ስፔን ላሊጋ 2012/13

ስፖርት - Sport related topics

ስፔን ላሊጋ 2012/13

Postby ቲኪ_ታካ » Tue Aug 21, 2012 9:23 pm

ሰላም እግርኳስ አፍቃርያን

ይህችን ፔጅ በስፓኒሽ ፉትቦል ዙርያ ያሉ ማናቸውንም ነገሮች መወያያ ትሆን ዘንድ ከፍቻለሁ:: ብቅ እያላቹ እንግዲህ ሞቅ አርጓት::

ባለፈው ዊኬንድ ባርሳ ሶስዪዳድን 5-1 አሸንፎ ካሁኑ መሪነቱን ተቆጣጥሮታል:: ከአምስቱ ሜሲ ሁለቱን ባፉ አድርጎአል:: ሪያል ማድሪድ በሜዳው ከቫሌንሽያ ጋ 1-1 ተለያይቶ ነጥብ ጥሎዋል:: የሪያል ቤቲስ እና አትሌቲክ ቢልባኦ ጨዋታ የሳምንቱ ምርጥ ጨዋታ ነበር:: በቤቲስ 5-3 አሸናፊነት ተጠናቋል:: በ ፋይናንስ ውጥረት ውስጥ የሚገኘው የ ማላጋ ቡድን ዘንድሮ ወደሊጉ የተቀላቀለውን ሴልታቪጎን 1-0 ሲያሸንፍ ካሜሩናዊው ፋብሪስ ኦሊንጋ ብቸኛዋን ጎል ከማቆጠሩም በላይ በ ስፓኒሽ ሊግ ታሪክ በእድሜ ትንሹ ጎል አስቆጣሪ ተብሎ ሪከርድ ተመዝግቦለታል:: ጎሏን ሲያገባ እድሜው 16 አመት ከ 98 ቀናት ብቻ ነበር::
ቲኪ_ታካ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 17
Joined: Tue Jun 05, 2012 4:58 pm

Postby ቲኪ_ታካ » Tue Aug 28, 2012 6:12 pm

ሄታፌ ሪያል ማድሪድን 2-1 አሸንፎ የሳምንቱ የላሊጋ ሰርፕራይዚንግ ዜና እንዲሆን አድርገዋል:: ለነገሩ ሄታፌ ትልልቅ ቡድኖችን ነጥብ በማስጣል የታወቀ ክለብ ነው:: ያለፈው ሲዝንም ባርሳን 1-0 ያሸነፉበት ጨዋታ ባርሳን የሊጉን ዋንጫ ያሳጣበት ዋነኛ ሽንፈት ነበር:: አሰልጣኛቸው ቀድሞ ሌቫንቴ የሚባለውንም ቡድን ሲያሰለጥን በተለይ ሆዜ ሞሪንሆን ሪያልማድሪድ ያስችገር የነበረ ቡድን ነው:: ስለሞሪንሆ ካነሳን ላይቀር በአሰልጣኝነት ዘመኑ ሶስት ጨዋታ ያለድል መዝለቁ የዘንድሮውን የመጀመርያው አድርጎታል:; ወትሮ ለተደጋጋሚ ሽንፈት ትእግስት የሌላቸው ማድሪዶች ነገሩ በዚሁ ከቀጠለ ምን ሊሉ እንደሚችሉ መገመት አያቅትም:: ማድሪድ ማለት የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ያስገኘን አሰልጣኝ የሚባረርበት ቤት ነው :: ሲጓተት የከረመው የሞድሪስ ከቶተንሀም ወደ ነጮቹ ቤት ዝውውር በመጨረሻ ተሳክቷል:: ሞድሪች ምን ስፍራ ላይ ሊሰለፍ እንደሚችል ምንም መገመት አይቻልም:: ኦዚል እና እሱን በማፈራረቅ? ወይንስ አንድ ላይ አሰልፎ ዣቪ አሎንሶን ቤንች ማረግ? ካለበለዛ ዲማርያን ማስቀመጥ? እሚሆነውን ለመገመት ይከብዳል:: ለጊዜው ግን ሞድሪች ነገ ለሚደረገው የሱፐርካፑ የመልስ ጨዋታ ፊትነሱ የሚያደርሰው አይመስለም:: ምናልባት በዊኬንዱ ሊግ ጨዋታ ጥቂት ደቂቃዎችን ሊያገኝ ይችል ይሆናል:: በተረፈ ባርሳም በታላቂ ሌዮኔል ሜሲ ሁለት የዘገዩ ጎሎች ለትቂት ከመሸነፍ ተርፈው ሙሉ 3 ነጥባቸውን ይዘው ወተዋል:: ሜሲ ጥሩ ሳይጫወት እንኳን በጎሎቹ ቡድኑን ከጉድ ማትረፍ የሚችል አስገራሚ ተጭዋች ነው:: ገና ካሁኑም በሁለት ጨዋታ 4 ጎሎች አስቆጥሩአል:;

የሳምንቱ ድንቅ ተጭዋች ደግሞ የአትሌቲኮ ማድሪዱ ነብር አጥቂ ራዳሜል ፋልካኦ ነው:: ፋልካኦ አትሌቲኮ የባስኩን አትሌቲክ ቢልባኦ 4-0 ሲረታ ሀትሪክ ሰርቷል:; በተለይ ሁለተኛው ጎሉ አስገራሚ ነበረች:: ባጭሩ ፋልካኦ የጎል ማሽን ነው:; ይህ ተጭዋችን አርብ እለት ለአውሮፓ ሱፐርካፕ አትሌቲኮ ማድሪድ ከቼልሲ በሚያደርጉት ጨዋታ እነ ጆንቴሪን እና ጌሪ ካሂልን እንደሚፈትናቸው ነው:; አሰልጣኝ ዲዬጎ ሲሞኒ በእውነቱ አትሌቲኮ አምድሪድን ሙሉ ለሙሉ ለውጧቸው ግሩም ቡድን አርጎዋቸዋል::
ቲኪ_ታካ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 17
Joined: Tue Jun 05, 2012 4:58 pm


Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests