍ የእስፓኝ ቡድን የመጀመሪያው ነው :: ጣሊያኖች የሚችሉትን ያህል ቢፍጨረጨሩም የእስፓኝን ውበት ያለው የ'ቲኪ : ታካ' አጨዋወት ማቆም አልቻሉም :: የእስፓኝ አጨዋወት ከብራዚል አጨዋወት ቀጥሎ የተከሠተ አዲስ ውበት ያለው የእግር ኳስ አጨዋወት ሆኖ ነግሧል ::

ኦላ እስፓኝ :D :D :D :D :D :D :D :D :D :D :D :D

ተድላ
:evil: :evil: :evil: ጋሽ ተድላ ! ባስኬትቦል አረጉት .. ! አይ አም ማድ!!!!
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ተድላ ሀይሉ » Sun Jul 01, 2012 9:55 pm

recho wrote:

ምነው ራሄል :) የጎል ብዛት እኮ አይጠላም : በእያንዳንዱ ጎል መጨፈር ስላለ :)

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ገልብጤ » Sun Jul 01, 2012 10:28 pm

recho wrote:
ተድላ ሀይሉ wrote:ሰላም የእግር ኳስ አፍቃሪዎች :-

እስፓኝ የዓለም የእግር ኳስ ነገሥታት : የአውሮፓን ዋንጫ ጣሊያንን 4 ለ ምንም በመርታት በተከታታይ ለሁለተኛ ጊዜ አነሡ :: የዛሬው የእስፓኞች ጨዋታ በእግር ኳስ ጨዋታ ታሪክ ተዓምር የታየበት ነበር :: በአውሮፓ ዋንጫ አንድ ቡድን በፍፃሜው 4 ለ 0 ሲያሸንፍ የእስፓኝ ቡድን የመጀመሪያው ነው :: ጣሊያኖች የሚችሉትን ያህል ቢፍጨረጨሩም የእስፓኝን ውበት ያለው የ'ቲኪ : ታካ' አጨዋወት ማቆም አልቻሉም :: የእስፓኝ አጨዋወት ከብራዚል አጨዋወት ቀጥሎ የተከሠተ አዲስ ውበት ያለው የእግር ኳስ አጨዋወት ሆኖ ነግሧል ::

ኦላ እስፓኝ :D :D :D :D :D :D :D :D :D :D :D :D

ተድላ
:evil: :evil: :evil: ጋሽ ተድላ ! ባስኬትቦል አረጉት .. ! አይ አም ማድ!!!!

ቅቅቅቅቅ...አይ የቋጣሪ ነገር $50 እዚህ ድረስ ይዛሽ መጣች ....ቅቅቅቅቅቅ ..እኔ ብሆን 5 ቢኪኒ ገዝቼ ገጠር ላለችው ሚስቴ እልክላት ነበር.. :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1680
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ተድላ ሀይሉ » Mon Jul 02, 2012 1:10 am

ገልብጤ wrote:
recho wrote:
ተድላ ሀይሉ wrote:ሰላም የእግር ኳስ አፍቃሪዎች :-

እስፓኝ የዓለም የእግር ኳስ ነገሥታት : የአውሮፓን ዋንጫ ጣሊያንን 4 ለ ምንም በመርታት በተከታታይ ለሁለተኛ ጊዜ አነሡ :: የዛሬው የእስፓኞች ጨዋታ በእግር ኳስ ጨዋታ ታሪክ ተዓምር የታየበት ነበር :: በአውሮፓ ዋንጫ አንድ ቡድን በፍፃሜው 4 ለ 0 ሲያሸንፍ የእስፓኝ ቡድን የመጀመሪያው ነው :: ጣሊያኖች የሚችሉትን ያህል ቢፍጨረጨሩም የእስፓኝን ውበት ያለው የ'ቲኪ : ታካ' አጨዋወት ማቆም አልቻሉም :: የእስፓኝ አጨዋወት ከብራዚል አጨዋወት ቀጥሎ የተከሠተ አዲስ ውበት ያለው የእግር ኳስ አጨዋወት ሆኖ ነግሧል ::

ኦላ እስፓኝ :D :D :D :D :D :D :D :D :D :D :D :D

ተድላ
:evil: :evil: :evil: ጋሽ ተድላ ! ባስኬትቦል አረጉት .. ! አይ አም ማድ!!!!

ቅቅቅቅቅ...አይ የቋጣሪ ነገር $50 እዚህ ድረስ ይዛሽ መጣች ....ቅቅቅቅቅቅ ..እኔ ብሆን 5 ቢኪኒ ገዝቼ ገጠር ላለችው ሚስቴ እልክላት ነበር.. :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:

ገልብጤ :-

ተው እንጂ ሚሥጢር እኮ የባቄላ ወፍጮ አይደለም የትም አይዘረገፍም :) እኔ እኮ ራሄል በዕውነት በጣሊያን መሸነፍ ሣይሆን በጎሉ ብዛት የተሠላቸች ነበር የመሠለኝ :roll: :roll: :roll: :roll: ለካ ነገሩ ሌላ ኖርዋል :wink: :wink: :wink:

ለእኔ ግን ለረዥም ዘመን የአውሮፓ እግር ኳስ አጨዋወትን ከሚጠሉት ወገን ነበርኩና ካለፈው የአውሮፓ ዋንጫ ጀምሮ የእስፓኝ ቡድን አዲስ የአጨዋወት ሥልት በአመርቂ ሁኔታ በማስተዋወቁ ኳስ ጠላዥ የነበሩት እነ ጀርመን እንኳን ኳስ መጫወት በመጀመራቸው ደስ ብሎኛል :D :D :D ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby recho » Mon Jul 02, 2012 1:56 am

ቅቅቅ ጋሽ ተድላ :lol: :lol: :lol:

ገልብጤ ከምር ግን እኔ የገባሁበት እየገባህ መጻፍ እኮ የግድ የለብህም ቅቅቅ ከዋርካ ሩልስ አንዱ አይደለም .. ከእግሬ ስር አልጠፋ አልክኮ ...ለማንኛውም ... ድህነት አያሳፍር መቸም ያለቺኝን $50 ተወራረድኩባት እና ተሸነፍኩ .... መቁዋጠር መሎሀል .. ድህነት :lol: :lol: :lol:

ለሁሉም.. የስፔን ደጋፊዎች ኮንግራ !
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ቲኪ_ታካ » Mon Jul 02, 2012 11:31 pm

ከሁሉም በቅድምያ ተድላ ሀይሉ ቤቱን ያለማስታወቅያ ጥዬ ስጠፋ ተንከባክበክና አድምቀክ ስለጠበከኝ በእጅጉ አመሰግናለሁኝ:: በመለጠቅ እስካሁን የተሳተፋቹትንም ምስጋናዬ ይድረሳቸ::
እንዳየነው ዩሮ2012 በስፔን ቡድን አሸናፊነት ተጠናቋል:: እንግዲህ ከሚቀጥለው ፈረንሳይ ከምታዘጋጀው ዩሮ2016 ጀምሮ ይህ ቅልብጭ ያለው በ 16 ምርጥ ቡድኖች መሀከል የሚደረገው ውድድር የተሳታፊ ሀገሮች ቁጥርን ወደ 24 በማሳደግ በግሳንስግስ ቡድኖች በመሙላት እንደአለምዋንጫ ለዛውን ሊያሳጡት ነው:: በ ፕላቲኒ የሚመራው የአውሮፓ ፉትቦል ማህበረሰብ እንደፊፋ ሁሉ ገንዘብ ማግበስበስን ዋናው አላማው አርጎ ለጨዋታ ፉክክርና ጥራት ግድየለሽነቱን አሳይቷል:: እሱን በሌላ ግዜ እምንወያይበት ርእስ አርገን እናቆየውና ላሁኑ ስለተጠናቀቀው የዩሮ 2012 ትንሽ ላውራ::

ስፔን ላለፉት 4 አመታት የአለም ፉትቦልን ህይወት መልሰው መዝራት ብቻ ሳይሆን ያንን ሲያደርጉም ክብረወሰኖችን በማስመዝገብና በፉትቦል ውበት እጅ እያሰጡ መሆኑ በእጅጉ የሚያስደስትና የሚያስገርም ነው:: እግረመንገዳቸውንም የምንግዜውም የአለም ምርጥ ቡድኖች ተርታ የተሰለፈ እንደውም ከሁሉም ቁንጮ የሆነ ቡድን ነው ለመባል አብቅቷቸዋል:: በበኩሌ በእድሜዬ እንደዚህ በክህሎተኛ ተጭዋቾች የተሞላ ሙሉ ብሄራዊ ቡድን አይቼ ስለማላውቅ የምንግዜውም ምርጥ ብዬዋለሁ:: እደግፋቸውም ስለነበር ደስታዬ እጥፍ ደርብ ሆኖልኛል:: በተረፈ ይህ ቡድን ገና በዚሁ ያበቃ አይመስልም:: ገና ወጣት ቡድን ነው:: ከስር የሚተኩ እሳት የሆኑ ልጆች አሉ:: አሁንም ካሉት ቁልፍ ተጭዋቾችን ለብራዚሉ አለምዋንጫ ዣቪ ብቻ ነው እድሜው 34 የሚደርሰው:: የልጁ አጨዋወት ደሞ በኳስ እውቀት ላይ የተመሰረተ በመሆኑና ስፔን አጨዋወቷን እስካልቀየረች ድረስ የእድሜው መግፋት ምንም አያሰጋም:: ዚነዲን ዚዳንም በ 35 አመት እድሜው ነው በትከሻው ፈረንሳይን ለ2006 አለምዋንጫ ፍጻሜ ከድንግ እንቅስቃሴው ጋር አይበቃት:: በረኛው ካሲላስም እድሜው አያሰጋውም:: እናም ስፔን አለምዋንጫውን ቢደግሙት አይግረማቹ:: ግን ፉክክሩ ጠንከር ይላል:: ምክንያቱም በላቲን አሜሪካ ምድር ዋንጫን የሳመ አውሮፓዊ ሀገር እስካሁን አንድም የለም:: በዛ ላይ ቡድኖች ዝም ብለው ባሉበት ቁጭ ብለው አይጠብቁም:: እንዴት ስፔንን ማቆም እንዳለባቸው ማክሸፍያ አጨዋወትን ይዘው እንደሚመጡ ይጠበቃል::

በድጋሚ ቪቫ ኢስፓኛ!!!!!
ቲኪ_ታካ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 17
Joined: Tue Jun 05, 2012 4:58 pm

Previous

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest