ሌዮኔል ሜሲ የሁልግዜውም ምርጥ እግርኳስ ተጫዋች

ስፖርት - Sport related topics

ሌዮኔል ሜሲ የሁልግዜውም ምርጥ እግርኳስ ተጫዋች

Postby ቲኪ_ታካ » Sun Jun 10, 2012 2:14 am

በዛሬው እለት አርጀንቲና እና ብራዚል በኒውጀርሲ መታላይፍ ስቴድየም ያደረጉት ጨዋታ እጅግ አዝናኝና በርካታ ጎሎች የተቆጠሩበት ከመሆኑን በላይ ታላቁ ሜሲ ሀትሪክ አስቆጥሮ አረንቲናም 4-3 እንድታሸንፍ ረድቷታል:: እሱን በተመለከተ የፉትቦል ህጎች ሞዲፋይ ካልተደረጉ በስተቀር ሜሲን ከሌሎች ጋር ማወዳደር አይቻልም:: ለምሳሌ እሱ የሚጫወትበትን የሚገጥም ቲም በ 15 ተጭዋች እንዲሰለፍ ወይንም ደሞ ከፔናሊቲ ሳጥን ውስጥ የሚያስቆጥራቸውን ጎሎች አለመቁጠር የመሳሰሉት ህጎችን ዲዛይን ካልተደረገ በቀር ይህን ሰው ሌሎችን ከማዋረድና በየአመቱ ከ70 በላይ ጎሎች ከማግባት የሚያግደው አይኖርም :: የምናውቀው እግርኳስ ለዚህ ድንቅ ልጅ በጣም ቀሎታል::
ቲኪ_ታካ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 17
Joined: Tue Jun 05, 2012 4:58 pm

Postby ተድላ ሀይሉ » Sun Jun 10, 2012 10:16 pm

ሰላም ቲኪ _ታካ :-

በእርግጥም ሊዮኔል ሜሢ ተዓምረኛ ተጫዋች ነው :: በአሁኑ ወቅት እርሱን የሚልቅ የእግር ኳስ አጥቂ ተጫዋች አለ ለማለት አይደፈርም :: የትላንቱ የብራዚልና የአርጀንቲና ጨዋታ ቅንጫቢ ይኼው :-

ምንጭ:- Posted by ongrojinho, Sun June 10, 2012. Brazil v Argentina.


በነገራችን ላይ እ.ኤ.አ ከ1994 ወዲህ የብራዚል ቡድን የሚጫወተው እንደ ቀድሞው የምዕራብ ጀርመን ቡድን እንጂ ድሮ እንደሚወደድላቸው ዓይነት ውበት ያለው እግር ኳስ መጫወት ትተዋል ::


ሜሤ በአጥቂነት ችሎታው ብቻ ሣይሆን ዱላ የሚችልና እንደሌሎች አጭበርባሪ አጥቂዎች (የፖርቱጋሉ ሮናልዶ) ሣይጎዳ በመውደቅ ዳኞችን ለማታለል የማይሞክር በመሆኑ ጭምር ይታወቃል ::

ምንጭ:- LeoMessiFootball, Published on May 19, 2012. Lionel Messi never dives (Ultimate Compilation).

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ቲኪ_ታካ » Mon Jun 11, 2012 12:43 am

ሄሎ ተድላ:: አመሰግናለሁ ስለሊንክና ገለጻህ:: ስለ ሜሲ ነገር ምን ያልተባለ አለ? አሁን አሁን የልጁን ችሎታ ለምደን ከርሱ የሚጠበቅ አርገን ስለወሰድነው በየጨዋታው የሚያረጋቸው ነገሮችን ችላ እንላለን እንጂ ብዙ ተአምሮችን ነው እየሰራ ያለው:; እኔም በበኩሌ እያንዳንዱ ጨዋታ ላይ የሆነ ነገር ተአምራዊ ክስተት ፈጥሮ የሚወጣ ተጭዋች ከሜሲ ውጭ አይቼም ለወደፊቱም የማይ አይመስለኝም:;ሜሲ ችሎታው ወረደ የሚባልለት ለሁለትና ሲስት ጨዋታ ጎል ካላገባ ነው:: ይህ ምን ያህል ስታንዳርዱ ከፍተኛ የሆነ ሰው እንደሆነ ያስገነዝበናል:: ጎሎቹ ባብላጫው ተራ ተጭዋች እንኳን ሊያገባቸው ሊያልማቸውም የሚከብዱት አይነት ናቸው:: በዛ ላይ እኔን ደሞ የሚገርመኝ ልጁ አይጎዳም ወይም ተጎድቶ ሲንፈራፈር አታየውም:: ደክሞትም አይቀየርም:: በጣም ነው የሚያስደምመው:: እንግዲህ እስኪያረጅ ድረስ ችሎታውን መኮምኮም ነው::

ስለብራዚል ያልከውም ትክክል ነው:: ብራዚሎች በስም ብቻ የቀረ ቡድን ናቸው:: አሁን ራሱ አውሮፓ ዋንጫ ላይ ጣልያን ሆላንድ ራሽያ እና ስፔን ከብራዚል መቶ ግዜ የሚሻል ማራኪ አጨዋወት አላቸው::ሁሉም ሰው ግን ብራዚል ብራዚል ይላል:: በእርግጥ ኢንዲቪጅዋል ችሎታ ያላቸው ጨዋታን ባንዴ መለወጥ የሚችሉ ሀይለኛ ተጫዋቾች አላቸው:: በቡድን አጨዋወት ግን ይህን ያህል ናቸው:: በኔ እድሜ ራሱ ብራዚል ሲደነቅ እንጂ በጨዋታው ከሌሎች በልጦ አንጀቴን አርሶኝ ያውቁም:: በድሮ በረ እያረሱ ይመስላል::
ቲኪ_ታካ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 17
Joined: Tue Jun 05, 2012 4:58 pm

Postby መጽናናት » Tue Jun 12, 2012 5:15 am

ጨዋታውን ላይቭ እንዳየሁት ሜሲ ያሳየው እንቅስቃሴ ተሚያምር ነው ግን ብራዚል ያሰለፈ የኦሎንፒክ ቲሙን እንጂ ዋናውን አይደለም አርጀቲና ያላትን በአጠቃላይ ለቃቅማ ነው የገባችው ብራዚል ግን ወሳኝ የሆኑ ፍልዶችና ተከላካዮች አልገቡም ግን እነዚህ ታዳጊዋች ያሳዩት እንቅስቃሴ የሚደነቅ ነው አገርዋ ላይ ዋንጫው እንደሚቀር ያሳያል ያመላክታል;;
መጽናናት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1133
Joined: Fri Aug 20, 2004 10:24 pm
Location: united states

Postby መጽናናት » Tue Jun 12, 2012 5:33 am

ሜሲ ጥሩ ተጫዋች ነው ግን አሁንም ቢሆን መታየት ያለበት ለአገሩ አንድ ነገር ሲሰራ ነው ማራዶና ስሙን የተከለው እና ሰሙ የሚነሳው ለናፖሊ ባደረገው ነገር ብቻ አይደለም ላገሩ ባደረገው እንጂ ለምሳሌ እነቫንባስተ ጉሌት ፕላቲኒ ያን ያህል ስማቸው ሲጠራ አይሰማም ለምን ላገራቸው የክልላቸውን ዋንጫ እንጂ የአለምን አላገኙም ብራዚልም ቢሆን እነዚኮ ሶቅራስ ፋልካዋ ስማቸው የለም ምንም ላገራቸው ያደረጉት የለም ከሶስቱም 9ሮናልዶ ትልቅ ነገር ላገሩ የሰራ ነው ለጉዳት ባይዳረግና ረጅም ጊዜ ባያርፍ እስካሁን መጫወት የሚችል ከፔሌ የበለጠ ታሪክ የሚሰራ ነው እስከዛሬ ማን ተጫዋች የሱን ያክል በአለም ዋንጫ ያገባ የለም 2002 የአለም ዋንጫ 2 አመትተኩል ኳስ ሳይነካ ትሬሊንግ ብቻ አድርጎ ለብራዚል ተሰልፎ 32 አመት በውሀላ በ7 ጨዋታ 8 በማግባት ተአምር የሰራ ተጫዋች ነው ስለዚህ ሜሲም ለአገሩ አንድ ነገር አድርጎ ማሳየት አለበት አለበለዛ እንደነ ባቲ ጎል ሲያቆም አብሮ ስሙ ይቆማል;;
Last edited by መጽናናት on Tue Jun 12, 2012 6:09 am, edited 1 time in total.
መጽናናት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1133
Joined: Fri Aug 20, 2004 10:24 pm
Location: united states

Postby መጽናናት » Tue Jun 12, 2012 5:39 am

የብራዚልና የአርጅንቲና ጨዋታ እስቲ በሀሳብክ ;ዳኔል አልቪስ ;ዲጎ ሲልቫ; ራማሬዝን አስገባና ካካን; ሮቢኒኖን ጭምረክ እየው ተአምረኛ ቲም ነው የሚሆነው; :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:
መጽናናት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1133
Joined: Fri Aug 20, 2004 10:24 pm
Location: united states

Postby መጽናናት » Tue Jun 12, 2012 5:58 am

መጽናናት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1133
Joined: Fri Aug 20, 2004 10:24 pm
Location: united states

Postby ኤጀርሳ ጎሮ » Tue Jun 12, 2012 8:38 pm

በትክክል መጽናናት አንድ ተጫዋች ለሀገሩ ካልሰራ ስሙ አይገንም ግን ሜሲ ገና ብዙ የሚጫወት ስለሆነ ጊዜ አለው;; እስቲ እንየው
ኤጀርሳ ጎሮ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 16
Joined: Wed Jul 14, 2010 3:26 pm

Postby ቲኪ_ታካ » Wed Jun 13, 2012 3:20 am

መጽናናት እንዲሁም ኤጄርሳ ጎሮ ጥሩ ነጥብ ነው ያነሳቹት:; እሱን እኔም ራሴ በፊት እለው የነበረው ነገር ነበር:: ሌዮኔል ሜሲ ግን በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ከአለም ዋንጫ በባሰ አስቸጋሪ ውድድርና የአለም የምርጦች ምርጥ ተጭዋቾች በያመቱ እየገጠመ ተአምራቶቹን ሳያቋርጥ እያስኮመኮመን ነው ያለው:: ማን ተጭዋች ነው እስኪ ሜሲ በአለፉት 5 ሲዝኖች ብቻ በቻምፒየንስ ሊጉ ያስገኛቸውን ድሎችና እሚገርሙ ታሪክ የማይረሳቸው እንቅስቃሴዎችን ያደረገው?
ለናሙና ያህል ካቻምና ከአርሰናል ጋር 4 ጎሎችን ያገባበት ጨዋታ, አምና ሪያል ማድሪድን በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ኑካምፕ ላይ ሲያሸንፉ ያገባቸው 2 ጎሎች ዘንድሮ ሪከርድ የሰበረበት ባየርን ሌቨርኩዝን ላይ ያገባቸው 5 ጎሎች ብቻ ማስታወሱ ምን ያህል ዶሚናንት ተጭዋች እንደሆነ ነው የሚያሳየን:: እርግጥ የሚጫወትበት ባርሴሎና ቲም ምርጦች የተሰባሰቡበት ቡድን ነው:: ግን ያለ ሜሲ እንደዚህ ለተጋጣሚ ፍዳ የሚያሳዩ ሊሆኑ እንደማይችሉ ከቼልሲ ጋር እርሙን ጎል መንገዱ ቢጠፋበት ያየነው ነገር ነው:: ሜሲ ፈረንጆች ultimate compitator የሚሉት እልህኛም ተጭዋች ነው:: በቀደም ራሱ ሲናገር እስካሁን ድረስ በቼልሲ ከ ውድድሩ የወጡበት መንገድ እያንገበገበው ንዴቱ እንዳልበረደለት ነው የተናገረው:: ፋውል ሲሰራበት የማይወድቀውና የማያለቃቅሰው ከምንም በላይ ማሸነፍ ከደሙ የተዋሀደና ስፖርቱን ከልቡ መጫወት የሚወድ ታላቅ ፕሮፌሽናል ስለሆነም ነው:: 90 ደቂቃን መጫወት ሁልጊዜ ዲማንድ የሚያረገው ኢጎ ስላለበት ሳይሆን ኳስ መጫወት ብቸኛና ብቸኛው ህይወቱ ስለሆነ ነው:: እሱን ቀምተከው ምን ይውጠዋል?
አለም ዋንጫ አሁን አሁን ለዛውን እያጣ የመጣ ውድድር ሆንዋል:: ድሮ በነፔሌ ግዜ ተጭዋቾች እንደልብ ከክለብ ክለብ የመዘዋወር ፍቃድ ስላልነበር አራት አመት ጠብቀው ነበር ሀገራት የሚፈታተሹት:: ውድድሩም በዛ ሰበብ በናፍቆት ይጠበቅ ነበር:; አሁን ግን ሜሲና ኔይማር ሲፎካከሩ ለማየት የግድ 4 አመት መጠበቅ የለብንም:: ክለቦች ሚኒ ናሽናል ቲም ሆነው በ ብሄራዊ ሊጋቸው አልያም በቻምፒየንስ ሊጉ ላይ ሲገናኙ እንደውም የምርጦችን ምርጥ አካተው ስለሚቀርቡ ፉክክሩም እጅግ የጠነከረ ነው:: ማራዶና ናፖሊን ብቻውን ይዞ ለድል ያበቃው አንድ ክለብ ከ 3 በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች መያዝ በማይፈቀድበት ዘመን ነበር:: እርግጥ የማራዶናን ድል ለማሳነስ አይደለም የፈለኩት ግን ያንን ዘመን እና ያሁኑን አመሳክሮ ሜሲ የግድ እንደዛ ይሁን ማለት ስለሚከብድ ነው:: በኔ አመለካከት የሜሲን ኮንሲስተንሲ እና አስደናቂ አፍ የሚያስከፍት ክህሎት በተደጋጋሚ ጨዋታዎችን ዶሚኔት የሚያርግበት ነገሩ አለም ዋንጫን እንኳን ባያገኝ የምንግዜውም ምርጥ ሊያስብለው የሚችልበት ሁኔታ ነው የሚታየኝ:: እንበልና ዴስቴፋኖ , ፔሌ, ፕላቲኒ, ማራዶና, ክራይፍ, ሮናልዶ(ብራዚሉ), ዚዳን እና ሜሲን በእኩል እድሜያቸው ላይ አምጥተንና when they are on top of their game ማን ልቆ ይታያል ብለክ ታስባለክ?

