ኢትዮጵያ በለንደን ኦሎምፒክ

ስፖርት - Sport related topics

ኢትዮጵያ በለንደን ኦሎምፒክ

Postby ቀደምት » Mon Jul 02, 2012 7:47 pm

ሰላም የስፖርት አፍቃሪዎች:

በዚህ አምድ በለንደን ኦሎምፒክ ላይ ስለሚሳተፉ አትሌቶቻችን ዜና እንደምታካፍሉን ተስፋ በማድረግ ለዛሬ ከታች ያለውን ጀባ ብያለሁ:: ኢትዮጵያ ከምትታዎቅባቸው የረዥም ርቀት በተጨማሪ በመካከለኛና በአጭር ርቀት ላይም ትኩረት እየሰጠን ነው ይላሉ አሰልጣኝ ይልማ በርታ:: ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ከፍተኛ የስፖርት ፍቅር አላቸው ስለተባለው ነገር ብዙም የማውቀው ነገር የለም:: እኔ የማስታውሰው ''ስታዲዮም ከመስራት ለገበሬው ማዳበሪያ ማቅረብ ይበልጣል'' አሉ የተባለውን የለበጣ ንግግራቸውን ስለሆነ በስፖርት ላይ እስከዚህም ይመስሉኛል:: ለማንኛውም ግን ወደ ዋናው ርእስ ስመለስ በ800ሜትር የሚወዳደረው መሐመድ አማን የኦሎምፒኪ ሜዳይ ለማግኘት ተስፋ ያለው ልጅ ነው:: በዚህም ምናልባት ለመጪዎቹ አመታት በመካከለኛና አጭር ርቀት በር ከፋች ይሆናል ብየ ተስፋ አደርጋለሁ::

http://cyberethiopia.com/news/?id=190652

.
ቀደምት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 761
Joined: Mon Feb 20, 2006 3:22 pm

Postby ዉቃው » Tue Jul 03, 2012 2:52 am

ጓድ ቀደምት
አቶ ብርሃነ ኪዳነማርያም ይህደጎ ከዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል የኦሎምፒክ ኮሚቲ ፕሬዚደንት : ወ/ሪት ዳግማዊት ግርማይ ብርሀነ በዋና ጸሀፊነት የሚመሩት አካል የሚያመጣውን ውጤት በተሰፋ ብንጥብቅስ ::
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
ዉቃው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1032
Joined: Sun Jan 07, 2007 2:48 am

Postby ቀደምት » Tue Jul 03, 2012 12:10 pm

ዉቃው wrote:ጓድ ቀደምት
አቶ ብርሃነ ኪዳነማርያም ይህደጎ ከዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል የኦሎምፒክ ኮሚቲ ፕሬዚደንት : ወ/ሪት ዳግማዊት ግርማይ ብርሀነ በዋና ጸሀፊነት የሚመሩት አካል የሚያመጣውን ውጤት በተሰፋ ብንጥብቅስ ::


ሰላም ውቃው:
አስተያየትህን አብራርተህ ስላልጻፍከው ሙሉ በሙሉ ተረድቸሃለሁ ለማለት አልችልም:: ግን ጠቅለል ያለ ምላሽ ልስጥህ:: በአሁኑ ወቅት የኦሎምፒክ ኮሚቴውን ስለሚመሩት ሰዎች መረጃ የለኝም:: ኢሕአዴግ ሁሉንም ነገር ለመቆጣጠር የያዘውን የስግብግብነት በሽታ ስለምረዳ በስፖርቱ አመራርም ''የራሴ'' የሚላቸውን ሰዎች እንደሚያስቀምጥ የታወቀ ነው:: መቼም ሙያና ባለሙያን ለማገናኘት ከመጣር ይልቅ ጥያቄው ''ማን የመሆን'' የፖለቲካ ጉዳይ ከሆነ ውሎ አድሯል::

ለማንኛውም ግን ለኔ ምንም አይነት ጥላ ቢያጠላ የኢትዮጵያዊነት መንፈሴን እንዳያደበዝዝብኝ እፈልጋለሁ/እመኛለሁ:: ስለሆነም በስፖርቱ የሚወዳደሩት ልጆችም በሚያስመዘግቡት ውጤት ኢትዮጵያዊነት እንዲቀጥል አስተዋጽኦ አለው ብየ ስለማስብ የወደፊቱን በተስፋ ከማየት አላቆምም:: መጥፎም ሆነ በጎ ዘመናት ያልፋሉ:: ከዘመን ዘመን ለመሸጋገር ታዲያ ተስፋና አወንታዊነት ጥሩ ስንቆች ይመስሉኛል::

!
ቀደምት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 761
Joined: Mon Feb 20, 2006 3:22 pm

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Wed Jul 04, 2012 3:27 am

የተከበሩ ጓድ ውቃው

ዉቃው wrote:ጓድ ቀደምት
አቶ ብርሃነ ኪዳነማርያም ይህደጎ ከዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል የኦሎምፒክ ኮሚቲ ፕሬዚደንት : ወ/ሪት ዳግማዊት ግርማይ ብርሀነ በዋና ጸሀፊነት የሚመሩት አካል የሚያመጣውን ውጤት በተሰፋ ብንጥብቅስ ::


ኮሚቴውን አቶ ብርሀነ እና ወ/ት ዳግማዊት ባይመሩት ኖሮ የኦሎምፒኩን ውጤት በተስፋ አይጠብቁም ነበር :?: 8)
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby ቀደምት » Sat Jul 28, 2012 8:54 pm

ለንደን ኦሎምፒክ ትናንት በደማቅ ሁኔታ ተከፍቷል:: የኢትዮጵያ አትሌቶች ግን ገና አልገቡም:: በሚቀጥሉት ቀናት ውስጥ እንደሚገቡ ተገልጿል:: ውድድሩ እስኪቃረብ ድረስ አዲስ አበባ መቆየታቸው ምናልባት ለኮንዲሽናቸው ይጠቅማቸው ይሆናል:: በመክፈቻው ሥርዓት ላይ የገቡትን ጥቂት ላኡካን ባንዲራ ይዛ የመራቺው የውሀ ዋና ተወዳዳሪ ናት የተባለች ያልታወቀች ሴት ነች:: ያኔት ገብረመድህን ትባላለች:: ስንት የኦሎምፒክ ሜዳይ ያላቸው አትሌቶች እያሉ እሷ የተመረጠችበት ምክንያት አልገባኝም:: ምናልባት የወደፊቱን ያገሪቱ ዋናተኞች ለማበረታታት ብሥራት እንድትሆን ታስቦ ይሆናል:: ብርቅየው! ወደር-የለሹ! ኃይሌ ገብረሥላሴ በዝግጅቱ ላይ የኦሎምፒክን ሰንደቅ ይዞ እንዲገባ መደረጉ በዓለም ላይ ያለውን ዝናና ክብር ያሳያል:: ታላቅ መኩሪያችን ነውና ደስ ብሎናል:: መልካም እድል ለኢትዮጵያ!

Ethiopian Athletics Team Set to Begin Departures for London Olympics


London (TADIAS) – The 2012 London Olympic Games are officially open as of the declaration during the July 28 opening ceremony, but the bulk of Ethiopia’s star athletics team will arrive in the English capital during the subsequent week, ahead of the athletics program that starts Friday, August 3rd.
Ethiopia’s opening ceremony flag bearer is swimmer Yanet Seyoum Gebremedhin, one of two swimmers making history as the nation’s first at the Olympics.
Of the athletics team led by 2008 double Olympic champions Kenenisa Bekele and Tirunesh Dibaba, the first wave will leave Addis Ababa on Monday July 30; while the final batch, the men’s marathon runners, will depart a few days prior to that race, which is being held on the last day of the Olympics, August 12.
DISTANCE DOUBLE POSSIBLE
Dibaba’s 10,000-meter race is the first track final of the Games and takes place on the evening of Friday, August 3, when she will be joined by Belaynesh Oljira and former world cross country champion Werknesh Kidane.
Unlike at the athletics world championships, Olympic team reserve members will, for the most part, not travel to London, unless replacing an already-injured athlete, and only three athletes per race can be accredited to stay in the Olympic Village at any time. In the 5000m, though, the announced reserves are themselves members of the 10,000m team — and they are in fact the defending Olympic champions in both events.
In addition to leading the men’s and women’s 10,000 teams, Kenenisa Bekele and Tirunesh Dibaba were named as reserves in the shorter event, so the possibility of both of them, Dibaba in particular, defending both titles remains.
Of the women on the 5000m team, the young Genet Yalew is significantly less accomplished than the runners she joined there, 2004 Olympic champion Meseret Defar and former world indoor 1500 champion Gelete Burka; and indeed, some athletes have referred to Yalew as the 5000m reserve.
If she contests the 5000, the former double world champion Dibaba will be tackling the first round heat in that event four days after her 10,000 final.
SELECTION BASED ON FAST TIMES
Contrary to media reports that referred to races in various European cities this summer as Ethiopian Olympic trials, selection to the nation’s Olympic team is based primarily on the fastest times run by athletes in their event this season, with their ongoing fitness also being taken into consideration. Typically, the year’s four fastest athletes in a given Olympic track event make up its roster of three runners and a reserve.
Dibaba contested just one 5000m track race this season, winning at the New York Diamond League in 14 minutes, 50.80 seconds, which is the fourth fastest among Ethiopian women this season, after the clockings of Defar, Burka and Yalew in Rome.
Similarly, Bekele ran the fifth-fastest Ethiopian men’s 5000m time of the year, 12:55.79, in Monaco (while the fourth-fastest athlete, his brother Tariku, is contesting just the 10,000m). The fastest times in the entire world this year were those of Ethiopia’s 2011 world bronze medalist Dejen Gebremeskel and his compatriots Hagos Gebrhiwet and Yenew Alamirew, who all ran under 12:50 in the same Monaco race.
OTHER FINALS ON THE FIRST WEEKEND OF ATHLETICS
The first round of the men’s 1500m, with Mekonnen Gebremedhin tackling the favorites, also takes place on the first day of athletics in London, followed the next morning by the 3000m steeplechase heats with Sofia Assefa and Hiwot Ayalew.
The night of Saturday August 4 features the men’s 10,000m final, an event in which Ethiopia has taken gold at every Olympics since 1996, courtesy of Haile Gebrselassie and Kenenisa Bekele. Former New York marathon champion Gebregziabher (Gebre) Gebremariam joins the Bekele brothers in London.
The women’s marathon final with 2009 world bronze medalist Aselefech Mergia and the women’s 1500m heats, featuring Dibaba’s world indoor champion sister Genzebe and newcomer Abeba Aregawi as contenders, round out the Ethiopian action in the first weekend of athletics.
While Ethiopia, historically a nation of long distance runners, has genuine 800m medal hopes this year in Fantu Magiso and especially Mohammed Aman, Bereket Desta is entered in the 400m having met the lower “B” standard of entry for the sprint event.
—–
Dates of London 2012 athletics finals with Ethiopian finalists anticipated:
Friday August 3rd: 9:25pm – Women’s 10,000m.
Saturday August 4th: 9:15pm – Men’s 10,000m.
Sunday August 5th: 11am – Women’s marathon; 9:25pm – Men’s 3000m steeplechase.
Monday August 6th: 9:05pm – Women’s 3000m steeplechase.
Tuesday August 7th: 9:15pm – Men’s 1500m.
Thursday August 9th: 8pm – Men’s 800m.
Friday August 10th: 8:05pm – Women’s 5,000m; 8:55pm – Women’s 1500m.
Saturday August 11th: 7:30pm – Men’s 5000m; 8pm – Women’s 800m.
Sunday August 12th: 11am – Men’s marathon.
Ethiopian athletes entered in London 2012 athletics events
(as previously announced, including, in italics, those reserves who will likely not travel to London):
400m
Men: Bereket Desta
800m
Men: Mohammed Aman
Women: Fantu Magiso
1500m
Men: Mekonnen Gebremedhin, Dawit Wolde, Teshome Dirirsa; Aman Wote (reserve)
Women: Abeba Aregawi, Genzebe Dibaba, Meskerem Assefa
5000m
Men: Dejen Gebremeskel, Hagos Gebrhiwet, Yenew Alamirew; Kenenisa Bekele (reserve)
Women: Meseret Defar, Gelete Burka, Genet Yalew; Tirunesh Dibaba (reserve)
10,000m
Men: Kenenisa Bekele, Tariku Bekele, Gebregziabher Gebremariam;
Lelisa Desisa (reserve)
Women: Tirunesh Dibaba, Belaynesh (sometimes spelled Beleynesh) Oljira, Werknesh Kidane;
Aberu Kebede (reserve)
Marathon
Men: Ayele Abshero, Dino Sefer, Getu Feleke;
Tadesse Tola (reserve)
Women: Tiki Gelana, Aselefech Mergia, Mare Dibaba;
Bezunesh Bekele (reserve)
3000m Steeplechase
Men: Roba Gari, Birhan Getahun, Nahom Mesfin
Women: Sofia Assefa, Hiwot Ayalew, Etenesh Diro;
Zemzem Ahmed (reserve)

ምንጭ: http://www.tadias.com/07/27/2012/ethiop ... -olympics/
ቀደምት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 761
Joined: Mon Feb 20, 2006 3:22 pm

Postby ባልዋ » Sat Jul 28, 2012 11:10 pm

i hope they will get 2 gold and 3 silver and 2 bronze medals
ባልዋ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 60
Joined: Thu Jul 12, 2012 2:20 am

Postby ቀደምት » Sun Jul 29, 2012 11:37 am

ባልዋ wrote:i hope they will get 2 gold and 3 silver and 2 bronze medals


ባልዋ መልካም ምኞትህ ሸጋ ነው:: ከዚያም በላይ የማግኘት ተስፋ ያለን ይመስለኛል:: ከአትሌቲክስ በተጨማሪ በአዲስ የስፖርት ዘርፍም ልንወዳደር ነው: ምክንያቱም አገሪቱን ባሕር-አልባ ያደረገው መንግሥት የውሀ ዋና ተወዳዳሪም ልኳል:: ስለ ያኔት የተጻፈ ዘገባ እዚህጋ አለ:

http://www.euronews.com/sport/1596620-e ... in-london/
.
ቀደምት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 761
Joined: Mon Feb 20, 2006 3:22 pm

Postby ገላጋይ-1 » Sun Jul 29, 2012 3:20 pm

ዳግማዊ ዋለልኝ wrote:ኮሚቴውን አቶ ብርሀነ እና ወ/ት ዳግማዊት ባይመሩት ኖሮ የኦሎምፒኩን ውጤት በተስፋ አይጠብቁም ነበር :?: 8)


አይይ ዋለልኝ .... አምላኪም ነህ ለካ ... ካድሬ ብቻ አይደለህም .... በእውነት ታምንበታለህ የጻፍከውን? ኢትዮጵያ ሌሎች ብቁ የስፖርት መሪዎች የሉአትም?
ገላጋይ-1
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 500
Joined: Fri Aug 25, 2006 5:43 pm

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Mon Jul 30, 2012 10:11 am

አቶ ገላጋይ-1

የመስሪያ ቤታችን ባልደረባና የሥነ-ምግባር ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ጓድ ውቃው በጁላይ 2, 2012 ያነሱትን አጀንዳ እና የሰጠነውን ምላሽ አስመልክቶ ያቀረብከውን ጥያቄ ኮሚቴው ተመልክቶታል.......እኔና የተከበሩ ጓድ ውቃው በተነሳው አጀንዳ ላይ ሰፊ የሆነ ክርክርና ግምገማ በመንፈስ አካሂደን;በመንፈስ ተግባብተን ጉዳዩን ወደመዝገብ ቤት ከላክነው ሳምንታት ተቆጥረዋል

አንተ ስለአጀንዳው ምንም አይነት ቅንጣት ግንዛቤ እንደሌለህ ኮሚቴው ጨምሮ አስምሮበታል.....ስለሆነም አሁን ወደኻላ ተመልሰን አጀንዳውን ለአንተ ለማስረዳት ህብረተሰቡ ከጣለብን ከፍተኛ ሀላፊነትና የሥራ ጫና አንጻር አመቺነቱም; አስፈላጊነቱም አልታየንም...ሆኖም ጓድ ውቃው በሻይ ሰዓታቸው ለመተባበር ፈቃደኛ ከሆኑ ጉዳዩን ከስር መሰረቱ አንስተው እንዲያብራሩልህ ጥያቄህ ወደእሳቸው ማስተላለፍ እንደምትችል እናሳውቃለን :!:

የግርጌ ማስታወሻ.......የጓድ ውቃውን ቢሮ ከዋናው በር በስተግራ ከመዝገብ ቤቱ ቀጥሎ ባለው ክፍል 3 ቢሮ ውስጥ ያለችውን ፀሀፊ ጠይቃት


ህብረተሰቡን ካለመሰልቸት ማገልገል የድርጅታችን ተቀዳሚ ዓላማ ነው :!:

ከምስጋና ጋር
ፊርማ የማይነበብ
ዳግማዊ ዋለልኝ
የቅሬታ ሰሚና እንባ ጠባቂ ኮሚቴ ሰብሳቢ

ገላጋይ-1 wrote:
ዳግማዊ ዋለልኝ wrote:ኮሚቴውን አቶ ብርሀነ እና ወ/ት ዳግማዊት ባይመሩት ኖሮ የኦሎምፒኩን ውጤት በተስፋ አይጠብቁም ነበር :?: 8)


አይይ ዋለልኝ .... አምላኪም ነህ ለካ ... ካድሬ ብቻ አይደለህም .... በእውነት ታምንበታለህ የጻፍከውን? ኢትዮጵያ ሌሎች ብቁ የስፖርት መሪዎች የሉአትም?
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby ጌታ » Mon Jul 30, 2012 5:44 pm

ገሌ - ዳጉ ወያኔው ድሮም ጥያቄ ጠየቀ እንጂ አስተያየት አልነበረም የሰጠው :lol: :lol: :lol: :lol:

ፈረንጆቹ የኒጀሩን ወንድማችንን በማይችለው ስፖርት እንዲሳተፍ ፈቅደው ሙድ መያዣ ሲያደርጉት ዝም ትላላቹ?

http://www.huffingtonpost.com/2012/07/2 ... d%3D185565
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ገላጋይ-1 » Mon Jul 30, 2012 6:08 pm

ጌታ wrote:ገሌ - ዳጉ ወያኔው ድሮም ጥያቄ ጠየቀ እንጂ አስተያየት አልነበረም የሰጠው :lol: :lol: :lol: :lol:

ፈረንጆቹ የኒጀሩን ወንድማችንን በማይችለው ስፖርት እንዲሳተፍ ፈቅደው ሙድ መያዣ ሲያደርጉት ዝም ትላላቹ?

http://www.huffingtonpost.com/2012/07/2 ... d%3D185565


ጌታ ታንክስ .... ደህና ነህ ግን? ... ዋለልኝ የጻፈውን በትክክል ሳልረዳው አስተያየት ሰጠሁ

.... ዋለልኝ በጣም ይቅርታ ... lesson taken.
ገላጋይ-1
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 500
Joined: Fri Aug 25, 2006 5:43 pm

Postby ጌታ » Mon Jul 30, 2012 6:15 pm

ገላጋይ-1 wrote:ጌታ ታንክስ .... ደህና ነህ ግን? ... ዋለልኝ የጻፈውን በትክክል ሳልረዳው አስተያየት ሰጠሁ

.... ዋለልኝ በጣም ይቅርታ ... lesson taken.