ለኔ መልሱ ቀላል ነው:; ሌዮኔል ሜሲ::

የአለም የሁልግዜውም የምርጦች ምርጥ ለመባል የግድ አለምዋንጫን ማሸነፍ ያለበት አይመስለኝም::
ቲኪ_ታካ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 17
Joined: Tue Jun 05, 2012 4:58 pm

Postby መጽናናት » Wed Jun 13, 2012 6:14 am

አባብልክን ለመቀበል እቸገራለው አንተ ድሮ እኔም እንደዛ እል ነበር ያልከው ያንተ ቡድን አርጀንቲና ይመስለኛል ከአለም ዋንጫ ጋር ስለተራራቁ የቆዩ መሰለኝ ስለዚህ ያለምን ዋንጫ ጣል ጣል አደረከው; :) :) ከእግር ኳስ ውድድሮች ሁሉ ከባድ የአለም ዋንጫ ነው;; አለም ዋንጫ ላይ ጥሩ ሆኖ ክለቡ ላይ ደካማ የሆነ ተጫዋች በብዛት አላየሁም ግን ክለብ ላይ ጎበዝ ሆኖ አለም ዋንጫ ላይ ደካማ ብዙ አለ;; አሁንም ስለሜሲ የምልህ ነገር ጎበዝ ነው በጣም ግን በምንም አይነት ከሮናልዶ; ፔሌ ;ማራዶና;ጋር አላወዳድረውም ምክንያቱ ትልቅ ግዙፍ ነገር ይቀረዋል;; የአውሮፓን ዋንጫ ውድድሩ ከባድ ቢሆንም ያልተጠበቁ ቲሞች ሲያገኙት ይታያል;;የአለም ዋንጫ ላይ ግን የለም ለምን የምርጦች ምርጥ የሚገናኙበት ስለሆነ ለምሳሌ ብትወስድ እራሳቸው ተጫዋቾች ለክለባቸው ዋንጫ ሲያገኙ እንባ ሲተናነቃቸው አይቼ አላውቅም ግን ያለም ዋንጫ ላይ የተለየ ነው ያሸነፈም የተሸነፈም ሲያለቅስ እናያለን ምክንያቱ ስምህን ለዘመናት የምታስጠራበት ነው ስለዚህ ሜሲም ይህ ፈተና ይጠብቀዋል ግን ችግሩ ባርሳ ያሉት ተጫዋቾችን አይነት ማግኘት አለበት አርጀንቲና ውስጥ ደግሞ ያሉ አይመስለኝም ስለዚህ እግዚህአብሄር ይርዳው;; በአሁኑ ሰአት ከነ ፔሌ; ማራዶና;ሮናልዶ ጋር አታወዳድረው ምክንያቱም ፔሌ 3 የአለምን አግኝቶ ማራዶና 86 ታሪክ ሰርቶ ሮናልዶ 3 የአለም ዋንጫ ላይ 2 ወርቅ እና 1 ብር መዳሊያ አግኝቶ ያለፉ ናቸው;;ሜሲስ.......
Last edited by መጽናናት on Wed Jun 13, 2012 9:58 pm, edited 4 times in total.
መጽናናት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1133
Joined: Fri Aug 20, 2004 10:24 pm
Location: united states

Postby መጽናናት » Wed Jun 13, 2012 6:23 am

ለላ የምጠይቅክ የአለም ዋንጫ ቀላል ከሆነ ሜሲ 2010 አለም ዋንጫ ላይ የት ነበር? ምንም ሳያሳየን የትሄደ? የክለቡን 25% እንኳን አልተጫወተ;; የጀርመን ተጫዋች አርጀንቲናን 4-0 ካሸነፉ በውሀላ ያለው ሜሲን ያየሁ ማልያ ስንቀያየር ነው; :lol: :lol: :lol: :lol:
መጽናናት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1133
Joined: Fri Aug 20, 2004 10:24 pm
Location: united states


Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest

cron