ገሌ የጥንቱ ወዳጄ በጣም ደህና ነኝ:: ዋርካ ላይ እየተላለፍን ሰላም እንኳን መባባያ ጊዜ ጠፋ አይደል? ዳጉን ይቅርታ በመጠየቅህ በጣም አኮራኸኝ:: እጅግ ሊበረታታ የሚገባው ባህል ነው!!!!
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby የተሞናሞነው » Mon Jul 30, 2012 6:48 pm

እኔ ምላችሁ....ጥሩ ጠይም ጥሩነሽ ዲባባ (እንዴው እሷንስ ላቭ አረጋታለሁ :) ) እና ቀነኒኬኛ አንበሳዬ አሉ አደል? እነሱ ካሸነፉልኝ ሌላው የራሱ ጉዳይ....ሀይሌ በሉት መሰረት ልባቸው እስኪፈነዳ እኔንም በስቃይ ውስጥ አብረው አስሩጠው በጣር በስቃይ ስለሚያሸንፉ....ኮንቪንሲንግ ቪክትሪ አይሆንልኝም::

ሌላም አለች....የደበረ ማርቆስ ልጅ...ስሟ ጠፋኝ...እሷም ትሮጣለች ይሆን? ጎጠኛ ህወሃቶቹ አካተዋት ከሆነና ከሮጠች የወንዜን ልጅ ጉድ ላክ ብያለሁ እሷንም :) :roll:
የተሞናሞነው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1129
Joined: Wed May 11, 2011 5:39 pm

Postby ጌታ » Mon Jul 30, 2012 7:19 pm

ሞንሟናው

ከ35ቱ ያገራችን ተሣታፎዎች የ30ዎቹ ፎቶ ይኸውልህ:

http://www.london2012.com/country/ethiopia/athletes/

ያምስቱ ፊልም ተቃጥሎ ነው መሰለኝ ላገኘው አልቻልኩም:: ድል ላገራችን ልጆች እንዲሁም ለመላው አፍሪካዊያን (ታዲያ ከኛ ጋር ካልሮጡ ነው)
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Tue Jul 31, 2012 3:37 am

አቶ ገላጋይ-1......ምንም ችግር የለውም.....አንዳንዴ ሁላችንም የቴክኒክ ስህተቶች ያጋጥሙናል......ይመችህ :!:

ታላቅ ሰው ጌታ........የኒጀሩ ወንድማችን ኢሳካን "በሚቀጥለው ይሳካል" ብየዋለሁ :D .....ከምር አድንቄዋለሁ

ገላጋይ-1 wrote:
ጌታ wrote:ገሌ - ዳጉ ወያኔው ድሮም ጥያቄ ጠየቀ እንጂ አስተያየት አልነበረም የሰጠው :lol: :lol: :lol: :lol:

ፈረንጆቹ የኒጀሩን ወንድማችንን በማይችለው ስፖርት እንዲሳተፍ ፈቅደው ሙድ መያዣ ሲያደርጉት ዝም ትላላቹ?

http://www.huffingtonpost.com/2012/07/2 ... d%3D185565


ጌታ ታንክስ .... ደህና ነህ ግን? ... ዋለልኝ የጻፈውን በትክክል ሳልረዳው አስተያየት ሰጠሁ

.... ዋለልኝ በጣም ይቅርታ ... lesson taken.
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Next

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests